December 11, 2021
7 mins read

የዐጤ ምኒልካዊ ሰብአዊነት እና ርኅራኄ

minilik

በዲ/ን ተረፈ ወርቁ

 

ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ዳግማዊ ምኒልክ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፡፡

ይድረስ ከሮም ሊቀ ጳጳሳት ሌዎን ፲፫ኛ፤ ሰላም ለርስዎ ይሁን፤

ክቡር ሊቀ ጳጳሳት ሆይ፡፡

በዚህ ደብዳቤ ቀጥሎ የሚጻፈውን ግፌን አስታውቅዎታለሁ። የኢትዮጵያ ነጻነቷና ራሷን የቻለች መንግሥት ባጠገቧም ጎረቤት የሌላት መሆኗ አስቀድሞ በዮሮፓ መንግሥታት ሁሉ የታወቀ ነው። ከግራኝ ዠምሮ እስካሁን በአሕዛብ እጅ ተከባ ዘወትር በጦርነት ድካም ነው ኑሯችን። ከዮሮፓ የጦር መሳሪያ አስመጥቼ ሠራዊቴን ዘወትር ከጦርነት ድካም አሳርፋለሁ ስል ከንጉስ ዑምበርቶ አባት (ዳግማዊ ቪክቶር ኢማኑኤል) ጋራ የፍቅርን ነገር ዠመርኩ። ንጉሥ ዑምበርቶም መንግሥት በያዙ ጊዜ እኔም እንደአባቴ ፍቅርን እወዳለሁ ብለው ቢልኩብኝ እኔም እንደአባትዎ ታፈቀሩኝ እሺ ብዬ ፍቅርን ተቀበልሁ።

ኮንት አንቶኔሊ የሚባል የኢጣልያ ሰው በገንዘብዎ ጠበንጃ ልግዛልዎ ቢለኝ ብዙ የዝሆን ጥርስና ወርቅ ሰጥቼው ይዞ ሄዶ ከንጉሥ ዑምበርቶ አስፈቅዶ ገዝቶልኝ ቢመጣ ከመንግሥት ፈቃድ በማግኘቱ እጅግ ደስ አለኝ። ሁለተኛም ንጉሥ ዑምበርቶ ኮንት አንቶኔሊን የመንግሥት መልክተኛ አድርገው ወደኔ ሰደዱት። ተልኮ ያመጣውም ቃል ይህ ነው። ነጋዴም እንዲነግድ የጦር መሳርያ እንዳይከለከል ይፈቀድልዋል። እርስዎም ባሪያ እንዳይሸጥ ይከለክላሉ በሌላ መንግሥት ያለ መሳርያ ሁሉ ብትፈልጉ በኛ በር ይወጣላችኋል አይከለከልም። እንደ ዮሮፓ ነገሥታት የተጠላው ውል (የውጫሌ ውል) በአምስት ዓመት ይለወጣል የተወደደው ይረጋል።

… ምጥዋ ሐሩር ሆኖብናል ለሰዋችን ማሳረፊያ ጥቂት ነፋስ ያለበት ሥፍራ እንዲሰጡን የፍቅርን ውል ይህን እናድርግ ብለዋል አለኝ። እሺ ይሁን ብዬ እኔም ለመንግሥቴና ለኔ የሚስማማና የሚጠቅም ቃል በአማርኛ በትክክል አድርጌ አስጥፌ ብሰጠው አስራ ሰባተኛው ክፍል ላይ ቃሉን በኢጣልያ ቋንቋ ለውጠው ከጥንት ዠምሮ ነፃ የነበረውን መንግሥቴን የሚያዋርድ የማይስማማኝ ቃል ቢሆንብኝ እኔ ባስጣፍኩት በአማርኛው ቃል ይርጋ ኢጣልያው ቋንቋ ከኔ ከአማርኛው ጋር ያልተካከለ ነው አሁንም በትክክል እናድርገው ብዬ ወደ ንጉሥ ዑምበርቶ ብልክባቸው ምላሽ ሳይሰጡኝ ቀሩ።

… እኔም ነገሩ ለተንኮል እንደሆነ አውቄ የክርስቲያን ደም በከንቱ እንዳይፈስ አስቀድሜ ለዮሮፓ ነገሥታት ሁሉ ከንጉሥ ዑምበርቶ በውሉ እንዳልተስማማን አስታወቅሁ፤ የእውነት ፍርድ አገኛለሁ ስል። ሁለተኛም አምስት ዓመቱ ሲደርስ የጠላነው እንዲቀር የወደድነው እንዲረጋ ሰው ይላኩልኝ ብዬ ብልክ እስከምላሹም አስቀሩት። ከዚህ ወዲህ ይልቅ ክፉ ነገር እየበረታ ሄደ። አሽከሬን ደጃች መሸሻን አለፍርድ አሰሩት። ልክ አበጅቼ የሰጠኋቸውን አገር አልፈው የሾምኩትን ሹም ራስ መንገሻን ወግተው አባረው አገሬን ትግሬን በሙሉ ያዙት። ከዚያ አልፈው ላስታ መሬት እስከ አሸንጌ ድረስ ወጡ። ከዚህ ወዲያ አገር የሚጠብቁ መኳንንቶች ከኔ ብሰድ አምባላጌ ላይ በር ይዘው ቆይተው ተዋጉዋቸው የእግዚአብሔር ኃይል በኔ ሰዎች አድሮ ድል አደረጉዋቸው።

እኔም ወደዚያው ተከትዬ ብሄድ መቀሌ እርድ ገብተው አገኘሁ። ጦርነት ተሆነ ከትልቁ ጋር እዋጋለሁ እናንተ ክርስቲያኖች በውኃ ጥም አትለቁ ብዬ እስከ መሳሪያቸው ከእርድ አሰጥቼ ለጀነራል ባራቲዬሪ ሰደድኩለት። እኔም ከዚያ ተጉዤ አድዋ እከተማዬ ሰፍሬ ጀነራል ባራቲዬሪ እውነት የመሰለ የእርቅ ቃል ላከብኝ። እኔም እርቅ ከፈለጉ ብዬ ሠራዊቴን ቀለብ ሰድጄ ሣለ እንደ ዮሮፓ ነገሥታት ሥራት ሁሉ ጠብ መፈለጋቸውን ሳያስታውቁኝ እንደ ወምበዴ ሥራት ሌሊት ሲገሠግስ አድሮ ሲነጋ ግምባር ካደረው ዘበኛ ጋር ጦርነት ዠመረ።

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከኢጣሊያ ጋር ለዕርቀ-ሰላም ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፣ እናም የዐድዋ ጦርንት አይቀሬ ኾነ፡፡ ድሉም ለኢትዮጵያ ኾነ፡፡ ዐፄ ምኒልክ ከዐድዋ ድል በኋላ መጋቢት 23 ቀን 1988 ዓ.ም. ለፈረንሳዊው ሙሴ ሸፍኔ በላኩለት ደብዳቤያቸው እንዲህ ብለዋል፤

‘‘… ከአላጌ ጦርነት በኋላ፣ ጣሊያኖችን ጦርነት ይቅር፣ የክርስቲያንም ደም በከንቱ አይፍሰስ፣ እርቅ ይሻላል ብላቸው እምቢ ብለው መጥተው በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግ ተው ድል ሆኑ፡፡ እኔ ግን በድቁርናቸው ብዛት የነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረግኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም፡፡ ነገር ግን በግፍ የመጡ ሰዎች ናቸውና እግዚአብሔር ግፉን አነጣጠረን…፡፡’’

ሰላም ለኢትዮጵያ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop