የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ  በጀርመን መግለጫ

/
መግለጫ May 25-2020

በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ማር ላይ በልውጠ ህያዋን (GMO) የሚደርሰው ብክለት ባስቸኳይ ይቁም።

በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ማር ላይ በልውጠ ህያዋን (GMO) በሚደርሰው ብክለት በስራቸው ብዙ ቤተሰብ  የሚያስተዳደሩ ቁጥራቸው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ማር አምራች እማወራዎች እና አባ ወራዎች ህልውና አደጋ ላይ ወድቆዋል።

የዚህ ልውጠ ህያዋን ብክለት አደጋ መንስኤ ዘረመሉ በተቀየሰው የቢቲ ጥጥ ሲሆን የንብ ማር ምርት ባለበት አካባቢ በግብርና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በተከፋፈለ

ከአስራሁለት ሚሊዮንን (12,000,000) በላይ የቢቲ ጥጥ ዘር በመዘራት ደ ከባቢ ተፈጥሮ በመለለቀቁ ነው።

ኢትዮጵያ በብዝሃ ህይወት በአለም ካሉት ጥቂት ሃገሮች በከፍተኛ ደረጃ የምትመደብ ሲሆን

በንብ ሃብትም በሌላው አለም የማይገኙ የተለያዩ የንብ ዝርያዎች ሲኖሩዋት እስካሁን በአለም ገበያም በተፈጥሮአዊ ማር አቅራቢነት አስረኛውን ደረጃ ስትይዝ በሰም አቅራቢነት ደግሞ አራተኛ ስትሆን ከጠቅላላው አፍሪካ በተፈጥሮአዊ ማር እና ሰም በአለም ገበያ አቅራቢነት አንደኛ ነች።

ከአንድ ሚሊዮን በላይ ንብ አርቢዎች የሚያመርቱት የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ማር ዘረመሉ በሰው ሰራሽ በተቀየሰው ቢቲ ጥጥ ልውጠ ህያዋን ብክለት ምክንያት በቅርብ ጊዜ በአለም ገበያ ተፈላጊነቱን እንደሚያጣ የሰምም ዋጋ እንደሚወድቅ አገሮችም በልውጠ ህያዋን ለተበከለ ማር በራቸውን መዝጋታቸው የማይቀር በመሆኑ ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለ እዳ አይቀበለውም ነውና የኢትዮጵያ ሰባአዊ መብት ኮሚቴ የኢትዮጵያን ብዝሃ ህይወት ይታደጉ ዘንድ በግልጽ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ክብርት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ አሳስቧል።

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ አገር ሆና ትቀጥል።

ከሰላምታ ጋር

ሥዩም ሀብተማሪያም ሥዩም

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ

ጀርመን

+49 160 4357232

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲስ የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ

menschenrecht-ethiopia@hotmail.de

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share