ተስፋችን በእግዜር ነው! (በኮሮና ቫይረስ አማካኝነት በዓለማችን ለተፈጠረው ታላቅ ቀውስ ማስታወሻ)

/

ዐይን በማትገባ በደቂቅ ህዋስ ጠንቅ፣
እየተጠለፈ አንድ-ባንድ ሲወድቅ፣
አእላፍ…ተከተተ በየጎጆው ዋሻ፣
ላስከፊው ጦርነት ምሽግ መዳረሻ፤
ዓለም ተናወጠች ፍጡር ተረበሸ፣
በዋለበት አድሮ እየነጋ መሸ።

..በጥበቡ መጥቆ ከምድር የዘለለ፣
ጨረቃ ላይ አርፎ ፈጣሪ የመሰለ፣
በብርሃን ፍጥነት ሮኬት አስፈትልኮ..፣
ሮቦት፣ ካሜራውን ወደ ማርስ ልኮ፣
የህይወት ምንጭን ፍንጭ በድካም ያሰሰ፣
የእውቀት ጥማቱን በህዋ ያራሰ…፣
አንዲት መናኛ “ጨርቅ” የፊት መሸፈኛ፣
አንዲት “ቬንቲሌተር” ንጹህ ትንፋሽ ማግኛ፣
ለዜጎቹ ማድረስ ተስኖት ሲዋትት፣
ይኸን የዓለም ምስጢር እንግዲህ ምን ይሉት?!

ተስፋችን በእግዜር ነው በማያመነታ፣
ሰማይና ምድርን በፈጠረ ጌታ!
ከራማ መንበር ላይ ቁልቁል በሚያስተውል፣
የዓለማት ገዢ ረቂቅ፣ ምጡቅ፣ ኃያል!
ተስፋችን በእግዜር ነው!

ጌታቸው አበራ
መጋቢት 2012 ዓ/ም
(አፕሪል 2020)

ተጨማሪ ያንብቡ:  <> - በልጅግ ዓሊ

1 Comment

  1. ለኮሮና ቫይረስ መድሀኒት አለው።መድሃኒቱ ደግሞ ID2020 በክትባት መልክ የሚሰጠው የአውሬው 666 ምልክት(the mark of the beast) ክትባት ነው። ሰይጣን አምላኪዎቹ ኢሉሚናቲዎች ችግሩን ሲፈጥሩ መፍትሄውን አስቀድመው አስበው ነው።በሄጌሊያን ዲያሌክትኪስ problem then reaction then solution ይባላል።ዮሀንስ ራእይ ምእራፍ 13 ስለአውሬው ምልክት አለ።
    የኮሮና አለም አቀፍ ክስተት ድንገት የተፈጠረ ቢመስልም እንኳን አስቀድሞ የታሰበበት ይመስላል።የአለም ህዝብ በክትባት መልክ የአውሬውን ምልክት ሳይወድ በግዱ አሜን ብሎ እንዲቀበል (indirect blackmail) ለማድረግ ቀስ በቀስ በተዘዋዋሪ እርስ በርስ መለያየት መናከስና መዳከም አለበት።በዚህ ስሌት መንግስታት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋሪ ወደውም ሆነ ተገደው የፀረ ክርስቶስን የአውሬውን ፓሊሲ በሀገራቸውና በህዝባቸው ላይ በመጫን ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።
    የእጅ መታጠቡና ሌላውም ወከባ በሽታውን ከመከላከል ጋር ብዙም ግንኙነት የለውም።አጠቃላይ ወከባው ህዝቡን ግራ ማጋባት ማሸማቀቅ እና psychological warfare በመፍጠር ለአውሬው ስርአት አገዛዝ የማለማመድ ሂደት ነው።ፈረንጆች it smells fishy እንደሚሉት የኮሮና ነገር ከበስተጀርባው ውስብስብ ሴራ ያለበት እንደሆነ ለመረዳት ብዙ አይከብድም።ሳታኒስት ኢሉሚናቲዎች በየሀገራቱ ያሉትን የአለም መንግስታት መቆጣጠር ከጀመሩ የቆየ ቢሆንም አለም በዚህ መልክ ለኮሮና የሰጠው መልስ የሚያሳየው ሳታኒስት ኢሉሚናቲዎች የአለም መንግስታትን እና ሀገራትን ሃይጃክ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ የኮሮናን ሰበብ በመፍጠር አጠቃላይ global lockdown ውስጥ እየከተቱት መሆኑ እጅግ አስደንጋጭ ነው።ህዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፋ ትንቢተ ሆዜ 4:6

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share