April 15, 2020
27 mins read

ማን አወቀው – ማንስ ለየው፣  የዛን የፅልመት ገበና ?  – አስቻለው ከበደ አበበ

ኢትዮጵያ ጥንታዊና የብዙ ባህሎችና ወጎች ሀገር ናት፡፡ አንዳንዱ ባህል ማህበረሰቡን በየግዜው ከሚያጋጥመው ተግዳሮት ማሻገር የሚችል ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደየግዜው ሁኔታ ህይወትን ለነዎሪው የሚያከብዱ ይሆናሉ፡፡ በየግዜው የሚነሳውም ፖልቲካ አጠገቡ ያለውን  ያለውን ባህላዊ መሳሪ ተጠቅሞ ዘመኑን ሊያራዝምና ሊያደላድል  ላይ ታች ሲል ይታያል፡፡ ሐይማኖት ደግሞ በባህል ውስጥ እንደ አንድ ክፍል ሆኖ ነው የሚገለጠው፡፡

2004 ዓ.ም. ላይ የደራሲ አስቴር ሰይፉ ”ፈተና“ በሚል ርዕስ ለስጋሚ ህትመት በበቃው  መጽሐፍ ላይ አምስት ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ ትንታኔ ለማቅረብ እድል አግኝቼ ነበር፡፡ የእራሷን ግለ ታሪክ የጻፈችው ደራሲዋ  ሩፋኤል ጋኑ ስር ይኖሩ ከነበሩት “ታዋቂው” ባለዛር አባቷ የወረሰቻቸው ዛሮች በሕይወቷ ያደረሱባትን ውጣ ውረድ አስነብባናለች፡፡

ደራሲዋን በአካል አግኝቼም ሆነ ከመጽሐፉ አንብቤ እንደተረዳሁት  አስቴር የተዋጣላት ነጋዴ ሆና አስቴር ጠጅ በሚል የንግድ ምልክት ጠጅ ወደ ውጭ መላክ ከጀመረች በኋላ በመንግስት ደረጃ ተሸልማበታለች፡፡ ያውም አቶ አርከበ እቁባይና ፕሬዝደንት ግርማ ወለደ ጊዬርጊስ በተገኙበት ነው  ሽለማቷን የወሰደችው፡፡ ከእነሱ ጋር የተነሳችውንም ፎቶ በመጽሐፏ ውስጥ ተካቶ ይገኛል፡፡

97 ዓ.ም፣  በነበረው ግርግር ግዜ ሆቴሏ ላይ ጥቃት በመፈፀሙና ለህይወቷ አስጊ በመሆኑ ወደ ደቡብ አፍሪካ መሰደዷን በመጽሐፏ ታትታለች፡፡ ለዚህ ሁሉ ምክነያቱ ደግሞ እንደ እሷ አስተያት፣ የቅርብ ሰው የሆነች ሴትና በግዜው ስልጣን ላይ የነበሩ ወታደራዊ መኮንኖች፣ ጀነራልን ይጨምራል፣ ይገኙበታል፡፡  እንደ መጽሐፏ  ከእሷ ታዳሚዎች መካከል አርቲሰቶች፣ ዶክቶሮች፤የጦር መኮንኖች…ይገኙበታል፡፡

የደርግ ስልጣን ማብቂያ አካባቢ በወላይታ ባልሳሳት የቡቻሞ እናት የተባሉ የባህል ፈውስ (Power healer) የሚያደርጉ ሴት ተነስተው ነበር፡፡ የኢሠፓ ሳንሱርን አልፎ  ስራቸው በቴሌቪዝን በግዜው መተላለፉን አስታውሳለሁ፡፡ ፈውስ የፈለገው ህዝብ ከመላው ኢትዬጵያ ተሰብስቦ ከቦቸው ተቀመጦም ነበር፡፡ በቤታቸው የነበረ የእየሱስ ክርሰቶስ ምስል የቲቪ ፐሮገራሙ አካል ሆኖ ሲተላለፍም ትዝ ይለኛል ፡፡

ከትንሽ ግዜ በኋላ ግን አንድ የአእምሮ በሽተኛ ሰዎች የተቀመጡባቸውን ትንንሽ ግዜያዊ ቤቶች እንዳቃጠለባቸው ተሰማ፡፡ ትንሽ ቆይቶ የአካባቢው ባለስልጣን የነበሩት የኢሠፓ ከፍተኛ አባል ፣ ጓድ ስምኦን ጋሎሬ የአገዛዙ ማብቂያ ላይ እንዲህ አሉን፣ “ጓድ ሊቀመንበር(መንግስቱ ኀይለማሪያምን ነው) የምናሰተዳድረው ህዝብ ከእኛ ይልቅ ባአካባቢው ያሉትን ጠንቋዬች ይሰማል… ”

ይገርማል ደርግ በባህል አብዮት ጅራፍ እያሳደደ ሲገርፈው የነበረው ጎጂ ልማድ እስከዚያው ግዜ ነበር ማለት ነው፡፡ በዚያን ወቅት ፕሬዝደንት መንግሰቱ ኀይለ ማርያም ሃምሳ ሶስት አመታቸው ላይ የስልጣን መብቂያ ዘመናቸው እንደሆነ በቡቻሞ እናት እንደተነገራቸው ወያኔ/ኢህአዲግ ሰሜን ሸዋን መቆጣጠር ሲጀምር አዲስ አበባ ውስጥ ይወራ ጀመር፡፡

አሁን አሁን ዩቱብ ስንከፍት የፕሮቴስታንት የነብያት ቤተ ክርሰቲያናትና የወንጌላውያኑ ቤተ ክርሰቲያናት በየወኪሎቻቸው የሚያደርጓቸውን እሰጣ ገባ የያዙት ዩቱይቦች ወዲያው ነው የሚወጡጡት፡፡ ከወላይታ የተነሳው እስራኤል ዳንሳ ደግሞ መአከላዊነቱን እየያዘ መጥቷል፡፡

የእስራኤል ዳንሳ አስተምህሮና አካሄድ ተቃራኒዎች ሁሉም ማለት ይቻላል የእሱ እንቅስቃሴ በወታደራዊ መኮንኖች የሚደገፍና እሱም ተቃራኒዎቹን በእነዚህ አካላት ስም እያሰፈራራ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ቄስ ግርማ በዩቱብ በሰጡት ምስክርነት ባደረጉት ማጣራት እንዲህ ባለው እንቅስቃሴ ውስጥ (ሌሎቹንም ነብያት ነን ባዮች ይጨምራል) ወታደራዊ ኮረኔሎች መገኘታቸውንና ጦር ኀይሎች ድረስ ሄደው እንዳጋለጧቸው እነሱም ይቅርታ እንደጠየቁ ነግረውናል፡፡ የኒህ ሰዎች ምስክርነትን የበለጠ አጠናክሮ ያወጣ ምስክርነት ደግሞ ሰሞኑን ከእራሱ ከእስራኤል ዳንሳ ሰምተናል፡ይቨውም የማይገባ ጥሪ ለመከላኪያ ማቅረቡነው፡፡ ምክነያቱም መከላክያ በሐይማኖት ጉዳይ ውስጥ አያገባውምና፣ ይህ ድርጊቱ አይዞህ ባዮች በዚያ እንዳሉት በእራሱ ጣት ጠቁሞ እንደማሳይት ነው የሚቆጠረው፡፡

እራሷን ንግስተ ነገስት ኢትዮጵያ ብላ የምትጠራው እህተ ማርያም(ስንዱ) በአንድ ወቅት በሰራችው ቪዲዮ እንቅስቃሴዋ በስጋ ለብቻዋ የማትቸለው በመሆኑ እሷ ቀብታ አንግሳኛለች የምትላት ማርያም በበመከላከያና ፌድራል ፖሊስ ውስጥ  ሰዎችን እንዳዘጋጀችላት ያውም ከዶ/ር አብይ ጎን ያሉ ሰዎች መሆናቸውን አውጃልን ነበር፡፡ የዶ/ር አብይ እናትና አባቱ ያወጡለት ስም አብዮት እነደነበር ሀገር ካወቀው ፀሀይ ከሞቀው በኋላ መሰማቷን የጫነችው የዩቱይብ ቪዲዮ ይመሰክራል፡፡ ምናልባትም የቀረቧት ወታደሮች ሹክ ብለዋት ይሆናል፡፡

በእውነት እንዲህ በሉ ሐይማኖታዊ እንቅሰቃሴዎች ውስጥ ከባለ አውልያ አሰከ ነብያት ነን ባዮች ጋር ጋሻ መከታ ሆኖ የሚሰራው መከላከያ እንደ ተቋም ነው? ወይስ ከመከላከያ እስከ ፖሊስ ያሉ ኋይሎችን ያዋቀረ፣ እንዲህ ባሉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሁኑ ብሎ በመግባት አላማ ላደረገው ነገር የሚንቀሳቀስ ኀይል አለ?

አንጋፋው የህወሃት መሪ ስብሀት ነጋ ከተነሱበት አላማዎች መካከል  ዋነኘው የአማራና ኦርቶዶክስ ሐይማኖትን አከርካሪ መስበር እንደነበር ነግረውናል፡፡ እሳቸው አደራጅተው ወደ ዋልድባ የስገቧቸው መነኮሳት ቦታውን ከሚሰገኘው የንግድና ጥቅም አንጻር አጥንተው ዶሴውን ካስረከቧቸው አስርት ዓመታት አልፈዋል፡፡ እርግጥ ነው ማሌሊት- ሕወሀት ያለፈው ስርዐት ባህላዊና ህዝባዊ መሰረት መገርሰስ አለበት የሚል፣ ሐይማኖት የደሐ ህዝብ አፍዝ አደንግዝ ነው ብሎ የሚያምን፣ ኒሂሊስምን በውስጡ የያዘ የኮሚኒስቶች ስብስብ ነው፡፡

ሕወሀት-ኢህአደግ ስልጣን ከያዘበት ግዜ ጀምሮ የተዘረፉትን የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳን ብንመለከት በእውነት ይህ ሁሉ ወንጀል በተደራጀ መልክ ወይንስ በዝርው የተፈጸመ ነው የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል፡፡ ከአዲስ አለም ማርያም፣ ላሊበላ እስከ ደብረዳሞ ድረስ የነበረውን ዝርፊያ እናስታውስ፡፡

መንግስት በመገናኛ ብዙሃን የደብረዳሞ ገዳም ንዋያተ ቅዱሳን ማስቀመጫ ዕቃ ቤት በመብረቅ ተመትቶ ተቃጠለ ብሎ ዘገበ፡፡ ከቦተው ከመጡ የአካባቢው ተወላጅ ከሆኑ መነኮሳት የሰማንው ግን ሌላ ነው፡፡ መጀመሪያ ንዋያተ ቅዱሳኑ ተዘረፉ፡፡ ቀጥሎ ዕቃ ቤቱ ተቃጠለ፡፡ ከዚያም በወታደራዊ ማክ የተዘረፈው ሁሉ ተጭኖ ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ፡፡ ባለፈው የካቲት ወር ከሃያ አንድ አመት በኋላ ከኒዘርላነድ ወደ ጨለቆት ስላሴ መቐሌ ዜርያ ትግራይ የተመለሰው ዘውድ በግዜው ለነበረው እንቅስቃሴ አይነተኛ ምሳሌ ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ አብሬ የምውላቸውን ሰዎች ተገን አድርጎ የመጣ አንድ ወታደራዊ ኮረኔል በጨዋታ መሃል ለምን የሐይማኖት ተቋማት ውስጥ ኢህአዲግ እጁን አዝልቆ ማስገባት እንዳስፈለገው በሞቅታ መሃል ሲናገር ሰመቼለሁ፡፡ እሱ እነደሚለው በኦትቶዶክስ ገዳማት ውስጥም ሆነ በፕሮቴስታነት ቤተ ክርሰቲያናት ውስጥ የደርግ ወታዶሮችና መኮንኖች የነበሩ መነኩሴና ሰባኪ ሆነው መንፈሳዊውን ቢሮክራሲ ስለተቆጣጠሩት እነሱን የሚመጥን ስራ ሳይሆን አልፎ የሚሄድ መረብ መዘርጋት ተገቢ መሆኑን ያምናል፡፡

ትንሽ ልከራከረው  ፈልጌ ምን አልባት ወደ መንፈሳዊነት መመለሳቸው የለም ያሉትን የአያቶቻቸውን አምላክ መማፀናቸውስ ቢሆን ብዬ ጠየቅኩት፡፡ መልሱ አላወላዳም፤ሸዋ ለሁለተኛ ጊዜ አያታልለንም ነበር፡፡

የተለመደውና አጼ ዮሃንስ ምንሊክ ላይ ሊዘምቱ በመጡ ግዜ ከደብረሊባኖስ የተላኩ የምንሊክ ባህታውያን ለምን የክርሰቲያን ደም ያፈሳሉ ምንሊክ ላይ ቢዘምቱ ያሸንፉና አርባ አመት ይነግሳሉ፣ ነገር ግን ጽድቅን አያገኙም፡፡ ወደ ደርቡሽ ቢሄዱ ግን ሰመዓት ይሆናሉ ከዚያም አክሊል ይደፋሉ የሚል ሕወሀት ሸዋን የሚያራክስበት ትርክት ነበር የኮረኔሉ ማረጋገጫ፡፡

ስንትና ስንት ርዕሳነ ገዳማት ካሉባት ትግራይ የመጡት፣ እንደ ስዩመ እግዚአብሔር መሪነታቸው ስልጣናቸውን ለማስከበር ማንንም ለማስወገድ ወደ ኋላ የማይሉት፣ እንደ ግዜ አቻዎቻቸው ሁሉ፤ ያደረጉትም፣ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት አጼ ዮሐንስ ይህን ምክር ተቀበሉ ማለት የጥላቻን ጥግ ከማሳየት ውጭ በምንም ስነ አመክንዮ አዋቂ አያሰኝም፡፡

ሕወሀት- ኢህአዲግ አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ  ከትግራይ የመጡ ወታደሮች የታጠቁትን ክላሽንኮብ ከቤተክርሰቲያን ቅጥር ውጭ አስቀምጠው ሲሳለሙ አይተናል፡፡ ይህ ማሌሊት-ሕወሀት ያልሻረው ክርሰትያናዊ ስብእና በወታደሩ ዘንድ እንደነበረ ያስረዳናል፡፡ የምኒልክ- ዮሐንስ ባህታዊያን ትርክትን  በሕወሀት ወታደሮችዘንድ ማራገብ  አስፈላጊ የነበረውም  ለዚህ ይሆናል፡፡

እንደ እኔ አመለካከት ሕወሀት -ኢህዲአግ ውስጥ የነበረው የታጠቀው ኋይል ከሐይማኖት ተቋማቱ ከምዝበራና ዝርፊያ ከሚያገኘው ጥቅም ውጭ ፖልቲካውን ስዩመ እግዚብሔር በመድረግ ለመጠቀም እንደ ሞከረ ነው የሚሰማኝ፡፡ ለዚህም ከተልዕኮው አንዱ፣ ተጽኖ ፈጣሪ መንፈሳዊ ሰዎችን በሚገባቸውና በሚመስላቸው መንገድ ቀርቦም ሆነ በሴራ ተብተቦ ባህላዊና ሐይማኖታዊ ለሆነው ህዝብ የተጫነበት ቀንበር እንዳይሰማው ፖለቲካ አዚም ማቅረብ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚንሰተር መለስ ዜናዊ 1997 ዓ.ም. ከምርጫው በፊት ግንቦት 4 ቀን የቤተ ክህነት ሰዎችን አራት ኪሎ ሰብስበው ነበር፡፡ የዚያን ግዜ ከመነኮሳቱ መካከል ለእየሱስ ክርሰቶስ በትንቢት የተነገረውን መዝሙር 71(72)

የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ

የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻ ያቀርባሉ፡፡

ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፡፡

አህዛብም ሁሉ ይገዙለታል፡፡

ይህ ላንተ ነው ብለው በግዕዝ ደገሙለት፡፡ ለሟቹ ጠቅላይ ሚንስተር ግን እጅ መንሻ ሲቀርብ አላየንም፣ የአረብና ሳባ ነገስታትም መጥተው አልሰገዱላቸውም፡፡

ሌላው የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ከባተ በኋላ የግንቦት ሃያ በዐል ሲከበር በነ መለስ ዜናዊና አቶ ስዩም መስፍን የተተረከው የሕወሀት ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ የደረገው መለኮታዊ ጉዞ ተጠቃሽ ነው፡፡ ሕወሀት/እሕአዲግ አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ ከሱዳን ወደ አዲስ አበባ በአይሮፕላን ተጭነው ሲመጡ የኤይሮፐላኑ ሞተሮች ጠፍተው አይር ላይ ግማሽ ሰዐት ያህል በተአምር እንደተንሳፈፉ ሟቹ ጠቅላይ ሚንሰቴርና አምባሳደሩ ተርከውልን ነበር፡፡ ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስልጣናችን በምድር የከበረ ብቻ ሳይሆን በሰማይም የተረጋገጠ ነው እንደማለት ነው፡፡

ሕወሃት በሐይማኖት ውስጥ ገና በጥዋቱ ታጣቂዎቹን አሰርጎ ለመስገባቱ አቡነ ጳውሎስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርሰቲያን ውስጥ ተደረገብኝ ባሉት የግድያ ሙከራ መረዳት ይቻላል፡፡ አቡኑን ሊገድል መጣ የተባለው ባህታዊ አውደ ምህረቱ ላይ ከአቡነ ጳውሎስ አካባቢ በተተኮሰ ጥይት ተገደለ፡፡ ገዳዮቹ ቀሚስ ለባሽና ነጠላ አጣፊ እንደነበሩ በቦታው የነበሩ ምዕመናን በግዜው ምስክርነታቸውን  ሰጥተዋል፡፡ የዚያን ግዜ ገጣሚ እንዲህ አለ/አለች፤

ንስሃ አባቴን አግኝቻቸው
መስቀል አሳልሙኝ ብላቸው፣

ተዉትና ማሳለሙን
ሽጉጥ አረጉት መስቀሉን፡፡

እንዲህ ያለው ግርግር ሕወሀት ሲዘውራት በነበረችው ኢትዮጵያ በኦርቶዶክስ እምነት ላይ ብቻ የተፈጸመ አይደለም፡፡ ሙሉ ወንጌል፣መካነ እየሱስ፣ አደቬንቲስት…ሞሰሊሙም ተቋድሰውታል፡፡ አህበሽ የተባለ አሰተምህሮ በመንግስት መዋቅር ሞስሊሙ ህዝብ ላይ ለመጫን የተሞከረበትም ግዜ ነበር፡፡

ወታደራዊው ህቡዕ ክንፍ  የጨነቀው እለት የማያደርገው ነገር የለም፡፡ እንደ ናዚ ፓርቲ መናፍስታዊው ኦከልት አለም ውስጥም ይገኛል፡፡1994 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከነ ሻምበል አክሊሉ ዘለቀ ጋር የምናዘጋጀው ጥቁር አንበሳ የተባለ ጋዜጣ ነበር፡፡ ለጥቂት ሳምንታት ወጥታ ነው የቆመችው፡፡ ያን ግዜ እኔ ለይኩን ጥበበ ብርሃን በሚል የብዕር ስም የጋዜጣው አማካሪም መጣጥፍ ጸሐፊም ነበርኩ፡፡

ከነበሩት እትሞች በአንዱ ላይ “ የረር ምስጥራዊ ተራራ” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ አውጥቼ ነበር፡፡ በተፈጥሮም ይሁን ወይም በእጅ  የተነካካ ፒራሚደ የሚመስል ነገር በየረር  አለ፡፡ እኔ የዚያን ግዜ ሄጄ በነበረበት ወቅት የፒራሚዱን ቅርጽ ያየሁት አሁን በዩቱብ እንደምናው በዱከምና ቢሸፍቱ(ደብረዘይት) መካከል ሆኖ በቅርበት በሚነሳ ፎቶ ሳይሆን በየረር ቴውድሮስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኩል ወደ ላይ ወጥቶ በአድባሯ ዛፍ ስር ቁልቁል ወደ ዋሻዎቹ ወርዶ ነው፡፡

ግራኝ መሐመድ የደገኞቹን የክርሰቲያን ኀይል ሽንብራ ቁሬ አዳማ(ናዝሪት) አካባቢ ሲያሸንፍ ቀሳውስቱ ታቦታቱን አምጥተው እነዚያ ዋሻዎቹ ውስጥ ደበቋቸው ነው የሚለው ታሪኩ፡፡ ከፒራሚዱ ስር መሚፋይደ የሆነ አሰከሬን አለ፡፡ ዳዊት ደጋሚው መነኩሴ በመባል ይታወቃል፡፡ እኔና ጓደኛዬ በዚያ ያገኘናቸው የተምቤን ተወላጅ ነኝ ያሉ ባህታዊ የፒራሚዱ ጫፍ ላይ በሬ በሂሊኮፍተር ተጭኖ መጥቶ በቀንዳም ቢለዋ በመብጣት ደሙ ብቻ ፈሶ እንዲሞት እነደሚደረግ የጉብታው ሹል ጫፍ ላይ ተንፏቀው ወጥተው የተመለከቱትን ነግረውኛል፡፡ የጉብታውን ቅርጽ ስመለከት ፒራሚደ እንደሚመስል የዚያን ግዜ ነው ያሰተዋለኩት፡፡

ነገሩን አራት ከሎ አምጥቼ ለማውቃቸው በአስማት ላይ ምርምር ላደረጉ አንድ ሰው ስነግራቸው፣  ይህማ ናሁ መልአክ ነው፡፡ በደቡብ ሰማይ ንፍቀ ክብበ የሚቀመጠው የዚያ የወደቀ መልአክ(Fallen Angel) ግብር እንዲህ ነው፡፡ ግብሩም በተራራ ጫፍ ላይ ባለ አራት መአዘን ቅርጽ ላይ ነው፡፡ የሚጠራውም ህዝብን ፀጥ ረጭ አድርገህ አስገዛልኝ ለማለት ነው፡፡ ሲመጣ የጠራውን ሰው ለአንድ ሰዓት ያህል እራስ ያስታል፡፡ ከዚያም ድኝ ድኝ ያሸትታል አሉኝ፡፡ እኔም በደብረ ዘይት አካባቢ ከመንግስት ሌላ ማን ሂሊኮፐተር ሊያበር ይችላል ስል እራሴን ጠየቅኩ፡፡ ይህ የተደረገው የሕወሀት መሰነጣጠቅን ተከትሎ ነበር፡፡

ሕወሃት በሁሉም እግሮቹ አንክሶ እዚህ ደርሷል፡፡ እንደ ነጻ አውጪ ግንበር አሁንም በትግራይ አለ፡፡ ይህ ህቡዕ ክንፉ በትግራይም ይሁን በተቀረው ስፍራ እንዳለ ነው ያለው፡፡ ይህ ቡድን ከነ ማፍያ ጠባዩ የሚነቀሳቀስ ስለሆን ውሎ አድሮ ስራውን ትግራይ ውስጥም ይቀጥላል፡፡

ጉንፋን ይዞት የለቀቀው ሰው ሁሉ በዚህ በኮሮና ዘመን እንዴት ተቃቀፉ ተሰብሰቡ ይላል? እንዴትስ መደሐኒቱ እኔ ነኝ ይላል? ይህ ሁሉ ደግሞ የሚሆነው በአምላክ ስም ነው፡፡ ይህን መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው አዋጅ የሚያሰተላለፉ ሰዎች ደግሞ ከራሳቸው አንደበት እነደ ሰማንው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በህቡዕ የተቀመጠላቸው ወታደርና ፖሊስ እንዳለ ነው፡፡

እንዲህ ባሉ ሃሳቦች ላይ በተመስጦ ሆኜ ስቆዝም በ2000ዓ.ም. ብሔራዊ ሙዚያም፣ ሳይንስ ፖየተሪ በሚል ርዕስ  በረ/ ፕሮፍሰር ደበበ ሰይፉ የብርሀን ፍቅር የግጥም መደብሎች ላይ ካቀረብኳቸው ግጥሞች መሃል ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ በሚላ ግጥሙ ውስጥ ያሉት እኒህ ስንቾች ወደ ፊት መጥተው ይታዩኛል፡፡

እስፔክትረም – የብርሀን ርችት – ቀስተ ደመና
ሲነጣጠል በቀለማት፣ ሲበታተን እንደ ፋና
ማን አወቀው – ማንስ ለየው፣ የዛን የፅልመት ገበና?

ከእኩል ይሆናል ኢኮሽኑ በሰተግራና ቀኝ የሚገኙት ቫሪያብሎች በተፈጥጥሮ ወለፈንዴነት ፓራዶክስ ሲፈጥሩ፣ ብርሃን አራሱ ጨለማ ሲሆን እንደ ማለት ነው፣ የዚያኔ በንፃሬ ቲዮሪ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ሊሾልክ ይችላል፡፡

ብርሀን በፐሪስም ውስጥ አልፎ ሲታይ ሰባት ቀስተ ዳመና ቀለማት ይሆናል፡፡ ወደፊት የሄደውን ፋና ተቃራኒውን  በፓራዶክስ ወደ ኋላ መልሰን የጨለማውን ገበና  ለይተን ማየት ስንችል፤ ምን ሴይጣን መልአክ ቢመስል ስንቁር ጭለማውን ከሚታየው ብርሃን መሃል ለይተን ማውጣት እንችላለን፡፡ የዚያን ግዜ ላይመለስ የመጣው ድላችንን በእጃችን ይዘን ወደፊት ማለት እንችላለን፡፡ ስለዚህም እንሆ የሀገሬ ሰው ሁሉ ንቃ!

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫነኮቭር ካናዳ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop