January 1, 2021
10 mins read

ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ” ነፃ፣ሚዛናዊ፣ሰላማዊ፣የሚታመን እና ዴሞክራሲያዊ ” መሆን አለበት – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“free, fair, peaceful, credible, and democratic.”

Election

Ethiopia’s 2015 elections confirm that the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF)—having won 100 percent of parliamentary seats—has chosen to entrench an authoritarian system. We argue that this total election victory was meant as a signal to party cadres that defection is not tolerated. Our analysis of intra-regime dynamics shows how the EPRDF has responded to the death of Meles Zenawi through greater reliance on trusted party stalwarts for high-level posts. We conclude that growing demands from lower-level party cadres threaten to transform the ruling party from a disciplined national organization into a patronage-based alliance of ethnic factions.

Journal of Democracy Volume 27, Number 1 January 2016

 ወያኔ/ኢህአዴግ በ2007 ዓ/ም ምርጫ 100 % የህዝብን ድምፅ አግኝቼ አሸነፍኩ በማለት የፓርላማውን መቀመጫ  ጠቅልሎ በመውሰድ በጉልበቱ መሪ ነኝ  በማለት ዛሬም ከአምባገነን አገዛዝ እንዳልተላቀቀ አስመስክሯል፡፡ይህ አይን  ያወጣ ቀጥፈት ከቶም የማይታገሱት ነው፡፡ ለካድሬው ግን ይህ ቅጥፈት አይገደውም፡፡ ሥለ ዴሞክራሲ የሚገደውን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ መናቅ  ምንም ተፅእኖ የማያመጣ  ሊመስለው  ይችላል፡፡

በእኛ በእወቀት ላይ በተመሰረተ ጥልቅ ግምገማ  ፣ከመለስ ዜናዊ  ሞት በኋላ ፤ገዢው ፓርቲ  በአምባገነንነት መግፋት ብቻ ሳይሆን ፣ በዝቅተኛው አመራር ደረጃ ካድሬ በማብዛት ና የጎሳ ፖለቲካን በማስፋፈት ፣ጭፍን ደጋፊና ና አጨብጫቢ እንዲበራከት አድርጓል፡፡በዚህ የተነሳም፣   በበዙ የጎሳ አንጃዎች  የሚመራ  ሥርዓት እንጂ ፤ቅቡልነት  ያለው የመንግስት መዋቅር (ተቋም)  እንደሌለው ተገንዝበናል፡፡  (ነጻ ትርጉም)

ይህ  ስለ ዴሞክራሲ ያገባናል የሚሉ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቦች የትላንትና ድምፅ ነው፡፡ የነገውን ደግሞ አብረን እናያለን፡፡ምረጫው ገና አምስት ወራት ይቀሩታልና እስከዛው የሚሆነው፣የሚፈጠረው፣የሚከሰተው አይታወቀም ና ቶሎ፣ቶሎ ብላችሁ የሚገባችሁን ስራ የምርጫው ደጋሾች ሥሩ፡፡የሚጠበቅባችሁ ይኸው ነውና፡፡

መንፈሳዊያን ደግሞ ሚናችንን ለይተን ከወዲሁ በኃይማኖታችን በፅናት መቆም ይኖርብናል፡፡ለሁለት ጌቶች መገዛት በራሱ ሐጥያት ነውና፡፡አንተ ሰው በአንድ በኩል ለወድምህ መታረጃ ቢላ ለገዳዩ ደብቀህ እየሰጠህ ፣በሌላ በኩል ፣ ፈጣሪህን ለማምለክ በየቤተ ክርስትያኑ እና መስጂዱ መገኘት ፈጣሪህን የማያሳዝነው ይመስልሃልን? …ለአንተ የመጣው ቅጣት ለንፁሐንም ይተርፋልና ፈጣሪ ዕደሜ ከጤና ጋር እንዲሰጥህ ከፈለገህ እጅህን ሰብስብ፡፡

ምርጫ  በአምስቱ የምርጫ መመሪያዎች ታግዞ   ሲካሄድ ባልነበረበት እና ፍትህ ተጨቁና በኖረችበት  አገር ውስጥ ሥለኖርን የነገው ምረጫ ያሳስበለና መንግስት ለፍተህ ከቶም ሳያንቀላፋ ዘብ በመቆም ፤የህግ የበላይነትን ማስከበሩ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ፣ ቢያንስ ሰላም እንዲኖር ተራ ሟቹ ህዝብ የፈጣሪን መኖር እንዲገነዘብና ጤዛነቱን እዲረዳ ማድርግ ከኃማኖት አባቶች ይጠበቃል ፡፡በበኩሌ የኢትዮጵያን የምርጫ  ታሪክ በቅጡ ሥለማውቀው የነገው ምርጫ በእጅጉ ከሚሳስባቸው የበዙ ሰወች መካከል አንዱ ነኝ ወደሰማይ በንጋጥጥ አይግረማችሁ፡፡

“ለምንድነው ይህ ስድስተኛው አገር አቀፉ ምርጫ እንዲህ ሊያሳስበህ የቻለው ? ” የሚል ጥያቄ ብጠየቅ  አገሬ ነፃ  ና ገለልተኛ ተቋማትን ባለመገንባትዋ እና የቋንቋን ፖለቲካ ስላላሶገደች ፣ ምርጫ አልባ ሰዎች ስለሚበዙ ምርጫው ሚዛኑን የጠበቀ ነጻነት ያለው፣ የሚታመን እና ዴሞክራሲያዊ  ስለማይሆን ሰላማዊ ሊሆን እንደማይችል እየታየኝ ነው፡፡

ይህ እይታዬ ከትላንቱ የውሸት  ምርጫ የተነሳ የተከሰተ ነው፡፡የትላንቱ ምረጫ ይሉንታ ቢስ ብቻ ሳይሆን ፍፁም ዘረኛ እና ከፋፋይ ነበረ፡፡ የኢኮኖሚ ችግርያለበትን አብዛኛውን ሰው በገንዘቡ እንጂ በሚተገብረው በተቀደሰ አሳቡ የሚገዛ አልነበረም፡፡የወያኔ አደረጃጀትም ጠርናፊ እንጂ እያንዳንዱ ዜጋ በህሊናው እንዲመራ የማያደርግ የግል ነፃነትን ከልካይ ነበር፡፡ ጠርናፊ በሆነው የቋንቋ ፖለቲካውም ሳብያ ሰውን እንደ ዕቃ የሚመለከት  ህሊና ቢስ ነበርና  መጨረሻው እንደ በጋ ጉም ብን ብሎ መጥፋት ሆነ፡፡

ዘረኝነትን የሚቀነቅኑ ሁሉ የሰው ልጅ ጠላቶች ናቸውና ብን ብለው  መጥፋታቸው አይቀርም፡፡የዳቢሎስ ልጆች ናቸውና ከመጥፋታቸው በፊት ግን ብዙ የዋህ ና ንፁሃን ዜጎችን የለጊዜቸው ሊያጠፏቸው እንደሚችሉ ታሪክ ይነግረናል፡፡ የዛሬ የእኛ ፋሺስቶች  ድርጊት ታሪክን ላላወቀ ነው እንግዳ የሚሆንበት፡፡ በማይጨው ጦርነት ጥቂት ዘረኝነት ያሰከራቸው “የእናት ጡት ነካሾች ” ባንዳዎች ከፋሺስት ኢጣልያን ገር አብረው ኢትዮጵያዊያንን ሲወጉ  የበዙ ኤርትራውያን ግን ከኢትዮጵያ ጋር እንደወገኑ ታሪክ የመሰክራል፡፡…

ይህ የዘረኝነት (ጎሣዊ ካንሰር ) ከአገራችን በአስቸኳይ መጥፋት አለበት፡፡ሳያጠፋን በፊት፡፡ሳያጠፋን በፊት ካላጠፋነው በስተቀር ሰላም አናገኝም፡፡ እያንዳንዱ ዜጋ አናሳ ጎሣ ይኑረው ብዙ ማንኛውም መብቱ ሊከበርለት ይገባል፡፡

ከዚህ አንፃርም ፣ በምርጫ ክርክር ወቅት የከተማ ነዋሪውን ውህድና ድብልቅ ወይም በጀነራል ጃጋማ ኬሎ በሰርገኛ ጤፍ የተመሰለ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፣ሰብአዊ፤ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊና ማሀበራዊ መብት ለማስጠበቅና በሀገሩ ጉዳይ ያገባኛል ባይነቱ እንዲጨምር   ለማድረግ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቅቡልነት ያለው ፣የሚተገበር  አዳዲስ  የፖሊሲ ሃሳብ ማቅረብ  ይጠበቅባቸዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲም በሥልጣን ላይ ለመሠንበት ከፈለገ እጅግ በጣም እንደሚፈልግም ይታወቃል፡፡በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ እውቅና የተሰጠው ፓርቲ ሁሉ ወደ ምርጫ ፉክክር እገባለሁ የሚለው ፣በህዝብ ቅቡልነት አግኝቶ አገርን እና ህዝቦቿን ለማገልገል እንደሆነ የታወቀ ነውና፡፡

ይሁን እንጂ የብልፅግና ፓርቲ ከወዲሁ ህዝብን ለማበልፀግ ከልባቸው መሰራታቸው በተረጋገጠ ግለሰቦች ተወክሎ በምርጫው ካልተሳተፈ በስተቀር በምርጫው ለማሸነፍ አይችልም፤እንደሚታወቀው የአንዳንድ ለምርጫ ተወዳዳሪ   ገበና ለህዝብ ያልተሰወረ ነውና ፣ምርጫው በአምስቱ የምርጫ ቅቡልነት ማረጋገጫዎች ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ ከሆነ በደ/ር አብይ ተወዳጅነት ብቻ ምርጫውን ለማሸነፍ አይችልም፡፡ ሌሎችም በፊታውራሪዎቻችሁ ተማመናችሁ ፓርቲዎች ከወዲሁ ራሳችሁን ብትፈትሹ መልካም ነው፡፡ ህዝብ ሰው ይፈልጋል፡፡ አገሩን ና ዜጎቿን በታማኝነት ና በእኩልነት የሚያገለግል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop