ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ምርጫውን ባለመሳተፍ ሃገርና ወገን አድኑ ጥሪ በማድረግ የብልፅግና ኢዜማ የፖለቲካ ሴራን አክሽፉ!!!
“ People always forget that it’s much easier to install a dictator than to remove one”
ከቀዝቃዛው ጦርነት በኃላ መዋቅራዊ ማሻሻያ ፕሮግራም፣፣የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም፣ የመድለ ፓርቲ ምርጫ ፕሮግራም የመሳሰሉት አሥርቱ ትዕዛዛት የአፍሪካ፣ ኤሽያና ላቲን አሜሪካ ደሃ አገራቶች መንግሥታት መሥፍርት ተነደፈላቸው፡፡ ከዛ ጊዜም ጀምሮ ምርጫ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ሆነ፡፡ የምርጫ ውታፍ ነቃዬች! በዘር ላይ የተመሠረተ ምርጫ ወጤቱ የዘር ማፅዳት ነው! በምርጫ በትረ-መንግሥት ተካይና ነቃይ ምሁር ተብዬ ውታፎች በአድርባይነት ምሳቸው የመንግሥትን አውራ ፓርቲ ህወሓት/ ኢህአዴግን በአምስት ዙር የምርጫ ውድድር ኮሮጆ ገልባጭ የምርጫ ውታፍ ነቃዬችና ተካዬች በመሆን አገልግለዋል፡፡ በጥንቷ ኢትዮጵያ ታሪክ የመሳፍንቱና መኮንቶቹ በዘመኑ ግልገል የውስጥ ሱሪ (ቡታንታ) ስላልነበራቸው ተነፋነፍ ሱሪያቸውን ከኃላ የሚያመቻቹላቸው ውታፍ ነቃዬችና ተካዬች ባለሟሎች ነበቸው ይባላል ብሎ ሃብታሙ አያሌው አውግቷናል ከእሱ በመዋስም ለዘመናዬቹ ተውሰናል፡፡ የምርጫ ውታፍ ነቃዬችና ተካዬች ዋና ሥራ በአፋቸው ምርጫውን ዴሞክራሲያዊና ዘመናዊ ካባ ማልበስ፣ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በቀይ ካርድ ማባረር፣ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሂደት ምስክርነት መስጠት፣ ኮሮጆ መገልበጥ፣ የምርጫ ህግን ለመንግስት በሚስማማ መልኩ ማኮላሸት፣መለጎምና መበረዝ ሥራ ማጋፈር ለሥራቸውም ውለታ በአንባሳደርነት መሾምና መሸለምለእነዚህ የእኔ ብጤ፣ የደሃ ልጆች ይከፈላቸዋል፡፡ የንጉስ ግብር አልበላ ማለት አረ እንዴት ይቻላል፣ የመንግስት ግብር እንባሳደር መባልሳ እንዴት ይታለፋል፡፡ ሆድ ካገር ይሰፋል ቢለው እንደ ሆዳሙ ነው አለው ይባላል እንባአደሮች እንደደጃዝማች ማዕረግ ጡረታ ከወጡም በኃላ የቀድሞው የሱዳኑ እንባደር ተያዙ ይለናላ መንግስት፣ የናንተም እንዴ ነው፣ ‹ማን ይፈራል ሞት!!!›
‹‹ምርጫ በፍርድ ቤት የመዳኘት ልምድ አለመኖር የ1997 ዓ/ም የምርጫ አጣሪ ኮሚሽን አጣሪዎች ለሁለት መቶ ሰዎች ሞት፣ ለአምስት ሽህ ሰዎች መቆሰልና ለሰማንያ ሽህ ሰዎች ወህኒ መውረድ ለህዝብና ለፓርላማ እስከካሁን ሳያቀርቡ ተድበስብሶ አልፎል፣ ዳኛ ፍሬህይወትና ዳኛ ወልደሚካኤል እስከዛሬ ለስደት ተዳርገዋል፡፡ “While in the 1960s and 1970s approximately 75% of African leaders were ousted through violent means (coup d’etats, rebellion), in the period 2000-2005 this number had dropped to 19%.”1
ህወሓት የሰሜን ዕዝን በመብረቃዊ ምት በቆረጣና ደፈጣ ድባቅ መታሆ ባለ ሁለት ሳምንት እራሱ ድባቅ ተመታ፡፡ በአህጉረ አፍሪካ በአስራዘጠን መቶ ስልሳዎቹና ሰባዎቹ ሰባ አምስት በመቶ የአፍሪካ መሪዎች በመፈንቅለ መንግሥት (ኩዴታ) ይወርዱ እንደነበር ታሪክ ይዘግባል፡፡ በአፍሪካ ኩዴታ ቀንሶል ከሁለት ሽህ እስከ ሁለት ሽህ አምስት እኤአ ባሉት አመታት ውስጥ አስራዘጠኝ በመቶ ወርዶል፡፡
የ1997 ዓ/ም የምርጫ ተበዳዬቹ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የነበሩ ቅንጅት፣ አንድነት፣ ህብረት ወዘተርፈ ስም ቀይረው ኢዜማ ብርሃኑ ነጋ፣ የኦፌኮ መረራ ጉዲና፣ ሶሻል ዲማክራቱ በየነ ጵጥሮስ፣ ኢዴፓ ልደቱ አያሌው በወያኔ ለተገደሉት ሁለት መቶ ወጣቶች ደም ደመከልብ አድርገው ዛሬ ወላጆቻቸውን ደግም ምረጡን ብለው ከአስራ ስድስት ዓመታት በኃላ ዓይናቸውን በጨው አጥበው መጥተዋል ወላጆች የልጆቻቸውን በግፍ መገደል የረሱት መስሏቸው፣ የአደረ አፋሽ ፖለቲከኞች ቁማር ጨዋታ እንዲነው፣ ከምኔው ከምኔው ከምኔው ተረሳ!!! እየመላለሰ ፓርቲያቸው አገሳ!!! እንባደሮች የታገሉት ለእራሳቸው ሥልጣን፣ ቤት፣ መኪና፣ ደም ወዝ መሆኑን አንርሳ!!!
የኢዴፓ ልደቱ አያሌው ከሃያ አንድ አመት ተፎካካሪ ፓርቲ ተወዳዳሪነት ለስድስተኛው ዙር የምርጫ መሥፈርቱን አታሞላም በማለት ፓርቲው መሠረዝና ያለፍርድ ለስድስት ወራት ማሰር የምርጫ ውታፍ ነቃዬችና ተካዬች የምርጫ ቆረጣና ሽመቃ ታክቲክና ስትራቴጂ መብረቃዊ ምት እንዳሽመደመዱት ይተርካሉ፡፡
‹‹ዛሬ በዓለማችን ብዙ አገሮች መደበኛው ዴሞክራሲ ሥርዓት ተከታዬች ሆነዋል፡፡ በዓለማችን ባለፈው ሦስት አሥርታት የሚያስገርም የፖለቲካ ሽግግር ተከናውኖል፡፡ ዛሬ ብዙ አገራቶች መደበኛ ዴሞክራሲ ከዋኒዎች ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጥንት ፍቱን የዴሞክራሲ መከላከያ የነበራቸው በለውጥ ጎዳና ላይ ይገኛሉ፡፡ የአረብ አብትዬ የተነሳ የቱኒሲያ፣ የግብፅ፣ የሊቢያና የየመን አንባገነን ገዥዎች ከሥልጣን መንበራቸው በአጠቃላይ ከመቶ ሃያ ዘጠኝ አመታት በኃላ ተገርስሰው ወድቀዋል፡፡ ከ2011 እኤአ መጨረሻ በኃላ በዓለማችን የቀሩ የአንባገነን አገዛዝ ሥርዓት ያላቸው አገራቶች ውስጥ አዘርባጃን፣ ባህሪን፣ ባይላሩስ፣ ቻይና፣ ኩባ፣ ኤርትራ፣ ኢራን፣ ካዛኪስታን፣ ኩዌት፣ ላኦስ፣ ኖርዝ ኮርያ፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ሲዊዚላንድ፣ ሲሪያ፣ ቱርኪሜንኢስታን፣ ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ፣ ቪትናም፣ እና ኡዝቤኪስታን ይገኙበታል፡፡
የኢትጵያ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ ዴሞክራሲያዊ መሥፈርትና የሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አለመረዳት
የመንግሥት ቅድመ ምርጫና ድህረ ምርጫ ታኳዎቹ ውጤት ለእንባሳደርነት፡፡
- በኢትዮጵያ ነፃ ፍርድ ቤት የለም፡፡ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ የእስክንድር ነጋ፣የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ልደቱ አያሌው፣ የአብሮነት ኢንጅነር ይልቃል፣ የኦፌኮ ጁሃር መሃመድ ወዘተ የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ሃምሳ ሦስት ፓርቲዎች የምርጫውን መሥፈርቶች አያሞሉም ብሎ ሲሰርዝ ከርሞል፡፡ የምርጫ መሥፈርት ባለማሟላት የሚታማ፣ ብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ያላደረገ፣ በጠቅላላ ጉባእ የምክር ቤትና ሥራ አስፈፃሚ ያላስመረጠ፣ የፓርቲውን ፕሮግራምና ደንብ በአባሎቹ ያላፀደቀ፣ የፓርቲውን አመራሮች ሰብሳቢ፣ምክትል ሰብሰቢ፣ ኦዲተር ያላሰመረጠ መሆኑን ልደቱ አያሌውና ኢንጅነር ይልቃል የኢትዮጵያን ምርጫ ቦርድ አባላትን የብልፅግና ፓርቲና ኢዜማ የምርጫ ውታፍ ነቃዬችና ተካዬች እንደሆኑ ደምድመዋል፡፡
- በኢትዮጵያ የህግ ሥርዓት ድክመት (Supreme Court) ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስለሌለ ነው፡፡ የህገ-መንግሥት ችግር የሚፈታ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አለመኖር እየታወቀ የምርጫ ቀውስ ቢነሳ ዉጤቱ ምን ይሆናል ብለው ይሞግታሉ እውቁ ጠበቃ ደረጀ ደምሴ
- ቅድመ ምርጫና ድህረ ምርጫ የሚያስተናግድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሳይመሠረት ተቆም ግንባታ ላይ ነን የሚሉን የሦስት ሽህ አመት ታሪክ ያላት ሃገር እውን ህግ አዋቂዎች አጥታ ነው ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ይጠየቁ፣ የሶሊያና ሽመልስም እንቶ ፈንቶ ዲስኩር ከምርጫ ውታፍ ነቃዬችና ተካዬች ባለሟልነት ሌላ የምርጫ ማስፈፀሚያ ሰነዶችና ካርዶች ብቻ ስለተሟላ ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ ያደርገዎል ክርክር ‹‹ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም!!!›› ከማለት ሌላ ምን ይባላል፡፤
- በኢትዮጵያ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት መከልከላቸው፣የምርጫ ውታፍ ነቃዬችና ተካዬች አልሰሙም፣ አይሰሙም፡፡ ለነገሩ ምርቻ ቦርድ የተመረጠው በመንስት፣ በብልፅግና በበላበት ላይጮህ ነው የምትሞገቱት ‹‹አህያ ከሩቁ ፈረስ ይመስላል!!!›› ይለኝ ነበር አባቴ በልጅነቴ፡፡ ፈረስና አህያን በደንብ እንድለይለት፡፡ ጨረቃን ፀሓይ ናት አልኩኝ ተመልሼ ብሎ ጥላሁን ድሮ ገና አዚሞልን ነበር፣ አልገባንም እንጂ ያስብላል ዘንድሮ፡፡
- የፌዴራልና የክልሎች አግላይ ሕገ-መንግሥት አይነኬነት አንዱን ኖሪ አንዱን መጤ፣ በአንድ የዘር ክልል ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ቌንቌ ተናጋሪዎች መብትና ግዴታ አይቶ እንዳላየ ማለፍ
- የድሬዳዋና (የአርባ አርባ ሃያ) የሐረር (ሃምሳ ሃምሳ ዜሮ) የአፓርታይድ ሥርዓት አይነኬነት
- የትግራይ ክልል በጦርነት ቀጠና ውስጥ በምርጫው አለመሳተፍ
- በሃገሪቱ ውስጥ በኮማንድ ፖስት ስር ያሉ ዜጎች ምርጫ እንዴት ሊካሄድ ይቻላል በቤኒሻንጉል ክልል የፓርቲ ጦር ታጣቂዎች የአማራና ሌሎች ዘር የማጽዳት እኩይ ተግባር እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የኦነግ ሸኔ የዘር ማጥፋት የግፍ ጭፍጨፋ ቀጣይነት እየታየ ምርጫ ማካሄድ ውጤቱ ምን ይሆናል፣
- የጎረቤት አገራት የጦርነት ሥጋት የሱዳን ጦር የኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ በመግባት ብዙ ግዛቶች ተቆጣጥረው እያለ፣እንዲሁም የሻብያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫ ማድረግ
- የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሦስትዬሽ ስምምነት ያለ ስምምነትሲስማማ ዓመታት ተቆጥሮል፣
- የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት መሠረት የዘር ማፅዳት እንዳልነበር ማድበስበስ ታይቶበታል፣ ከማይካድራው ያልተናነሰ በቢኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ቀድሞ የተከናወነ ጀኖሳይድና በወለጋ እስካሁን የሚደረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም ያወቀው ፀሓይ የሞቀው ያደባባይ ሚስጢት ሆኖ ‹‹በፖለቲካ የወገብ ልምሻ›› እንዴዘው ሰው መጥመልመል ከታሪክ ተጠያቂነት አያድንም፡፡ ዛሬም በኦሮሚያ ክልል አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ እንዳለ ዶክተር ዳንኤል በቀለ አሳስበዋል ብለዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ ጉዳዩን እንዴት ያየዋል በምርጫው ጊዜ ለሚደርስ ግጭት ምርጫ ቦርድ ኃላፊነት ለመውስድ ብርቲካንና ኮሚሽነሮቹ ‹ኮማሪዎቾ› ተጠያቂ መሆናቸውን ሊያውቁ ይገባል እንላለን፡፡
