January 29, 2022
5 mins read

ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ማነዉ? ክፍል አንድ (በንጉሤ ዶሌቦ)

272885808 3164197707151495 8350916947574303456 nጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ከአባቱ ከአቶ ጴጥሮስ ሎዳሞ እና ከእናቱ ከወይዘሮ ሸዋዬ አብርሃም በአሁኑ ደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ምስራቅ ባዳዋቾ ወረዳ አንደኛ አምቡርሴ ቀበሌ ሐምሌ 13 ቀን 1943 ዓ.ም ተወለደ፡፡(ፎጊ) በሚል የበረራ ኮድ ስሙ የሚታወቀዉ የሰማዩ ጀግና ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ከቤቱ ሶስተኛ ልጅ ነዉ፡፡

ከልጅነቱ ጀምሮ በመልካም ፀባዩ የሚታወቅ፣ደፋር፣ቁጡ ግን ደግሞ ይቅር ባይና ተግባቢ ባህሪይ ያለዉ ሲሆን በትምህርት አቀባበሉ ንቁና ጎበዝ እንዲሁም ወታደር የመሆን ዝንባሌም ነበረዉ፡፡ ዕድሜዉ ለትምህርት ሲደርስ ት/ቤት ገብቶ የተከታተለ ሲሆን እስከ አስራ አንደኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ድረስ ትምህርቱን በሆሳዕና ከተማ በቀድሞ ራስ አባተ ቦያለዉ በአሁኑ የካቲት 25/67 ትምህርት ቤት ተከታትሏል፡፡የአስራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርቱን በዚሁ ት/ቤት እየተከታተለ እያለ በወቅቱ የኢትጵያ አየር ኃይል ባወጣዉ ማስታወቂያ ተወዳድሮ የተሰጠዉን ምዘና በብቃት በመወጣት ጥር 26 ቀን 1961 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ተቀላቅሏል፡፡

272825110 3164197770484822 3456787643376327575 nየኢትዮጵያ አየር ኃይልን ከተቀላቀለ በኋላ በተቋሙ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን በብቃት ተከታትሏል።ከተከታተላቸው የሥልጠና ዘርፎች ውስጥ፦ የስድስት ወር መሠረታዊ የዉትድርና ኮርስ፣የሰባት ወር መሠረታዊ የበረራ ኮርስ፣የስድስት ወር የመጀመሪያ ደረጃ የበረራ ሥልጠና ኮርስ፣የአዉሮፕላን አብራሪነት ዲፕሎማ እንዲሁም ከፍተኛ የተዋጊ አዉሮፕላን ሥልጠና ኮርስ በሀገር ውስጥ ሰልጥኗል።ከሀገር ዉጭ በሀገረ አሜሪካ እና በቀድሞ ሶቭየት ህብረት የሚሰጠውን የበረራ ትምህርት ስልጠና ተከታትሎ በብቃት አጠናቋል፡፡በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት በወሰዳቸው የሥልጠና ኮርሶች ባገኘዉ ዕዉቀት እና ክህሎት እንዲሁም ባዳበረው ልምድ በአየር ኃይል ዉስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለረዥም ጊዜ ተዛዋዉሮ አገልግሏል፡፡

272875315 3164197740484825 4506295346793785849 nኮሎኔል በዛብህ አገልግሎት ከሰጠባቸው የተለያዩ ቦታዎች ውስጥ በተዋጊ አዉሮፕላን አብራሪነት፣በበረራ አስተማሪነት፣በስኳድሮን ምክትል አዛዥነት፣በተዋጊ ስኳድሮን የበረራ አስተማሪነት፣በበረራ ትምህርት ቤት የትምህርት መኮንን በመሆን (በተደራብነት)፣በበረራ ትምህርት ቤት አዛዥነት በተደራቢ፣በሰሜን አየር ምድብ ጥገና አዛዥነት፣በኤል-39 አዉሮፕላን በረራ አስተማሪነት፣ በበረራ ትምህርት ቤት ምክትል አዛዥነት፣በበረራ ማሰልጠኛ ት/ቤት የሥርዓተ ትምህርት ደረጃ እና ምዘና ኃላፊነት፣በበረራ ት/ቤት የዕቅድና ስርዓተ ትምህርት ኃላፊነት፣በኤል-39 አዉሮፕላን ስኳድሮን አዛዥነት እንዲሁም በምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ ተደራቢ በመሆን የሰራባቸው ቦታዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሠራዊት አባል ሆኖ በተሰማራባቸው አውዳ ውጊያ ግንባሮች ከፍተኛ ጀብድ እየፈፀመ የኖረ የሀገር ኩራት የሆነ ጀግና ነው።ጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ከወይዘሮ ወይንሼት ኃይሌ ጋር ትዳር መሥርተው ሶስት ወንድና ሁለት ሴት በድምሩ አምስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop