ለኢትዮጵያ ባለስልጣናትና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይሄን ጊዜ እንጠቀምበት – ሰርፀ ደስታ

ከ60ዎቹ ጀምሮ የበቀሉ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ እግዚአብሔርንና አገርንን ሕዝብን የካዱና የናቁ እርግማኖች በነዙብን የእርግማን አስተሳሰብ ቀስ እያለ ብዙ የሚባል የሕዝብ ክፍል ለዚሁ የወራዶች አስተሳሰብ ባሪያ እንደሆነ እየታዘብን ነው፡፡ እስከዛሬ ወያኔን ዋና ተጠያቂ ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን አስቂኙ ነገር ወያኔና አጋር እርግማኖች ከዘረጉት የአስተሳሰብ ባርነት ቀንበር የገባው በተለይ ደግሞ ፖለቲከኛ ነኝ በሚል በወያኔና አጋር አርግማኖች ሥርዓት ቁማሩ የተመቸው የአርግማኖቹን ሥርዓት ማስቀጠል አለብን የሚል ሙጥኝ ብሎ እየታዘብን ነው፡፡  ዛሬ ሌሊት (እኔ ጋር) ከወንደሜ ጋር ስናወራ ብዙሀኑ ዝም ያለው ጥሩ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ያለው ነው አለኝ፡፡ ችግሩ ግን ዝም ማለቱ እንደሆነ አላስተዋለም ነበር፡፡ የፈለከውን በቁጥር ብዙ ብተሆንም ዝም ካልክ በቁጥር ትንሽ የምትላቸው አገርና ሕዝብን ማፍረሳቸውን የሚያግዳቸው የለም፡፡ በሻሸመኔና በተለያዩ ከተሞች ያ ሁሉ ሲሆን እንደተባለውም ብዙሐኑ ዝም ማለቱ እንጂ ዝም ባይልማ እየታረደ ቢያንስ ራሱን ለመከላከል ይሞክር ነበር፡፡ ዝም ባይል ኖሮ አረመኔዎቹም አይደፍሩትም ነበር፡፡ ችግሩ እንድህ ነው፡፡ ሁለት ጓደኛሞች መንገድ ሲሄዱ ውለው ሲመሽ ይደክማቸውና አንድ ዛፍ  ይተኛሉ፡፡ በተኙበት አንድ ጅብ ይመጣና የአንዱን እግር መብላት ይጀምራል፡፡ ከጎኑ የተኛው ሌላው ጓደኛ የሆነ የሚቆረጣጠም ነገር ሲሰማ እየተበላ ያለውን ጓደኛውን ምንድነው የሚንቋቋው ይለዋል፡፡ እየተበላ ያለውም ዝም በል ጅብ የእኔን አገር እየበላነው ይለዋል፡፡ ጓደኛው በዚህ ጊዜ እንዴ አንተን ሲጨርስ ወዴኔ መምጣቱ አደለም እንዴ ይልና ብድግ ሲል ጅቡ ጥሉ ይሻሻል፡፡ ዝም ያለው ብዙሀን እየተበለ ያለው የኢትዮጵያውያን ዝምታ ይሄን የመስላል፡፡  ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትል ሁሉ ተግባራዊ የሆነ እንግስቃሴና እርምጃ ይጠበቅብሀል፡፡ የማንም ወሮበላ አገር እያፈረሰና ሕዝብን እያመሰ ዝም ባልክ ቁጥር የእነሱ ጉልበትና ቁጥር እየጨመረ ለከፋ አደጋ እየተጋለጥህ መሆኑን አስተውል፡፡

የሚከተሉትን እላለሁ

ለኦሮሞ ባለስልጣናትና ፖለቲከኞች፡- ለይቼ የኦሮሞ ባለስልጣናትና ፖለቲከኞችን የማነሳው አሁን ላለው የኢትዮጵያ ችግር ወነኛ ስለሆኑ ነው፡፡ በእርግጥም ወያኔም ትልቅ ጉልበት የሆናት ከኦነግ ጋር በአስተሳሰብ ባርነት ሥር የከተተችው ብዙ ተማርኩ የሚለው ኦሮሞ ብዙ የኦሮሞ ወጣትን ለወያኔ የአስተሳሰብ ባርነት እንዲገዛ ስላደረገ ነው፡፡ ይሄን በተደጋጋሚ ገልጫለሁ፡፡ ኦሮሞ ዛሬ በብዛት ታሟል፡፡ እንደታመመም ማወቅ የተቻለው አይመስልም፡፡ ጤነኛ ኦሮሞ ነን የሚሉ ትልቅ ሥራቸው ሊሆን የሚገባው ይሄን ማሕበረሰባቸው ውስጥ የገባውን ወረርሽኝ ማጥፋት ነው፡፡ 50 ዓመት ሙሉ በጥላቻና በዘረኝነት ይበልጠውን ኢትዮጵያን የሰሩና የመሩ በደምና በአጥንታቸው አቆይተው ለዛሬ የደረሷትን የኢትዮጵያ  የቀደምት ጀግኖች አባቶቹን ታሪክ አደራ (በደምና አጥንት የተጻፈ) አስክደው በብታችነትና በአልቃሻነት ስሜት በጥላቻና ዘረኝነት ተመረዞ እየማቀቀ እንዲኖር የተደረገው በዋናነት ኦሮሞ ነው፡፡ እንጂማ በምንና እንዴት ባለ ምድራዊ አመክንዮ ኦሮሞ ከወያኔ ጋር ወግኖ መታየት ነበረበት? እንደምናሽሞነሙና አደለም፡፡ እውነቱ ብዙ ኦሮሞ በተለይ ትንሽ ፊደል ቆጠርኩ ያለው ምን አልባት አብዛኛው በዚህ ባርነት ወድቋል፡፡  አዝናለሁ፡፡ ያ በውዴታው የካደው የአባቶቹ አደራና እውነት እርግማን እንደሆነበትም ይሰማኛል፡፡ ዛሬ የወያኔ መመታት ለብዙ ኦሮሞ የውስጥ እግር እሳት ነው የሆነበት፡፡ እንታዘባለን፡፡ ድንቅ ጓደኝነት አለን ያልናቸው ሁሉ ወያኔ ጦርነት በጀመረችበት ወቅት ደስታቸው ወደር አልነበረውም፡፡ በተቃራኒው የኢትዮጵያ ሠራዊት ወያኔን ዋጋዋን መስጠት ሲጀምርና ከቀን ወደ ቀን የወያኔ ሞት አውን እየመጣ ሲሄድ ከትግሬ ወያኔ ደጋፊ ባልተናነሰ ብዙ ኦሮሞ እጅግ ደነገጠ የሰላም ተሸላሚው ሕዝብ እየጨረሰ ነው በሚል ዋና ወንጃይ ሆነ፡፡

አብይ አህመድን ለዓለም ሠላም ኖቤል መታጨትን ሀሳብ ካቀረቡት ምን አልባትም እኔ ከመጀመሪያዎቹ እንዱ ነኝ፡፡ የመጀመሪያውም ካልሆንኩ ነው፡፡ ወቅቱ አብይ ስለኢትዮጵያ በሲመቱ ወቅት የተናገረው ለብዙ ኢትዮጵያውያን እጅግ ተስፋ የሆነበት ከኤርትራ ጋር የነበረን ድሮም የሕዝብ ያልሆነ የባለስልጣናት ሽኩቻ የሆነውን በመሀል የነበረውን ግድግዳ የፈረሰበት ሰሞን ነበር፡፡ ይሄ ማለት አብይ አሜሪካ ዲያስፖራን ለመጎብኘት ከመምጣቱ በፊት ነው፡፡ አብይ አሜሪካ መጥቶ ከነጀዋር ጋር ከተገኛኘ በኋላ ያለውን ሁኔታ በደንብ ሳስተውል ግን ነገሮች ጤነኝነታቸው አጠራጠረኝ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ በነበረኝ ተስፋ በመልካም ደጋፊነት ቀጠልኩ፡፡ ቆይቶ ግን የጠረጠርኩትና የፈራሁት አልቀረም፡፡ አብይ የኖቤል ሽልማት በሚሸለምበት ወቅት ኖቤል ለኢትዮጵያ መሪ መሸለሙ ቢያስደስተኝም አብይ ግን በማጭበርበር አሸንፏል ብዬ የደመደምኩበት ወቅት ስለሆነ እንደሌሎች ብዙም ደስ አላለኝም፡፡  በወቅቱ ያ ኖቤል ለአብይ ሳይሆን በትክክልም ለዛ ታላቅ ሠላም ምክነያት የሆነው የኢትዮጵያና ኤርትራ ሕዝብ መነፋፈቅና የምርም ድንበር በተከፈተ ወቅት የነበረው የሕዝብ ስሜት የኖቤሉ ተሸላሚ ቢሆን ብዬ ነበር፡፡ ኖቤል ሸላሚዎቹንም ዛሬ ከሚደርስባቸው ወቀሳ ባዳነ ነበር፡፡  ያም ቢሆን እንደ እውነቱ ኖቤል ኢትዮጵያ በማግኘቷ እምብዛም አልከፋኝም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምክር ቢጤ ለውድ እህቴ ለመስከረም አበራ

ዛሬ ኖቤል ተሸላሚው አብይ አንድ ዐመት ባልሞላ ጊዜ ጦርነት ከፈተ የሚሉን ያኔ ደጋፊ ሆኖው ሲዘምሩለት የነበሩ ናቸው፡፡ ሲጀምር ኖቤል ተሸልሚያለሁና አገርና ሕዝብ ቢወድምም በአውዳሚዎች ላይ ጦርነት አልከፍትም ብሎ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ መሪ ተጠብቆ ከሆነ አዝናለሁ፡፡ ሲቀጥል ሠላም ሠላምን ስለወደዱ የምትመጣ አደለችም፡፡ ይልቁንም አለም ላይ ያለው እውነት ሠላም የሚገኘው ለጦርነት በመዘጋጀት ነው፡፡ በደንብ ከተዘጋጀህ ጠላት ስለሚፈራህ ጦርነት አያነሳም፡፡ ደካማ ሆነህ ከአየህ የቱንም ያህል ሠላም ብትፈልግ ደም የጠማው ጦርነት ያነሳብሀል፡፡ ለጦርነት ከምታጠፋው በላይ ሕዝብ ያልቅብሀል፡፡  ሲሰልስ ዛሬ በወያኔ ላይ የተደረገው ጦርነት ኖቤል ሸላሚዎቹ ጭራሽ አኮረፉበት እንጂ የኢትዮጵያ መከላከያና የኢትዮጵያ ሕዝብ  ሰው በላ፣ አረመኔና ለምስራቅ አፍሪካ ብሎም ለአህጉሪቱ ሁሉ ትልቅ ነቀርሳ የሆነው እስከአፍንቻው ታጥቆ የነበረውን የዓለማችን ቁጥር አንድ አሸባሪ ኃይል በዚህ ፍጥነት ከምድረገጽ በማጥፋቱ ዳግም ኢትዮጵያ የኖቤል ተሸላሚ በሆነች ነበር፡፡ ለዚህ ሥራ የተባበሩን በተለይም አሸባሪዋ ወያኔ ጦርነቱን ቀጣናዊ ይዘት እንዲኖረውና ኤርትራ በጦርነቱ እንድትቀላቀቀል የሮኬት መዓት ቢያዘንቡባትም በትግስት ለወያኔ ተንኮል ምላሽ ባለመስጠት ግንባር ቀደም ተባባሪያችን የሰላሙ ኖቤል ተካፋይ በሆኑ፡፡ ኢትዮጵያውያንና መላው የምስራቅ አፍሪካ ሕዝብ ብሎም የአህጉሪቱ ሕዝብ ይሄንኑ የሰላም ኖቤል ሽልማት ዘመቻ ለ2021 በጀመሩ፡፡ የዓለም ምላሽ ምንም ይሁን ምን የምድራችንን ቁጥር አንድ ነብሰበላ አረመኔ አሸባሪ ኃይልን በአጭር ጊዜ ከምድር ገጽ ላጠፉ የኖቤል ሽልማቱ እጬ አድርጎ ዘመቻ መጀመሩ ትልቅነት ነው፡፡ እንግዲህ ብዙሀን ዝም ያልክ ይሄን ብታደርግ እላለሁ

ወደተነሳሁበት ስመልሳችሁ ይሄ እውነት ነው ብዙ ኦሮሞን ዛሬም በስልጣን ላይ ያሉትን ሳይቀር ያስደነገጠው፡፡ እንደሰማሁት ለዘመናት የወያኔ ቀኝ እጅ የነበሩት ሌንኞ (ዮሐንስ) ለታ ወያኔ በፖለቲካው የሚኖረው ተሳትፎ መቀጠል አለበት እያሉ ነው አሉ፡፡ እኔ ሲሉ ከሰውዬው አልሰማሁም፡፡ ሊሉ ግን ከሚችሉ ስለሆኑ የተባለው ሐሰት ለመሆኑ ማረጋገጫ የለኝም፡፡ ወያኔ አሸባሪ ተብሎ ይፈረጅ ሲባል አይሆንም ያሉት አሁንም የኦሮሞ ባለስልጣናት እንደሆኑ አስተውሉ፡፡ ጉዳዩ ወያኔና ኦነግ በጥምረት የሰሩት የብዙ ዓመት አረመኔያዊ ወንጀል ስላለ ከወያኔ ቀጥሎ ወደእኛም መምጣቱ አይቀርም በሚል ይመስላል፡፡ የሆነ ሆኖ ምክሬ የኦሮሞ ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞችና ተማርነት የምትሉ በዘረኝነትና ጥላቻ አእምሮአችሁ የመረቀዘ አስቡበት፡፡ አሁን ያለው ችግር ግልጽ ነው፡፡ አዲሱ አረጋ የገዳ ስርአት ትምርት በሚል በተለያየ ክፍል የሚሰጥ መጻፍ እየለጠፈልን ነው፡፡ ጋዳ ለኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያ የታሪክ ክስተት አንዱ ሆኖ ሊሰጥ ይችል ይሆናል በየትኛውም መሥፈርት ግን አንድ የትምህርት አይነት ሆኖ የሚቅርብበት እውነት የለውም፡፡ ይሄን አይነት የሞተ አስተሳሰብ በያዙ ግለሰቦች አሁንም አገር ወደ አደጋ እየተመራች መሆኑ አስተውሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በሰፊው እመለስበት የሆናል፡፡ ይሄ እንደጥቆማ ነው፡፡ የኦሮሞነት እሳቤ ወርዶ ወርዶ በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ደርሷል፡፡ የዛሬው የኦሮሞ ፖለቲከኛ የተቃኘው በወያኔና ኦነግ የበታችነት ስሜት ባርነት ውስጥ እንጂ የሕግ፣ ፍትህና ሥርዓት ፈላስፎቹ በእኔ ፊት አውራሪ ሐብቴ ዲነግዴ (አባ መላ) አደለም፡፡ አዝናለሁ፡፡ ገዳንም ሆነ ሌላውን ምን እንደሆነ የማያውቅ የተበላሸና በባርነትና በበታችነት ስሜት እየማቀቀ ያለ አእምሮ በሕዝብ ላይ ከዚህ በኋላ የሚረጨው መርዝ ሊቆም ይገባል፡፡ በነገራችን ላይ ገዳን የሚያውቁት ቦረና በተወሰነ ደረጃ ሸዋ እንጂ ሌላው አያውቅም፡፡ ቦረና ገዳን ይዞ እንዲቆይ ያደረጉት ደግሞ አጼ ሚኒሊክ ናቸው፡፡ መራራው እውነት ይሄ ነው ፡፡ ይሄን አስመልክቶ ከዚህ መረጃውን አቅርቤ ነበር

ፍትህና እውነትን ማስፈን፡– ኢትዮጵያ ውስጥ ወሮበሎች እየነገሱ ፍትህና ሥርዓት እየጠፋ አሁን መያዣው ሁሉ እየጠፋ አገርና ሕዝብን ለአደጋ እየተጋለጠ ነው፡፡ ሶስት ተቋማት የመንግስት (የሕዝብ) ሆነው ሊደራጁ ይገባል፡፡ ፍትህ፣ ሕግ አስከባሪውና ደህንነቱ አንዲሁም መከላከያው፡፡ እነዚህ ተቋማት ማለት የአንድ አገር መንግስት ማለት ናቸው፡፡ መንግስ ማለት የፖለቲካ ፓርቲ አደለም፡፡ በምርጫ የሚያሸንፍ የፖለቲካ ፓርቲ የመንግሰት ሥራ አስፈጻሚ እንጂ መንግስት አደለም፡፡ መረዳት ያልቻልነው አንዱ ችግር ይሄ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ተቋማት ፍጹም አገራዊና ገለልተኛ ሆነው ካሉ ማንም ቢጨፍር መስመር ካለፈ ልጓም ይገባለታል አስፈላጊም ሲሆን ይወገዳል፡፡ ብዙ አገራት ፓርላማ በትነው እንደ አገርና መንግስት ሲቀጥሉ የምናየው