እስኪ ልጠይቃት ኢትዮጵያን ምን ነካት፤?
አይኖቸ እያዩ እንደ እናት አልችልም ፍጹም ጸጥ ማለት።
በግብጽ ተጀምሮ እስከ ክርስቶስ ልደት፤
በጀርመን በሂትለር ድግሞም በሌላ አህጉራት፤
ተጨፍጭፈው ነበር የአይሁዶች አባላት።
እኔ አይደለሁም ይህን ያወራሁት፣
ተምዝግቦ አለ ክፍታችሁ አንብቡት።
“ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች በመከራ ገዙአቸው።…
እናንተ የዕብራውያንን ሴቶች ስታዋልዱ፥
ለመውለድ እንደደረሱ ባያችሁ ጊዜ፥
ወንድ ቢሆን ግደሉት ሴት ብትሆን ግን በሕይወት ትኑር።
… ፈረዖንም የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፥
ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
ሴቲቱም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅም ወለደች፤ … ሦስት ወር ሸሸገችው። ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፥
የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤
ሕፃኑንም አኖረችበት፥ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው።…” (ዘጸአት 1፡13-20 እና 2:2-10)
የአይሁድ ልጅ የሱስም ሲወለድ የሆነው ተነጽፏል፤
ሄሮድስ ንጉሱም ፈረዖን እንዳደረገው ሕፃናትን አርዷል።
የአይሁድ እናቶችም እጅግ አንብተዋል፣
ዛሬም የኢትዮጵያ አማሮች የዘመኑ አይሁዶች
ሊጽናኑ አልቻሉም በእንባቸው ታጥበዋል።
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤
ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤
የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።” (ኤርምያስ 31:15)
እላንት የሰው ልጆች እስኪ ያንን ታሪክ ንገሯት፤
ያጽናናት እንደሆን ያችን የአማራ እናት።
ያአይሁድን ጭፍጨፋስ ታሪክ መዝግቦታል፤
በዋሽንግተን ዲሲ ትራምፕ በነገሰበት፣
ድርጊቱ እንዳይደጋገም ሃውልት ተሰርቷል፤
እዩ ተመልከቱ የዘመኑ አማሮች አይሁዶች ሆነዋል።
እስኪ ልጠይቃት እነሡ ራሳቸው አገሪ የሚሏትን፤
በጣሊያን ወረራም በዱር በገድሉ የተሰውላትን።
ኢትዮጵያን ምን ነካት፤?
አማሮች እንደ ከፍት ሲታረዱ እያየሁ፣
እንደ እናት አልችልም እንዲያው ጸጥ ማለት፤
ደግሚም ልጠይቃት አገሪን ኢትዮጵያን ከቶ ምኑ ነካት።
ተው አትከልክሉኝ እኔ ላልቅስላት፤
“አይጥ በበላ ያው ዳዋ ተመታ” እንዲሉ፣
ስደቱ ፍንቀላው ግድያው በዝቶባት፣
በዚአያች በአማራ እናት፤
በአይኖቸ እያየሁ በጀሮም ሰምቸ፣
እናት በመሆኔ አልችልም ጸጥ ማለት።
ተው አትከልክሉኝ
ሌላ ማድረግ ባልችል እኔ ላልቅስላት።
አገሪ ኢትዮጵያ ምኑን መርዝ ጠጣሸው፣
እርሃቡስ ቢበዛ ምኑን ምርዝ በላሽው፤
ለቀብር ዳርጎሻል ከሆድሽ ያደገው።
ተው አትከልክሉኝ ለዚያች ለአማራ እናት፤
ሌላ ማድረግ ባልችል እኔ ላልቅስላት፤
በጎጧ ባሐገሯ ልጆቿን እያየሁ ሲያርዱባት።
© Lemlem Tsegaw, October 25, 2020
Tsegawlemlem853@gmail.com