በዶክተር ደረጀ በወንጌል አማኞችና በ360 ሚዲያ ላይ የሚነዛው ነቀፋ ነውር ነው – ቻፕልያን ፓስተር ኤዲ (አድፍርስ) መካሻ

August 27, 2020
8 mins read

ለተገፉት ተናገርላቸው (ምሳሌ 31:8)

ፍርድን አድርጉ የተበዘበዘውን አድኑ (ትንቢተ ኤርሚያስ 22:3)                                                                     መገናኛ ብዙሃን ሚዲያ ሰዎች የማውቅ መብታቸውን የሚያስከብርና  ቅን መሰተዳደርና  ፍትህ ይኖር ዘንድ  የተመስረተ መልካም ስርአት ቢሆንም በሰዎች ራስ ወዳድነት የግፍና የጭቆና መሳሪያ መሆኑ ያሳዝናል:: በተለይ በሃገራችን ኢትዮጲያ ሰዎች መሰረታዊ የመናገር የመጻፍ መብት በተነፈጉትና  ለይስሙላ  የገዝዎቹን ክፋት እስካልገለጠ ድረስ  የተፈቀደው የመገናኛ ብዙሃን መብት ተብሎ ሊወደስ አይገባም:: በንጉሱ ዘመን የተራበ ህዝባችንን ሰቆቃ ሳይዘግብ የንጉሱን የልጅ ልጅ ልደት ለማክበር ከባህር ማዶ በመጣ ኬክ  ሲከበር ወይንም የንጉሱን ውሻ ክብካቤ የዘገበ ንጉሱን ጸሃዩ ያለኝ ምንደኛ እንጂ ጋዜጠኛ ሊባል አይገባውም:: በደርግ የህዝቦች ሰቆቃን መናገር ያቃተው የኢሰፓ ምስረታን ፈንጠዝያ ሲዘግብ የወያኔን የከፋ ምዝበራና ሃገር የከፋፈለ የዘረኝነት ጥፋት ሳይዘግብ “ባለራእዩ ብሎ” ቢያሞካሽ በመደመሩ የአብይ ኣሀመድ መንግስት ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ ሲፈናቀሉ ከአያት ቅድም አያቶቻቸው ጀምሮ ከኖሩበት በዘራቸውና በሃይማኖታቸው  ምክንያት ሲታረዱ ሲፈናቀሉ  ሳይዘግብ የከተማ ፓርክና ችግኝ ተከላውን ቢከትብ ያንን ሚድያ አልልም  የገዥዎች ልሳን  እንጂ::

በሰሞኑ  በየዘመናቱ የሃገሩን የኢትዮጲያን ሁኔታ ከጉግማንጉግ ፍልስፍና ‘ሰው ከዝንጀሮ መጣ’ ከሚለው ጀምሮ “ዝንጀሮ አይደለሁም” ብሎ የመከተ በኪነት ለአብዮቱ ዘምር ሲባል እምቢ በማለት መጀመሪያ በጋምቤላ ከሃገር ለመውጣት ሲሞክር በፓስተር ኦኬር  ምክር ተመልሶ በኬንያ  በኩል ከሀገሩ የተሰደደው በስደትም ለሃገሩ “አስባት ሃገሬን” ብሎ የማለደው ዶክተር ደረጀ የዶክተር አብይ ኣህመድ ዋነኛ ሃላፊነት የሆነውን የህግ የበላይነት ማስከብር መዘንጋትና የብዙ መቶዎች ወገኖቻችን አሰቃቂ  ጭፍጨፋን መተቸቱን በመቃውም የተሰነዝሩት የዶክተር ደረጀን የወንጌል አማኞችና የ360ሚዲያን ስም የሚያጎድፉ ትችቶችና ስድቦች ነውርና ጸያፍ መሆናቸውን ከአጼ እስከወያኔ  የሃገራችንን ጉዳዮች የማውቀው በጥቂቱም ከጥንቱ ብስራተ ወንጌል ቆይቶ የምስራች ድምጽ መገናኛ ዘዴዎች  ያገለገልኩ ሃቁን መስክራለሁ::

ሚዲያ ሚዛናዊ መሆኑን ያስተማረኝ ብስራተ ወንጌል ከወንጌላዊት መካነኢየሱስ በተጨማሪ ለተዋህዶ ኦርቶዶክስ በሰጠው የአየር ጊዜ ሲሆን ባልደረቦቹ አንጋፋዎቹ  ዘውዱ ታደሰ  ንጉሴ ተፈራ በዚያን ወቅት የሃያላኑን የሰለለ ድርጅቶች ኬጅቢንም ሆነ ሲአይኤን የምስራቁንም የምእራቡንም ፍልስፍናዎች ሲያስረዱን ነበር::  ዛሬ ግን በግልብ ወገናዊነት የመገናኛ ብዙሃን የስዎችን ስሜት በቀላሉ በሚነኩ የዘርና የሃይማኖት ጽንፈኛ ቃላት ገንዘባቸውን ለመሰብሰብ የሚተጉት ሚዲያዎችን ክፉ ዘር ውጤት  ከሰሞኑ በልዩ ለዩ የሃገራችን ክፍሎች በተለይ በኦሮሚያ የደረሰው ሰቆቃ  የሁላችንም በተለይ ዶክተር ደረጀና መሰሎቹን  የውሁድ ብሄረሰቦች ትውልዶችን  በጣም ያመናል ያሳዝነናል::ስለዚህም ከያለንበት በግልጽም በህቡእም የሃገራችንን ጉዳይ መዘገብ መምከር መገሰጽ የሚያስመስገን እንጂ የሚያስነቅፍ አልነበረም:: ገዥዎቹን በጭፍን ሲመርቅ በኖረ የሃገራችን ሚዲያ ዛሬም ለጥቂት ጊዜ በትውልድ ሃገሬ ያየሁት ማህበረሰቡን የሚጎዱ የአልኮል መጠጥና የአደገኛ እጾች  ትምህርት ሰጭ መጽሃፍትና የሃገራችን ታሪክና ፖለቲካ ሚዛናዊነት የሚመክር መጥጥፌን ያለው መንግስት ሚዲያ ድርጅት ሃላፊዎችና ባልደረቦች  ሊያስተናግዱ የማይፈልጉ ሃገራችን ትፈርስ ዘንድ መሃል ሃገር ተቀምጦ  ብዙ የመንግስት መረጃ በማቀበል የሃገሪቱን መከላለያ ያስፈጀ ኢኮኖሚውን ገደል የከተተ የቀድሞ የስራና የኮሌጅ ባልደረባዬ ሊላይ ሃይለማርያምን የመስለውን የመደመሩ( የማግበስበሱ)  መንግስት ሚዲያ ልሳን ምን ያህል ትኩረት እንደሰጠው ስመለከት የመደመሩ መንግስት የቀደመው ከፋፋይ ወያኔ መንግስት እርሾ እንዳለበት አረጋግጣለሁ::

ለማህህበራዊ ቀውሶች መፍትሄ  ጊዜ የሰጡ የ360 ሚዲያ ርእዮት አለሙናና የአውስትራሊያው  SBS ካሳሁን ሰቦቃን  በሚዛናዊነት ሁሉንም ባማረ መልኩ የሚያቀርበው የ”በነገራችን ላይ” አዘጋጅ ደረጀን  በዚህ አጋጣሚ ላመስግን እወዳለሁ::

ለማጠቃለል  በሃገራችን በመደመሩ መሪ ዶክተር አብይ የተደረጉ ልብ መሳጭ ንግግሮችና በጎሰኞች የተጠላች ኢትዮጲያ ከቤተመንግስት ጀምሮ መወደስ እሰየው የሚያሰኝ ሲሆን  ያለው መንግስት የሰሞኑን አንድ ጳጳስ “ስብከቱን ለሃይማኖት ሰዎችተዉልን”ምክር በመሰማት ሃገርን ሃገር በሚያሰኛት የህግ የበላይነትና የዜጎች ጥበቃ ላይ ያተኩር ዘንድ በመንግስት ዙሪያ የሚያሸረግዱትን ምንደኞች  ሙገሳ ብቻ ሳይሆን  ጠንከር ያሉ የዶክተር ደረጀን መሰል ነቀፌታዎችንም  ያስተናግድ ዘንድ ማሳስብ እወዳለሁ::

