August 31, 2020
20 mins read

የዘረፋና ኢትዮጵያን ወደኦሮሞነት የመቀየር ዘመቻ – ስርፀ ደስታ

አሁን ሜይቴክ ማረኝ ወያኔ ማረኝ መባል ተጀምሯል፡፡ በዚህች አጭር ጊዜ ሁለት ዓመት ውስጥ የታየው ጉድ የ27 ዓመት የወያኔን የዘረፋና አገርና ሕዝብ ማጥፋት ወንጀል እያስከነዳው ነው፡፡ እኔ የኦሮሞ ጉዳይ ከበፊቱም አደጋ እንደነበር ገብቶኝ ነበር፡፡ ትንሽ ለማ መገርሳ ፈር ያሲዘዋል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር እንጂ፡፡ አብይ የተባለው ሰውዬ ግን እጅግ አስመሳይ እንደነበር ከበፊቱም ታውቆኛል፡፡ ኋላ ላይ እሱም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሲልና አንዳንድ ነገሮችን ማከናወን የጀመረ መስሎኝ እስኪ የራሴን ግምት ልተውና ለሚሆኑ ነገሮች ልሸነፍ ብዬ ለተወሰነ ጊዜ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች መከተል ጀመርኩ፡፡ ያም ሆኖ ግን አልፎ አልፎም ቢሆን መለኪያ የምላቸውን መስፈርቶች እንደ ምልክት አስቀምጥ ነበር፡፡ ቆይቼ ሁኔታዎች ሳስተውል አልተሳሳትኩም፡፡ አብይ አህመድ ብዙ ቲፎዞ እያሰማራ ወጣቱን ለመማረክ ሞክሯል፡፡ ከእነዚህ እንደምልክት እንዲሆናችሁ አንድ ምህረት ደበበ የተባለ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስቦ ባዶ ሲያደርጋቸው ታዝቤ ነበር፡፡ ግለሰቡ (ምህረት ደበበ የተባለው) ለራሱ አንዳች እውቀት የሌላው ትልቅ እውቀት እንዳለው አድርጎ ወጣቱን ሲያደነዝዝ ነበር፡፡ አውቃለሁ ምሁር ተብሎ ነው፡፡ ለነገሩ እኮ አብይንም ሰዎች ያመለኩት በአስመሳይ ወሬው ነው፡፡ ገና ከመሹሙ በፊት ልክ ልዩ እውቀት እንዳለው ሲያወራ ይገርመኝ ነበር፡፡ ሰውም ያንኑ ተከትሎ ሲያደንቅ አስተውዬ ሁኔታው አደገኛ ሊሆን እንደሚችል እገምት ነበር፡፡ በተደጋጋሚ እንዳልኩት እስካሁንም ያልተዋጠልኝና ልረዳው ያልቻልኩት የለማ መገርሳን ነገር ነው፡፡ እውን ለማ መገርሳ አስመሳይ ነበር? አሁንም ለእኔ እንቆቅልሽ ነው፡፡ ምን አልባትም ለማ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ተቀይሮ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ነው ያለኝ፡፡ ለማ የኦሮሚያ  ፕሬዘደንት ከሆነበት ቀን ጀምሮ በጣም የምከታተወለው ሰው፡፡ ትግል የተባለውን (እነአብይ ሥልጣን የያዙበት) ነገር ከመጀመሩ በፊት ራሱ ለማን በብዙ ነገሩ አደንቀው ነበር፡፡ የንግግር ቃናውም የውሸት አይመስልም፡፡ እኔ ሰዎችን ከምገመግምበት ዋነኛው የንግግራቸው ሁኔታ ነው፡፡ አብይ አህመድ እንደዛ አደለም፡፡ እጅግ ብልጣብልጥና አስመሳይ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ አሁን ለማም አብይም አብይም አሁን በምናየው ስለሆኑ ብዙው ሰው ተረድቷል፡፡  ያም ሆነ አሁንም ከለማ ይልቅ አብይ ለኢትዮጵያ አደጋ እንደሆነ አስተውላለሁ፡፡

እንግዲህ ወያኔን የጠላንው ትግሬ ስለነበሩ አደለም፡፡ ፍትህና ሥርዓት በሚል እንጂ፡፡ አሁን ከወያኔ ብዙ እጅ የከፋ አደገኛ የኦሮሞ ቡድን/ቡድኖች ኢትዮጵያን እያመሰ መሆኑን አለማስተዋል አደጋ ነው፡፡ አንድ ሰሞን ስለሜይቴክ ጉድ ብለን ነበር፡፡ በዚህ ሁለት ዓመት የሆነውን ጉድ ማስተዋል ስንጀምር ምን ልንል እንደምንችል አላውቅም፡፡ ሜይቴክስ በስርቆት መልክ ነው፡፡ ያሁኑ እኮ በግልጽ ዘረፋ ነው፡፡ ባንኮች ከ20 ጊዜ በላይ ተዘርፈዋል፣ አሁን እየተሰሩ ያሉ ፕሮጄክቶች ሁሉ ለከፍተኛ ዘረፋ የተጋለጡ ናቸው የአዲስ አበባ መናፈሻ ሥራዎችን ጨምሮ፡፡ ይሄው ደግሞ ሰሞኑን ዜጎች ለዘመናት ከሚበሉት ቆጥበው የሰሩትን ቤታቸውን በይፋ ዘርፈው ለሌላ አደሉ የሚለውን ወሬ እያሟሟቅን እንገኛለን፡፡ ግልጽ ነበር እኮ አብይ ታከለ ኡማን ከኦሮሚያ በቀጥታ አዲስ አበባ ላይ ሲሾም ምን ሊሰራ መስሎን ይሆን? ይሄው አሁን ሌላዋን ሾሟል፡፡  ይችው ለቀጣይ ዘረፋ የተሾመችው ግለሰብ ገቢዎች በነበረችበት ጊዜ መዋቅሩን ሁሉ በኦሮሞ አስይዛ ይፋ የሆነ የኦሮሞዎች ሕገ ወጥ ንግድ ስታስነግድ ነበር፡፡ ሊያውም ሌሎችን ለማጥፋት የሚሆኑ መሳሪያዎችን ሁሉ ስታስገባ፡፡ አሁንም ያ መዋቅር ያው ነው፡፡ ለሐብት ቢሆን በተሻለ ነበር፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁራ ሕልም ሌላውን ሁሉ አጥፍቶ ኦሮሞ ብቻ የሚኖርባት ምድር መፍጠር ስለሆነ በዚህ ሁለት ዓመት ሙሉ አቅማቸውን ለዚህ ጥፋት ሲዘጋጁ ነበር፡፡ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እየተባለ ሲሰለጥን የነበረው ይዚሁ እቅድ አካል ነበር፡፡  ይሄን ሁሉ ያደረገው ማን ነው?  አብይ አደለም? አሳምነው ጽጌ ይሄ ሴራ ስለገባው መሠለኝ እሱም የራሱን ዝግጅት ጅምሮ የነበረው፡፡ ውጤቱን አይተናል፡፡ ሳዕረም የተገደለበት ዋናው ዓላማ በወያኔ ትብብር ቢሆንም ከዚሁ የእነ አብይ ኢትዮጵያን ወደ ኦሮሞነት የመለወጥ ዘመቻ እንደነበር እናስተውላለን፡፡

ይሄው አሁን በይፋ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች  አረመኔያዊ ግድያንና ሌሎችን በመጨረስ ወደ ምድሩንም ሰውንም ኦሮሞ ሲያደርግ የነበረውን ገዳ የተባለ ሥርዓት ለማስተማር አውጆ እናያለን፡፡ ገዳ እንደ አብይ የሰላ ኖቤል ሽልማት በማጭበርበር በተባበሩት መንግስታት የትምህርትና ቅርስ ድርጅት ተመዝግቦ እናያለን፡፡ አብይ አህመድ አለመን ሁሉ በአስመሳይነቱ በማታለል የኖቤል የሰላም ሽልማት መውሰዱ ዛሬ ብዙዎች እየጠየቁ ያሉት ክስተት ነው፡፡ የአረመኔያዊው ገዳ ሥርዓትም በዚሁ መልኩ ነው ዩኔስኮ ሊመዘገብ የቻለው፡፡ ኢትዮጵያውያን አሁንም ሊነቁ ይገባቸዋል፡፡ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ዓላማ ያ  የአረመኔያዊውን የገዳን ሥርዓት በኢትዮጵያ ማስፈን ነው፡፡ ልክ ብዙ የእስልምና ተከታይ ቦታዎች ሸርዓን ለመመስረት እንደሚሞክሩት፡፡ ሸሪዓ ሁሉንም እስላም በማድረግ ነው፡፡ ገዳ ደግሞ ሁሉንም ኦሮሞና እምነት የለሽ በማድረግ ነው፡፡ በዚህ የሁለት ዓመት እድሜ ነው ይሄን ሁሉ ወንጀል የተፈጸመው፡፡  ከዚህ በኋላ ለኦሮሞነት እድለስ መሥጠት እንደ ሁለቱ መንገደኞች ነው፡፡ ሁለት መንገደኞች መንገድ በሌሊት ሲሄዱ ይደክማቸውና እንቅልፋቸው ሲመጣ ሜዳ ላይ አረፍ እንዳሉ ጅብ ይመጣና የአንዱን እግር መብላት ይጀምራል፡፡ ሌላኛው ይነቃና ምንድነው የሚቆረጣጥመው ሲል እየተበላ ያለው ዝም ብል ዝም በል ጅብ የእኔን እግር እየበላ ነው ይላል፡፡ ያኛ ታዲያ እንዴ የአንተን ሲጨርስ ወደኔ መምጣቱ አድል እንዴ ይልና ከተኛበት ብድግ ሲል ጅቡ ደግንግጦ ይሸሻል፡፡ በዚህ ምክነያት ራሱንም ጓደኛውንም ቢያንስ ሙሉ በሙሉ ከመበላት አዳነ፡፡ የቀን ጅብ እያሉ በወያኔ ላይ ሲሳለቁ የነበሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞችና ምሁራን ከወያኔ በብዙ እጥፍ በከፋ አውሬነታቸው እየታየ ነው፡፡  ብንሸሸው አይሆንም፡፡ ሙሉ በሙሉ በልተው ሳይጨርሱን በፊት ሁሉም ሊነቃ ይገባል፡፡

በታሪክ ብዙ ሕዝቦች ወደ ኦሮሞነት የተቀየሩበት የ16ኛው ክፍለዘመንና ከዛም በኋላ ያለውን ዘመን ዛሬ እየሆነ እንደሆነ እናስተውል፡፡ የኦሮሞ ገዳዊ አስሳሰብ ይሄው በትውልድ ተጋብቶ እያየንው ነው፡፡ ሌላ ብለው የሚያምኑትን ሕዝብ ሙሉበሙሉ ወይ መጨረስ ወይ ማንነቱነት ሙሉ በሙሉ አጥፍቶ ኦሮሞ ማድረግ ነው፡፡ ቦታዎችን በፍጥነት በኦሮሞ ሥም መስጠት በሕወት የተረፉ ሰዎችን የተፈጥሮ ዝርያቸው (ባዮሎጂካል) እንዳይታወቅ ሙሉ በሙሉ የአባቶቻቸውንና አያቶቻቸውን ሥም በመቀየር ኦሮሞ ማድረግ የአረመኔው ገዳ ሥርዓት መገለጫ ነበር፡፡ ይሄው ራሱ ነው ዛሬ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች እያደረጉ ያሉት፡፡ ሌላ ቀርቶ ኦሮሞ የሚል አዲስ ሥም ያወጡት እነሱ እንጂ ኦሮሞ የሚል ቃል ራሱ ከ200 ዓመት (በጣም አርዝሜው ነው) በፊት አልነበረም፡፡ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት በአብዛኛው ዛሬ ኦሮሞ እየተባለ የሚጠራው ሁሉ ኦሮሞ አልነበረም፡፡ ሌላ ቀርቶ በደርግ ጊዜ ብዙዎች አሮሞ አይባሉም ነበር፡፡ ለዚህ ዛሬ ኦሮሞ የሚባለውን የጂማን ሕዝብ ዋቢ መጥቀስ ይቻላል፡፡ አባ ጂፋር ኦሮሞ ይመሩት የነበረ ሕዝብ ኦሮሞ ተብሎ አይጠራም ነበር፡፡ ሐረር ኦሮሞ አልነበረም፡፡ ለዚህ በደርግ ጊዜ የነበረ የ4ኛ ይሁን የ6ኛ ክፍል ሕብረተሰብ ማንበብ በቂ ነው፡፡ ባሌ ባሌ፣ አርሲ አርሲ፣ ሐረር ቆቱ፣ ይባሉ ነበር፡፡  ይሄን ነው ሰዎች ዛሬ ልክ ታሪክ ያስቆጠረ ሥያሜ አስመስለው የሚነግሩን፡፡   እንዚህ የሕብረተሰብ መጻሕፍ፣ ሌሎች ዛሬም ባለ ሥያሜያቸው አሉ፡፡ ኦሮሞ የሚባ ነገር አልነበርም፡፡ በእርግጥም በወቅቱ ባሌ፣ ጂማ፣ በተለይ ሙስሊም አካባቢዎች ኦሮሞ መባልን አይፈልጉም፡፡ ትርጉሙ ጥሩ ስላልሆነ፡፡ ሸዋም ኦሮሞ አልነበረም፡፡ ይሄን የምለው በደርግ ጊዜ ነው፡፡ እንደሚመስለኝ በዛም ወቅት ወለጋ ራሱን ኦሮሞ ይል ነበር፡፡ ዲህ በቆይታ እውነቶች ከትውልዱ እየጠፉ ነው አደጋ እየመጣ ያለው፡፡

የኦሮሞነት ልክፍት እንዴት አገርን እያጠፋ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ በዘር ስንመለከት ዛሬ ኦሮሞ የተባው ሕዝብ በጣም የተለያየ የዘር ግንድ ያለው ነው፡፡ ይሄን በባለፈው ጽሁፌ በግልጽ መረጃውን አሳይቻችኋለሁ፡፡ ሸዋ ኢትዮጵያ ነገስታት ዘር ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል፡፡ በአረመኔው የገዳ ሥርዓት ነው ወደ ኦሮሞነት የተቀየረው፡፡ እነ አጼ ሚኒሊክና ጎበና ይሄን አሳምረው ያውቁት ነበር፡፡ ለዛም ነበር ሕብረታቸው፡፡ ይችን እውነት የዛሬዎቹ የኦሮሞ ምሁራን ትንፍሽ አይሏትም፡፡ ጎበናን ሌሎች ታላላቅ ዛሬ ኦሮሞ ከተባለው ሕዝብ የተመደቡ ጀግኖች የአጼ ሚኒሊክ ተላላኪ ያደርጓቸዋል፡፡ የአጼ ሚኒሊክና የጎበና ግንኙነት ግን በዘር ማንነት እንደሆነ ብዙዎች አይገባቸውም፡፡ የኃይለሥላሴ አባት ራስ መኮንን ኃይለሚካኤል ጉዲና በስም እንጂ ሰዎች እንደሚያስቡት ከወላቡ የመጣ ኦሮሞ ዘር ኖሮባቸው አደለም፡፡ አዋቂዎችን እየገደሉ ልጆችን ሥምን ሙሉ በሙሉ የእነሱ በማድረግ ማንነትን ደብዛ የማጥፋት ስልት የአረመኔው የገዳ ሥርዓት ስለነበር፡፡ ዛሬ ዘመናዊው ሳንስ የሚያሳይን እውነት እንደወረደ ይህን ነው፡፡  እስኪ እንደው ለትዝብት እንዲሆናችሁ ሌላ አንድ እውነት ልንገራችሁ፡፡ የታላቁ የአደዋው ጀግና ገበየሁ ጎራና አጼ ሚኒሊክ የወለዱት አንድ ቀን አንድ መንደር አንጎለላ እንደነበር ታውቃላችሁ፡፡ ዛሬም በአንጎለላ የታላቁ ጀግና የገበየሁ መታሰቢያ አለ፡፡ በእነሱ ጊዜ ወላጆቻቸው የሆነውን ሂደት በደንብ ይነግሯቸው ስለነበር ነው፡፡ ጎበናና ሚኒሊክ በአንድ የተሰለፉት፡፡ ከአረመኔው ገዳ በፊት ሸዋ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የታላቁ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ዘሮች ጭምር ነበሩ፡፡ አምነታቸውንም፣ ማንነታቸውንም ያጠፋው ይሄው አረመኔው ገዳ ነው፡፡ ይሄን እውነት ግን ዛሬ መሸሸግ አይቻልም፡፡ ፊቼ ላይ ኦሮሞ ያልከውንና ደብረሲና ላይ አማራ ያልከውን ሰው ደም መርምር፡፡ እንኳን ሰው የደብረሲና ጽድና የመናገሻ ሱባ ጽድ አንድ ናቸው፡፡ እንደሜ ለዘረያቆበት ምልክቱን አኑሮልን አልፏል፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ሁሉ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች አረመኔያዊውን የገዳ ሥርኣት መልሰው በኢትዮጵያ ሊያቆሙ እንዴት እየሰሩ እንደሆነ አስተውለህ ከዚህ በኋላ በመሸፋፈን ሳይሆን በግልጽ ልትቃወመው ግድ ይላል፡፡ ዛሬ በዋናነት አማራ፣ በእምነት ደግሞ ኦርቶዶክስ ነው ኢላማ የተደረገው፡፡ ምክነያቱም እነዚህ ሁለቱን ማጥፋት ከተቻለ ሌላውን በቀላሉ ማጥፋት ይቻላል የሚል ሥሌት ነው፡፡ የሁለቱን መንገደኞች ታሪክ አስታውስ፡፡ አማራና ኦርቶዶክስ ተበልቶ ካለቀ በአንድ ሌሊት ሙሉ በሙሉ የኦሮሞ ሊያደርጉህ ነው ሐሳባቸው፡፡ በተለይ የደቡብ ኢትዮጵያን ሕዝቦች በዚህ ስሌት ነው እየጠበቁ ያሉት፡፡ ይሄ አሁን በአይንህ እያየህ ያለው እውነት ነው፡፡ ማስተዋል ከቻልክ፡፡  ይሄው ባለፍው ሁለት ዓመት ያላ አንዳች ይሉኝታ ነው ሴራቸውን እያከናወኑ ያሉት፡፡ ዛሬም ኢትዮጵያ አትፈርስም እያለ የሚያባብልህን አብይ አህመድን ትሰማለህ፡፡ በተግባር ግን በፍጥነት የኢትዮጵያ የመንግስት መዋቅሮችና የገንዘብ ሰንሰለቶችን በጸረ-ኢትዮጵያ ኦሮሞዎች እንዳስያዘ አስተውል፡፡  ይሄው ጊዜውን ለመጠቀም የአረመኔውን የገዳ ሥርዓት ሊያውም በአዲስ አበባ አስተምራለሁ ብሎ እያወጀ ነው፡፡ በኦሮሚያ አደለም፡፡ ኦሮሚያ ወደ ኦሮሞነት መቀየር አያስፈልገውም፡፡ አዲስ አበባ ወደ ኦሮሞነት ከተቀየረ ያው ከላይ እንዳልኩት ነው፡፡ ሌላው ቀላል ነው፡፡ እስከዛሬ እየተባበለ ብዙ ጥፋት ደርሷል ቢያንስ ከዚህ በኋላ ሁሉም ይንቃ፡፡ በነገራችን ላይ ዓለም በተወሰነም ቢሆን እየተረዳ ነው፡፡ በተለይ የሜሪካ መንግስት ሁኔታው ከጅምሩ ያውቅ ነበር፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop