እቺ ወፍ ዘቅዝቃ ነፋች – የአስናቀ ይርጉ ተንኮል ቀስቶ ነኝ (ከባህር ዳር)

ጅል ሰው ጅል ነው ጅል ነገር ያመጣል፣
ጅል ነገር አምጥቶ ራሱን አይችልም፣

አነካክቶ ይሄዳል ያንንም ያንንም፡፡È ሲል እንደ ዛሬው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ምሽት ቤቶች ሳይዘጉ አንድ የምሽት ቤት አዝማሪ ስለ ጅል ሰው በዜማ ያንቆረቀረውን የግጥም መልዕክት ለጦማሬ መነሻ አድርጌአለሁ፡፡

በተለያየ ዘመን በአገራችን የሚነሱ ግጭቶችና የእርስ በርስ ዕልቂት መነሾው የጅል ሰዎች አስተሳሰብ እንደሆነ መናገር ይቻላል፡፡ ደርግ ነጭ ሽብር በቀይ ሽብር ይደመሰሳል በሚል ከንቱ ጉራ በአገራችን እጅግ አስቀያሚ የደም መፋሰስ የተከሰተው አርቆ ካለማስተዋልና ከደካሞች አስተሳሰብ የመነጨ ድርጊት እንደሆነና በአግባቡ፣ በሰከነ መንገድ ሳይጠናና በአጭር ጊዜ ወደ መፍትሄ ባለመገባቱ የተፈጸመ ተግባር ነዉ፡፡

በቅርቡም ከለውጡ በፊትና በኋላ በየክልሉ ጎራ ተለይቶ ሕዝብ ከሕዝብ፣ ብሔርን ከብሔር የሚያጋጩና ለዕልቂት የሚዳርጉ ደርጊቶች የተፈጸሙ በጅሎች ጥርቅም አስተሳሰብ በመነጨ እኩይ ተግባር ነው፡፡ ቀደም ሲል ያነሳሁት ነጥብ የአዋጁ በጆሮ ቢሆንም አነሳሴ ከአደባባይ ግጭት ባልተናነሰ የያዙትን ስልጣን መከታ በማድረግ በየተቋሙ ሠራተኛን የሚያምሱና ዘርን ጎጥንና ሃይማኖትን እየለዩ አላሰራ የሚሉ አሸባሪና ጅል ኃላፊዎችን  የአማራ ክልል መንግስት ሃይ (ሰላም ሳይሆን) እንዲላቸው ለማሳየት ነው፡፡

በእርግጥ የክልሉ መንግስት ሰርክ ቢነገረው የማይሰማ በመሆኑ የጅሎችና የደካሞች መጠራቀሚያ ከመሆኑም በላይ የአምባገነኖች ጡንቻ የሚደነዱንበትና የሹመት ዕድሜያቸው እየረዘመ የለፍቶ አደሩ ባለሙያና የአገልግሎት ፈላጊው ሕዝብ ዕንግልት እየጨመረ በመምጣቱ ግፉ ለማመላከት ነው

በአማራ ክልል ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እንዲመራ የተቀመተው አስናቀ ይርጉ የተባለ ጅልና መንደርተኛ ግለሰብ በሰላምና በፍቅር አብረው ተሳስበው የሚኖሩትን ጎጃሜና ጎንደሬን እያፈጀ ስለመሆኑ ከስር መሠረቱ ልነሳና እዉነተኛ መረጃ ላካፍላችሁ፡፡ አስናቀ ይርጉ በ2005 ዓ.ም የደቡብ ጎንደርን በጎጥ የሚመራዉ የፈንታ ደጀን ቤተሰቦች አግማስ ቼኮልና ሸጋዉ የጠባሉ ግለሰቦች በኃላፊነት ከሚመሩት ከአማራ ክልል የከተሞች ልማትና ግንባታ አክሲዩን ማህበር የሎጀስቲክ ዘርፍ እንዲመራ ይመደባል፡፡ በዚህን ወቅት በነበረው የአቅም ማነስና በሥራ አለመግባብት ከሥራና ደመወዝ ይታገዳል፡፡ ያለምንም ችሎታና ብቃት ግዙፉን የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትክሽን ቢሮ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ይሾማል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በደም የተከበረ የዓለም ሠራተኞች ቀን፤ ሜይ ዴይ

ይህን ስልጣን እንደያዘ የተመደበበትን ዘርፍ ከመምራት ይልቅ በተቋሙ ያሉ  ጎንደሬዎችን ማሳደድ ቀዳሚው ተግባር ነበር፡፡ ለዚህም እንደማስረጃ የማቀርበው ረዥም የሥራ ልምድና የተሻለ የትምህርት ዝግጅት የነበራቸውንና ያላቸውን ጎንደሬ የሆኑት የተቋሙን ከፍተኛ ባለሙያዎች  ከአጠገቡ ማራቅ ነው፡፡

1 እሱባለዉ በለጠ
2.ይመር ታረቀኝ

  1. ሙሉቀን ፈንቴ
  2. ካሰዬ አረጋዉ
  3. ብርሃኑ ታደሰ
  4. ተስፋዬ በላይ
  5. ሞገስ በሬ
  6. እያሱ አድማሱ
  7. አስቴር ዘመነ
  8. አደረጀዉ አላባ
  9. ቢልልኝ ማረዉ
  10. ዘመናይ እዉነቱ

የተባሉ ባለሙያዎች ጎንደሬ በመሆናቸው ብቻ አንድ የትምህርት ዝግጅትና ያለምንም ሥራ ለመጣው ሁሉ የሚያጎበድድ ሰለሞን መሰለ በተባለ በውክልና የህግ አማካሪ ተብሎ በተጎለተ የአገሩ ልጅ እየተከሰሱና ዛቻ እየደረሰባቸው የሚሰማ የመንግስት አካል በመጥፋቱ ገሚሱ የሚወዱትን ሕዝብና ሙያ ትተው ተቋሙ የለቀቁ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ ወደ ሌላ የሥራ ክፍል ለመዛወር ተገደዋል፡፡

አስናቀ በዚህ ብቻ አላበቃም ጎንደሬ የተባለ ኮንትራክተር አካባቢዉን ቀይሮ ካልተናገረ በስተቀር ጉዳይ ይዞ መስተናገድ አይችልም፡፡ አስናቀ ህዘብን እያባበለ ወደ ደም ማፋሰስ የሚያደርስ ስራ እየሰራ ነዉ፡፡ አደረጀዉ አላባን ከአመራርነት እንዲወጣም ሞክሮ ነበር ፡፡ አደራጀዉ አላባን አስመርሮ የሰደደዉ አስናቀ ይርጉ ነዉ፡፡ ሥራ አይችልም  ነገር ማመለላስና ማፋጀት ይችላል፡፡

በእምነቱ ተደብቆ ያለው ዘረኛ አስናቀ ይርጉ

በእምነቱ ጠንካራ ለለመስል ዳዊት ተሸክሞ ይዞራል፡፡ግን ደግሞ በጎጥ ለይቶ ሠራተኛውን ያምሳል፡፡ ስርዓቱን የሚደግፍ መስሉ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ የባለስልጣናት የባለሃብቶችን ስም ሲያጎድፍ ይዉላል፡፡ በሌላ ጎን ድርጅቱን ሲያማና ሲያንቋሽሽ ይሰማል፡፡

ጉቦ የማይወድ ስለመሆኑ የሰለጠኑ ቀስቃሾች አደራጅቶ ስሙ እንዳይነሳ አፍ ያሲዛል፡፡ በየአካባቢዉ ዘራፊ መሃንዲሶች አደራጅቶ ለዘረፋ አመቻችቶ ከሚገኘው ገቢ ድርሻውን ያነሳል፡፡ በየስበሳበዉ በኮንስትራክሽን ዘርፍ በኪራይ ሰብሰባቢነት ተሰማሩትን ግለሰቦች ሲያንቋሽሽ ይዉላል፡፡ ዘርፉ የኪራይ ሰብሳቢዎች ብቻ ሳይሆን የአስናቀ ምሽግ እስከ መባል ደርሷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ ድንጋይ ቢቆሉት አይሆንም ቆሎ ”

በደካማ ሥራው ያባረሩትን የአማራ ክልል የከተሞች ልማትና ግንባታ አክሲዮን ማህበር ኃላፊዎች ለመበቀል በከተማ ልማት በሙያቸው የተሰማሩ ጎንደሬዎችን ማሳደድ ምን አመጣው Çእቺ ወፍ ዘቅዝቃ ነፋችÈ ይሉሃል የአስናቀ ይርጉ ተግባር ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ዘርፍ በክልሉ እንዳያንሰራፋና የሕንጻ አዋጁ በአግባቡ እንዳይተገበር ከሚያደርጉት ዋነኛ ጋሬጣ አስናቀ ይርጉ በመሆኑ የክልሉ መንግስት ይህን ደካማ ሃላፊ በማንሳት በምትኩ ዘርፉን በተሻለ ሁኔታ የሚመራ ኃላፊ እንዲመድብ በአማራ ሕዝብና በተቋሙ ሠራተኛ ስም እየተማጸን ተቋሙ እንድትታደጉት አደራ እላለሁ፡፡

5 Comments

  1. ፈንታ ደጀንን እናውቀዋለን። የጎንደር ፖለቲከኞችንም እናውቃቸዋለን። ካለሀፍረት መላው አማራን ከወያኔ ጋር ሆነው ለ28 አመታት አሰቃይተዋል። ያ እድል አሁን የለም። በዚህ ምክንያት ነው ወያኔና የፋርጣ ፖለቲከኞች እያለቀሱ ያሉት። ከሀገር ውስጥ እስከውጭሀገር ድረስ ተደራጅታችሁ ስም ብታጠፉም ሆነ ብትጮሁ ማንም አይሰማችሁም። ምክንያቱም ስለምናውቃችሁ ነው። የሰራሀው ወንጀል ተዘርዝሮ ወህኒ ባለመውረዳችሁ ብልጽግናን አመስግኑ። ማፈሪያወች

  2. ኪነት ያገነነው አፄ መጽሃፍ ደራሲ – አብዱል ጀሊል አሊ ፡እንዲህ ይላል፦
    -ቴዎድሮስ በእናታቸው ቅማንት በአባታቸው ትግሬ ናቸው
    -ሙሉ ስማቸው ካሳ ሃይለጊዮርጊስ ወልደጊዮርጊስ እንጂ ካሳ ሃይሉ አይደለም (ካሳ ሃይሉ ተብሎ የሚጠራው በአባታቸው ትግሬ መሆናቸው እንዳይታወቅ ነው)
    -የቴዎድሮስ የጦር አበጋዝ የነበረውን ገብርዬ ተብሎ የተሰየመው ትክክለኛ ስሙ ገብረሂዎት ነው(የሰሜን ትውልድ ያለው ነው፡ሙሉ ስሙ ተጠርቶ የማያውቀው ለዚህ ነው) ፡ለዚህም ነው ቴዎድሮስ ያልዘመቱበት ቅማንትና ትግሬ ላይ ብቻ የነው
    -ገዳዮችንና ጨካኞችን ጀግና እናደርጋለን ፡ ገዳይነትን በላያችን እናውጃለን (ደርግ ህዝብ ሲፈጅ የነበረበት የእልቂት ጥሪ ቴዎድሮስን እየጠራ ነበር) ፡ትልቅ ለሰራ ለአገር ባለውለታዎች ግን ዳተኞች ነን
    -ቴዎድሮስን ያገነናቸው ኪነት(አዝማሪ) ነው ፡ እሳቸው ታሪክ ሲተነተን ሳይሆን በዘፈንና በልቦለድ ድርሰት ማጣፈጫነት ብቻ ነው የሚውሉት፡ በደርግ ዘመንም ጥሩ ለመስራትና ለመልካም አስተዳደር ሳይሆን ለክተት አዋጅና የእልቂት ጥሪ ማጀቢያ ነበሩ።እሳቸው ለውይይት ቀርበው የማያውቁት ብዙ ችግር ስላለ ነው
    -ቴዎድሮስ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን አያውቋትም ነበር
    -ቴዎድሮስ በሽፍትበት ጀምረው በሽፍትነት ነው ያጠናቀቁት ፡ቴዎድሮስ ምን ጥሩ ስራ ሰርተዋል?
    -ቴዎድሮስ የገጠማቸው ትልቅ ውጊያ ወደ ሸዋ ዘምተው በነበረበት ጊዜ – ውጊያው ሊደረግበት በነበረበት ዋዜማ ሌሊት ንጉስ ሃይለመለኮት ሞተው አደሩ(በመርዝ ነው ይባላል) -በዚህም ሸዋ መሪ ስላልነበረው ባገኘው የጎበዝ አለቃ ስር እየተደራጀ ለመከላከል ሞከረ – በዚህ ጊዜ ነው ከደጃች ሰይፉ ጋር ተጋጥመው ቴዎድሮስ ለጥቂት ከሞት ከተረፉ በኋላ ፡” ጀግና ገና ዛሬ ገጠመኝ” ብለው የተናገሩለት ውጊያ ነው
    -የናፒር ጦር የመጣው ኢትዮጵያን ሊወጋ ሳይሆን ቴዎድሮስን ሊቀጣ ነበር ፡ ከመጣው የናፒር ሰው ውስጥ አንድም እንኳን አልሞተም ነበር፡፡ለዚያ ነው ዘረፋ እንጂ ውጊያ አልተካሄደም ነበር የሚባለው
    -ኢትዮጵያ በታሪኳ አንድ የውጭ ጦር ገብቶ ሲወጣ ምንም እርምጃ ያልወሰደበትና ድምጽ ያላሰማበት ፡ በታሪኳ በብዙ ቶን የሚገመት መጻህፍትና ቅርስ የተዘረፈበት ብቸኛው ክስተት ያ ወቅት ነው
    -ግራኝ መልካም ሰርቷል ብዬ አምናለሁ
    -ቴዎድሮስ የተጣሉት ከሁሉም ጋር ነበር ፡ቤተክርስቲያን ማሰራት ቀርቶ አቃጥለዋል ፡የተጣሉት ከክርስቶያኑም ከሙስሊሙም ፡ከፈረንጁም ካበሻውም ነው
    -ቴዎድሮስ ለመግዛት የሞከሩት የኢትዮጵያን 1/3 ክፍል እንኳን አይሆንም ። የአማራውን አካባቢ እንጂ – ቤንሻንጉል ፡ጋንቤላ፡ ኦሮሚያ፡ ሶማሌ፡ አፋር ፡ ደቡብ ፡ሃረሪ ሁሉ ቴዎድሮስን አያውቋቸውም ነበር
    -ናፒር የመጣው ኢትዮጵያን ለመውረር ሳይሆን ቴዎድሮስን ለመቅጣት ብቻ ነበር – ከእሱ ሰዎች አንድም የሞተ አልነበረም
    -ወሎ ላይ ከስምንት ጊዜ በላይ ዘምተውበታል ፡ ጎጃምን አጥፍተውታል ፡ጎንደርን አቃጥለዋታል
    -በቅርቡ ሞጣ ላይ የተከሰተው ጥቃት ከቴዎድሮስ አስተሳሰብ የመጣ ነው
    -በሴት ተገደለ? ለናፒር ያስረከባቸው ህዝቡ ነው
    -የአእምሮ ህመምተኛ?
    -አፄ ቴውድሮስ ፈሪም ተብለዋል(ከቅደላ ለማምለጥ ሁለት ጊዜ ሞክረው ዙሪያቸውን በገበሬ ተከበው ስለነበር ሳያመልጡ ቀሩ)
    -ጀግናው ባሻ አሰኔ ነው
    -የቶዎድሮስን ጭካኔ ቃላት አይገልጸውም ———
    እስኪ ሙሉውን አንቡና ጊዜ ካላችሁ አንድ በሉበት።በእውቀትና ማስረጃ ላይ ተመስርተን እውነቱን እውነት ሃሰቱን ሃሰት እንበል እንጂ ለምን እውነት ተነገረ አንበል።
    ———–
    ይለናል ወንድም አብዱ ጀሊል —
    በማስረጃ ሞግቱኝም ይለናል ።

  3. ጅል ግን እሱ ሳይሆን አንተ ነህ አብይ አህመድ አሳምነውና ጓዶቹን እርስ በእርስ አጨራርሶ ያልሆነለትን አንተ ተደብቀህ ትጽፋለህ ማን ያውቃል ትግሬም ልትሆን ትችላለህ። በአማራው መሀል እንዲህ ያለ ግጭትና ጥርጣሬ መፍጠር ጥቅሙ ለማንነው?ሰውዬውን እንደምታውቀው ይገመታል ወደኛ ከመላክ ለምን ወደሱ ስም ቀይረህ ለማስተማሪያነትም ሆነ ለማስፈራሪያነት አልላከውም ? ሳስበው ሸለምጥማጥ ነገር ሳትሆን አትቀርም። አማራው በየቦታው ተቀስፎ አንተ ደግሞ አሳቢ መስለህ ትበትነዋለህ።
    ምን ታደርግ አላማህ ሳይስተዋል ስድብ ይለጠፍልሀል።

  4. አስናቀን ለማወቅ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ማግኘት በቂ ይመስለኛል ።እነርሱን ብታገኝ ኖሮ በእርግጠኝነት ይህን አትለጥፍም ነበር።

  5. ፀሀፊው ዋው ?? የቃላት አጣጣል አሪፍ ነው። ግን ቀንደኛ ጎጠኛ መሆንህን ያሳብቅብሀል፤ከዛም በላይ የ ሌባና የ ጎጠኛ ቃል አቀባይ ነው የምትመስለው ። በተረፈ የ አዝማሪ ቤት ግጥሟ ደስትላች በቃ እንግዲህ የማታ ማደሪያህ በኮሮና ስለተዘጋ ??? for u.Shalom ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share