ኢትዮጵያ በውሀ ሀብት ትልቅ አቅም ያላት እንደሆነች ቢታወቅም ከጊዜ ወደጊዜ እደረሰ ባለው የተፋሰሰ መራቆት ምክነያት የተፈጥሮ የውሀ አካላቶቿ ለከፍተኛ አደጋ እየተጋለጡ ነው፡፡ የዓለማያ ሐይቅ አይናችን እያየ ደርቋል፣ አቢያታ ሐይቅ ሊጠፋ ትንሽ ነው የቀረው፡፡ ከዚሁ ሐይቅ ጋር የተያያዙ በርካታ የአእዋፍ ዝርያዎችም አደጋ ላይ ናቸው፡፡ የዝዋይ፣ የጣና፣ የአዋሳ ሐይቆችም እንዲሁ አደጋ ላይ ናቸው፡፡ ትልልቅ የኤሌክተሪክ ማመንጫ ግድቦቻችንም እንዲሁ እድሜያቸው አጭር ነው፡፡ ይሄ ሁሉ አደጋ እየደረሰ ያለው ተፋሰሶች በመራቆታቸው ምክነያት በጎርፍ እየታጠበ በሚወርደ ደለል እየተሞሉ በመሆኑ ነው፡፡ የአባይ ገባር ሆነው የአዲሱ ግድብ የውሀ ምንጭ ከሆኑት ትላልቅ ወንዞችም ከፍተኛ የሆነ የደለለ አፈር ተሸክመው የሚጓዙ ናቸው፡፡
ጣናን መታደግ ለምን አልተቻለም
ኢትዮጵያ ተፋሰሶቿን በአግባቡ ካልያዘች እንኳንስ ሐይቆቿና ግድቦቿ ታላላቅ ወንዞቿም ከክረምት ጎርፍነት በቀር ወንዝ ሆነው ላይቀጥሉ ይችላሉ፡፡ ዛሬ ግብጽን የመሳሰሉ አገራት በኢትዮጵያ ተፋሰሳት የጋራ እቅድ አቅዶ ልማቱን ከማገዝ ይልቅ ለኤሌክትሪክ ማመንጫ ውሀ ግድብ ውስጥ አታስገቡም የሚሉ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ግድቧን የመሙላትና የመጠቀም ብቻም ሳይሆን ለግብጽም ሆነ ለሱዳን ሌሎች አገራትም እያጠጡ ላሉ ወንዞቿ ከተጠቃሚ አገራቱ የአካባቢያዊ ጥበቃ የአገልግሎት ክፍያ መጠየቅ መብት አላት፡፡ ስለዚህ ከግብጽም ሆነ ከሌሎች ጋር ድርድሩ አባይን ግድብ እንሞላለን ብቻ ሳይሆን ከዛም ተርፎ ለሚጠቀሙት ውያ ክፍያ ሊከፍሉ እንደሚገባቸው ታሳቢ ያደረገ ውል መሆን አለበት፡፡ ይሄ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እየተሰራበት ያለ አካሄድም ነውና፡፡ ወደፊት ግን ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪክ ብቻም ሳይሆን ለመስኖም መጠቀሟ አይቀርም፡፡ በገዛ ሀብቷ ከዚህ የሚያግዳት አይኖርም፡፡ ሆኖም ለኢትዮጵያም ሆነ ለሌሎች አገራት በቂ የሆነ የውሀ ምንጭ እንዲኖር የተፋሰስ ልማቱ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ይሄን አስመልክቶ ባለሙያዎች እንደሚከተለው ይመክራሉ፡፡
አመሰግናለሁ
ቅዱስ እግዚአብሔር ጥበብና ማስተዋሉን ይስጠን!
አሜን!
ሰርፀ ደስታ