ቻፕልያን ፓስተር ኤዲ (አድፍርስ) መካሻ

4 Comments

 1. በዉነቱ ኢትዮ 360 በኢትዮጵያዊነት መነጽር ሲታይ በክፉ ቀን የተገኘ የኢትዮጵያ ባለ ዉለታ የሆነ የሚዲያ ተቋም ነዉ። ከጊዜዉ ቀድሞ በመሄድ ወደ ሗላም በመመለስ እንድንማር፤እንዳንታለል፤እንድንጠነክር አበክሮ የሰራ የሚዲያ ተቋም በመሆኑ ለማመሰገን ጊዜ ስጠብቅ ይህ አጋጣሚ በመፈጠሩ ደስ ብሎኛል። ባላቸዉ ጥቂት ሪሶርስ ሙሉ ጊዜያቸዉን ለኢትዮጵያ ህዝብ በማዋለቸዉ ሊቸራቸዉ የሚገባዉ አድናቆትና ድጋፍ በመላላቱ በጣም አዝናለሁ ኢትዮጵያዉያን ከነሱ የተሻለ ሚዛን የጠበቀ የሚዲያ ተቋም ለጊዜዉ አላገኘንም።
  ከመጀመሪያዉ ጀምሮ ነገሩ ያላማረኝ ኢሳት የተባለዉ ድርጅትም ጌታዉን ተከትሎ ወደ ሀገር ገብቶ ለኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ለአገዛዙ ሺንጡን ገትሮ ከሚሟገት አድር ባይ የዜና ተቋም አንጻር ኢትዮ 360 የከፈለዉ መስዋእትነት በእጂጉ ሊመሰገን የሚገባዉ ነዉ። ጋዜጠኞቹ በእዉቀት የተካቡና የአይን ምስክርነታቸዉን የሚሰጡ ስለሆነ ለታማኝነት ከነሱ የቀረበ ሰዉ ሊኖር አይችልም፡፤
  ይልቅስ ኢትዮጵያዉያን ለእኛ አይንና ጆሮ በመሆናቸዉ በምንችለዉ አቅም ብንደግፋቸዉ የድጋፋችንን ያህል የነጠረ ዜና እናገኛለን እላለሁ። በዚህ አጋጣሚ ርእዮት ሚዲያና አዘጋጁ አቻምየለህን ጨምሮ ከአንድ ብርጌድ ጦር በላይ ምታችሁ ከባድ በመሆኑ በያዛችሁት ጥራት ትቀጥሉ ዘንድ አደራ እንላለን።
  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 2. Some time ago, I met with a gentleman through a friend. We were doing some transactions and start spending hours talking together that went for many days. The talk some how changed into religion. He showed me a verse from the bible and said that believing in Jesus is what it takes to inherit the kingdom of God regardless of our deeds. I started reading a little and found out martin Luther protested at the pop and invented this abomination doctrine. Most the mayhem of the world started after that. Anybody can kill, steal, exterminate, rob poor peoples’ lands or houses or kids or wives, do adultery, do anything they want, and the kingdom of God is theirs as long as they believe in Jesus. Breaking all the ten commandments and still believing to inherit the kingdom of God is beyond imagination. Because of this doctrine, Americans exterminate the native Indians. because Protestantism, Americans enslave and segregate blacks. because Protestantism, the Anglo Saxons exterminate the Australian and New Zealand aborigines. because of Protestantism the Nazis killed 6 million Jews and 20 million Russian orthodox Christians. Because of Protestantism, south Africans blacks were enslaved by apartheid. All the world problem at this moment is directly or indirectly related to “I can do anything and inherit the kingdom of God” doctrine. As we speak Prime minister Abiy is promoting this disgusting doctrine to millions of clueless masses using prosperity as a pretext and portraying Orthodox as backward neftegna. Many people become protestant not because they know the doctrine but because they hate the neftegna Orthodox. So Mr. pastor, please examine what you believe first before looking for a solution. For me Protestantism is the same as satanism.

 3. Dear Yosef
  Thank you for th very ethical comments that I appreciate very much.
  There are some truth in your opinion that evil leaders abuse the christian faith in particular the protestant faith and I wish to call it with the appropriate name the reformation faith ተሃድሶ.It was our nation Ethiopia the pioneer in evry thing including the faith in one God before Christianity and other faiths began in the planet.Also our Ethiopian faith father ደቅእስጢፎ and friends were beginning the reformation before the German monk Martin Luther began it in Europe. Unfortunately our achievements and civilization failed for some reason as professor Mesfin Woldemariam defined it መክሸፍ.The essential goal of Martin Luther and our Ethiopian faith fathers was not creating a new religion or protesting the former religion but they are called protestant as they protested the evil practice of the existing religion.So my advice for you would be just to read the bible and know the message of Christ and practice it.

 4. ይህን ጽሑፍ ያቀረብክልን ፓስተር ኢዴ መካሻ እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ሀገር የምታድገው እንደዚህ ሥንሆን ነው – በምንም ሣንከፋፈል ለሀገር ቀና ቀናውን ስናስብና ጥሩ ስንሠራ። በዘር፣ በሃይማኖትና በመሣሰለው ሥንቧደን ውጤቱ አጥፊ ነው፥ እሥኪያንገሸግሸን አየነው፤ እያየነውም ነው።
  እኔም ባለፈው ዶ. ደረጀን ጠቅሼ በአንድ መጣጥፌ ልጅ ይውጣልህ ብያለሁ፤ በዚቺው ዘሀበሻ ድረገፅም ታትሟል። ትንሽ ልጠቅሥ እችላለሁ፦

  በምሥጋናና አድናቆት ልጀምር፡፡ ሰው በሚሠራው መጥፎ ተግባር ከተወቀሰ በሚያበረክተው በጎ አስተዋፅዖም ሊመሰገንና አድናቆትም ሊቸረው ይገባል፡፡ …

  ዛሬ ዕለቱ ሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ነው፡፡ ባሳለፍኳት ሌሊት ኢትዮ360 ዩቲዩብ ላይ ከአንድ ዕውቅ ኢትዮጵያዊ ለዶክተር አቢይ የተላከ ግልጽ ደብዳቤ ሲነበብ ሰማሁ፡፡ ሰሚ ቢገኝ ድንቅ ወቅታዊ መልእክት ነው፡፡ “ምክር የድሃ ነበርሽ፣ ማን ቢሰማሽ” ይባላል፡፡ ድህነት ሲባል ደግሞ የሀብት ብቻ አለመሆኑን ልብ ይሏል እዚህ ላይ፡፡ ቤት ሙሉ ገንዘብ እያለህም በአንድ ወይ በሌላ ነገር ድሃ የምትሆንበት አጋጣሚ ሞልቷል፡፡ … ያ ታዋቂ ሰው በኔ የልጅነት ዘመን እጅግ መሳጭ የፕሮቴስታንት መዝሙሮችን ሲያሰማንና ወደ እግዚአብሔር መንገድ እንድንታደም ሲጋብዘን የነበረው በአሁኑ አጠራር ዘማሪ ዶክተር ደረጀ ከበደ ነው፡፡ ዶክተር አቢይ ብዙም ሳይረፍድበት ይህን ደብዳቤ አንብቦ ማድረግ የሚችለው ነገር ካለ ቢሞክር የምትቀርቡት ምከሩት፡፡ ለራሱም ነው፡፡

  የዶክተር ደረጃ ከበደን ጦማር በአርምሞ አድምጬ ከጨረስኩ በኋላ ስለግለሰቡ ይበልጥ ለማወቅ ኢንተርኔት መጎርጎር ያዝኩ፡፡ በአንድ አስፈንጣሪ ወደ አንድ የትግርኛ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጓዝኩ፡፡ ቃለ መጠይቁ በትግርኛ የተጻፈ ነው፡፡ አነበብኩት ፤ ግሩም ነው፡፡ “ይህ ሰው በነካ እጁ በፕሮቴስታንት እምነት ውስጥ የተሰገሰጉ የቀን ጅቦችን ምናለ ልክ ልካቸውን ቢነግርልኝ!” ብዬ አስቤ ስለነበር በዚያ ቃለ መጠይቅ ውስጥ የልቤን አድርሶልኝ አገኘሁት፡፡ በዚያም ምክንያት ምስጋናየንና አድናቆቴን ልሰጥ ወደድኩ፡፡ ሰው ማለት እንዲህ ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ አብርኆት (enlightenment) ደረጃ ሲደርስ ወይም ሲቃረብ የእውነትን ችቦ ከፍ አድርጎ ያበራል፡፡ በእውነትም ብርሃን ይጓዛል፡፡ በማስሎው የሰውነት መለኪያም አንድ ሰው self-actualization የሚሰኘው አምስተኛው የንቃተ ኅሊና ደረጃ ላይ ሲደርስ ከራሱ አልፎ ሕይወቱን ለሌሎች እስከመስጠት በአስተሳሰብ ያድጋል፡፡ ዓለምን የናቀና ስብዕናን ያከበረ አንድ ዜጋ ወደዚያ የልዕልና ደረጃ ሲደርስ በመንጋ እያሰበ ንጹሓንን በሜንጫ አንገታቸውን አይቆርጥም፤ ለሥልጣን ዕድሜ መራዘም ሲል ከፀሐይ በታች የሚገኙ ዕኩይ ሥልቶችን አይጠቀምም፡፡ ያ ዓይነቱ ማህተመ ጋንዳዊና ማዘር ቴሬሣዊ ስብዕናን የተላበሰ ሰው ከዘረኝነት፣ ከሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት፣ ከፖለቲካዊ ሸፍጥና ሤራ፣ ከመንደርተኝነት፣ ከጎጠኝነትና ከመሳሰለው ኅሊናንና የአእምሮ ጤንነትን ከሚያቃውሱ የትንሽነት መከለያ አጥሮች ይወጣል፡፡ ዶክተር ደረጀን ያየሁት በዚህ መነጽር ነው፡፡ ልጅ ይውጣለት፡፡ ቀሪ ዘመኑ የተባረከ ይሁን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ዕንባም አያብሰው (ዘ-ጌርሣም)

Next Story

የአሜሪካ መንግስት በህዳሴው ግድብ ምክንያት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን አስከ $130 ሚሊዮን ዶላር (4.7 ቢሊየን ብር) የሚጠጋ እርዳታ ማቆሙን ፎሬን ፖሊሲ ድረገጽ ዘገበ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop