ፓለቲካው ይደር ለክብርት ሀገር – ምንድነው ዝምታው?  –  ከአባዊርቱ

ወቅቱ ኢትዮጵያን ማፍረስ ወይንም ማዳን ላይ ነው :: ዛሬ በስራ ላይ ያለው መንግስትን አጠናክሮ ሀገርን ማዳን ወይንም ቦርቡሮ  ለውጪ ጠላትና ለውስጥ ባንዳ ማስርከብ ትንቅንቅ ላይ ነው ያለነው። ግልጽና ግልጽ ነው።
የሀጫሉን ተቆርጦ የቀረውን በልብ ስብራት ሰማሁት። የዚህን ድንቅ፣ ቆራጥና ጀግና ልጅ ወኔ ከአወረጫጨቱ ጠያቂውን አጣሞ እስከ ማስቀመጥ ድረስ የዘለቀ ነበር። እንዲህ ነው ጀግና።  ፊትለፊት የሚናገር በጽኑ እምነት። በአንጻሩ ያንን የሳጥናኤል አለቃ ብርሀነ መስቀል ሰኚንም አየሁት – ከ ኮምፒውተር ጀርባ ሆኖ የጥፋት መርዙን ሲረጭ። የሁለቱን ፊት ገጽታዎች ለንጽጽር እያንዳንዱ ወገን ማየት አለበት። የጀግናና በጥራቃን ከሀዲ ትርጉም ዲክሽነሪ መፈለግ አይኖርበትምና።
ለተከበራችሁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች
ከዶር ኦባንግ እስከ ዶር ብርሀኑ፣ ከ ዶር አረጋዊ እስከ ዶር በየነ ጴጥሮስ ፣ የሀጫሉ እልፈትና የህዝቡ እልቂት የሚገዳችሁ ወገን የዖሮሞ ምሁራን በሙሉ እናም  በተለየ መንገድ ታማኝ የኢትዮጵያ ፓርቲ የክብር እንደራሴ ታማኝ በየነ (ባለህበት)
በኢትዮጵያ አምላክ የሆነ አስቸኳይ አገርና ወገን አድን ትብብር ፍጠሩና የሆነ ቢሮ ጠይቃችሁ እዚያው ጠ/ሚር መ/ቤት አካባቢ የምክክር ጊዜያው መ/ቤት አቋቁሙና ዶር አቢይን እርዱት። ታድያ ሁላችሁንም ተቃዋሚ ተብዬዎች  አይደለም  (ህውሀት የለየለት ጠላትን በብዙ ማይልስ ራቋቸው – ባለማፈር እኛሳ እንዳይሏችሁ ነው)። ምንድነው የሚጠበቀው ወገኖች? ፖለቲካውን እርግፍ አድርጋችሁ ተውት እስቲ ለ 6 ወራት ያህል።ለአገር ህልውና ላይ ብቻ ከጠ/ሚሩ እየተቀናጃችሁ ምከሩ። እስቲ አንድ ቀላል ምሳሌ ልስጥ። በጣም የምትወዷት እናታችሁ በጸና ታመዋል ልበል (አያድርስባችሁና)። እኒህ እናትን ለመታደግ በአካባቢያችሁ የመንግስት ክሊኒክ የለም አሉ። ቦታው ገጠር ነው ክሊኒክ የሌለው። ያለው አማራጭ የባህላዊ ሀኪም ነው፣ እሱ ደግሞ በ ሁለት መቶ ኪሜ ርቀት በቅሎና ፈረስ እንጅ መኪና የማይገባው ቦታ ላይ ነው። በርግጠኝነት ፈዋሽ ነው ሰውዬው። ይህንን እያወቃችሁ አይደለም በፈረስና በበቅሎ መሬቱን በእጅም ቢሆን እየቧጠጣችሁ የዳዴ ሄዳችሁ ያንን መድኃኒት አዋቂ ለእናታችሁ አምጥታችሁ ነፍሳቸውን ትታደጋላችሁ ወይስ በህመም ይሙቱ ትላላችሁ? ኢትዮጵያ እኮ ነች የታመመችው።በቃሬዛም ያለችው ወገኖች። እንዴት ዝም ይባላል? እንደምንስ ለመንግስት ብቻ ይተዋል? ምን እንርዳ፣ በሉ እንጅ ። ካደረጋችሁት እሰየው፣ ስላልሰማሁ ነው። ይህን ስል ደግሞ ከዚህ ቀደም የጥምረት መንግስት ብለው የጅቦች መንጋ እንደሚያሾፉት ሳይሆን በመንግስት ጥላ ስር ሆናችሁ የኢትዮጵያን ህልውና ማስጠበቅ ላይ ተባበሩ ማለቴ ነው። እናንተ እያላችሁ፣ በአለም ተበትነን ስንት ምሁራን፣ አዋቂዎች አገራችን አፍርታ እንደ ብርሀነመስቀል ሰኚ አይነት አውሬ በቴሌቪዥን ኡትዮጵያን የምታህል ክቡርና ድንቅ አገር በአደባባይ በግልጽ በቲቪ ሚስማር በትኑ፣ መንገዶችን ዝጉ፣ አገር ትቃጠል አይነት ትእዛዝ ይስጥብን? እንዴት አገራችንን ህዝባችንን ቢንቅ ነው? እኔ ከዚያ ወንዳታ ሀጫሉ  እልፈት ጭራሽ እሣት የለቀቀብኝ ይህ ነው። ሀጫሉስ የወንዶች ቁንጮ ፊትለፊት ናት። አይ ልጅ። እባካችሁ የተቆረጠውንና የወጣውን ቪዲዮ እዩት። ለዚህ ጀግና ለሚሰራለት ሀውልት ማሾፍም ተጀምሯል በዲጂታሎቹ። ሀውልት ቢያንሰውም በቲቪ የማንነቱን ሀውልት ትቶልን አልፏል – በቁም በጥላቻና ዝምታ ሀውልት ሆነን ለቀረነው ይብላኝልን እንጅ
ወገኖች!
ለየልን እኮ። አሁን ኡትዮጵያን ለማዳን ብሎም እያንዳንዳችንን ለማዳን ህብረታችንን የምናሳይበት ወቅት ላይ ነን። ምን መደረግ አለበት? እስቲ ለጊዜው የታየኝን እንዲህ ልበል፣
1) እያንዳንዱ የፓለቲካ መሪ ለተከታዮቹ መሪ ቃል መስጠት። የትብብርና አገር አድን ጥሪ ዘልቆ ይግባ
2) መዋቅሮቻችሁን ለመንግስት አቅጣጫ ማሳለጫ ማዋል
3) ኢንፎርሜሽን መቀባበል
4) ከየክልሉ ሀላፊዎች ትብብርን ማሳለጥ
5) ከዳያስፖራው በመቀናጀት ከሞት ተርፈው አሁንም አየር ላይ ተንሳፈው ላሉት ወገኖቻችን እርዳታ ማሰባሰብ። በአካልም እየሄዱ አይዟችሁ ማለት
6) ከዳያስፖራው የተለያዩ የህግና የሴኩሪቲ ተቋሞች ቅንጅትና ህብረት መፍጠር። እንደ አል ማርያም ያሉ ሳተናዎች እንደ አበበ ሰኚን አይነት ከሀዲዎች በህግ ፊት ገትሮ እርቃኑን ማቆም። ለካንስ ከስራ ስላባረሩት ነው ይህ ከሀዲ?
7) እያንዳንዱ ከውጭ “በሏቸው” ያሉትን ሁሉ በነፍስ እየተለቀሙ ፣ ወረቀት የሌለው ቦዘኔ ተጠርዞ ኢትዮጵያ እንዲላክ፣ የውጭ ዜጋ የሆነውን ደግሞ የብዙ ሺህ አመት አገራችንን ጣልቃ እንደገቡ ሰላቶዎች ተቆጥረው ፍርድቤት እንድትገትሯቸው በአለቁት ደሀ ወገኖቻችን ስም እለምናለሁ። አይደለም ስንት አገር በቀል ምሁራን በውጭ የተወለዱት ልጆቻችን እነዚህን ከሀዲዎች ፍርድቤት መገተር አያቅታቸውም። እንዴት ዝም ይባላል?
8) በቀደም በኢሳት ያየሁዋቸው የቀድሞ ሰራዊት አባላት ጋር  ቅንጅትና ምክክር አድርጉ
9) ግስላዋን አዲሲቱን አቃቤ ጄኔራል አዳነች አቤቤን በተለየ ሁኔታ የሚረዱ የጠበቆችና በኢንተርናሽናል ጀርስፕሩደንስ የተካኑ የህግ ጠበብቶችን ማሰባሰብና ማቀናጀት። ይህ ጉዳይ እነዛን የሰው ጅቦች ሁሉ ዘልቆ ለአለም ሸንጎ ለማቅረብም ጥርግያ መንገድ ይከፍታል። የአቢይን ትእግስት ከመጤፍም አልቆጠሩም። ጭራሽ አይናቸውን በጨው ታጥበው ይህ ሁሉ ሆኖ በእልቂቱም ማግስት ሊያስፈራሩን ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ እናንት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ዝም ይባላል? የኢዜማ፣ የብልጽግና፣ የምንምን መርህ ሳይሆን የኢትዮጵያን በህብረት እናድን አርማን ከፍ አድርጋችሁ አስደምሙን እንጅ? ይህን ካላረጋችሁ እመኑኝ እንኳን ልትመረጡ በሚቀጥለው ምርጫ ከነ መፈጠራችሁም የሚያስታውሳችሁ ኡይኖርም። ለዚያውም አገር ከተረፈች ነው። እናም ይህ ለማሰብ ጊዜ የሚፈልግ አይደለም። JUST DO IT!!
ማጠቃለያ!
ከፖለቲካ ፖርቲዎች ባለፈ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ወገን ትብብሩን ከመንግስት ያሳልጥ። በየክልሉ ያላችሁም በተለይ ወጣቶች ሰከን በሉ። የመንግስትን መግለጫ ተከታተሉ። ዶር አቢይ ተገቢ የአገር አድን እርምጃ እየወሰደ ነው። ባሁን ጊዜ የሚወስደውን እርምጃ የሚቃወም ጥፋታችንን የሚሻ ነው። እርምጃ ስል ደግሞ ህጋዊና ተመጣጣኝና ተአማኒ ማለቴም ነው። በዶር አቢይ ይሁን በሺመልስ አብዲሣ ስም ሆነው፣ ስልጣንን መከታ አድርገው ውስጣቸው ተሰንገው ግፍ የሚፈጽሙትን ከሀዲዎች ፈልፍሎ የሚያወጣው ህዝቡ ነው። እነዛ ክፉዎች እንዳንተማመን በአደገኛ ሽቦ ተብትበውን ፈርጥጠው እንጅ እንዲህ መጫወቻና የፈረንጅ መዘባበቻ አንሆናትም ነበር። ኢትዮጵያ ስንት ጀግና እንዳላፈራች እንዲህ መሳለቅያ ሆንና አረፍነው። ከአፍሪካ ሀገራት አስቀድመን ህግና ስርአትን እንዳላስተማርን፣ የአፍሪካ ሀገራትን ወክለን ስለነጻነታቸው በአለም ሸንጎ ይሁን ሀያላንን ፊትለፊት በሙሉ ልብና ስብእና እንዳላስተማርን በምሁር ተብዬ የሰው ግሪሣ ስብእናችን ተናግቶ የፈረንጅና ፋና ወጊ ሆነን ለወግና ማእረግ የተዋሱንን አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ሳይቀሩ በትዝብትና አግራሞት ሲያዩን ልብ ያቆስላል፣ መፈጠርንም ያስጠላል።  እናም ወገኖች ይህ ጊዜ የማይሰጥ ስለሆነ ትብብራችን ነገ ተነገወድያ የማይል ነው።
ዶር አቢይ ብዙ ሊያጠፋ ይችላል ። አጥፍቷልም። ዶር አቢይ ኢትዮጵያ ማለትም አይደለም። አገራችሁን የምትወዱ በሙሉ ለአቢይ ብላችሁ ነው እንዴ?  አቢይን ለመውቀስ፣ ይህ ቢሆን ያ ቢሆን ለማለት የቅንጦት ጊዜ ላይ አይደለንም። ለነገሩ በአብዛኛው የሰውዬውን መከራ የሚያበዙት እነዛው ወፈፌዎቹ ወይም ጭምብሎቻቸው ናቸው። ሆኖም እስቲ አገራችንን እናድንና ስነስርአት ባለው መንገድ እንወቃቀሳለን። ይህ ጥቃት በኦሮሞ፣ አማራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የተቃጣ ነው።  ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ ኦሮሞ ሆነው በክርስቲያንነታቸው ብቻ የተጨፈጨፉትን?:: ዛሬ በእኔ እይታ ይህ ኢትዮጵያውያንን ገድሎ ለማገዳደል ረቆ በስራ ላይ የዋለው የዘራፊው ወያኔ እባብ ስራ ነው::
አመሰግናለሁ ይህን እድል በማግኘቴ።

13 Comments

 1. ግራ ያጋባል እንዲህ ያለ ብሄራዊ ቀዉስ ሲፈጠር ሀገሩን የሚወድ ዜጋ በአንድነት ሊሰባሰብ ይገባዋል። የችግራችን ምንጭ ከአደዋ በሗላ ባቄመብን ፈረንጆችና እሱን ተከትሎ ባደረብን በራስ መተማመን የተበሳጩብን የጠላቶች ሴራ ይመስለኛል። አለበለዚያማ ምን አጠፋን ችግራችንን ችለን የምንኖር ህዝቦች ነን። ታዲያ እኛ እራሳችንን ቀና አድርገን ስንሄድ ባንዳነት አንገታቸዉን ያስደፋቸዉ የባንዳ ልጆች መተናኮሳቸዉን ቀጠሉ እኛም ተዘናጋን ይኸዉ ዛሬ ተሳካላቸዉ።
  መዉደቅ ምንም አይደለም ወድቆ መቅረት እንጂ ኢትዮጵያዉያን የሸፍጥ ፖለቲካን አቁመን ኢዝላሚስት ሐይሎችን ባይነ ቁራኛ እያየን የሻቢያን እርዳታ ሳንጠይቅ ጥሩ መሪ ካለን በኩራት እንሻገራለን። ያ ሳይሆን ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ ሀገር መሪ አረመኔዉ ኢሳይያስ እግር ስር መዉደቁ እኔን ለመሰለዉ ኩሩ ኢትዮጵያዊ የሚመች አይደለም።
  ገና ሲጀመር ስብከቱን ከማስቀደም የወንጀለኛ ትግሬን የባንክ ሂሳብ ማቀዝቀዝ ንብረት ማገድ ዝዉዉራቸዉን መገደብ ነበረበት እሱ መስረቃቸዉን እና መግደላቸዉን አረጋግጬ ነዉ የሚል ቀልድ አመጣ ስንት እሱ የሚያዉቀዉ መረጃ ሞልቶለት። በየጊዜዉ ሊገድሉት ከማድፈጥ አልፈዉ ዛሬ ላይ የእኔ የሚላቸዉን አስተባብረዉበት መከራዉን ያሳዩታል። አሁንም ይህ አጋጣሚ ተፈጥሮለታል ይህ ካለፈዉ እንግዲህ ስራህ ያዉጣህ ነዉ የሚባለዉ። ሲጀመር እነዛ ጡረተኞች (ዳዉድ ኢብሳ/ሌንጮ ለታ/ባቲ/አረጋዊ በርሄ/ዲማ ነገዎ…..) ከዚህ እድሜ በሗላ እንዲማሩ ነዉ ምን ብሎ ነዉ ያስገባቸዉ? ጦር የላቸዉ አያስፈሩት ተሰላችተዉ ሞት የሚጠብቁትን ሆቴል ከፍሎ ክትፎና ዉስኪ እየቀለበ ጥጋብ ቢሰማቸዉ በነሱ ይፈረዳል። ኦ ኤም ኤን እና ጁዋርን ጉልበት ስሞ ማስገባትሰ ከምን የመጣ ነዉ? ሰዉየዉ እራሱ ላይ ጣጣ ያበዛ በምናብ የሚኖር ሰዉ መሰለኝ።

 2. “ለየልን እኮ!!” አባዊርቱ።
  የሂትለር Mein Kampf (ማይን ካምፍ / ትግሌ) ከሚለው መጽሃፍ ለ7ኛው ዐጼ አቢይ አህመድ ስዩመ ሴራ ዘእምነገደ ተዘራ፣ ንጉሠ ነገስት ዘምንልክ ግቢ እየተረጎምክለት ነው!? Joseph Goebbels መሆንህ ነው?? እብደታችሁ ከልክ አላለፈም?? እንዴት ነች ቤተመንግስት ግቢ፣ ወደ እብዶች ሆስፒታል ተቀይራለች መሰል??
  እውነትም ለይቶላችኋል!
  ምናልባት ከመሃላችሁ አንድ ራሱን ያልሳተ ካለ የኦሮሞን ብህል ስሙ > “marihatanii malee maraatanii biyya hin bulchani!” – በምክክር እንጂ በእብደት ሃገር አትመራም!

   • I know of one psycopath in Minilik’s palace and the another is one who wrote this piece! If I am a psycopath, what would you call this writer who cries ግደለው፣ፍለጠው! ? አጨብጫቢዎች!

 3. Abba Caala,
  ቀድሞውኑ ነበር መጥኖ መደቆስ
  አሁን ምን ያደርጋል ድስትን ጥዶ ማልቀስ
  አገርቤት ያሉት በተግባር ኢትዮጵያን ሲያወድሟት እናንተ ውጪ የምትኖሩት በመፈክር እያወደማቺኋት ምን የጋራ እሴት ኖሮን ነው የምንመካከርው ?
  ማነው እብዱ ወንድሙን የሚገል ፣ ሀብት ንብረት የሚያወድም ፣ ትውልድ ሀገሩን በባዕድ አገር አውራ ጎዳናዎች እየዞረ የሚሳደብ ?

 4. አባ ጫላ አባዊርቱን ትተህ ሀሳቡን ተቸው ፊደል ሳትቆጥር አልቀረህም አንተ ከቆዳህ በማይመሳሰሉ እገር መብትህ ተጠብቆ ትኖራለህ አገሪቱን ከጠላት ተናንቀው ያቆዩትን የጀግኖች ልጆች ታርዳለህ የአካባቢው ነዋሪ የሚጠቀምበትን ትምህርት ቤትና የንግድ ተቊዋም አቃጥሉ ትላለህ። ቢያንስ ከ10ኛ ክፍል መሪህ ከተስፋዬ ገ/አብ በተሻለ ስብእና ላይ ተገኝ። ብአዴን የሚባለው ሙትቻ ላንተ አላማ እጅ ባይሰጥ ተከባብረን እንኖር ነበር። አሁንም አልረፈደም እስከዛው ከተረትህና በሚወረወርልህ ፍርፋሪ የዳከረች ህይወትህን በሰባዊ ፍጥረት ሰቆቃ አስደስታት።

 5. የኦሮሚያ ህገ መንግስት ኦሮሚያን ለኦሮሞዎች ኢእኩልነት እና ኢህገመንስታዊ በሆነ መልኩ ለኦሮሞዎች ብቻ በባለቤትነት ይሰጣል ምንም እንኩዋን በሚሊዮኖች ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊን የሚኖሩበት ክልል ቢሆንም ።This is against the universally accepted democratic motto ” One man, One vote ‘

  Consequently በኦሮሚያ ኦሮሞ ያልሆኑ መጤ፣ ሰፋሪ፣ነፍጠኛ እየተባሉ በተለይ ላለፉት 28 ኣመታት ሰቆቃ ሲደርስባቸው ቆይቶኣል።

  ኣሁን በስራ ላይ ያለው የኦሮሚያ ህገ መንግስት የንእሳኑን / Minority rights /መብት የማይጠብቅ ነው። The problems emanate from this defective and undemocratic constitution which is at odds with the currently in use National Constitution.

  ስለዚህ የለውጡ ሀይል እና ዴሞክራት ኦርሞዎች፤

  1.ኦሮሞ ያልሆኑ የክልሉ ኢትዮጵያዊ ነዋሪዎች ከተወላጁ እኩል መብት እንዳላቸው በማያሻማ ሁኔታ በህግ ሊያረጋግጥላቸው ይገባል ።ነዋሪዎቹ የመደራጀት፣ ባህላቸውን የማስፋፋት፣ በፖለቲካው ኣመራር የመምረጥ ብቻ ሳይሆን የመመረጥ መብታቸው …..ወዘተ ከኦሮሞው ወንድም ፣እህቶች እኩል እንዲከበርላቸው መንደንገግ ይኖርበታል።

  2.እንዳስፈላጊነቱ ኦሮሞ ያልሆኑ ስብስቦች የለዩ ዞን ማቁዋቁዋሚያ መብትሊሰጣቸው ይገባል።

  3.የኦሮሞ ሊሂቃን እና ፖለቲከኞች ኦሮሚኛ የፌዴራል የስራ ቁዋንቁዋ እንዲሆን የሚታገሉትን ያህል conversely በክልላቸው የሚገኙት ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰቦች/ Minorities / የፈዴራል የስራ ቁዋንቁዋ ሆኖ እያገለገለ ያለው ኣማሪኛ ከክልሉ ቁዋንቁዋ እኩል ( on a par ) optionally በስራ ላይ እንዲውል መፍቀድ ይገባል ።

  4.Other legal and structural measures should be taken to empower the minorities , otherwise the same tragedy will occur now and then .

  • Is that the problem?
   የችግራችሁ መነሻ፣ ኦሮሞ ሃገር የለውም፣ በኦሮሞ ሃገር ላይ የምናዘው እኛ (ራሳችንን ኢትዮጵያዊ የምንል > የነፍጠኛ ዉሊዶች) ብቻ ነን፣ ኦሮሞ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የለውም፣ ፌደራሊዝሙ ተገርስሶ የአጼዎቹ ጠቅላይ ግዛቶች ይመለሱ ነው የናንተ አላማ እና ጦርነት።
   “የኦሮሚያ ህገ መንግስት ኦሮሚያን ለኦሮሞዎች ኢእኩልነት እና ኢህገመንስታዊ በሆነ መልኩ ለኦሮሞዎች ብቻ በባለቤትነት ይሰጣል” ሁሉም ሃገር ባለቤት አለው! የትኛው ሃገር ነው ማንም ከዬትም መጥቶ እንደልቡ፣ የጥንት ነዋሪውን እያፈናቀለ መሬት የሚቀማ > ኦሮሚያ ብቻ! እኔ ጎጃም ወይም ጎንደር ሄጄ ኢትዮጵያዊ ነኝና አንድ ሁለት ሄክታር የእርሻ መሬት ስጡኝ ብል እሺ ጌታዬ ተብሎ ሊሰጠኝ ነዋ!?
   “በኦሮሚያ ኦሮሞ ያልሆኑ መጤ፣ ሰፋሪ፣ነፍጠኛ እየተባሉ በተለይ ላለፉት 28 ኣመታት ሰቆቃ ሲደርስባቸው ቆይቶኣል።” ኦሮሞው ከዚያ በባሰ መልኩ ሰቆቃ ሲደርስበት አልነበረም?? ኦሮሞ ላይ የመሳሪያ እና የስነልቦና ጦርነት ከመክፈት፣ መቀሌ የመሸገው ማፊያ ላይ ለምን አታደርጉትም??
   “ኣሁን በስራ ላይ ያለው የኦሮሚያ ህገ መንግስት የንእሳኑን / Minority rights /መብት የማይጠብቅ ነው” ኦሮሞው የራሱን ህግ መንግስት እንድጽፍ መቼ ዕድል ተሰጠው?? እናም በጉልበት ልታገኘው ትሞክራለህ?
   “እንዳስፈላጊነቱ ኦሮሞ ያልሆኑ ስብስቦች የለዩ ዞን ማቁዋቁዋሚያ መብትሊሰጣቸው ይገባል” > Only for indigenous minorities, if any. ማንም በጦር ህዝብ ፈጅቶ መሬት ቀምቶ የሰፈረ ሁሉ ይህን ሊያገኝ አይችልም! ይህማ ናዚዎችን መሸለም ይሆናል!
   “የፈዴራል የስራ ቁዋንቁዋ ሆኖ እያገለገለ ያለው ኣማሪኛ ከክልሉ ቁዋንቁዋ እኩል ( on a par ) optionally በስራ ላይ እንዲውል መፍቀድ ይገባል” አይሆንም! መጀመሪያ የፈዴራል እንዲሆን አማርኛን ማን መረጠው?? የሃገሪቱ የቋንቋ ፖሊሲ እንደገና መጠናት አለበት።
   ለነገሩ አልኩኝ እንጂ፣
   ከ150 ዐመታት ወዲህ ተከታታይ የሃበሻ መንግስታት እስከአሁኑዋ ሰዐት ድረስ የኦሮሞን ህዝብ በሃገር ጠላትነት ፈርጀው፣ በያመቱ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ እንቁ ልጆቹን በግፍ መግደላቸው እየባሰ በመቀጠሉ፣ በአንድ ባንዲራ ሥር የመኖር ተስፋ ጨርሶ ተሟጦአል! ከዚህ በኋላ የኦሮሞ ህዝብ ፍትሃዊ ትግሉ ነጻ የሆነች የገዳ ኦሮሚያን መመስረት ብቻ ነው! የምድሩም የሰማዩም ህግ መብት ይሰጠናል!

   • ወንድሜ ኣይተ ሂርቆ እና ከላይ የሞነጨረው ወንድምህ እናመሰሎች በ 21 ክፍለ ዘመን ኣስተሳሰባችሁ ቢያንስ 100- 200 ኣመት ወደ ሁዋላ የቀረ ይመስላል። ኣንዳዴም ሳስብ በምናብ በሚኒሊክ ዘመን የምትኖሩ ቅዥታሞች ትመስሉኛላች ሁ።

    እንደ በቀቀን ትደጋግሙታላች ሁ እንጂ፣ ራስን በራስ ማስተዳደር፣ የዲሞክራሲ እና የዜግነት / citizenship /ጽንሰ ሀሳብ ጨርሶ የገባች ሁ ኣይመስለኝም።የሚያሳዝነው ለማወቅም ፍላጎት የላች ሁም ፣ whether educated or illiterate.

    ፊዴል የቆጠርከው በኣማሪኛ ነው ፣ቁቤ ፣ ኦሮሚያ …….የተፈጠሩት ትናንት ነው ።የኣማሪኛን ሚና ማጣጣል ቢያንስ ውለታ ቢስነት ነው ።ኣማሪኛን ያዳበሩት የኦሮሞ ሙሁራንም ጭምር ነው ቢገባህ።

    ኢትዮጵያ ጥንታዊት ሀገር ናት – እናንተ በኣውቆ ድንቁርነት/ by choice / እና ለፈጠራ narratives እንዲያመቻ ችሁ በታሪክ ቀዶ ጥገና በሚኒሊክ ጊዜ እንደተፈጠረች ኣርጋች ሁ ያለ እፍረት ትቀርባላችሁ።ሁሉም እንደ እናተ የሚያስብ ኣርጋችሁ ማሰባችሁ ነው የሚያሳዝነኝ።

    ዛሬ መጤ፣ ሰፋሪ ፣ ነፍጠኛ፣ ገዳ ኦሮሚያን እንፈጥርበታለን የምትለው መሬት ቅድመ ሚኒሊክ በማን ስር እንደሆነ፣እነማን ኢትዮጵያ መድከሙዋን ኣይተው የወረሩዋት/ Migration / መሆኑኑን ገና ኣንብበህ የደረስክበት ኣይመስለኝም። የሚሉሽን በሰማሽ ፣ ገበያ ባልወጣሽ እንዲሉ።

    Bottom line ,ኢትዮጵያችን በሴራ እና በባንዳነት የተፈጠረች ሳይሆን ለዘመናት በደም እና በኣጥንት የተመሰረተች ሀገር ናት።
    ኢትዮጵያ ውስጥ እኖራለ ሁ ካልክ ሉኣላዊነቱዋን ፣ ክብርዋን ጠብቀህ; እኩልነትህ ተረጋግጦ ኑር፣ ፣ ኣይ ካልክ ያለህ ምርጫ ከኢትዮጵያ መውጣት ብቻ እና ብቻ ነው ።

    በገዛ ዳቦዬን ልብ ልቡን ኣጣሁት እንዲሉ።

    በዚህ ኣጋጣሚ ሰፊውን ደጉን የኦሮሞ ህዝብ፣ ኣስተዋይ ሙህሮቹን ጸሃፊውን ጨምሮ የማይመለከት መሆኑንን በት ህትና ይታወቅልኝ።

    God bless Ethiopia.

    • ዬትኛውን ነርቭ ነካሁ? ያንተን ዲክታት ሳልቀበል ቀረሁ?
     “የወረሩዋት” በለው /Migration/ የናንተው ፈጠራ ነው ፣ ነው የምንለው! የተወረረው ኦሮሞው ነው፣ በዘርዐ ያዕቆብም ዘመን ሆነ በምንልክ! ኦሮሞ ነባር ህዝብ ነው፣ ነበር፣ ነገደ ሃበሻት ቀይ ባህርን ሳይሻገር! እርምህን አዉጣ!
     ኢትዮጵያ ባሁኑዋ መልክ የተቋቋመችው፣ በአጼ ምንሊክ ነው፣ ከዚያ በፊት ከሰሜን ሸዋ በስተደቡብ የሃበሻ ግዛት አልነበረም፣ ምናልባት አልፎ አልፎ የሃበሻ ነገስታት ገድል ወስጥ የተጠቀሱት፣ ለማስገበር ይደረግ በነበረው የጦርነት ወግ ውስጥ ብቻ ነው! ከይኩኖ አምላክ (1270AD) በፊት የሚታወቁት የአክሱም እና የዛጉዌ (ላሊበላ) ስርወ መንግስታት ነበሩ፣ ኢትዮጵያ ተብላ አትታወቅም።
     “ኢትዮጵያችን … ለዘመናት በደም እና በኣጥንት የተመሰረተች ሀገር ናት” > የነማን ደም ፈሶ፣ የነማን አጥንት ተሰብሮ?? የመንግስቱ ሃ/ማርያም ቀረርቶ አልተረሳህም?
     “የዲሞክራሲ እና የዜግነት / citizenship /ጽንሰ ሀሳብ” በምን ላይ ይመሰረታል? አንድን ሰው የአንድ ሃገር ዜጋ የሚያደርገው ምንድር ነው? መቼም ዲሞክራሲያዊ በሆኑ ምዕራብ ሃገራት “ዜጋ”ም ሆነህ ይሆናል የምትኖረው? ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ አለ? በዛሬው ዘመን ያለዲሞክራሲ (ከነትርጉሙ ህዝባዊ አስተዳደር) እና ሄራ (constitution) ዜግነት ( citizenship) ሊኖር ይችላል?? just educate me!
     “ኢትዮጵያ ውስጥ እኖራለ ሁ ካልክ …” የምትለዋ የህጻን ማስፈራሪያም እንኳ አትሆንም! የመኖሩን መብት ማን ለማን ይሰጣል፣ ማንስ ሊነፍግ ይችላል?? የግል ርስትህ አደርግካት እንዴ? ኦሮሞው ሃገር አለው፣ አማራውም ሃገር አለው፣ ትግሬው፣ ሶማሌው፣ ሲዳማው፣ ወላይታው፣ ሁሉም ሃገር አለው! ሁሉን እኩል የምትመለከት የሁሉም እናት የሆነች የጋራ ሃገች (ኢትዮጵያም በላት ሌላ) ካለች፣ ማምን ከሌላው በልጦ ዉጣ ግባ! የሚል አይኖርም! ሳይታወቅህ ያመለጠህ ዛቻ ግን ልትደብቁት የማትችሉት፣ በኢትዮጵያ ላይ አዛዥ እና ናዛዥ እኛው ሃበሾች (አማሮች) ብቻ ነን የሚል ንቀት የሞላበት ግብዝነታችሁ ነው።
     “ያለህ ምርጫ ከኢትዮጵያ መውጣት ብቻ እና ብቻ ነው!” አሜን! ከዚህ በኋላ ታዲያ ወደ ኦሮሚያ ዞር እንዳትሉ!!

     • “ያለህ ምርጫ ከኢትዮጵያ መውጣት ብቻ እና ብቻ ነው!” አሜን! ከዚህ በኋላ ታዲያ ወደ ኦሮሚያ ዞር እንዳትሉ!!

      ”ዶሮ ብታልም ጥሬዋን ” እኒዲሉ ማን በደሙ እና በኣጥንቱ ያቆማትን ሀገር ነው እንደ ቅርጫ ስጋ የሚከፋፈላት ??
      ኦሮሚያ ፣ ሲዳማ፣፣ ትግራይ ፣ ኣማራ …….ወዘተ በኢትዮጵያ ጥላ ስር ያሉ ለኣስተዳር ኣመችነት የተከፋፈሉ ክፍለ ሀገሮች ናቸው ። Period
      ኢትዮጵያዊነትህን ኣክብረህ ፣ታማኝነትህን ጠብቀህ ፣ መብትህ ተጠብቆ ፣ከሌላው እኩል ኣልኖርም ካልክ ከኢትዮጵያ ግዛት መውጣት ነው ። Period.
      የስታሊንን ቲዎሪ እቤትህ ኣነብንበው።
      ንጹሀንን ማረድ፣ የወገንን ኣካል መቆራረጥ ፣ትምህርት ቤት ፣ ክሊኒክ ፣ ኣምቡላንስን ማቃጠል ;ስስትን፣ ጥላቻ፣ ሰውን ከነህይወቱ ገደል መጨመር፣………..ect ነው ለትውልዱ ያስተማራች ሁት።እንኩዋን ለሌላው ለራሳችሁም ኣትበጁ።
      ጀግንነትንየኢትዮጵያህዝብያውቅበታል፣ትእግስቱንኣትፈታተኑት።
      ሞኝ ሰው ሲያከብሩት የፈሩት ይመስለዋል።

 6. ወንድሜ አባዊርቱ በጣም ጥሩ ሃሳብ አምጥተሃል::መፍትሄ ይሆናል ያልከውን ሃሳብ እንዳንድ ማሻሻያ ተደርጎበት ቢስራበት መልካም ነው::ይህም ሊሆንየሚችለው የመንግስትመልካም ፈቃደኝነት የአገሪቱን ችግር በቅጡ ያጤነና በችግሩን ተንተርሶ ሁሉም በኢትዪጵያ ችግር ላይ ያገባኛል ያለ ፓርቲ ቡድን ምሁር የእምነት አባቶች ከህዝብ ጋር ቁጭ ብለው መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው;::ቅንነትህ አገርን እምዬ መውደድህን አደንቃለሁ;;
  አባዊርቱ: ሲጀመር የኢትዪጵያ ችግር ሁኔታው ከአጣዳፊ ምክንያት ወደ ከፋ ደረጃ /Chronic case/ ተሸጋግሩዋል::እየተከስት ያለው በተለይም በኦሮምያ ስር የስደደ ቀንድ ያወጣ ውብድና ዝርፍያ አረመኔአዊ ግድያ እጅግ አደገኛ ፀልምተኝነት የመለስ ዜናዊና ኦነግ ኢትዮጵያን ህዝብ ያገለለ ህገ መንግስት ያስከተለው ይበሽታ አምጪ እፅ(microorganism) በጥቂት ተማርን የሚሉ የኦሮሞ ሊህቃን ውስጥ ስርፆ እየመረዛቸውና እነርሱም ሮጠው ላልጠገቡ በልተውያልጠገቡ በአግባቡ ያልበሱ ከፍትኛ ኢኮኖሚ ችግር ይለባቸው በትምህርት ቤት ገብተው መማርና ራሳቸውን መለወጥና ራእይ የሌላቸው ወጣቶች በሽታውን እያስተላለፉባቸው የሚያሳዩት ምልክት ልክፍት ውጤት እንጅ ደሀው ወላጆቻቸው በሙቻቻል በፍቅር ከሌላው ወገኑ ጋር እየኖረ ም ነው:;
  እንግዲህ የበሽታው ደረጃ ስር የስደደ መሆኑና ላይ ከተግባባን መፍትሄው የሚሆነው ከሲምፐታቲክ ትሪትመንት ለየት ያለ የበሽታውን መንስኤ የለየ መንታ አቅጣጫ( multi direction) መንደፍ ያስፈልጋል:: አሁንም ስጋት መንግስት አብይ እራሱ አቶ ንጉሱም የሚናገሩትን ሳጤን መንግስቱ ሃይለማርያን ያስታውስኛል::መንጌ ያን ሁላ በጀብደኝነት በማን አለብኝነት የራሱን ሀሳብ ብቻ እየተከተለ ምርጦችን እየገደለነ እይገለለ በሽብርተኝነት ታፔላ እየለጠፈ ወህኒ ሲዶል ሲገድል ያተረፈው ሀገሪቱን ይዞ ወድቆል::አሁንም ዶር አብይ እንደሚነግሩን ኦሮሞ በነፍጠኛው የትበደለውን ነፃ ለማውጣት እንደታገሉ አሁን ግንኦሮሞ ነፃ ወጥቶል ብለው አርፈዋል:ለምን ?ኦሮሞ ስልጣን ላይ ስለወጣ:: ይህም ግራዘመም አመለካከታቸው እንደ እስክንድር እይነት ጤናማ አመለካከት ያለው የአዲስ አበባ ህዝብ ራሱ በመረጠው ወኪል ይተዳደር;::አዲስ አበባ የሁላችንም ናት!ልዩ ጥቅም ለኦሮምያ መባል የለበትም!የአዲስ አበባ ሲጠቃ ዝም ብሎ ማየት የለበትም ራሱን መከላከል አለበት ነው ይህንና መሳል የመብትጥያቄ ዶር አብይ ለኦሮሞ መብትእንደታገለ ሁሉ ስለታገለ ዶር አብይአስቀድሞ የሽብርተኛ ታፔላ እንደ መንጌ ለጠፈበት !መሳቅይ በሚሆን ክስ ደብድቦ አስረው;እነዚህን የመስለ ችግር ያለበትየአብይ መንግስት ስሞኑን እያደርገ ባለው ውል የሌለው እስር የኢትዮጵያን መፍታትአይቻልም!!ድያስፖራው ርጥባን እያሰበበ ለተጎዱት መርዳት መፍትሄ አያመጣም ችግሩን ከመረመጥ ወደ ከፍ ያለ የተባባስ ችግር ከማስተላለፍ በስተቀር; ስለዚህ
  1:መንግስት የአገሪቱን ችግር በውል አጢኖ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ራሱን ማዘጋጀት
  2:መንግስት አሁን የሚከተለውን ፅንፈኝነት ቆም ብሎ የተለያዩ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ያሉ ፓርቲዎች ቡድኖች አክቲቪስቶዥች ምሁራኖች የተለያዩ የብሄረስብ ወኪሎች በአገር ውስጥ ያሉ የእምነት አባቶች ራሱን ህዋትን ጨምሮ ረዘመ ያለ ግዜ ወስዶ የችግሩን መንስኤ በጥልቀት መወያየትና መፍትሄ ማውጣት
  3;ለዚህ ችግር የዳረገን ቆንቆን ዘርን ያመከለ ህዝቡ ያልመከረበት ያልተወያየበት የህውህት ህገ መንግስት ለውይይት ማቅረብ
  4:መንግስት ስሞኑን ከወንጀሉ ጋር ምንም ወንጀል ያልተያያዘ አስቀድሞ ራሱ ያወገዛቸውን ባለደራስ ብሶት የወለዳቸው ይህዝብ አለኝታ መሆናቸውን በመገንዘብ በአስችኮይ እንዲፈታ !እንጅነር ይልቃልን ጨምሮ ከወንጀሉጋር ምንም ንኪኪ የሌሌቸውን እንዲፈታ
  5;በወንጀሉ ላይ የተሳተፉትን : የቀስቀሱትን ሃላፊነታቸውን ሳይወጡ ወገንን የጥቃት ስለባ ያደረጉትን ከመከላከያ ስራዊት ጀምሮ አጠናክሮ በሀቅ ለፍርድ ማቅረብ
  6:ቤተስባቸውን ላጡ ቤተስብ ካሳ እንዲሁም ንብረታቸዋ ለወደመባቸው ወገኖች የክልሉ እሮምያ መንግስት ተጠያቂ ስለሆነ የክልሉን በጀት በማውጣት እንድያቆቁም::እንዲሁም በይወርዳው ጉዳት የደረስባቸው ከተሞች ራሱ ተጠያቂ በመሆኑ እንደጉዳቱ መጠን የገንዘብና የጉልበት ቅጣት በመጣል ለመልሶ ማቆቆምያው እንዲሳተፍ ማድረግ
  7:ዶር አብይ በዙርያቸው ያሉትን አማካሪዎች በኤሮመነት ብቻ ያስቀመጡአቸውን በመበወዝ በችሎታቸው አንቱ የተባሉትን ከውጭ በመስብስብ ስብጥር ማድረግ ቅደመ ግዴታ ማድረግ
  8:የሌሎችሽአፍሪካ ሀገሮች ተሞክሮ ልምድ ያላቸውን በግዜአዊነት የመፍትሄው ቡድን አካል ማድረግ
  8: ምርጫውን ቢያንስ ለሁለት አመት ማራዘም;;የህዝብ ቆጠራ በትክክል ማድረግ
  9;:ጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኔአቸውን መበወዝ ለዘላቂ መፍትሄ መነሳሳት
  10: በተለይም ባለ መቶ ብር ኖት መቀየር
  የመሳሰሉትን መስራት
  ወንድሜ ኡባዊርቱ ይብቃኝ
  እግዚአብሔር ቅን ልቡናን ይስጠን!
  እንደ አባ ጫላ የመስሉ ይሁዳዎች ወይምእንክርዳዶች ወይም አረሞች ምንግዜም አይጠፉምና ልንረሳቸው ይገባል::አስፈላጊም ሲሆን አረሙን እንደምናጠፋው ሁሉ ከህዝባችን ጋር ሆነን እንነቅልቸዋለን!
  በቸር ስንብትልኝ ወንድም አለም!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.