- የኢትዮጵያ ምርጫ ኮሚሽን ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳና ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ በመለስ ዜናዊ ዘመን የክልል አስራአራት ዳኛ ሆኖ የተሸመ፣ በኢህአፓነት ሦስት አመታት ወሕኒ የታሰረ፣ በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ ሆኖ የተሸመ ሹም አዳኝ (fortune hunter) ለንዋይ፣ ለቤት፣ ለመኪና ለጥቅም ‹‹በሃገር ፍቅር የነደደ›› ውታፍ በዚህ ባልሰከነ የምርጫ ሰሌዳ ሞቾች ተጠያቂነትነት ሊወስዱ ከወዲሁ ግድ ይላቸዋል፡፡
- ተፎካካሪ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ምርጫውን ባለመሳተፍ ሃገርና ወገን አድኑ ጥሪ በማድረግ የብልፅግና ኢዜማ የፖለቲካ ሴራን እንዲያከሽፉ እንጠይቃለን!!!
- ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊው የስብአዊ እርዳት ድጋፊ እንዲደረግ ማድረግ፣ በሃገር ውስጥና በባህር ማዶ የሚገኙ ኢትጵያዊያን የእርዳታ ድርጅቶች የገንዘብና እቃ በማሰባሰብ በአስቸኮይ በጦርነት ተጎጂው ህዝብ እንዲቀርብ ማድረግና በሃገር ውስጥ ያሉ የክልል መንግስቶችም ለትግራይ ህዝቡ በቶሎ በመድረስ ከፖለቲካ የፀዳ ስብኣዊ የእርዳት እጃችሁን በመዘርጋት ህዝቡን ልትታደጉት ይገባል፡፡ ‹‹የነገ ሞች ዛሬ አስክሬን ይሸኛል›› እንዳሉት አባታችን፡፡
ብልፅግና ፓርቲና ኢዜማ በህገመንግሥቱ አይነኬነት፣ በኢትዮኤርትራ ግንኙነት የፖለቲካ ሴራ፣ በኤርትራ ወረራ አጋፋሪነት፣ በምርጫ ፀረ ዴሞክራሲያዊነት፣ የኢትዮጵያን ምርጫ ቦርድ አባላቶች የምርጫ ተካይና ነቃይ የአስኳላ ውታፎች!!! ታኳዎች!!! በማድረግ ለሰሩት ውለታ የነገ ተጠያቂዎች ብልፅግናና ኢዜማ በዴሞክራሲ ስም እየማሉና እተገዘቱ ሃገሪቶን ወደ ማያባራ ጦርነትና ትርምስ እየከተቶት እንደሆነ ከዚህ ስድስተኛ ዙር ምርጫ ወጥመድ ሰንት ሰው ማለቅ ይገባው ይሆን፣ ስንት ሰዎች ዘብጥያ ይወርዱ ይሆን፣ ስንት ዜጎች ከክልላችን ውጡ፣ አትምረጡእየተባሉ በዘር ማፅዳት በየክልሉ የሰየፉ ይሆን፣ ብልፅግና ፓርቲና ኢዜማ ከስልጣን መንበራቸው እስኪፈናጠጡ ድረስ፡፡ የሃገራችን ሁኔታ ምርጫ ለማድረግ የተመቻቸ አይደለም፣ ምርጫው ይቆይና ማንኛውም ሰው በህይወት የመኖር መብቱ በፊት ይከበርለት፣ ስብዓዊ መብቱ ይጠበቅለት፣ የህግ የበላይነት ይከበር፣ የዘር ማፅዳት ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡለት፣ ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር ዐብይ አህመድ ቃሉን ጠብቆ ከኦሮሙማ ዘረኛና ተረኛ ሃሳብ ተላቆ ሁላችንንም በእኩል ዓይን አይቷ ያስተዳድረን፡፡ ምርጫው ይቆየን ነው ያልንው፣ የመታረጃ ካራው፣ ሜንጫው፣ ገጀራው፣ ጦሩ፣ በፊት ይሰብሰብልን ብለን ተማፅነናል፡፡ የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት አልሰማ ብሎ ነው ግፍ ሞልቶ በመፍሰሱ ለወሬ ነጋሪ የጠፋው፡፡ የኦነግ የጦር አበጋዞች መንግሥት የነገ ተረኛና ዘረኛ የኦሮሙማ ዕጣ ፈንታ ከዚህ ካለፈ ቃል ለምድር ለሰማይ ይሁን!!! ከህወሓት ኦነግ ይማር እንላለን፡፡ የኦነግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ከአማራ የጦር አበጋዞች መንግሥት ጋር ጦርነት ለመግጠምና ለመቶ አመታት እንገዛለን የተረኝነት የእብሪት ስሜት በሌሎች የኢትዮጵያ ልጆች ህብረትና ፍርድና ፍትህ ሰጪነት ይቆጫል፡፡ ትናንትና ዛሬ ሃገር የሚተራመሰው በሻብያ፣ በወያኔ፣ በኦነግ ጣምራ የጦር አበጋዞች መንግሥት የፖለቲካ ሴራ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተገንዝቦል፡፡ “While elections may be essential in promoting legitimacy, stability and development, they can also be deeply problematic. Elections can spark violent conflict, especially when they generate ‘winner takes all’ dynamics that raise the stakes of political competition. As the example of Kenya in 2007 illustrates, this can be especially treacherous where ethnicity or other fault lines of conflict such as region or religion determine political allegiance. For example, a recent study has estimated that between 1990 and 2007 one in five elections in Sub-Saharan Africa suffered significant violence and only about 40% were entirely violence-free.”2 በዓለማችን ከሦስት ሰዎች አንዱ በፈላጭ ቆራጭ አንባገነን ሥርዓት ውስጥ ይኖራል፡፡ እንደ ኢኮኖሚስት ኢንቴሌጀንስ ዩኒት ዴሞክራሲ ኢንዴክስ 2011 እኤአ ጥናት መሠረት ስድሳ ሁለት በመቶ የዓለም ህዝብ በመደበኛ ዴሞክራሲ ሥርዓት መሳይ አስተዳደር ይመራሉ፡፡ በአንፃሩ ሠላሳ ስምንት በመቶ በአንባገነናዊ ሥርአተ አስተዳደር ይገዛሉ፡፡ ቻይና ብቻዋን ሃምሳ አንድ በመቶ ህዝብ በመደበኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሥር አይስተዳደርም፡፡ ምርጫ በአመዛኙ የዓለም አቀፍ ሥርዓት መገለጫ ሆኖ ነፃና እንከን የለሽ ምርጫ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ምርጫ፣ ሚዛናዊና የሚታመን ምርጫ፣ በማድረግ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችና መንግስት በሚያደርጉት የምርጫ ውድድር የህዝብ ህይወት ስጋት ውስጥ ይገባል፡፡ በዓለማችን በምርጫ ተሸንፈው በጸጋ አልቀበልም ያሉት ፕሬዤዳንት ትራንፕ ሥልጣናቸውን በሰላም ለጆባይደን አላስረክብም በማለት በአሜሪካ ምክር ቤት በካፒቶል ሂል ትራምፕ የመፈንቅለ መንግሥት ወረራ አድርገው አራት ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዓለማችን ከ2000 እኤአ ጀምሮ ምንም ምርጫ ያላካሄዱ አገራቶች ውስጥ ቻይና፣ ኤርትራ፣ ኮታር፣ ሳውዲ አረቢያና፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ይገኙበታል፡፡ የኢትጵያ ምርጫ ደህና ቀን እስኪመጣ ቢሸጋሸግ ዴሞክራሲያችን ይቀጭጫል ብለው ይሆን የምርጫ ተካይና ነቃይ የአስኳላ ውታፎች!!! ታኳዎች!!!
(መታወሻነቷ፣ ለኢትዮ 360 የወደፊት የዴሞክራሲ ትንታጎች!!! ሰው በሃሳብ በወይይት እንዲሞገትና እንዲከራከር ለሃሳብ ልዕልና በር ከፋቾች ናችሁና ኮራሁባችሁ፣ በጋዜጠኝነት ሙያችሁ አትደራደሩ፣ ለሃቅ ቁሙ ለህሊናችሁ ሠላም!!!፡፡ “Something which we think is impossible now is not impossible in another decade. “
ምንጭ፡-
(1&2)Ten Things to know about election 10 and democracy Alina Rocha Menocal
(3) Constance Baker Motley)