በእነዚህ ተቋማት ነው፡፡ እነ ወያኔ አሁን የፈጠሩት አስተሳሰብ ፓርቲ መንግስት ነው የሚል እሳቤ ሁሉም ተሸክሞ ቤተመንግስት እየገባ አገር እንደ አገር መቀጠል አትችልም፡፡ ዛሬ የአሜሪካውን መሪ ትረምፕን ከሥልጣን እያወረዳቸው ያለው ሕግ እንጂ በደጋፊና ቲፎዞ ቢሆንማ ከባይደን የሚፎካከር ድምጽ አግኝተዋል፡፡ የአገሪቱን መንግስታዊ ደህንነት የሚጠብቁ ጠንካራ ተቋማት ስላሉ ግን በሕግ አግባብ እየተሸነፉ ነው፡፡ በዛው ልክ ደጋፊዎችንም አግባብ በአለው መልኩ ማስተናገድና ኃላፊነት በሚጠይቅ ሁኔታ የአገርን ሠላም ማስቀጠልን ሁሉ የተሸከሙ ተቋማት አሉ፡፡ ይሄ እውን ሲሆን ማንም እንደፈለገው አይጨፍርም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:   የአፋልጉኝ ጥሪ ለምንና ለማን ? - ጠገናው ጎሹ

የወያኔና ተባባሪ የእርግማን ምልክቶችና ሥርዓቶችን በአስቸኳይ ማስወገድ፡- ሰሞኑን የአመራ ክልል ሀውልት ማፍረስና የባህርዳርን ኤርፖርት ስም መቀየሩን አይተናል፡፡ እኔ ይሄን ያህል ጊዜ በመዘግየቱ ባዝንም ብዙዎችን ያስደሰተ ሆኗል፡፡ ዛሬ ሕዝብ ጉልበት ስላለው ስለፈሩ ይመስላል እንጂማ ባለፉት ሁለት ዓመታት የት ነበሩ፡፡ በዚህ አዝናለሁ፡፡ ዛሬም ከወያኔ የተሰጣቸውን ባንዲራ እያውለበለቡ እናያለን፡፡ ቢያንስ ሌላ ተለዋጭ እስከሚወስኑ በአዋጅ ያን ባንዲራ በአማራ ክልል ማውለብለብ ሊታገድ በተገባው፡፡ አሁን ያለው ሥርዓት ሁሉም እንደወረደ ከወያኔ የተወረሰ ነው፡፡ ሕገ መንግሰት የተባለው የአገር ጠንቅ፣ የዘር ፌደራሊዝም፣ የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የተቀመጠው ኮከብ፣ የአኖሌ ሀውልት፣ ሌላም ሌላም፡፡  በነገራችን ላይ አኖሌን የሚፈልጉት አሮሞን በበታችነት ባርነት ይዘው የንግድ እቃ አድርገው ለመቀጠል የሚፈልጉ እንጂ የኦሮም ሕዝብ ይቅርና የአርሲ ሕዝብም አደለም፡፡ የሚገርም ሀውልት ነው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሕዝቡ እራሱ ያፈርሰዋል፡፡ የጀግንነትና የሕዝብን ስነልቦና ቀና የሚያደርግ ሀውልት መስራት ያባት ነው፡፡ በውሸት ትርክት ህዝብን እስከወዲያኛው እንዲህ ነበርክ ታሪክህ የተያያዘው እንዲህ ባለ የባርነት ግፍ ነው እያሉ ትውልድን በጥላቻ፣ ዘረኝነትና የበታችነት ስሜት መግደል ይልሀል ይሄ ነው፡፡ ዛሬ በኦሮሞ ዘንድ የታላላቅ ጀግኖች ታሪክ ትንፍሽ አይባልም፡፡ ነውር ነው፡፡ እንዲህ ትውልድን እየገደለ ያለ ተማርኩ የሚል ፖለቲከኛ ነው እንግዲህ መሪ ነኝ የሚለው፡፡

ሁሉም ዲያስፖራ ገንዘብ በሕጋዊ መልክ ወደ አገር ቤት መላክ፡- የወያኔ ትልቁ የገቢ ምንጯ ዲያስፖራው እንደሆነ ከበፊቱም የሰማኝ ነበር፡፡ ለዛ እርግማንም እግዚአብሔር አላጋለጠኝም፡፡ እኔ አንድም በሕጋዊ መንገድ ገንዘብ ከሚያስተላልፉ የገንዘብ አስተላላፊዎች ውጭ በግለሰቦች ገንዘብ ወደ አገር ቤት ልኬ አላውቅም፡፡ አሁን ላይ ሳስበው የበለጠ ትልቅ እርግማን አንደነበር ይሰማኛል፡፡ በቅርቡ አብይ ይሄን ችግር አንስቶ ሲናገር ነበር፡፡ በትክክልም የምጋረው ዋነኛ ሕዝብ እየታረደበት ያለው ገንዘብ ከዚሁ ከዲያስፖራ የሚላክ ገንዘብ እንደሆነ አሰብኩ፡፡ ይሄንንም በሌላ ጊዜ ራሱን ችሎ አነሳዋለሁ፡፡ ከምንም በላይ ግን ዛሬ ነገ ሊባል የማይገባው ሁሉም ወገን አለኝ የሚልና ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሀሉ ከሕጋዊ አስተላላፊዎች ውጭ ገንዘብ ወደ አገር ቤት ባለመላክ የወገንን እልቂት ሊያስቆም ይገባል፡፡ በቃ ወያኔ በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ገንዘብ ሁሉ ዘርፋ በአጃቸው አስገቡ በኋላ ወደ ዶላር መነዘሩት፡፡ አሳዛኙ ነገር ዶላሩ አገርቤት እንዳይገባ በማድረግ አገር እንዳትለማ ከማድረግ ባሻገር ዛሬ እንደልባቸው በዶላር በመንቀሳቀስ ሕዝብን እያረዱበት ይገኛሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ሚዲያ ነን የሚሉ መናገር አይፈልጉም እንጂ እውነታው ከምንም በከፋ በሕዝብና አገር ላይ የተደረገ ወንጀል ነው፡፡ እንግዲህ አስቡት ከሁሉም አገር የሚላከው ገንዘብ እየተመነዘረ ያለው በሕገወጥ ነው፡፡ ከጥቂት በቀር፡፡ ይሄ ሁሉ ገንዘብ በማን እጅ እየገባ እንደሆን አስቡት፡፡ ኢትዮጵያን በረፉበት ገንዘብ መልሰው ዶላር እየገዙ ሕዝብ እየጨረሱ ነው፡፡ ዲያስፖራ ነኝ የምትል እምነት ያለህ ሁሉ በዚህ መልኩ የምትልከው ገንዘብ ሕዝብ እየታረደበት የለ እርግማን እንደሆነ አውቅህ ከዛሬ ጀምሮ ሕጋዊ መንገዶችን ተጠቀም እላለሁ፡፡

ሌላው መንግስት ተብዬው የዚሁ የሕገወጥ የዶላር ንግዱ ዋና ተባባሪ ነው፡፡ ምክነያቱም አብዛኞቹ ዶላሩ ወደአገር ቤት ከመግባቱም በፊት ሆነ ከገባም በኋላ በሕገወጥ እየነገዱበት ያሉትን ሆን ብሎ እድል ሰጥቶ እናያለን፡፡ አገር ቤት ከገባ በኋላ እንኳን እንደፈለገው ሆኖም አብዛኞቹ የዶላር መግዣ ሱቆጭ ጭራሽ ከባንክ ፊት ለፊት ነው ያሉት፡፡ ይታወቃሉም፡፡ እነዚህ ሕገወጥ ቢሆኑም ግን ከውጭ ገና ዶላሩ ሳይገባ በብር እንደሚቀይሩት አደለም፡፡ ቢያንስ አገር ቤት ዶላሩ ከገባ ወድም ቢሆን ለአገር ይውላልና ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ሁሉንም መንግስት ተብዬው እንደ ልዩ የደህንነት ችግር በማየት እርምጃ መውሰድ ቢፈልግ ብዙም ከባድ አይደለም፡፡ ግማሾቹ ጭራሽ ብንክ ውስጥ የሚሰሩ የባንክ ሠራተኞች እንደሆኑም እናውቀለን፡፡ ኢትዮጵያን የሚያህል አገር ዛሬ እነ አሜሪካና አውሮፓ በጥቂት መቶ ሚሊየን ዶላር እቀባ ሲየስፈራሩ ይገርመኛል፡፡ ባለፈው አሜሪካ 150 ሚሊየን ያዝኩ ብላን ነበር አሁንደ ደግሞ አውሮፓ 90ሚሊየን፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ዲያስፖራው ወደ አገር ገንዘቡን በአግባቡ ማስገባት ቢቻል እኮ እነዚህ እርግማኖችን ከእነጭርሱም ምናቸውንም አንፈልገውም፡፡ በአረብና ሰሜን አሜሪካ ብቻ ያለው ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ በቂ ነው፡፡ በአፍሪካ በተለይም ደቡብ አፍሪካ ያለው ራሱ ቀላል አደለም፡፡ ለመሆኑ ስንት ሚሊየን ገንዘብ የሚልክ አለ ወደ ኢትዮጵያ? ከዚህ ጋር በተያያዘ መንግስት ነኝ የሚለው አካል የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ አሁን ገንዘብ በተቀየረበትና ይሄ ገንዘብ ተመልሶ ወንበዴዎች እጅ በብዛትከመግባቱ በፊት ሊያድርገው ይገባል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የከተሞቻችን ፅዳት እንዲህ ከሆነ መሰልጠን መገለጫው ምን ይሆን? - በ ሙሉጌታ ገዛኸኝ

የውጭ ምሁራንና ባለሐብቶች አገርን ማሰብ፡- ለዚህ አብይ መጀመሪያ እንደተናገረው ቀጥሎ ቢሆን ትልቅ ቦታ በተደረሰ ነበር ባለፉት ሁለት ዓመታት፡፡ ያቺ በወር አንደ ዶላር ያላት እንኳን ጥቂት ሳምንታት ብዙ ከሄደች በኋላ የአብይ ንግግር በተግባር ከመሆን ይልቅ ጭራሽ ይኢትዮጵያ ጠላቶችን በተግባር በኢትዮጵያ እድል እንዲኖራቸው መሸፈኛ ሆኖ ሲገኝ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ውል ወጡ፡፡ እልሁና ቁጭቱ በደንብ መጥቶ ነበር፡፡ ከወያኔ ወሮበላ ወደ ኦሮሞ ኦነጋውያን ወሮበሎች ነገሮች እንደተላለፉ በተረዳ ጊዜ ኢትዮጵያዊው ሁሉ አዘነ፡፡ ይህ የማይካድ የሆነ እውነት ነው፡፡ አዲስ አበባ በይፋ የወሮበሎች መፈኝጫ ሆነች፡፡ ከወያኔም በከፋ፡፡ አሁንም ይህን ወንጀል የፈፀሙ ሲሾሙ እንጂ በሕግ ሲቀጡ አናይም፡፡ የሕዝብን ኮንደሚኒየሞችና የከተማውን ቦታዎች በወሮበላነት የዘረፈና ያስዘረፈ ከንቲባ ዛሬ ሚኒስቴር ሆኖ በተሾመባት አገር ኢትዮጵያውን ከማን ጋር ነው ውላቸው? በተቃራኒው ይሄን የዝርፊያ ዘመቻ ሲያጋልጥና ሕግና ሥርዓት እንዲከበር ብዙ መስዋዕትነትን የከፈለው እስክንድርና አጋሮቹ ይሄው ዛሬ በወሮበሎች ውሳኔ እስርቤት ከነፍሰገዳዮች ጋር ተከሰው እናያለን፡፡ ይገርማል፡፡ ይሄ ሁሉ በአስቸኳይ ሊወገድ የሚገባው ነው፡፡ እንግዲህ የመንግሰት አሰራር በፖሊሲ፣ ሕግና ሥርዓት ብቻ የሚወሰን ሲሆን ያቺ አንድ ዶላር በቀን የምትለዋ ቁጥቁጥ ብቻም ሳይሆን ዳጎስ ያለ ገንዘብ ወደ አገር ቤት ሊያስገቡ የሚችሉ ምሁራንና ባለሀብቶችም ነበሩ፡፡ እኔ ራሴ የማሰባስበው ትልቅ የምሁራን ስብስብ ወደ አገር ቤት ከተለያዩ የገንዘብ ለጋሽ አካላት በፕሮጄክት መልክ ወደ ኢትዮጵያ ለማስጋበት እስካሁንም ትልቅ እንቅስቃሴ ላይ ነን፡፡ በፊት ጀምረነው በተፈጠረው ተስፋ አስቆራጭ የኦሮሞ ኦነጋውያን ወሮበሎች በወያኔ መተካት ምክነያት ቢቋረጥም አሁን በተፈጠረው አጋጣም ዳግም መንግሰት ነኝ የሚለው አካል እንዲያስበበት ተስፋ በማድረግ አሁን ላይ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም እውን የሚሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ለዚህ ግን መንግስት ነኝ የሚለው አካል ቁርጠኝነቱ ወሳኝ ነው፡፡ እንግዲህ እስከዛሬ ሲሳበብ የነበረው ወያኔ ወድቋል፡፡

በነገራችን ላይ መንግስት በፖሊሲና ምሁራኑ በሚጠይቁት ሁኔታ ተባባሪ ከሆነ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የሴፍቲ ኔት በሚል ሕዝብን በለማኝነት ተፍንገው የያዙ አሰራሮችና እርዳታ ላይ ጥገኛ የሆኑ ፕሮጄክቶችን ሁሉ መባስቆም ሙሉ በሙሉ ልማት ላይ የተመረኮዘ የሕዝብ የምግብ ዋስትና ብቻ ሳይሆን ትርፍ ምርት በማምረት ትልቅ ገበያንም መፍጠር የሚያስችሉ ንድፎች ይዞ የተነሳ ስብስብ ነው ስብስባችን፡፡ የወያኔ ባለስልጣናት ሲነግዱባቸው የነበሩ የአላማጣ፣ ሁመራ መሬት ብቻ በአግባቡ ማምረት ቢችል እርዳታ የሚባል ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ይቆማል፡፡ ሁሉም አካባቢ እንደየ ቦታው ሁኔታ የራሱን ምርት በማምረትና እሱ የማያመርተውን ከሌላ በማመጋገብ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በአስተማማኝ ሁኔታ በምግብ በማስቻል ለአካባቢ አገራት ለመካከለኛው ምስራቅ ሳይቅር ትልቅ ገበያን መዘርጋት ይቻላል፡፡ ይቻላል ስንል ደግሞ ምናብ አደለም ጥናታዊ እውነቶችን በንተራስ እንጂ፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ወያኔ እንደወረደች የፖሊሲ ለውጥ ይመጣል በሚል ትልቁ ተስፋ ነበር፡፡ ብዙም የተለየ ነገር አልተፈጠረም፡፡ አሁንም መነግስት እንደመንግስት ቁርጠኛ ከሆነና በተግባር ከተገለጠ ይሄ ሕልም ሳይሆን እጅ ላይ ያለ እውነት ነው፡፡ በወያኔ ፖሊሲና ሥርዓት ግን በምንም መልኩ ይሄ የምናስበው እውነት እንደማይሆን እናውቀዋለን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ!

1 Comment

  1. “አብይ አህመድን ለዓለም ሠላም ኖቤል መታጨትን ሀሳብ ካቀረቡት ምን አልባትም እኔ ከመጀመሪያዎቹ እንዱ ነኝ፤፤”
    ሰርጸ ደስታ – aka አማራው ዶ/ር አወል አሎ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share