ፖለቲካ እውነትም ሸር…ጣ  ነው! – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም (በሀጫሉ ግድያ ሰበብ የተዘጋው ኢንተርኔት እንደተለቀቀ የሚላክ)

ይህችን ወረቀት በመዝገብ ስሜ ብጽፋት ደስ ባለኝ፡፡ ግን ለዚያ አልታደልኩም፡፡ ትንሸ ይቀረኛል፡፡ የዕድሜ ሣይሆን የአጋጣሚ ነገር ሆኖ “በወጣትነቴ ካልተቀጨሁ” በስተቀር ያንን ወርቃማ ጊዜ እደርስበት ይሆናል፡፡ ለማንኛውም “SAF” በሚል የደሞዝ የስም ዝርዝር ይያዝልኝ፡፡ ጭላንጭል ይታየኛል፡፡…

በሰው ሞት የሚደሰት ሰው፣ ሰው መሆኑ ያጠራጥራል፡፡ ጠላቴ የምለው ሰው ቢሞት በባህላችን ምሥጥ ሆኜ እንደማልበላው መገለጡ ትልቅ ቁም ነገር ያለው መሆኑ እንዳለ ሆኖ በሃይማኖቴ “ጠላትህን ውደድ” መባሉ ራሱ እንደሰውኛ ስሜት በማልወደው ሰው ሞት እንዳልደሰት ገደብ ይጥልብኛል፡፡ ስለዚህ የሚገድለኝን ሰው ራሱ ከአግባብ ውጪ በዘፈቀደና አለፍትህ እንዲሞት በፍጹም አልፈልግም፡፡

ስለሆነም የሀጫሉ ሁንዴሳ ያልጠተበቀ ሞት እጅግ ያሳዝነኛል፤ ያመኛልም፡፡ ሀጫሉ ኦሮሞነቱን ማስቀደሙ መብቱ ነው፡፡ እኔም ኢትዮጵያዊነቴን ማስቀደሜ መብቴ ነው፡፡ ሀጫሉ የኔን መብት ከተጋፋ፣ እኔም የርሱን መብት ከተጋፋሁ ችግር መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ሀጫሉ የኔን መብት መጋፋቱ በገሃድ የተመሰከረ ቢሆንም እኔ ግን የርሱን መብት በመጋፋት ለመስዋዕትነት እንደማልዳርገው ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል፡፡ እኔ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሀጫሉ “እንዲህ አለ፤ እንዲያ አለ” በሚል ሰበብ ልገድለው ይቅርና ዝምቡን እሽ እንደማልለው ሰማይም ምድርም ሊያውቁ ይገባል፤ ጠንቅቀው ያውቁማል፡፡ እርሱን በመግደል ሃሳቡን መግደል እንደማይቻል ስለምገነዘብ ብቻ ሣይሆን ሀጫሉ በሕይወት ኖሮ ከስህተቱ እንዲማርና ሰው እንዲሆን ከመመኘት ባለፈ ይህን መሰል የጭካኔ ተግባር በርሱ ላይ እንዲፈም በጭራሽ አልፈልግም፡፡ ይህን ዕኩይ ተግባር ሊፈጽም የሚችል ትልቅ ዓላማና ተልእኮ ያነገበ አካል ብቻ ነው፡፡

የሆነ ሆኖ የሆነው ሆነ፡፡ ለምን የሆነው እንደሆነ ትልቅ ሰው ይቅርና ጡት ያልጣለ ሕፃንም ያውቃል፡፡ ጡት ያልጣለ ሕጻን ስል እነሕዝቅኤል ጋቢሳንና ፀጋየ አራርሳን አይጨምርም፡፡ምክንያቱም እነሱ ገና አልተወለዱምና፡፡ ባይወለዱም በተሻላቸው፡፡ የይሁዳ ዕጣ የነሱም ነውና አለመወለዳቸው ይበልጥ እንደሚጠቅማቸው የፊታችን ጊዜ ታላቅ ምሥክር ነው፡፡ ከነሱ ይልቅ የሂትለር መጨረሻ በስንት ጣሙ!

ሀጫሉን አማራ አይገድለውም፤ 99.9 በመቶ እርግጠኛ መሆን እችላለሁ፡፡ 0.09 በመቶ የተውኩት የእግዚአብሔርን ቦታ ላለመሻማት ነው፤ እርሱ ብቻ ነውና ፍጹም፡፡ “ሀጫሉን አማራ ወይም ነፍጠኛ ገደለው” የሚለው ድራማ ከወንዙ በላይ በኩል ሆኖ እየጠጣ እያለ ከወንዙ ታች ሆና እየጠጣች የነበረችውን አህያ “ውኃውን አታደፍርሽብኝ!” ብሎ የተቆጣውን የአያ ጅቦን ታሪክ ያስታውሰኛል፡፡

አማራ እንኳንስ እስከመፈጠሩ የማያውቀውን ሀጫሉን በተቀነባበረ ሁኔታ ሊገድል ይቅርና በጉያው አቅፎ የሚያኖራቸውን ብአዴን ተብዬዎቹን በፊት የወያኔና አሁን የኦህዲድ አሽከሮች ከነመፈጠራቸውም አያስታውሳቸውም፡፡ አትታዘቡኝና አማራ ልክ እንደማንኛውም ‹ቤርቤረሰብ› ሁሉ መግደል የማይችል ሆኖ አይደለም – ግን ገና “አልተፈቀደለትም”፡፡ እስኪፈቀድለት መጠበቅ ግን ጅልነት ነው፡፡ አማራ ሁሉን ነገር ለፈጣሪው ሰጥቶ ፍርዱን ከላይ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ እነአጅሬ ጃዋር ግን ከጥምር አለቆቻቸው በወረደላቸው ትዕዛዝ መሠረት በተጠና መልክ ድራማቸውን ካቀነባበሩና ካከናወኑ በኋላ “የነፃነት ታጋያችንን ነፍጠኛ ገደለብን” በማለት እሪታቸውን አቀለጡት፡፡ በሰበቡም የፌዴራል መንግሥቱን ገልብጠው በሮማንያው የቻውቼክስኮ ወንበር አወዳደቅ ሥልት በሀጫሉ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰበብ በአክራሪ ቄሮ የጦዘ የስሜት ግለት አራት ኪሎን በመቆጣጠር ሥልጣን ለመያዝ ቋመጡ፤ በእግረ መንገድም ሁለቱን ታላላቅ ሕዝቦች ለማጨራረስ የሲዖል በሮችን ሁሉ ከፋፈቱ፤ ግን በብዙ መስዋዕትነት ከሸፈ፡፡ መማር ለሚፈልግ ማንኛውም ወገን ይህ ጊዜ ከምንምና ከማንም በላይ አስተማሪ ነው፡፡ ቢያንስ አሁንና ለጊዜው እነጃዋር የፈለጉት አልተሳካም፡፡ ነገ ደግሞ ማንን የአብርሃም በግ እንደሚያደርጉ አድረን የምናየው ይሆናል፡፡የመቀሌ፣ ካይሮና ኦኤምኤን(ኦነግና ግብረ አበሮቹ) የሦስትዮሽ ውል ግን እንዲህ በቀላሉ እንደማይተወን ልብ ማለት ይገባል፡፡ ፈጣሪ ይሁነን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የምስራች ለኢህአዴግ የምጡቅ ጭንቅላት ባለቤትነት ምልክቶች በአንድ ካድሬ ተገኘ

ወደ ዋናው ሃሳቤ ልግባ፡፡ ፖለቲካ ሸርሙጣ ነው የሚባለው በጣም አውነት ነው፡፡ ሸርሙጣ እንዲያውም ከፖለቲካ እጅግ ትሻላለች፡፡ ያለፍኩበት ስለሆነ እኔም ምስክሯ ነኝ፡፡ ገንዘብ ከፍያት አብሬያት ላድር ከተስማማሁ “ተይዣለሁ” ትላለች እንጂ የፈለገውን ያህል ልክፈልሽ ቢላት ለገንዘብ ብላ በሌላ ሰው አትለውጠኝም ነበር፤ የዛሬዋን አላውቅም፡፡ ስለዚህ ሴተኛ አዳሪን ከፖለቲካ ሸርሙጦች ጋር አናወዳድር፡፡

የዘንድሮው በተለይ ፖለቲካ  ዐይን ያወጣ ሸርዳጅና አሽሙረኛ፣ አስመሳይና ቀጣፊ ነው፡፡

ከጠ/ሚኒስትር እስከ ቀበሌ መስተዳድር አንዱ የሌላውን፣ የታችኛው የላይኛውን የስሜት ፍሰት እየተከተለ ማስመሰሉንና መመሳሰሉን ተያይዞታል – ላንዲት እንጀራ ሲባል፡፡ አክራሪ ኦሮሞን ለማስደስት በሚመስል ሁኔታ አንድን ተራ ግለሰብ ከንጉሠ ነገሥት በላይ በመሾም ሰይጣን ራሱ እስኪታዘብና በሣቅ እስኪፈርስ ድረስ አዳሜ ማሽቃበጡን ተያይዞታል፡፡ ሀጫሉም ትልቅ ሰው ሆኖ በርሱ ሞት ሀገር ምድሩ “በፍቅሩ እየተቃጠለ” ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትን የሚያስጠላ ትዕይንት እየታዘብኩ እኔም በመቃጠል ላይ ነኝ፡፡

ቲቪውና ራዲዮው ሁሉ ሌላ ሥራ የለውም፡፡ ፕሮግራሙን ሁሉ አጥፎ ሁሉም ሚዲያ በመኮራረጅ የሀዘን ማቅ ለብሷል፤ ሙዚቃውም ሁሉ የሀዘን ነው፡፡ የአማራው ቲቪ ሳይቀር ምን ይሉኝን እርግፍ አድርጎ ትቶ ከል ለብሶ እያለቀሰ ነው፡፡ ላለውና ለባለጊዜ ማሸርገድ ማለት እንዲህ ነው፡፡ የስንት ውድ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ደመ ከልብ ሆኖ አንዲትም ለማስታወሻነት አንዲትም ሰባራ ሣንቲም ሳይወጣላቸው ለዚህ ልጅ ግን ከመንገድ እስከ ትምህርት ቤት፣ ከመናፈሻ እስከ ሀውልት … ምኑ ቅጡ … “ለኢትዮጵያ አንድት እስከኅልፈተ ሕይወቱ” ለታገለው ለዚህ ልጅ ዝክረ ሰማዕት ሊሠራለት የመሠረት ድንጋዩ በየቦታው እየተጣለ ነው፡፡ እውነት ከኢትዮጵያ ኮበለለች፤ ማስመሰልና ማጎብደድ በምትኳ ደረታቸውን ነፍተው እየተንጎማለሉ ነው፡፡ ይብላኝ ለታሪክ – ይህን ሁሉ ጉድ ለሚታዘብ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቢይና ሽመልስ ኦሮሞን በቁም እየገደሉት ናቸው!! - ይነጋል በላቸው

ለማንኛውም ሀጫሉ በሞቱ ከበረ፤ በመገደሉ ነገሠ፡፡ ይህን የምለው የሀጫሉ ሬሣ ሥራ ማስፈታቱና ለበርካታዎች ሞትና የንብረት ውድመት ምክንያት መሆን አስቀንቶኝ አይደለም – በጭራሽ፡፡ ሞት አያስቀናም፡፡ ግን ለአንድ ሕዝብን ከፋፋይ ዜጋ ይህን ያህል ማሸርገዱና ለበርካታ ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ማወጁ የሥሙኒ ዶሮ የብር ገመድ ይዛ እንደጠፋቸው ዓይነት ምሣሌ በመሆኑ ከዛሬ ይልቅ ነገን ይበልጥ እንድንፈራው ያደርጋልና ሀዘናችንን በቅጡ እንድናደርገው የሀጫሉ አስተዛዛቢ ክስተት ሊያስተምረን ይገባል፡፡ ይሄኔ በኮሮና ወይም በመኪና አደጋ ቢሞት ኖሮ ከአሥር ደቂቃ ያላለፈ የሚዲያ ሽፋን ባላገኘ ነበር፡፡ ግን ግን እንዴት ያለ አስመሳይ ወጥቶናል እባካችሁ! ሁሉም የሆዱን በሆዱ ይዞ “ሀጫሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋልታና ማገር፤ ኢትዮጵያ በጭንቋ ጊዜ ያጣችው ብቸኛ አንጡራ ሀብት… ቲሪሪም ቲሪሪም…” ሲባል እኔ በውነቱ በሀፍረት ተሸማቀቅሁ፡፡ ሁሉም ከል ለብሶ ስመለከት የመለስንና የኪም ኢል ሱንግ ልቅሶ አስታወሰኝ፡፡ እንዲያውም የርሱ ከነሱ በለጠ፡፡

ተመልከት! “ሀጫሉ ለብሔር ብሔረ ሰቦች እኩልነት የታገለ ድንቅ አርቲስትና የሰብኣዊ መብት ተሟጋች ነበር! ሀጫሉ ለኦሮሞ ብቻ አልነበረም የታገለው – ለሁሉም እንጂ” ሲል ይቀደዳል አንዱ፡፡

ሀጬኮ ደግሞ እንዲህ ይልልሃል፡- “የኦሮሞ ጠላት ዱሮም ሆነ አሁን፣ ወደፊትም ሆነ ወደኋላ አማራና አማራ ብቻ ነው! ምኒሊክ በአህያ መጥቶ የሲዳ ደበሌን ፈረስ ቀምቶ ባለፈረስ ሆነ… “

ምን ማለት ነው?  ሚዲያዎች ምን እያሉ ነው?  ባለሥልጣናት ምን እያሉ ነው? አቢይ ምን እያለ ነው? አሸርጋጁ ደመቀ መኮንንስ ምን እያለን ነው? ስንት ሽህ ዓመት ሊኖር ነው እንደዚህና እስከዚህ ለማስመሰል መሞከሩ? ኅሊናችን ምን ይታዘበን? ለውሸት ለምን ለከት አይኖረውም? በስመ አብ!!

አቢይ በውሸት ቆርቦ በውሸት ይህችን ምድር ለመሰናበት የቆረጠ ይመስለኛልና ግዴለም፤ እሱን አንቀየመውም – ተፈጥሮን ደግሞ ተመክሮ አይለውጠውም፤ እሱም እኛም አልታደልንም በዚህ ረገድ፡፡ እንጂ ለምሣሌ ከየትኛው ጊዜው ቀንጭቦ ነው የሀጫሉ የረጂም ጊዜ ጓደኛ ሊሆን የሚችለው? – እርሱ እንደተናገረው ማለቴ ነው፡፡ አቢይና ሀጫሉ የረጂም ዘመን ጓደኛሞች ሊሆኑ የሚችሉበት ሁኔታ ከፖለቲካ ፍጆታ ባለፈ ሊታየኝ አልቻለም፡፡ የዕድሜ መበላለጡን አስቡት፤ የሙያ አለመመሳሰሉን ጨምሩበት፤ የፖለቲካ ጎራ ልዩነትን አትርሱ፤ የአቢይን ከዱሮ ጀምሮ በሥራና በትምህርት መወጣጠር አትዘንጉ፤ እናሳ! ጓደኝነታቸው በስልክና በኢሜል ይሆን? ታውቃለህ – ግነት ለከት ሲኖረው ያምራል፡፡ ወይ አቢይሻ!

ሀጫሉ የኢትዮጵያ ነፃነት ታጋይ እንዳልሆነና እንዳልነበረም የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ራሱ በግልጽ ነግሮናል፡፡ አስከሬኑ የለበሰው ባንዲራ የግብጽን እንጂ የኢትዮጵያን አልነበረም፡፡ ለሀጫሉ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ይህ ብቻውን በቂ ምስክር ነው – እንዲህ መናገሬ መረር እንደሚል አውቃለሁ፡፡ በቀብሩም ወቅት ልቅሶው ሁሉ ኦሮሞ ኦሮሞ የሚል ቅኝት ይበዛበት ነበር፡፡ ያም ከንቱነት ነው፡፡ ሲጀመር ሀጫሉ ሰው እንጂ ኦሮሞ አይደለም ወይም አልነበረም፡፡ ከሰውነትም ሲያንስ ኢትዮጵያዊ ነበር – ቢያድለው፡፡ ከዚያ አንሶ ኦሮሞ ኦሮሞ ማለት ግን ከእንስሳም ማነስ ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ ነገድ ደረጃ ወርዶ ከዘቀጠ ኅሊናው ይታወራል፡፡ ከዘሩ ውጪም አያስብም፡፡ ከዘሩ ውጪ ያለው ሁሉ ሰው አይመስለውም፡፡ ይህን በአክራሪ ኦሮሞዎች የሚስተዋል የዘረኝነት አዝማሚያ ከአክራሪ ትግሬዎች ውጪ በሌሎች ብዙም አናይም፡፡ ለምሣሌ አያርግበትና አቶ እርገጤ ቢሞት “አማራው እርገጤ፣ አማራው እርገጤ፣ ውይ ዋይ ዋይ አማራው እርገጤ” እየተባለ አይለቀስም – አልተለመደም፡፡ “ጅግናው አማራ አቶ እርገጤን በዛሬው ዕለት ተነጠቀ! ወይ የአማራ አለመታደል! ዕድለቢሱ አማራ፣ አቶ እርገጤን በዛሬዋ ዕለት ኦነግ/ኦህዲድ ቀጠፈው…!” እየተባለ ቢለቀስ ልቅሶው እንዴት ወደሳቅ እንደሚለወጥ ይታያችሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአብዛኛዎቹ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ የሆነ ዝንባሌ… - መሰረት ተስፉ

ትንሽ ሰው ምን ጊዜም ትንሽ ነው፡፡ የርሱ ትንሽነት ብቻውን ምንም አይደለም፡፡ ግን አንሶ ያሳንሳል፡፡ ለምሣሌ እኔን፡፡ እንጂ እነ “ፕሮፌሰር” ሣጥናኤል ማነው ሕዝቅኤል ከድንችና ከካሮትም አንሰው በአሁኑ ሰዓት አማራንና ኦሮሞን ለማፋጀት ምን እያደረጉ እንደሆነ እያየንና እየሰማን ነው፡፡ ሤራቸው ለጊዜው በመክሸፉ አብደዋል፡፡ ፈረንጆቹ እንደሆኑ ዋና ዓላማቸው ኢትዮጵያን ማጥፋት በመሆኑ ከ“አይዟችሁ ግፉበት” በስተቀር በገንዘብ፣ በሃሳብና በሞራል ከመደገፍ በስተቀር ምንም አይሏቸውም፡፡

እነአቢይ ግን በጀመሩት ቢገፉበት ቢያንስ ራሳቸውን ከጭዳነት ይታደጋሉ – ለውጥም እያሳዩ ነው፡፡ እነእስክንድርን በመናጆነት ማሰራቸው ግን አግባብነቱ በፍጹም አልታየኝም፡፡ ስለምንም አይደለም – ግን “ከአክራሪ የኦሮሞ ቄሮዎች ተጠበቁ” ብለው እንወክለዋለን የሚሉትን ማኅበረሰብ ማስጠንቀቃቸውና በቀላሉ ለጥቃት እንዳይዳረጉ ማደራጀታቸው ከማስመስገን አልፎ  እንደወንጀል ሊቆጠር እንደማይገባ እንኳንስ እኔ አሳሪዎቹ ራሳቸውም የሚረዱት ይመስለኛል፡፡ ግን ይሄ “ከዘር ልጓም ይስባል” የሚባል ነገር እየማረካቸው በስህተት ጎዳና መትመምን መርጠዋል – እንደወያኔ እስኪንኮታኮቱ፡፡ ይህ አካሄዳቸው በሌላ በኩል ሊያስደስቱት የሚፈልጉት ወገን መኖሩን ይጠቁማል፡፡ በስንቱ አርረንና ተክነን እንዘልቀዋለን ግን ጎበዝ!

ትልቁ ነጥብ አሁን በተያያዝነው የዘር መሥፈርትና የዘረኝነት ፖለቲካ የትም አንደርስም፡፡ ኢትዮጵያ ከሙታን መንደር እንድትነሣ ከፈለግን የትምህርት ደረጃ፣ የሙያ ብቃትና ልምድና ችሎታ ዋና መሥፈርት ሊሆኑ ይገባል፡፡ የ8ኛ ክፍል ምሩቅ ሚልኬሣ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ የማስትርስ ዲግሪ ምሩቅ ዘበርጋ ዘበኛ ከሆነ፣ አሥር አለቃ ሐጎስ በሚመራው የሻምበል ጦር ሻለቃ ዘበርጋ የግምጃ ቤት ኃላፊ ከሆነ፣ የዲፕሎማ ምሩቁ ስንሻው በርዕሰ መምህርነት በሚመራው ኮሌጅ የፒኤችዲ ምሩቁ ኡጁሉ ምክትል ዲን ከሆነ … አደጋ አለው! ዕውቀት በዘር ተረገጠ፤ እውነት በዕብለት ዕድገትም በውድቀት ተሸነፈ፡፡ በሀገራችን እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ Meritocracy should be reinstated, ASAP ma74085@gmail.com.

10 Comments

  1. It is really so enlightening! Fact is is always fact, you can’t hide it though it may be bitter. I have observed my country Ethiopia how she is suffering from the so called “teregninet”, ‘a turn to rule’. This time around is I think the worst of all times in the history of Ethiopia.
    Just very minor correction to the writer, 99.9 needs 0.01 to be 100, not 0.09 as mentioned in the piece. Just minor numeric error. The rest, no words! Just best!

  2. ድንቅ ነዉ አንድ ሃሳብህ ላይ አልተሰማማሁም በኮሮና ወይም በመኪና ቢሞት በተመሳሳይ ሁኔታ ይለቀስታል የሀገርና የህዝብ ንብረትም በተመሳሳይ መልኩ ይወድም ነበር። ምክንያቱም የያዘዉ ኮሮናም ሆነ የገጨዉ መኪና አማራ ኮሮና ወይም አማራ መኪና ተብለዉ በኦሮማዉያን ይታሰቡ ነበር። ዉዳሴዉ ከደርግ ጀምሮ የተጠናወተን አዝማሪነት ሲሆን ያ ሁሉ ጥፋት ቀደም ሲል በፕሮግራም ተይዞ ጊዜ ሲጠበቅለት የነበረ ነዉ በሀጫሉ ሞተ ተተገበረ።
    አቶ ሕዝቅኤልንም ያነሳህ መሰለኝ ግለሰቡ ሰነዱ ሲፈተሺ ለአለም ያበረከተዉ ልዩ የሆነ ነገር አለ በዚህም እስከዛሬ በተጠቃሚዎቹ በእጅጉ ተመስግኖበታል ኢትዮጵያ ዉስጥ የደረሰዉ ጥፋት የሱን የምርምር ዉጤት ቄሮ በመጠቀሙ ነዉ። ምርምሩንም ያደረገዉ እራሱ እጹን ለ30 አመት ያህል በመጠቀሙ ነዉ ከዚህ ጽሁፍ ሌላም አልጻፈም ምን በወጣዉ? ያም የምርምር ስራዉ አብዝቶ ሲጠቀምበት የነበረ አሁንም በዱቄት መልኩ የሚገለገልበት ጫት ስለተባለዉ ተክል ነዉ።
    ይህ ተክል ጠቃሚነቱ የጉድ ነዉ በተቀመጥክበት አለምን አቅርቦ ያሳይሃል አቀበቱንና ገደሉን ሜዳ አድርጎ ያሳይሀል ጥቅሙ ብዙ ነዉ የምርመራዉን ዉጤት እንዳላሳንስበት ፈልገህ አንብበዉ ካላነሳዉ በመጽሀፍ መልክ እቸበችበዋለሁ ብሎ ካላሰበ።
    ጸጋዬ አራርሶን በተመለከተ አባቴ ኦሮሞ ነዉ ይላል ይዉለደዉ ያሳድገዉ የተረጋገጠ ነገር የለም የተረጋገጠዉ ግን እናቱ አማራ መሆናቸዉ ሚስቱ ትግሬ መሆኗ ልጁ ደግሞ አማኦሮትግ ነዉ ነገዱና ዜግነቱ። ይህ የአእምሮዉ ሚዛን በእጅጉ የተቃወሰ ግለሰብ ልጁን እዉቅና ለማይሰጥ ስርአት ስጋና ነብሱን ያባክናታል። ከሱስ በአንድ መልኩ ይችን አለም የተገላገለዉ ሀጫሉ ሳይሻል አይቀርም። እስቲ ግን የመልሱን ምቱን እያነበብኩ ለመሳቅ ወደ ምሽጌ ገብቻለሁ።

  3. አይ ጒዱ ቀበሮ፣
    “ሀጫሉ ኦሮሞነቱን ማስቀደሙ መብቱ ነው፡፡ እኔም ኢትዮጵያዊነቴን ማስቀደሜ መብቴ ነው” ብለህ ቀለሙ ሳይደርቅ “አማራ እንኳንስ እስከመፈጠሩ የማያውቀውን ሀጫሉን በተቀነባበረ ሁኔታ ሊገድል ይቅርና በጉያው አቅፎ የሚያኖራቸውን ብአዴን ተብዬዎቹን በፊት የወያኔና አሁን የኦህዲድ አሽከሮች ከነመፈጠራቸውም አያስታውሳቸውም፡፡ አትታዘቡኝና አማራ ልክ እንደማንኛውም ‹ቤርቤረሰብ› ሁሉ መግደል የማይችል ሆኖ አይደለም – ግን ገና “አልተፈቀደለትም”፡፡ እስኪፈቀድለት መጠበቅ ግን ጅልነት ነው፡፡ አማራ ሁሉን ነገር ለፈጣሪው ሰጥቶ ፍርዱን ከላይ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል” የሚል ፉከራ አሰማህ! አማራ ነኝ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለትህ ይሆን? “ኢትዮጵያዊ”ን ለምን መሸፈኛ አረግኸው? ወይንስ አማራ ብቻ ነው ኢትዮጵያዊ እያልከን ነው? ቃላተኛ ስለሆነክ ቀላሉን ነገር ታወሳስባለህ! ሀጫሉ እስከ ገባኝ ከሆነ ኦሮሞ ነኝ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ ነው የሚል የነበረ። ለዚህም ነው አክራሪዎች ቅር የተሰኙበት!

    • አመሰግናለሁ ሥዩሜ! አማራ ማለት የአፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ የሆነ ማለት ከሆነ ልክ ነው የመጀመሪያ ቋንቋ”የ” አማርኛ ነው። ቋንቋ በመሠረቱና በእውነቱ የሁሉም እንጂ የግለሰብ ንብረት አይደለም። ቋንቋ ከሸሚዝና ከናቲራ የማይለይ በዐይን የማይታይ ረቂቅ የመግባቢያ መሣሪያ ነው።
      እኔ አማራ ነኝ አላልኩም። አማራ ሁሉም ነው፤ ሁሉም አማራ ነው። ዋናው ደግሞ በሰው ልጅነት ማመን ለው።
      እርግጥ ነው በአንድ እካባቢ መኖር የሚያመጣው የተወሰነ ማኅበራዊ፣ ባህላዊ፣ ሥነ ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ የጋራ ገጽታ ይኖራል። ያን መሰሉ ተራክቦ አንዱን ማኅበረሰብ ከሌላው በበለጠ እርሥ በርሥ ሊያቀራርበውና የጋራ የሆኑ ዕሤቶች ባለቤት ሊያደርገው ቢችል የሚጠበቅ ነው። ከዚህ አኳያ በአማራነት ተፈርጆ ቤተሥኪያን እንደገባች ውሻ የወያኔና ኦነጋውያን ተከታታይ ዱላ ሰለባ የሆነው ህዝብ ራሱን መከላከል ቢጀምርና በርግጥም ሲጀምር የአሁኑ የፈሪ ዱላ እንደማይቀጥል እሙን ነው፤ ያን መግለጼ እንጂ ለጉራና ለዕብሪት አይደለም አንተ የጠቀሥከውን መጥቀሤ። “ከንግዱህ ዝም ብዬ አልሞትም፤ እየገደልኩ እሞታለሁ” በሚል የትግሥቱንም እንበለው የፍርሀቱን ካባ ካወለቀ ይሄ ሁሉ የፈሪዎች ዱላ የት ድረሥ እንደሚነጉድ ሌላው ሁሉ ቢክድ እኔ በሚገባ አውቃለሁ፤ …ደግሞም አትጠረጠር ኢትዮጵያዊም ሰውም አማርኛ ተናጋሪም ነኝ። ይቅናህ፤ ከሥድብ በሥተቀር ለገምቢ ውይይት ምነዜም ዝግጁ ነኝ።

      • አያ ጉዱ፣
        “ቀበሮ” ያልኩህ ከአጻጻፍህ ተነስቼ አንተን ለመግለጽ ተስማሚ ስለሆነ እንጂ ለስድብ አይደለም። ከአነጋገር ይፈረዳል ሲባል አልሰማህ? ወይ አክሮባቲስት ይሻልህ ይሆን? አማርኛ ተናጋሪ እንጂ አማራ አይደለሁም፤ አማራ አማርኛ የሚናገር ነው፤ ቋንቋ “ከሸሚዝና ከካናቴራ አይለይም” ትለናለህ። ሲፈለግ ይለበሳል፣ ሲፈለግ ይወልቃል ነው? ወልቆ የት ይደረጋል? ላውንደሪ ውስጥ ይታጠባል? ስታታልል ከተያዝክ ጨምረህ ታታልላህ እንጂ ስሕተትክን አትቀበልም።

        ሃጫሉ ሞቶ አጥንቱ ሳያርፍ “የኢትዮጵያ ነፃነት ታጋይ እንዳልሆነና እንዳልነበረም የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ራሱ በግልጽ ነግሮናል፡፡ አስከሬኑ የለበሰው ባንዲራ የግብጽን እንጂ የኢትዮጵያን አልነበረም” ትላለህ። ዘመዶቹ እና ወዳጆቹ ይህን ሲያነብቡ ምን ይሰማቸው ይሆን ብለህ አስበሃል? በ “ጉዱ ካሳ” ጭንብል ተከልለሃል፤ ከእውነት ጋር ስላልቆምክ የሰው ፊት ያስፈራሃል! ይኸ አገላለጽህ ነውር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር የጎደለው ነው። ጥላቻህ እንደ ጃዋር እና እስክንድር እውነታውን እንድታዘባርቅ አድርጎሃል። ኦሮሚያ የሚሉትን አገርና ባንዲራ ከዚህ ያደረሰው ህወሓትና ኦሮሞን ነጻ እናወጣለን የሚሉ፣ ራሳቸው ነጻ ያልወጡ ሰዎች ናቸው፤ 60 ዓመት ዕድሜ ያለፈው ሰው ይዘናጋል፣ ቃሉ እንዲህ ይምታታል ብዬ አልጠበኩም! ለማንኛውም ቅን እስካልሆንክ፣ ብልጥነትህ የትም አያደርስህም!

        በነገራችን ላይ፣ ዘሐበሻና ሳተናውን ሳይ ጸሐፊዎቹ ከአንድ ወንዝ የተቀዱ ናቸው። ስም ቀያይረው አስተያየቱም ጋ እነርሱው ናቸው። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሉ፣ የሚቆረቆሩ ይመስላሉ። ምግባራቸው ግን የህወሓት ነው። ከጧት እስከ ማታ ኦሮሞ እንዲህ አረገ፣ ኦሮሞ እንዲህ አለ ይላሉ፤ ከእነዚያ ወገን ደግሞ አማራ እንዲህ አለ፣ እንዲህ ሆነ ይላሉ። የህወሓትም እቅድ ይኸው ነው፣ ማተረማመስ ነው። የጥላቻ ድቤ በመደለቅ አገር መገንባት አይቻልም፤ በ 50 ዓመት መማር ያቃተን ይህንን ነው። ስለ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ያልከውን እስማማለሁ፤ እንደ ቀደሙት ጓዶቹ የሥልጣን ጥመኛ ነው። ጊዜ ባለፈበት ትእይንት ያደናግራል፤ ውጤቱ ሲከፋ ፈርጥጦ የሚገባበትን ምሽግ አዘጋጅቷል። የማልስማማው ችሎታውን ማሳነስህ ላይ ነው፤ ከፍተኛ ችሎታ እንዳለው ያስታውቃል። የመለስ ዜናዊን ጒብዝና መካድ አይቻልም፤ በተለይ ፈረንጆቹን ሲጫወትባቸው መመልከት። ቅን ሁን፤

        በአንድ በኲል “አማራ ልክ እንደማንኛውም ‹ቤርቤረሰብ› ሁሉ መግደል የማይችል ሆኖ አይደለም – ግን ገና “አልተፈቀደለትም”፡፡ እስኪፈቀድለት መጠበቅ ግን ጅልነት ነው፡፡ አማራ ሁሉን ነገር ለፈጣሪው ሰጥቶ ፍርዱን ከላይ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል” ትለናለህ። ደግሞ ሰላም ወዳድ ለመምሰል ትሞክራለህ፤ ለጠቡማ ህወሓትም፣ ኦሮሞውም አይተናነስም። ይህን አስበህ ታውቃለህ፤ ለጠብ ማንም ከማንም አያንስም። በእልቂት ማግሥት ገና ሕዝብ እንዲጫረስ ማነሳሳትህ አስተሳሰብክን እንዳሰብከው አልደበቀልህም! ለመሆኑ፣ አንተና መሰሎችህን ለማስተማር ስንት ሕዝብ ማለቅ አለበት?

        • በጥሞና አነበብኩህ። አሥር ሸክም የደሬ ፍልጥ ቢነድብህ የማትበሥል የደናቁርቱ ቡድን አባልነትህን በማረጋገጤ ካንተ ጋር ሃሣብ መለዋወጥ ድንጋይ ላይ ውኃ ማፍሰስ ነው። “እንዳገርህ ቀድሥ እንዳገሬ እቀድሣለሁ” እንደተባለው ‘ተፋታሁህ’። ይቅናህ ወንድማለም። አንተን ያሥደሥትልኝ እንጂ እንዳልሄንኩ ባውቅም ያልከኝን ሁሉ እንደሆንኩ ቁጠርና ተደሰት። ቻው!

    • ጸሃፊው አማራ ይሁን ምን ይሁን የሚያመለክት ነገር አላየሁበትም፡፡ በእርግጥ የአማራን ጸባይ በቀላል ቋንቋ በማጠቃለል ገልጾታል ይሄውም ፈሪሃ እግዚአብሔር እንደሆነ ፡ አማራነትን በኢትዮጵያዊነት የማይቀይር ህዝብ ነው፤ እናት አገሩ ኢትዮጵያ ምንግዜም መጀመሪያ ነው ክምንም በላይ! ጠላቱን ቢገድልም ስነምግባር ያለው ህዝብ ነው እና ጀግናም ህዝብ ነው፡፡

  4. በሃገሪቱ ውስጥ የሚታየውን የፓለቲካ መታመስና በውጭ በየሰበቡ ጥገኝነት ጠይቆ የተጠለለውን ዝብርቅ ህዝብ ሃሳብና ድርጊት ስሰማና ስመለከት ምድሪቱ ተስፋ የላትም እላለሁ። የኢትዮጵያ ችግር ይበልጡ የሚመነጨው ከራሳችን ነው። ንጉሱን ኋላ ቀር፤ ዘራፊ፤ በማለት መንግስታቸውን አሽቀንጥሮ በመጣል እልፍ የሃገሪቱን ምርጥ ልጆች በየምክንያቱ አፈር መለሰባቸው። የሃገሪቱ ሞትና መፈራረክ የጀመረው ያኔ ነው። የወታደሩ መንጋ አንድ ጥይትና አንድ ሰው እስኪቀር እንዳላለ ወንበዴ እያለ በሚጠራቸው ሻቢያና ወያኔ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ከስልጣን ተባረረ። ለእናት ሃገራቸው ለዘመናት የተዋደቁ ልጆች የሻቢያ ታንክ በላያቸው ላይ ተነዳባቸው። ወያኔ ከስር ከመሰረቱ የወታደሩን መዋቅር በማፈራረስ በራሱ ሰዎች ተካው። ሞቶ መነሳት የሚለውን የካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን መጣጥፍ ጉግል ላይ ፈልጎ ማንበብ ወያኔ ምን ያህል ገና ከጅምሩ አረመኔ እንደሆነ ያሳያል። ሻቢያ በአስመራ ወያኔ በአዲስ አበባ አለቆች ከሆኑ በኋላ ደግሞ ባልተጠበቀ ሁኔታ ዱባ በማያበቅል የምድረበዳ መሬት ሰበብ ግብ ግብ ገጥመው ተጨራረሱ። የፓለቲካ እብደት ማቆሚያ የለውም። ሻቢያና ወያኔ ወንድምና እህታቸውን ገድሎው ከበሮ የሚመቱ፤ ክራር የሚከረክሩ ድውያኖች ናቸው። ዛሬ ከ 30 ዓመት በህዋላ የኤርትራን ነጻነት ምን እንደሚመስል፤ የወያኔን ውርደትና ተንኮልና መሰሪነት ከመቀለው ምሽጋቸው ሆነው የሚሰሩትን እያየነው ነው።

    አሁን እንሆ ከወያኔ የተንኮል ጆኒያ አፈትልኮ የወጣው ዶ/ር አብይ የሃገሪቱ ጠ/ሚ ከሆነ በህዋላ መልካም የለውጥ ንፋስ ቢነፍስም በፊትም በኦሮሞ ህዝብ ሲነግዱ የነበሩት የሻቢያና የወያኔ ስልት ግርፍ የኦሮሞ ድርጅቶች ለምድሪቱ ሰላም አልሰጧትም። የተንኮላቸውም መራራነት የሚመዘነው ከወያኔ ጋር በመመሳጠር ሃጫሉን መግደላቸውና በወለጋ ህዝባችን በሰላም እንዳይኖር ማመሳቸው ነው። በመሃል ሃገርና በአመራር ላይ ተሰግስገው በዘርና በሃይማኖት ሰው ተለይቶ ሲያልቅ ቆመው ያዪት የኦሮሞ ፓሊስ፤ ልዪ ሃይልና የስለላ መረቡ ነው። በአዲስ አበባ ቤቶችን፤ መሬትን ባለቤት ሳያውቅ ሌላ ደባል ሰው የእርሱ እንደሆነ የሚደረገው ስልታዊ ወረራም ከዚሁ የኦሮሞ የፓለቲካ ግለኝነት ጋር የተዛመደ ሴራ ነው። ይህ ደግሞ ግጭት እንዲያመጣ ሆን ተብሎ የሚሰራ የከተማ ሽፍታነት ነው። በመሰረቱ ሃገሪቱ ከወያኔ የግዛት ዘመን በከፋ መልኩ አሁን ማጥ ውስጥ ናት። እኔ አንድ ነገር ይገርመኛል። ተደጋግሞ “የኦሮሞ ህዝብ ነጻ ወጥቷል” ሲባል እሰማለሁ። ከማን ነው ነጻ የሚወጣው? ምን ለማለትስ ተፈልጎ ነው? የኦሮም ህዝብ ነጻ መውጣት ካለበት መውጣት ያለበት ከራሱ ነው። እንደ ምድር አሸን ቁጥራቸው የበዛው የኦሮሞን ህዝብ እንወክላለን የሚሉት የአሁን እና ጡረተኛ ፓለቲከኞች ቀና ብለው ጊዜና ሰዓቱን ሊያዪ ይገባል። ዛሬም የሚመሩበትና የሚያስቡበት ጭንቅላት የሚተነፍሱበት ሳንባ ከ 60 ዓመት በፊት በተገጠመላቸው ነው። እንዴት ሰው እድሜ ልኩን ፓለቲካ ሲጋት ይሞታል? ህይወት እኮ ራሷ ያለ ፓለቲካ አጭር ናት። ስንት የሚሰራ፤ የምንማረው፤ የሚታይ ነገር እያለ የአማራ ነጻነት፤ የትግሬ ጭቆና የኦሮሞ ህዝብ ገለ መሌ ስንል ዓለም ጥሎን አለፈ። ሰው በቋንቋው መናገሩ የነጻነት ምልክት አይደለም። ወንዝ የማያሻገር ቋንቋ የሰውን ህይወት አይለውጥም። ቋንቋዬ፤ ሃይማኖቴ፤ ምድሬ፤ መንደሬ እሺ ቀቅለህ ብላውና ከረሃብ ያተርፍህ እንደሆነ እንይ! የሰው ማሳ እያቃጠልክ ተራብኩ ብትል ማን ይሰማሃል? ዓለም እንደሆነ ጥቁሩን ህዝብ ጠልቶታል። የራሳችን ሃገር እሳት ለኩሰን ባስጠጉን ሃገራት ችግር ፈጣሪዎች ነንና!
    በመሰረቱ ፓለቲካ ከሸርሙጣም ሸርሙጣ ነው። የአሻሮ አስተሳሰብ። እስቲ ይታያችሁ ሰው ለመግደል ጣውላ ላይ ምስማር አስገብተህ፤ በጀሪካ ቤንዚን ይዘህ፤ ቢላዋና ቋንጨራ ታጥቀህ የሌላውን አንገት ስትቀላና በድኑን ስታቃጥል፤ ንብረት ስትዘርፍ ነገ አንተን የሚገል እንደሚኖር እንዴት ይጠፋሃል? ግን ደም አፍሳሾች እኖራለሁ እንጂ እንሞታለን አይሉም። የከሰረ ፓለቲካ ይህ ነው።
    ልጅ ጉድ ካሳ – ገና ብዙ ሃበሳ በምድሪቱ ላይ ይዘንባል። በምንም መልኩ በዘርና በጎሳ በጥቅማጥቅም እና በክልል የተሰመረ ድንበር የጥልና የብጥብጥ ምልክት ነው። ወያኔ በአዲስ አበባ “ለኦሮሞ ልዪ ጥቅም” ይሰጥ ያለው ራሱ ግጦ ከጨረሰ በህዋላ ሰውና ሰውን ለማናከስ እንደነበር ሊታወቅ ይገባል። አሁንም አዲስ አበባንና ከባቢዋን በኦሮሞ ለማጥለቅለቅ የሚሰራው ሰውና ግልጽ ደባ ከዚያው ክፋት ዙሪያ የመነጨ ነው። እናማ ምንም ብርሃን አይታየኝም። በሃይማኖት ሰው እየተመረጠ አንገቱ በሚታረድባት ሃገር፤ የእብድ መንጋ እንደ አሸን ሰው ለመግደል በሚፈጥንባት ምድር ሰው በሰውነቱ ተከብሮ ይኖራል ብየ አላምንም። ወያኔም ይገነጠላል። ኦሮሞም ይገነጠላል ከዚያ ዝንተ ዓለም ሲገዳደል ይኖራል። የእኔ ብቻ የሚለው ፓለቲካ ፍሬው ሞትና ጥፋት ነው። “Meritocracy should be reinstated” ብለሃል አይ አንተ እስቲ ይህን መጽሃፍ አንብብ The Meritocracy Trap: How America’s Foundational Myth Feeds Inequality, Dismantles the Middle Class, and Devours the Elite by Daniel Markovits. አይን ከፋች ሆኖ አግቼዋለሁ። ዓለማችን ተዘቅዝቃለች። ከስሯ ተቀምጠው አይን አይኗን እያዪ የሚያለቅሱ አይኖች በዝተዋል። ይስቁ የነበሩም እድሜ ለኮቪድ 19 ከማቴሪያል የመነጨ ሃሴታቸውን ቀስ በቀስ እየተነፈጉ ነው። ከዋሻ መጣን ይሉን ነበር አዋቂ ነን የሚሉ እረ አሁንስ ዋሻ ውስጥ አይደል እንዴ ያለነው። ለዚያውም ሰልጥነናል ብለን ሰይጥነን! በቃኝ

  5. Dear Gudu Kassa,

    In our mother land Ethiopia, politics is prostitution and politicians are indeed prostitutes. Individuals whom we worshiped yesterday as saviors of Ethiopia joined Woyane or the “BALETERA OROMO” and preferred to deny Ethnic cleansing by wild animals in the name of kero. How painful and sad!!!
    While I feel sad by the untimely death of Hundessa, I do not understand why all these hoopla given the deceased person was an ethnonationalist preaching not for democracy and equality of Ethiopians but the dominancy of oromo. A country that never bothered to provide food and shelter to families of people killed in the most barbaric manner or displaced by oromo wild animals is busy in renaming the main attractions of the city after Hundessa.

    Free Eskinder Nega, Yilkal Getnet and co.

  6. ጽሁፍህ ያማል! ዘፋኙንማ ቀለዱብን፡፡ “አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ነው””። ጊዜው ከመቼውም በላይ ኢትዮጵያዊነታችንን ማንነታችንን የተፈታተኑበት ዘመን ነው፡፡ ሱማሌ እንኳን አገር ለመባል እየጣረች እኛ በዚህ ዘመን ኦሮሞ መጀመሪያ እያልን የገዛ ወጎኖቻችንን በአጸያፊ መንገድ ነፍስ ስናጠፋ ማየቱም መስማቱም ይዘገንናል፡፡ ጣሊያን እንኳን ከመርዝ ጭሱ በስተቀር እንደዚህ አይነት ጥላቻና ጭፍጨፋ አላደረገም ቢባል እውነትነት አለው፡፡

    ጠ/ሚሩ ከኦነግ ቄሮ ደንቆሮዎች ጋር ኢትዮጵያዊ መሆናችንን ከሚያሸማቅቁ ደንቆሮዎች ጋር ቁማር ሲጫወት በተለይ በአማራ እና በከርስቲያን ወጪ እዚህ አድርሶናል፡፡ አሁንም ሰላም ሊኖር እና ግድያን የሚቀንሰው በጥበቃ ሃይል ውስጥ ያሉትን ሹማምንቱን በየጠ/ግዛቱ ያሉትን ደንቆሮዎች አውርዶ አዲስ መዋቅር ያስፈልገዋል፡፡ የኦነግ ን በየድርጅቱ ውስጥ መሰግሰግ ፍጥጥ ብሎ ወጥቷል ጉዳቸው፡፡ የበለጠ ህዝብ ከማሳለቃቸው በፊት ጠ/ሚሩ መንጥሮ ማውጣት አለበት፡፡ እነሱ ለኦሮሞነታቸው እንጂ ለኢትጵዮጵያ እንዳልሆኖ ቁልጭ አድርገው እያሳዩን ነው፡፡ ሌላው ኦሮሞ መጀመሪያ እያሉ ኢትዮጵያዊነታቸውን ከሃዲ ጠ/ግዛቶች ወደ ሌላ ግዛት እንዳይሄዱ በኬላ ማጠር፡፡ እዛው ጨጨብሳውን እየበላ ይቀመጥ፡፡ ለማንም ለምንም አይጠቅሙም ሰው ከማረድ በስተቀር፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share