” በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው… ” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ 

ሰዎች በህይወት ሳሉ፣ አሥቂኝ ና  አሳዛኝ ገፀ ባህሪን ተላብሰው ሲተውኑ በየቀኑ ይስተዋላሉ።ይህንን እያንዳንዱ አዋቂ ሰው የዛሬውን የሙሉ ቀኑን እና የአዳሩን ህይወት ብቻ ሳይሆን ያሳለፋቸውን ዕድሜዎች የኑሮ ሂደት በትዝታ መነፅር ፈትሾ  ምን ያህል የተዋጣለት የምድር ተዋንያን መሆኑን መገንዘብ አያዳግተውም።በእርግጥ ገቢር አንድ መቼ እና እንዴት እንደተጀመረ ና አሁን እየከወነ ያለውን የእውነተኛ ተውኔት ፍፃሜን ባያውቅም።
  ሰው ልጅ፣  ፈጣሪ ፍጡራኑን ጥረህ ግረህ ብላ ብሎ በቅጣት ከኤደን ገነት አስወጥቶ በጣላው በዚች ምድር ላይ እስከመቃብር እየተወነ የሚኖር ምሥኪን ፍጡር ነው።
   “እንደ ሰው”ከቶ  ማንም የለ፣እያንሰፈሰፈ አንጀት የሚበላ ፣ሆድን የሚያባባ፤
  የእኔ፣የእኔ፤እኔ፣እኔ አክትሞ፣ራቁት በድኑን በከፈን ጠቅልሎ መቃብር ሲገባ።”(መሻወጊ)
    ሰው የፈጣሪ ኪነት ነው።ሰው የፈጣሪ ሥነ-ፅሑፍ ነው።ሰው የፈጣሪ ቅኔ ነው።ሰው የፈጣሪ ሥዕል ነው።በአጠቃላይ ሰው የፈጣሪ ድንቅ የፈጠራ ውጤት ነው።
      ፈጣሪ ፍጡሩን ሲፈጥረው ውስን አድርጎ ፈጠረው።  በቦታ፣በጊዜ በሁኔታ ገድቦ።እናም ቤቱ ውስጥ ካለ ከቤቱ ውጪ የሚሰራውን ይቅርና ኮርኒሱ ውስጥ፣  የምታየውን አይጥ እርሱ ማየት አይችልም።የደላውም ሳሎን ተቀምጦ በወጥ ቤቱ ምን እንደሚከናወን ለማወቅ ከቶም አይችልም።
      ሰው የፊት ለፊቱን እንጂ የጀርባውን እንኳ ማየት የማይችል ሆኖ ሳለ፣ የጀርበውን የሚያይለት ቁስ በምጡቅ ጭቅላቱ መፍጠሩ እሙን ነው።ሰው አልባ ድሮን የተባለ ጥያሪም በመፍጠር ዓለምን ይሰልላል።ጠላቶቼ ናቸው ያላቸውንም  የራሱን አምሳያ ይገላል።
    እርግጥ ነው፣ሰው ምርምሩን ከምድር ውጪ ሰማይ ላይ ካደረገ ሰነበተ።ማርስ የተባለችውን ፕላኔት የነገ መኖሪያው ለማድረግ እያለመ ሌላ  ከምድር ተመሳሳይ የሆነ ፕላኔት እንዳለ አበሰረ።ሆኖም ዝርዝር መግለጫ ኃያላኖቹ አልሰጡም።ልብ በሉ የጋራ የምርምር ጣቢያ በሰማይ ቤት አላቸው።
እጅግ ፈጣን የሆነ የምድር ባቡር ፣እጅግ ፈጣን እና ዘመናዊ  የሆነ የአየር  ማጓጓዣ ፣እጅግ ጉዙፍ ና ዘመናዊ የጦር መርከብ ሰሩ።
     በህክምናው ዓለምም ሁሉንም አካላችንን ነቅለው ለመትከል የሚችሉበት ደረጃ ደረሱ።ጭንቅላትን ከፍተው ዕጢን እስከማሶገድ ዘለቁ። የልብ የተለያየ ችግርን የሚቀርፍ መሣሪያ ፈለሰፉ።ሆኖም ራሱን በየጊዜው  እየቀያየረ የሰው ልጅን የሚያጠቃውን   “ቫይረስ”  ለመቆጣጠር ግን አልቻሉም። ይልቁንም በየጊዜው በአንድ አካባቢ  የሚከሰቱ  ሞቶችን የሚከስቱት ከኃያሉኑ የቫይረስ  የምርምር ጣቢያዎች  በምሥጢር  የወጡ ቫይረሶች ናቸው ብለው የግል ግምታቸውን የሚሰጡ ምሁራኖች እንዳሉ የተለያዩ  የዓለም   ሚዲያዎች አሳውቀውናል።
    ኮሮና ወይም ኮቪድ 19 ቫይረስ ፣ ከቻይና፣ ከአሜሪካ ፣ ከጀርመን፣ከሩሲያ፣ከእንግሊዝ፣ከየትኛው ሀገር የምርምር ጣቢያ ወጥቶ የሰው ልጅን መውጋት እንደጀመረ ለማወቅ ባይቻልም፣ሥለ ቫይረሱ ከተሰጡ ትንተናዎች እና አሥቀድመው ከወጡ ፊልሞች፣እንዲሁም  ዛሬም ከሚደረጉ የሚዲያ ቅስቀሳዎች አንፃር ይህ ቫይረስ አደገኝነቱ ምን ያህል እንደሆነ አሥቀድሞ ታውቆ ነበር ያሰኛል።
    ኮቪድ 19 ሳርስ 2 SARS 2 ወይንም ቻይናዎች ( NCP)  novel  corona  pneumonia  በማለት የሚጠሩት ፣ ሰውን በብዛት  ይይዛል፣በጥቂቱ ይገላል።ልብ በሉ  ቫይረሱ በውሃን ቻይና ከተከሰተበት  ከታህሳስ 2012 ዓ/ም እስከ   27/7/2012 ዓ/ም  በዓለም ላይ በቫይረሱ   የተያዙት(ወደ አራት ወር ሊጠጋ ነው) 1,245,375 ሰዎች ሲሆኑ ፣የሞቱት ደግሞ፣67,914 ፣ሲሆኑ ከበሽታው ተፈውሰው ከሆስፒታል የወጡት፣256,668  ናቸው።
   አሁን በህክምና ላይ ያሉ (ዛሬ) 920,793 ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ  ፣875,843 ወይም 95 % ያለ ፅኑ ህመም መታከሚያ ክፍል እየታከሙ ሲሆኑ፣44,956 ወይም 5% ህሙማን ግን፣ጤንነታቸው በአሥጊ ሁኔታ ላይ በመሆኑ   በፅኑ ህሙማን ክትትል ክፍል(Intensive Care Unit) ውስጥ የሚታከሙ ናቸው። ከቫይረሱ ገዳይነት አንፃር ታክመው የዳኑት በፐርሰንት ታክመው ከሞቱት ጋር ሲነፃፀር ፤ታክመው  የወጡት፣256,668 ወይም 79% ሲሆኑ፣67,914 ወይም 21%  ሞት ነፍሳቸውን የነጠቃቸው ናቸው።
  ቫይረሱ ብዛት ማጥቃት ከመቻሉ አንፃርም፣ሰው ለጅ ጦርነቱ ከብዶታል። በጦርነቱ አውድማ ላይ ሆነው ከቫይረሱ ጋር ተናንቀው የሞቱ የህክምና ባለሙያዎችም ቁጥራቸው ትንሽ አይባልም። ከአራቱ ሟቿች አንደኛው የህክምና ባለሙያ ነው።(they are courageously death in the battle field )
 የቫይረሱን አደገኝነት በህክምናባለሙያዎች ሞት መገንዘብ ይቻላል።ከቫይረሱ ጋር ጦርነት ላይ ነን የተባለውም ከዚህ አንፃር ነው።አንዳንዶችም መድኃኒት ወይም ክትባት ቶሎ ያለመገኘቱ ምሥጢር  ታላቅ ሤራ ነው።ብለው ያምናሉ።
     ሥለ ሴራዊም   በዋቢነት ሁለት ፊልሞችን ይጠቅሳሉ።ፈልሞቹ  በ2007 እና 2011 እንደ ጎርጎረሳዊው ካሌንደር የተሰሩ ሲሆን ሁለቱንም “corona virus movie ” በማለት በዩቲዩብ YouTube መመልከት ወይም ማውረድ እና ማየት ትችላላችሁ። ምን ያህልም፣አንደ ፐርሰንቶቹ ይህቺን ዓለም ለመቆጣጠር የሚያሥችል ፣የዓለምን የተለመደ አኗኗር እና የሰው ልጅን ማህበራዊ ኑሮ ባልተለመደ መንገድ ለማሥኬድ ጉልበት እንዳላቸውም ትገነዘባላችሁ ።በበኩሌ ኮቪድ 19  ታሪክ መሆን በኋላ ፣የዓለም ሁሉ  ነገሯ ይቀየራል።ብለው ከሚያምኑት ጎራ እሰለፋለው።
   ከኮቪድ 19 የቫይረስ ጦርነት ፍፃሜ በኋላ(ቢበዛ ከ4ወር በኋላ) የዓለም  የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ የቀደመው አካሄድ መቀየሩ አይቀርም።ዓለም “በቫይራል ዋር” ፍራቻ የተነሳ በኒኩለር መመካቷን በማቆም በመከባበር ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ ትሆናለች።ምክንያቱም እያንዳንዱ በሩን ዘግቶ መቀመጥ እና ከዓለም ሀገር ጋር አልገናኝም ማለት አይችልም እና በቫይራል ምርምር ጣቢያዎቻቸው ላይ የደህንነት አውታራቸውን አጥብቀው በሰላማዊ ትብብር የህዝቦቻቸውን ህይወት ለማሥቀጠል በምሥጢር  ቃል ይገባሉ ብዬ አስባለሁ።
   በዚህ ቫይረስ ሰበብም የቢል ጌት አይነት እና ተያያዢ ምርት አምራቾች  ሰፊ ገብያ ያገኛሉ።የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎች የየበሰና የአየር ትራንስፖርቶች ላይ ይገጠማል።በየመዳረሻዎች ላይም ጤነኛና ህምተኛ መለያ መሣሪያ የገጠምና በዛውስጥ መንገደኞች እያለፉ የጤናቸው ሁኔታ እየታየ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል።እያንዳንዱ የመንገደኛ ሻንጣ ከማንኛውም ባዮሎጂካዊ የጦር መሣሪያ ነፃ መሆኑን በሚለይ መሣሪያ ተፈትሾ ይጫናል።እያንዳንዱ የመንገደኛ አውሮፕላን  24 ሰዓት በካሚራ ቁጥጥር ሥር ይውላል።ለእነዚህ ሁሉ መሣሪያዎች ማምረቻ ና ግዢ በመቶ ቢሊዮን የሚቆጠር ብር ይመደባል።
   የሠለጠነው ሀገር ግብይቱን ከወረቀት ብር ያላቅቃል ።አጠቃላይ ግንኙነቱንም ከወረቀት የፀዳ በኮፒዊተር መረብ እና በዘመናዊ ሥልኳች አማካኝነት ያደርጋል። የአላባባ ካባኒ  ገብያው ይደራል።
     በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በመንግሥት ደረጃ ይህንን አሠራር ተግባራዊ ያደርጋሉ።አየር መንገዶቻቸውን እና ቤተ መንግሥታቸውን በዘመነኛው መንገድ ያጠናክራሉ።…
   የአለምን አካሄድ ለመቀየር የበለፀጉት ሀገሮች የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው ይቀጥላሉ።ይሁን እንጂ ፈጣሪ እነሱ በፈለጉት የጠቅላይነት መንገድ እንዳይዘልቁ ኮቪድ 19  ሥላደረጋቸው፣በፍርሃት ቆፈን ይዋጣሉ።ምን ጊዜም ፈጣሪ ትክክል እንደሆነ ቢያንስ የዓለም ኃያላን መሪዎች ይገነዘባሉ።
     በተለይም በእኛ ሀገር ከቫይረሱ ድል መሆን በኋላ ፣በሐገሪቱ ፈርሐ እግዚአብሔር  ይሰፍናል። የፖለቲካው መጠላለፍም በግማሽ ይቀንሣል።  ቫይረሱ ዘር፣ቋንቋ፣ ቀለም፣ብሔር እና ጎሣ ሣይመርጥ በመግደሉ   የተነሳ  ታላቅ ትምህርት የሀገሪቷ ህዝቦች ተምረው “ዘረኝነትን ጥንብ ነው።” ብለው፣በአደባባይ ይቀብሩታል።
      በቋንቋና በዘር ጉልበት ወደ ሥልጣን መንበር ለመውጣት የሚከጅል  ፓለቲከኛ የኮሮና ቫይረስ እልቂት ሰው መሆኑንን ያሳወቀውን ባለአገር በምርጫ ቅስቀሳ “አንተ እንትን ነህ ።የእኔ ብቻ ነህ።” ብሎ ማሳመን ያዳግተዋል።አንተ ዘር ነህ።አንተ ቋንቋ ነህ የሚል ፖለቲከኛ ቢኖር እንኳ መጠሪያው “ኮረና! ” ይሆናል።
     ሰው መሆኑን ዘንግቶ በቋንቋና በዘር ሲበላላ የነበረው ጥቂት የማይባለው የሀገሬ ሰው፣ዘመንኩ ያለው ሰው ፣ በገዛ ሐጢያቱ የመጣበትን እልቂት ተመልክቷልና ፣ከእንግዲህ ከወንድምና ከእህቱ ከሀገሩ ሰው ጋር በፍቅር ኖሮ ተፈጥሯዊ ሞትን እንጂ ፣”ቋንቋን ነው የማገባው።” ብሎ በዘር ቅኝት  አይመፃደቅም።ምክንያቱም ፈጣሪ ለሰው ፊት እንደማያዳላ ለሁሉም እኩል ፍርድ እንደሚሰጥ፣   በኮሮና ቫይረስ ሰበብ በዓለም ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ቅጣት በዕውኑ አይቷልና !!
   እዚህ ላይ ፈጣሪ ሰው አይደለምና ፣ ማንንም ሰው በጭካኔ ለመግደል እንደማይፈልግ መገንዘብ አለብን።ይሁን እንጂ ሰዎች ራሳቸው “አሥርቱን ትዕዛዛቱን በመካድ “፣እንዳሻቸው ሲሆኑ ሞት ያገኛቸዋል።በነሱ የተነሳም ፃድቃኖችም አበሳቸው ይተርፋቸዋል።ለሐጥያን የመጣ ሞት ለፃድቃን ምጣቱ አይቀሬ ነው።…እነሥ…? ለማውገዝ እንኳ ፈርተን ነበር እኮ !!
   ሰው በድብቅ ሌሎችን ለማጥፊያ  ቢላዋ ይሥላል፣ሆኖም ግን ወደ ግቡ ሳይደርስ ያ ቢላ ራሱን ያጠፋዋል።…በድፍረት በሰዎች ፊት  “በሰይፍ ገናና የሚሆን በሰይፍ ይጠፋል።”እንዲሉ።  ይህ ኮሮና ቫይረስ እንደ ፈጣሪ ሰይፍ ቁጠሩት።ከተማርንበት የወደፊቶቹ ሀገር ተረካቢዎች ሥርዓት ያለው ህይወትን እንዲኖሩ መንገድ እንጠርጋለን።
     በነገራችን ላይ ዘግናኝ የማህበራዊ ትስስር ያላቸው፣ተፈጥሯዊውን ግንኙነት የሻሩ እና የወንድ ለወንድ ጋብቻን የፈቀዱ ሁሉ ፣ዛሬ ሊያፍሩ ይገባል። እንዲህ ያለው ኢ ተፈጥሯዊ ተግባር በስመ ዴሞክራሲ ህጋዊ መሆኑ ያሳፍራል። ይህንን ኢ -ተፈጥሯዊ ድርጊት ዓለም እሥካላወገዘ ድረሥ ነገም  ከመቀጣት አይድንም። ልብ በሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ መጀመሪያ የተከሰተው በግብረ ሰዶማዊያን ላይ ነው።
    ፈጣሪ ሥራው ረቂቅ ሥለሆነ በየት እና በምን አይነት ሁኔታ ና ጊዜ እንዴት እንደሚቀጣን አናውቀውምና ሐጥያትን ከመሥራት እንታቀብ።እኛስ ፈጣሪን አምነን ሥናጠፋም ማረን እያልን ነው።ከእነሱ ውስጥ ግን አንዳንዶች በግልፅ የፈጣሪን መኖር ክደው ነውና ሐጢያት የሚሰሩት እንዴት ምህረትን ሊያገኙ ይችላሉ?
   በዚህ፣ መጥፎ ጊዜ እነ ቢል ጌት እና ቡፌት ሌያተርፉበት ይችላሉ።ማሥክ እና የኦክሥጂን ሰጪ መሣሪያ(ቬንትሌተር) አምራቾች፣ ዶክተር ማሥክ እና አልባሳት አምራቾች፣የቫይረሱን ሥርጪት ገቺ መድሃኒት አምራቾች፣ጎንት እና ቫይረሱን መግደያ ዲሥኢንፌክታንት አምራቾች፣ ወዘተ ሊበለፀጉ ይችላሉ።በአንፃሩ ፣ ሆቴሎች ፣ቡና ቤቶች፣ቲያትር ቤቶች፣ሲናማ ቤቶች፣ሎጆች፣ሪስቶራንቶች ፣ካፊዎች፣አሥጎብኚ ድርጅቶች፣የትራንስፖርት አቅራቢ ግለሰቦች፣የግል ትምህርት ቤቶች ፣በጥቃቅን የህትመት ሥራ ላይ የተሰማሩም ሙሉ ለሙሉ ንግዳቸው ይቆማል።እናም ነገ ሠርተው ለማገገም ወራትን ይፈልጋሉ።ይህ ደግሞ በአጠቃላይ የሀገር ኢኮኖሚን ያደቃል።ከዚህ የኢኮኖሚ ድቀትም ለመውጣት አመታትን ሊጠይቅ ይችላል።
    አሁን  ዓለም ሐጢያቷን ተገንዝባ በንሥሐ ጠበል ሐጢያቷን የምታጠብበት ወቅት ላይ ደርሰናል።የዓለም ህዝብ ፈጣሪውን ፈርቶ፣በመጠንና በልክ መኖር ካልጀመረ፣እና በእንስሳነቱ ከገፋ ከዛሬው ኮሮና የከፋ ገዳይ ህመም ያጋጥመዋል።የሐጢያት ክፍያ ሞት ነውና!!
  በመጨረሻም፣  የፈጣሪያችን ቃል በመፀሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የመከረንን ላሥታውሳችሁ እወዳለሁ።ከፈጣሪያችን ቃል የበለጠ አፅናኝ የለምና።
(James 1 )
 ————
 12 በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
 13 ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።
 14 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
 15 ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።
 16 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።
 17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
 18 ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።
19 19 ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
 20 የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።
 21 ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
 22 ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
 23 ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
 24 ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።
 25 ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።
 26 አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
 27 ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.