October 3, 2020
6 mins read

ዛሬ ሌላ ቀን ነው!! – አንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ

መስከረም 23፣ 24፣ 25-30/2013 እንደ ሰኔ 2010 / 11/ 12 አይደለም!!
አንድነት ይበልጣል – ሐዋሳ – መስከረም 23 ቀን 2013

ከፖለቲካ፣ ከሕግ የበላይነት፣ ከጸጥታ፣ ከኃይል ሚዛንና ከአሰላለፍ አንጻር ዛሬ ሌላ ቀን ነው!! ለዚህ ብዙ ማሳያዎች አሉ፤ በርካታ የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ሆኖ …፡
– ዛሬ አብዛኛው የኦሮሞ ወጣት ባኗል – እየሰከነ ነው፤ ወያኔም በትግራይ ወጣቶች (ፈንቅል) እና በውስጥ ቅራኔ ተወጥሯል …፣
– ዝምታን መርጦ የቆየው የኦሮሞ ሕዝብ ለጽንፈኞች ጆሮውን መስጠት እያቆመ፣ ዝምታውን በመስበርም ¨በቃ!¨ ማለት እየጀመረ ነው፤ የትግራይ ሕዝብም እንዲሁ …፤
– የኦነግ አመራር ጥያቄና ዓላማዬን ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ነው የማራምደው ብሎ ራሱን ከሸኔ/ሽፍቶች መለየቱን አስታውቋል፣ የወያኔ የትሮይ ፈረሶች/በጎች እንደወትሮው ¨ላታቸውን¨ ውጭ ለማሣደር መድፈር አቁመዋል፣
– ዋነኞቹ የሽፍቶቹ መሪዎች፣ አሰማሪዎችና ከፋዮች ከሥራ ውጭ ከሆኑ ሰነባበተ፤ የሚያገግሙም አይመስለኝም፤
– ወያኔ የብር ኖቱ ቅያሪ ተጨምሮባት መተንፈስም እያቃታት ነው! (የእንቅልፍ ኪኒን ገበያው ደርቷል ነው የተባለው? – ይህ የ Over ደረጃ ብቻ ሣይሆን መመለሻ የሌለው የ ደረጃም ነው፤) …
– የግብጹ አልሲሲም በሕዝባዊ ተቃውሞ ተወጥሮአል፤
– የኤርትራ መንግሥት ቀጠናውን ለማተራመስ ለሚሞክርና የኢትዮጵያም ጠላት ለሆነ ኃይል፣ ጆሮና መሬት አለመስጠት ብቻ ሣይሆን ይቀጠቅጠዋል! (በኤርትራም የጥገና ለውጥ ቢጀምሩ የበለጠ ጥሩ ይሆን ነበር)፤
– የኢትዮጵያ መንግሥት ዛሬ እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት በታሪኩ ታይቶ የማይታወቅና የማይታጠፍ ነው፤ በፖለቲካ ቁማር ጨዋታ ጉራ የሚነዙትም መስከን ግድ ሆኖባቸዋል፤
– በገዢው ፓርቲና በመንግሥት ውስጥ የተሰገሰገው ቀልባሽና ባለተራ ኃይልም ቀስ በቀስ እየተዳከመ ነው፤
– የጸጥታ ኃይሎች ቁርጠኝነትና ዝግጁነት የሚያስመካ ነው፤
– አማራና ክርስቲያንን ጨምሮ ቆሞ ለመታረድ ዝግጁ የሆነ የኢትዮጵያ ዜጋ ከእንግዲህ አይኖርም፤ የለውጥና የጸጥታ ኃይሉ ሕዝቡ የራሱንና የአካባቢውን ጸጥታ ለመጠበቅ የሚያስችለውን አዲስ ሥርዓትና አደረጃጀት በፍጥነት ቢዘረጋ እንዴት ጥሩ ይሆን ነበር!?
– ከሁሉም በላይ ፈጣሪ ከሠይጣኖች ጋር ሣይሆን ከእኛ ጋር ነው!!
– የዜጎች ሚናና ኃላፊነት፡ የለውጥ ትግሉን በመንግሥት ውስጥ ያለው የለውጥ ኃይል ብቻ ጉዳይና ችግር አድርገን አንይ፡፡ እንኳን የፖለቲካ ድርጅቶች ብዙ ተራ ዜጎችም ጀምረን ገና ያልጨረስነው የለውጥ ሥራ እንዳለን እናስታውስ፡፡ እና የኛ የአሁን ሥራ፣ እንደ ኳስ ሜዳ ተመልካች የለውጥ ቡድኑ / መንግሥት ጎል ሲያገባ ማጨብጨብ ሲገባበት ጸጉር መንጨትና ማውገዝ ብቻ ሊሆን አይገባም፡፡ ዜጎች የራሳችንን ንቁና ጉልህ ሚና መጫወት – ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን፡፡ መታገል ማለት የለውጥ ኃይልን መኮርኮምና ማዛል ማለት አይደለም፡፡ በግልጽ የምናውቃቸውን ፀረ ለውጥ ኃይሎችና የኢትዮጵያን ጠላቶች በግልጽና በቁርጠኝነት እንታገል፤ ይኼኔ ብቻ ነው የናፈቅነውን ሰላም፣ አንድነት፣ ነጻነትና ዕድገት ማረጋገጥ የምንችለው

– ለውጡ ቀስ በቀስ እየጠነከረ የመምጣቱን ማሣያዎች አየን፡፡ በአንጻሩ ጠላት ምንም የደከመ መሆኑን ብናውቅ፣ ብናምንና ብናረጋግጥም፣ መናቅና መዘናጋት አለብን ማለቴ ግን አይደለም!!
– ለምሳሌ ዛሬ የአዲስ አበባ የኢሬቻ በዓል አከባበር የጸጥታ ጥበቃ ሥራው እጅግ የተሳካ ነበር፡፡ የጸጥታ ኃይላችንን እናመሰግናለን፡፡ ሆኖም 95% ስኬት ቢታይም 5% ክፍተት ካለ እንኳን ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ መዘናጋት የለብንም፡፡ የጸጥታ ኃይላችንን በምንችለው ሁሉ መደገፍ አለብን፡፡
ፈጣሪ ይርዳን!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop