March 12, 2022
10 mins read

ገዥዎቻችንና የሃይማኖት አባቶቻችን ከየት ነው የመጡት? – ፊልጶስ

96c286a0ba4869818001ca10a83426cdበአፍሪካ ምድር የሚፈጸመውን ግፍና በደል  ስንመለከት በ”ርግጥ ገዥዎቻችን እንደ ህዝብ  ሰዎች ናቸው ወይ? እንደ ሰው፣ እንደ አካባቢያቸው ተወልደው ጭቃ እቡክተው በማህበሩ ውስጥ አብረው ችግሩንም ሆነ ደስታውን አይተውና ተካፍለው ያደጉ ናቸው ወይ?

ከቀበሌው ገዥ እስክ ከፍተኛው  የስልጣን እረከን ድረስ ትላንትም ሆነ ዛሬ ያሉት፤ ሥልጣን ሲይዙ ከሰው ወደ አውሬነት ተቀይረው የመጡበትንና ቃል የገቡትን  ‘ረስተው፤  የገዛ ወገናቸውን  የምድርን ስቃይ ሁሉ የሚያሳዩት ለምን ይሆን?

በተለይ ደግሞ ዛሬ  በእኛ አገር ገዥዎቻችንና አጫፋሪዎቻቸው የሚፈጽሙት  በ”ርግጥ እነዚህ ሰዎች በኢትዮጵያ ምድረ የተፈጠሩ ናቸውን? እንመራሃላን የሚሉት ወገናቸው  ያለቅሳል፤ እነሱ ይስቃሉ፤ ህዝብ በሃዘንና  በረሃብ ይጠበሳል፤ እነሱ በደስታና በቁጣና ተይዘው ይፈነጩበታል።

ኑሮ ማሸነፍንና በሰውነቱ ብቻ ተከብር መኖር የሚፈልገውን ትውልድ የፈጠራና የጥላቻ ታሪክ  እየጋቱና  ”ርስ -በርስ እያስተራረዱ በሚፈስ ደም ስልጣን ሲይዙ፣ ገንዘብ ሲሰበስቡ፣ መድረክ ላይ እየወጡ ሲደሰኩሩና ሲደነፋ፤ በ’ርግጥ እንደ ሰው እንቅልፍ ይወስዳቸዋል ወይ? እንደ ሰው አንድ ቀን እንሞታለን ብለው ያስባሉ ወይ?

—-እንዲህ በዚህ ግዜ -እንዲህ በዚህ ሰዓት

ከጠዋትእስከ ማዕልት፣ ከማዕልት እስከ ንጋት፤

ኢትዮጵያን—— ያየ ሰው

ድምጿን——- የሰማ ሰው፤

የጭካኔው ዓይነት – የሰቆቃው ብዛት

ቀመር ስለሌለው፣ በሰባአዊ -ፍጥረት፤

ውሉ ስለጠፋ፣ መነሻ-መድረሻው

እንኳንስ  የሰው ልጅ፤  ግራን- ግራ ገባው::—–

ሰውየው ህልማ ያያል፤ ህልመኛው ሰውየ፤ ለሊቱን ሙሉ ያየው ህልም ሰለረበሸው በጠዋቱ ተነስቶ  ወደ ታወቁት ህልም ፈች ሄደ።፡

ህልመኛውም ለህልም ፈችው ያየውን ህልምና የለቀቀበትን ፈርሃት ማስረዳት ጀመረ።

”የሚያስፈራ ህልም ነው ያየሁት፤ ሁለት ዓይኔ ጠፍቶ፣ ሁለቱም ጆሮየ ደንቁሮ፣  አልሰማ፣ አላይ ፣ ማሰብም ሆነ ማገናዘብ አቅቶኝ፣ ከሙት ሬሳ ጋር እየታገልኩ፣ ሙሉ ለሊት ስሰቃይ ነው ያደርኩት። ምን ኣይነት ስቃይ ሊመጠባኝ ይሆን? ” በማለት ህልም ፈችውን ጠየቀ።

ህልም ፈችውም ፈገግ ብለው ”በጣም ጥሩ ህልም ነው ያየኽው። ልትደሰት ይገባሃል።” አሉት።

ህልመኛው ” እየቀለዱ ነው አይደል? ወይስ ሊያጽናኑኝ ነው?” አላቸው።

”አየህ ! ያየህው ህልም የሚያሳየው፣  በቅርቡ ገዥ ትሆናለህ። ሥልጣን ትይዛለህ።” እሉት።

ቀጥለውም ” አየህ!  በኢትዮጵያ ምድር የዘመናችን  ገዥዎች  ዓይን አላቸው ግን አያዩም። ጀሮ አላቸው ይነገራቸዋል፤ ግን  አይሰሙም፤ አያዳምጡም ። ጭንቅላት አላቸው ግን ህሊና የላቸውም። የፈለገውን ያህል ቢሞት፣ ቢገደል ምናቸውም አይደልም። እናም  የህልምህ ፍቹ የሚያሳየው በቅርቡ ትልቅ ባለሰልጣን እንደምትሆን ነው።” በማለት ነግረው አሰናበቱት።

በ’ርግጥም ገዥዎቻችን የሚያይም ሆነ የሚሰማ ጀሮና የሚያገናዝብ ህሊና ቢኖራቸው ከዚህ ደራጃ ባልደረስን ነበር። ማን ነበር ” በኢትዮጵያ ወስጥ ባለሥልጣንና ባለሃብት ለመሆን ከፈለክ፤ ደደብና ደፋር ሁን።” ያለው።

አሁን ካሉት ከጠ/ሚንስተር አብይ አህመድ ጀምሮ ትላንትም የነበሩም  ገዥዎቻችን፤ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደራጃ በኢትዮጵያ ምድር የተውለዱና ያደጉ፤  መራብን ፣ መጠማትን፣ መታረዝን፣ በአጠቃላይ መገለጫችን የሆነውን ድህነትን ያዩና ያጣጣሙ ናቸው። ወደ ፓለቲካው ዓለም ለመግባትና ሥልጣን ለመያዛቸውም ምክንያትና ዋና አላማ የሚያደርጉት፤ የደሃ ወገናቸውን ህይወት መቀየርና የህግ የበላይነትን ለማስፈን በመስበክ ነው። ግን በሚዘገንን ሁኔታ   በተለይም በአሁኑ ግዜ  እንኳን ደሃ ወገናቸው  ትዝ ሊላቸው  ፤  ንብረትና ሃብቱን ግጠው ጨርሰው፣ የኢትዮጵያዊ ደም የሚጠማቸውና የሰው ደም ካላዩ  ስልጣን ያላቸውና የገዙ የማይመስላቸው ገዥዎች መበሩን ይዘው፤ ከየተ እንደመጡና ሰው መሆናቸውን  ለመጠራጠር  ተገደናል።

የስቃያችን እና የመከራችን  ‘’እግዚኦታ!” ደግሞ መራራ የሚያደርገው፣ የሥጋን ዓለም ንቀው ፣ ለእግዚአቢሄር አደርን ከሚሉ የሃይማኖት ተቋምም ሆነ ”አባት” ስለ ህዝብ ስቆቃና ስለ ገዥዎቻችን እረመኔነት  መናገርና መገሰጥ አይደልም ተባባሪ ሆነው፤ እነሱም በህዝብ ገንዘብና ንብራት የዘመኑን የቅንጦት ኑሮ ሲኖሩ ማያታችን ነው።

በእውነቱ ”ቆም” ብለን እናስብ። እስከ አሁን የጠፋው ህይወት፣ የፈሰሰው ደም፡ የወደመው ንብረት፤  የደረስው ስቆቃና ዋይታ አዕምሮ ከሚገምተው በላይ ነው። እስከ መቼ  እንቀጥላለን? ኢትዮጵያ ሰላስ ሺ ወይም አምስት ሺ ወይም ሶስት ሺ ወይም  መቶ ዓመት ወይም የአንደ ወር እድሜ ይኑራት፣— ዛሬ እኔ፣ አንች፣ አንተ፤ ሰው በመሆናችን ብቻ ተከባብረን የህግ-የባለይነትን አሰፍነን የማንኖርበት ምክንያት የለም። አይኖርምም። ለዚህ ደግሞ እደግመዋለሁ፤  ሰው መሆናችን በቂ ነው።  አንድ ታዋቂ ፈላስፋ ”አገሬ ዓለም ነው፤ ዘሬም የሰው ልጅ ነው።” ይል ነበር አሉ። ይህ ፈላስፋ አሁን በህይወት ቢኖር ” አገሬ ዓለም ነው፤ ዘሬም የሰው ልጅ ነው፤ ከኢትዮጵያ በቀር።”  የሚል ይመስለኛል።

ገዥዎቻችንም ሆናችሁ የሃይማኖት አባቶች እስቲ ታሪክ ሰርታችሁ ለትውልድ የሚጠቅም ስራ ሰርታችሁ ለማለፍ ነገ ሳይሆን ዛሬ ተነሱ። ህዝብም ከፋፍለው የሚገዙንን እና በሃይማኖት ስም የሚነግዱብንን  ግብዞች ”በቃችሁ!” እንበላቸው። ምክንያቱም  ከየትም አልመጡም፤ከእኛ ከራሳችን የወጡ ናቸውና። በጎሳም ሆነ በመንደር ተቧድነን የትም እንደማንደርስ አየተነዋል።  ቅዱሱ መጸሃፍ፤ ”ርስ-በርስ ብትጣሉ፤ ርስ-በርስ እንዳትተላለቁ ተጠንቀቁ–” ይላል።

ኢትዮጵያ ለሁላችንም ከበቂ በላይ ነች። ሥልጣን ለሚፈልገው ፣ ሥልጣን፣ ሃብት ለሚፈልገው፡ ሃብት፡ በአጠቃላይ  ሰርተን ልንበለጽግባትና ሁላችንም ማስተናገድ የምትችል አገር ናት።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

—–//—ፊልጶስ

መጋቢት-2014

E-mail: [email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop