July 13, 2021
4 mins read

ለመላው የአማራ ህዝብ የቀረበ ህዝባዊ የትግል ጥሪ!

አማራ ህዝብ ከባድ ዋጋ ከፍሎ ያስወገደው የትህነግ ሀይል ዳግም እንዲያንሰራራና ህዝባችን በመስዋእትነት ያስከበረውን ማንነት በፖለቲካ አሻጥር እንዲገፈፍ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት የለውም።

በአሁኑ ሰዓት የአማራ ህዝብ አፅመ ርስት የሆኑት የኮረምና አለማጣ አካባቢዎች በትህነግ እጅ ስር እንዲወድቁ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ አቋም የወሰደ መንግስታዊ ክፍል ስለመኖሩ የተረጋገጠ ጉዳይ ሆኗል።

ከመነሻው ህዝባችን የፖለቲካ ቁማር ማስያዥያ እንዳይሆን በሚል ያልተቋረጠ ጥሪ ስናቀርብ ብንቆይም የተለያዩ አካላት በፈጠሩት ውዥንብርና የአመራር ክፍተት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ዳግም ለህልውና አደጋ ተጋልጦ ይገኛል። ትህነግ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በርካታ ህዝብ ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ መፈፀሙም ታውቋል።

ስለሆነም:-

1/ መላው የአማራ ህዝብ ይህ ጉዳይ የታሪክና የማህበራዊ ክብር እንዲሁም የማንነት ጉዳይ መሆኑን በመረዳት አጠቃላይ ጥቃቱን ለመመከት አስቸኳይ ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲያደርግ፣

2/ የአማራ ወጣቶች በየአካባቢያችሁ በመምከርና በመደራጀት፣ ራሳችሁን በማስታጠቅ ለሁለንተናዊ ዘመቻ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ፣

3/ በሁሉም አካባቢዎች ያላችሁ የአማራ ፋኖዎች በአሁኑ ሰአት ህዝባችን ያጋጠመውን የህልውና ትግል ለመቀልበስ በግንባር ለመንቀሳቀስ ፈጣን ዝግጅት እንድታደርጉ፣

4/ መላው የአማራ ህዝብ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና በተለይም በመካከላችን ሆነው ሴራና ጥቃት የሚያቀናብሩ፣ በሰርጎ ገብነት መረጃ ለጠላት የሚያቀብሉ አካላትን በንቃት በመከታተል የማክሸፍና የመቆጣጠር ስራ እንዲያከናውን፣

5/ በተለያየ የአመራር ጥፋትና ጥሰት ያላግባብ ተገፍታችሁ ከፀጥታና ከወታደራዊ አመራርነታችሁና ሙያችሁ ውጭ የተደረጋችሁ የአማራ ልጆች በሙሉ ህዝባችሁን ለመታደግ የሚደረገውን ታሪካዊ እንቅስቃሴ ለመቀላቀል ዝግጅት እንድታደርጉ፣

6/ ሂደቶችን በአስተውሎት እየተከታተልንና መረጃ እየሰበሰብን በመቆየት ነገሮች ይሻሻላሉ በማለት ብንጠብቅም ችግሮቹ በፍጥነት ሲወሳሰቡ በማየታችን ለህዝባችን ህልውና ይህንን ጥሪ ለማድረግ ተገደናል።

ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ በዚህ አግባብ በፖለቲካ ሸፍጥና በአመራር ክፍተት ምክንያት የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ለሚደረገው ሁለንተናዊ ዘመቻ በትጥቅና ስንቅ አቅርቦት እንዲሁም በደጀንነት ርብርብ እንዲደረግ ንቅናቄያችን ይሄን ታሪካዊ ጥሪ እያስተላለፈ፣ የህልውና ዘመቻውን በሙሉ እንዲቀላቀሉ እና እንዲያሰረተባብሩ ለሁሉም የንቅናቄያችን አባላትና አመራሮች ትዕዛዝ የተላለፈ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop