እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ስለሚጠብቃት እንጂ ብዙ ጊዜ እጅግ ዘግናኝ ሊሁኑ የሚችሉ አደጋዎች ነበሩ፡፡ ከሁሉም የከፋው አደጋ ግን በአሸባራ ወያኔ የታሰበው አደጋ ነበር፡፡ በዚህ ዛሬ የወያኔ አሸባሪ ቡድን ሰማይ ከነካው ትዕቢት በዚህ ፍጥነት የተዋረደበት ሂደትን ሳስብ ደግሞ የእግዚአብሔርን በመጽሐፍ የአነበብንውን ተዓምራዊ ክስተቶችን ያስታውሰኛል፡፡ እውነትም ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር የዘረጉ ልጆች እንዳላት ተረዳሁ፡፡ ወያኔ ምድር ላይ ከአሉ አሸባሪዎች ሁሉ የበለጠ መሳሪያ እጇ ላይ ነበር፡፡ ታስቦ የነበረውም በተለይም በአማራ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ ማውደም አዲስ አበባን ጨምሮ ሌሎች ትልልቅ ከተሞችንም የጦር ቀጠና ማድረግና ከፍተኛ የሆነ እልቂትን መፈጸም ነበር፡፡ ይህ ዝግጅት የአንድ ሰሞን አይምሰላችሁ፡፡ በመንግስትነት በነበረችበት ጊዜ ስታከማች የነበረቸው እንጂ፡፡ ከመከላከያው ከዘረፈቸው ሌላ ማለቴ ነው፡፡ የዛሬ ሶስት ዓመት ትግሬዎችን እየመረጠች ከጎንደር በአውሮፕላን ወደመቀሌ በሰበሰበችበት ወቅት የወያኔን ጥሪ ተቀብለው የሄዱት ትግሬዎች ዛቻቸው እናንተን ዓመድ አድርገን አገሩን ተመልሰን እንኖርበታለን የሚል እንደነበር በወቅቱ ሰምቻለሁ፡፡ አሁንም የሚያሳዝነኝና የሚያሳስበኝ ብዙ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞቹ በተለይም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ትግሬዎች መረጃ ተሰጥቷቸው እንደውም ቤተሰባቸውን ወደመቀሌ እንደወሰዱ ይነገራል፡፡ የተወሰኑት ግን አዲስ አበባ ቆይተው ጦርነቱ ሲጀመር እነሱም ከአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ እልቂትን የሚፈጽሙ አደጋቸዎችን ለማድረስ ነበር፡፡ አንዳንድ ከሌላ ማህበረሰብ የሆኑ የወያኔ የጥፋት ድግስ ተባባሪዎች ቢኖሩም ለእነሱ እንዲህ ያለው ሚስጢር አይነገራቸውም፡፡ በወቅቱ ጦርነት ባህላዊ ጫወታችን ነው እያሉ ሲያቅራሩ የነበሩትም የጥፋት ዝግጅቱ ስለተነገራቸውና ወያኔ በአስተማማኝ ሁኔታ ታሸንፋለች ብላ ነበር፡፡
እግዚአብሔር ግን እንደ እኛ ሳይሆን በእሱ እይታና ምን አልባትም እንደተባለው እጆቻቸውን ወደሱ ስለዘረጉ ሰዎች ይሄ ጥፋት ሳይሆን ወያኔን አሁን በምናው ሁኔታ እናገኛታለን፡፡ ይሄ ወያኔ ያሰበቸው ጥፋት እውን ቢሆን ኖሮ ግን ኢትዮጵያ ከጥፋቱ የሚተርፍ እንኳን ቢኖር ወደከፋ እርስ በእስርስ ጦርነት እንደምትገባ ነበር፡፡ መቼም በየከተማው ወያኔ ያዘጋጀቻቸው ትግሬዎች አደጋ ሲያደርሱ ትግሬን ሁሉ ወደማጥቃት እንደሚገባ፡፡ አጋጣሚውን በመጠቀም ደግሞ ሌሎች ጥፋቱን እንሚያከፉት እሙን ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ዛሬ ላይ እንደሆነውና ቀሎ እንደምናው አደለም፡፡ የተወጠነውን ሴራ አስከፊነት ሳስብ በድጋሜ እላለሁ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በልዩ ሁኔታ እንደሚጠብቃት ተረዳሁ፡፡ የመከላከያችንንም ስኬትና ብልሀት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነው፡፡ ወያኔዎች ትንሽ እንኳን እንጥፍጣፊ ስብእና ስሌላቸው መሳሪያውን ተሸከሙት እንጂ እውቀቱም፣ ወኔውም እንዲከዳቸው ሆኑ፡፡ ዛሬ ላይ ምን ዓልባት ጥቂቶቹ ማሰብ ጀምረው ይሆናል፡፡
ይሄ ሁሉ ምልክት ቢሆነን፡፡ በተቃራኒው ብዙ ኢትዮጵያውያንን ወደአንድነት ያመጣና በእርግጥም የኢትዮጵያ ጠላት የሆኑትን በግልጽ አበጥሮ ያወጣ በመሆኑ ትለውቅ እድል እንደሆነ አስባለሁ፡፡ በመሆኑም ሁላችንም ዛሬ ቀሎ እንዳገኘነው አናስብ፡፡ ታስቦ የነበረውን ጥፋት እናስተውል፡፡ ባለስልጣናት እባካችሁ ተማሩ፡፡ ቅንነትና ኃላፊነት ሳይሆራችሁ ስልጣኑን ብትወዱት አጥፊያችሁ እንደሆን አስተውሉ፡፡ ለነገሩ ለመማር ወያኔን መጠበቅ ባላስፈለግም ነበር፡፡ ታላላቅ ነን ያሉ ስንቶች ምድር ላይ በእኛው ድሜ እንዳለነበሩ ሆነው ሲወድቁ አገራቸውንና ሕዝባቸውንም ማባሪያ ለሌለው ችግር ሲዳርጉ አይተናል፡፡ ሳዳም ሁሴን፣ ጋዳፊ ሌሎችም ይኖራሉ፡፡ በእኛው አገርም እየሆነ ያለው አዙሪት ቢገባን ይሄ ነው፡፡ በ60ዎቹ እግዚአብሔር የለም ብሎ የተነሳው ትውልድ እርስ በእርሱ መተላላቁ ሳያንስ እስከዛሬም የቀጠለ የአጥፊነት መንፈስ ተጠናውቶት ይሄው ትውልድን ሁሉ በክሎ አገራችንን ለአደጋ ዳርጎ እናያለን፡፡
አሁን ስልጣን ላይ ያላችሁ ባለፈውም እንደጠቆምኩት ይሄ ሁለተኛ እድላችሁ ነው፡፡ ሌላ ጊዜ ተመልሶ ላታገኙት ትችላላችሁ፡፡ የመጨረሻው ሊሆን ስለሚችል፡፡ አስቡበት፡፡ ሕዝብ አገር ማለት ምን ማለት እንሆነ ይግባችሁ፡፡ ትልቁ ቤት ስራችሁ ወያኔ የፈጠረቸውን መዋቅር፣ አሰራርና ሕግና ደንብ መቀየር ላይ ይሆን ወያኔ በፈጠረቸው አስተዳደራዊ መዋቅርና አሰራር መቀጠል ሌላ ጥፋት መጋበዝ እንደሆነ እወቁ፡፡ ወያኔ የፈጠረቻቸውን አሰራሮች፣ ደንብና ሥርዓቶች በሙሉ ከኢትዮጵያ አስወግዱ፡፡
ለፖለቲከኞች (ስልጣን ላይ ያላችሁትንም ተቃዋሚዎችንም) ለስልጣን ከመጓጓት ይልቅ ወደፊት በዚህ ከቀጠለ ወደ አደጋ እየሄዳችሁ እንደሆነ ተረድታችሁ ከስልጣን በፊት አገር ለማስተዳደር የሚያስችል ሥርዓት ሥሩ፡፡ ሁሉም ቁጭ ብሎ አስቦ አገርና ሕዝብ የሚተዳደርበትን ሥርዓት ያዋቅር፡፡ አዲስ መፍጠር አይጠበቅም ከቀድሞው የአገሪቷ እሴቶች ከሌሎችም በመጨመር መስራት ይቻላል፡፡ ቢያንስ ከምንም በፊት የነገሮች ሁሉ ምንጭ የሆነው ሕገመንግሰት የተባለው ሰነድና ጎሳን መሠረት ያደረገ ፖለቲካ እንዲቀር ሥሩ፡፡ በዘር ማንነት ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አቃቁሞ በኢትየጵያ ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ በሕግ ይታገድ፡፡ በመሆኑም ምርጫ የተባለው ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ ቅድሚያ መስተካከል የሚገባቸው ነገሮች ይስተካከሉ፡፡ አሁን በአለው ሁኔታ ወደምርጫ ቢኬድስ ምን አዲስ ነገር ሊመጣ ነው? እንደገና ሌላ አደጋ ካልሆነ፡፡ መቼም ምርጫ በተደረገ ቁጠር የሚሆነው እናውቀዋለን፡፡ ያም ባይሆን በወያኔ አሰራር እየተመሩ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያን እንደ አገር ማቆየት አደጋ ነው፡፡
የወያኔ አሰራር ለጥቂቶች እጅግ ተመችቷቸዋል፡፡ ለኢትዮጵያውያን ግን ሲኦል ነው፡፡ ብዙዎች ግን በወያኔ አመለካከት ስለተለከፉ የጥቀም ተካፋይ ባይሆኑም የወያኔ መርዝ አእምሯቸውን በዘረኝነትና ጥላቻ ስለበከለው የወያኔ ስርዓትን መቀጠል እንሚፈልጉት አውቃለሁ፡፡ ብዙ ትግሬ ዛሬ የወያኔ ደጋፊ ሆኖ ታይቷል፡፡ በትግራይ ያለውን እውነት ስንታዘብ ግን ወያኔ እራሷ ከፈጠረቻቸው የዘረፋ ድርጅቶች በቀር የግል የሚባል ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር ድርጅት እንኳን የለም፡፡ ይሄ ከሌላው ክልል ትግራይን ለየት የሚያደርገው እውነት ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ያስብበት፡፡
ሌላው ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ የማስጠነቅቀው የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ ባልስልጣናትና አንዳንድ ምሁራንን ነው፡፡ ዛሬ በግልጽ የወያኔን ቦታ የያዘ የኦነጋውያን ቡድን እንዳለ ይሰመርበት፡፡ ይሄ ኦሮሞንም እስከዛሬ ከኖረውም በከፋ ችግር ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ሁሉም ቢያስብበት ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ የምናየው እውነታ ዝርዝር ውስጥ መግባት አልፈልግም፡፡ ብዙ ጊዜም ስለተናገርኩት፡፡ ግን ከወያኔ እንኳን ቢሆን ተማሩ፡፡ ሰሞኑን በወልቃይት ፀገዴና ራያ ጉዳይ የኦሮሞ ኦነጋውያን እብድ ሆነው ታዝበናል፡፡ አይምሰላችሁ፡፡ ነገሮች እውነት ላይ ናቸው፡፡ በየትኛውም መስፈርት ቢሆን የእነዚህ ቦታዎች ወደነበሩበት የጎንደርና የወሎ መሬት ሆነው መተዳደራቸው ግድ ከመሆንም በላይ ነው፡፡ ለመሆኑ ግን እንደው ይሁን ተብሎ ወደ ትግራይ ቢካለሉ ሲግድላቸው የነበረው የትግሬ ፖሊስ አሁንም ፖሊሳቸው ሊሆን ነው? ሲጀምር አብዛኛው በሚባል ደረጃ ትግሬ በወያኔ መርዛማ አመለካከት ተበክሏል፡፡ እንኳንስ በተግባር የወያኔን አረመኔነት ለ30 ዓመት የወረደበት ወልቀይትና ጸገዴ ራያ ይቅርና ትግራይም ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከትግሬ አስተዳዳሪዎች ነጻ ቢሆን ጥሩ ነው፡፡ አየን እኮ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ሳይቀሩ ምን ያህል ከወያኔ ጋር ትስስር እንዳላቸው፡፡ ለትግራይ ደሀ ሕዝብ ትግራይ ከሌላውም በከፋ መከራ የሚያይባት ስትሆን ለወያኔ ደጋፊዎች ግን መፈንጠዣቸው ነበረች፡፡ ትግራይን ማስተዳደር የሚችል ሰው እውን ከወያኔ ያልተነካካ ማግኘት ይቻል ይሆን፡፡ ጥቂት እንዳሉ ብናውቅም ሙሉውን ትጋራይ ግን ሊያስተዳደር የሚችል ለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡ የአሁኑ የኦሮሞው ኦነጋውያን እውነት ከወያኔ በከፋ ቢሆን እንጂ አያንስም፡፡ የከፋ የሚያደርገው ከጥቅምም ይልቅ ጥላቻንና ዘረኝነትን ስለሚያስቀድም ጭምር ነው፡፡ ወያኔንም እሰከዛሬ ጎልበት ሆኗት የኖረውም ይሄው የኦነጋውያን ዘረኝነትና ጥላቻ መርዝ ነው፡፡ ስልት እንኳን ሳይቀይሩ ነው አሁን ያላቸው እንቅስቃሴ ከወያኔ የቀዱት፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! ማስተዋሉን ይስጠን!
አሜን!
ሰርፀ ደስታ