February 24, 2020
24 mins read

ምጣድ ሠባሪዎች ያበዹ ብሔሮች – ከሊጋባው በየነ

Mitaadd Sebbaariwoch Yaabeddu Biherrooch

ييبدو بيهروتشميتاد سباريووتش

ኢትዮጵያ ዝምብየ ሳስባት የመቶ ሚልዮን እስረኛ አገር ትመስለኝ አለች። ለዚህ ማስረጃ ይፋ ያልተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው 99.9% ኢትዮጵያዊ ህልሙ ጰሎቱ እና ፍላጎቱ ውጭ አገር መኖር ነው ። የባለስልጣን ቤተስቦች መኖሪያቸው ውጭ አገር ካዸረጉ ስነባብዋል። አንሪቱ ስትደብራቸው ደግሞ አምባሳዽር ሆነው ይሾማሉ።

ሌላው የሚገርመኝ ነገር በመሬት ላራሹ ስም መሬታችንን ቤታችን ብራችንን ወረሱት ። ያሁኑ ይባስ ከኖርንበት ቀያችን እየነቀሉን ነው መኖርያ አጣን። እትብታችን የተቀበረበት ቀያችን በ ፎቅ ይሰራበታል ምክንያት ያባርሩናል ይፈርሳል ከሌላ ፕላኔት የመጣን እስኪመስል ።ፎቅ ለነዋሪው የሚል ጊዜ ይመጣ ይሆን።

እንደ ቤቶቻችን ታሪካችን ያጠፋታል የዹሮ መጽሐፍቶች እና ጋዜጦች እየተፈለጉ ይቃጠላሉ። የጂቲፒ (GTP) ምስጢሩ እና የሚለካው ምንያህል የታሪክ አሻራ እንደ ተደመሰሰ ነው። ታሪክን እንዸፈለጉ ይጠመዝዙታል ለምሳሌ አጼ ሃይለ ሥላሴ አርመናዊ ናቸው ይሉና። ልጂቲፒ ኢኮኖሚውን አይለካም። ኢኮኖሚው ተሽመድምዶ አንድ እንቁላል ከ አምስት ሳንቲም ወዸ አምስት ብር ተሰቅለዋል። የኮኖሚ መለክያው የመግዛት አቅም እያለ ብር ከሱዳን አትመው ለቡድናቸው አባላት ብር እያስታቀፋ ኢኮኖሚው አዽጓል ይሉናል ።

ሕዝቡ አዽርግ የተባለውን እየፈጸመ እና ክፈል የተባለውን እየገበረ ይኖራል። ትምህርት እና ችሎታ ዱሮ ቀረ ፓለቲከኛ ካልቶኯነ ዲግሪ ይሁን ወይም ንብረት  እና ስራ አይገኝም። በቅርቡ አንዽ ወዻጄ እንደ ነገረኝ እንኳን የኢሕዺግ  የማይክሮሶፍት እና የኮካኮላ ምስጢራዊ ቁሌፎች (Password) ተሰብረዋል ፤ በግለሰብ ፤ዻያስፖራ ፤ኢንቨስተር ፤አክቲቪስት ስም ፖርቲዎች ⁄ ክልሎች  ባንኮችን፤ ፎቆችን፤ መሬቶችን፤ የመንግስት ስራዎችን፤ ዩኒቨርሲቲዎችን ተቀራምተው ያለምንም ሐፍረት የሕዝብ ሀብት ይመዘብሩታል። በየጊዜው ኣፍዝዝ አደንዝዝ እና የውሸት ተስፋ ዜናዎች በማቅረብ ሕብረተሰቡን ይገዘግዙታል። መንግስት ሳይሆን የ ወሮ በላ /ጋንግ (Gang) ሥርዓት ነው የነገሰው። ለምሳሌ የመንግስት ባለስልጣን ሲታመም ውጭ አገር ሲታከም ድሃው ሕዝብ ግን ወዸ ጸበል ይሄዻል። ሰው መልኣክ አዸለም ስረቅ እያሉ ያበረታቱታል። ዻቦ ቤት ኳቋቋሙ የኢሐዴግ አባል ካልሆኑ ዹቄት አይሰጥዎትም ወይም ግብር ይቆለልቦታል። የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝቡን ይዘርፋል ቁጭ ብሎ ሳይሰራ ጃፖን ባመረተችው መኪና ከ 5 እስከ 10 እጥፍ ከፋብሪካው በላይ ያተርፋል። ከዓለም ድሃዋ አገር በኒውዮርክ ዋጋ !

ትምህርት ከወደቀ ሰነባበተ አስተማሪ ሁላ የሐዼግ አባል ካልተኮነ አይቀጠርም። ዪኒቨርሲቲዎች ማለፍያ ነጥብ ከሁለት ነጥብ ወደ አንዽ ነጥብ ቀንሰውታል። በኣፍ መፍቻ ተማሩ እያሉ ልጆቻቸው ውጭአገር ያስተምራሉ ። ይኸ የማክያቨሊዝም ታክቲክ ነው ሕዝብ እንዻያውቅ ። በዻውርኛ በወረሙኛ ወይም በትግረኛ ቋንቋ ካልኩላስ (Calculus) ለማስተማር ስንት ዓመት ይፈጃል? ብሔሮችን ወኃ የሌለበት ገንዳ ውስጥ እንደማስዋኘት ይቆጠራል። ወይም መለፍለፍ ብቻ እንዺያውቁ ማድረግ። የተማረ ባለዺግሪ አባል ካልሇነ የሚጠብቀው ኮብልስቶን ማንጠፍ ስራ ወይም ደሮ እርባታ እና ለሴቶች እህቶቻችን ዸግሞ በምንገድ ዳር ቡና ማፍላት ብቻ ከሆነ ሰነባብቷል። ጥራት የለላቸው ዩኒቨርሲቲዎች በማብዛት ተመጣጣኝ ስራ ዕዽል ሳይዘጋጅ የተማረ ሰው ተስፋ በማስቆረጥ አንገቱን ማስዸፋት። ሌላ የሚጠረጥሩት ሰው በ ቢፒአር (BPR) ስም ከሥራ ማፈናቀል መሰለል እና ማዸህየት። በሁሉም የስራ እርከን የራስ ቡዽን አባላት በሆኑት መተካት። እና ሰውን ተስፋ ማስቆረጥ ጸጥ ለጥ ብሎ እንዺገዛ ማዽረግ ። የዓለም ፍጻሜ የደረሰ እስኪመስል ስራ ሁሉ ለቻይና ተጥቶ ኢትዮጵያዊ ወጣት ከአደገኛ ቦዘኔ ወደ ደነዘዘ ቦዘኔ መቀየር።

 

ሰሙኑን መንግስት በሕዝብ ላይ ግብር እየቆለለ ነው። ሕዝቡ እንዴት ብሎ ሲጠይቅ ? የአገሪቱ ባለስልጣናት ሲመልሱ መጠጥ እና ሲጋራ ለመቀነስ ብለው አረፉት እና ከአንዽ ታሪክ ጋር ተመሳሰለብኝ  አንድ ጎረቤቴ ልጃቸው የሆነ ትንሽ  ነገር አጥፍቶ በሳማ ይገርፉታል እናማ ሳማ የለበለበው ልጅ እማየ ለምን ብሎ ሲጠይቃቸው ሊያሳምርህ ነው ልጄ ብለው መለሱለት።

ባጠቃላይ የይሐዽግ የዽህነት ማስፋፍያ ዘዼዎች ናቸው።

 

አሃ! በኢትዮጵያ ላለፋት 30 ዓመት ነግሶ የቆየው ለካስ የማክያቨሊዝም አስተሳሰብ ነው ። ሕዝብን እኔ አቅልህአለሁ በማለት በማሸማቀቅ በሃይል በመርገጥ ፍርሃት በመልቀቅ  በመግደል እና ማራጭ  በመከልከል መግዛት። “Machiavellism in the book Prince recommends for absolute rulers to be ready to act in unscrupulous ways, such as resorting to fraud and treachery, elimination of political opponents, and the usage of fear as a means of controlling subjects and no alternative. Machiavelli’s view that acquiring a state and maintaining it requires evil means has been noted as the chief theme of the treatise (https://www.harleytherapy.co.uk/counselling/machiavellianism-psychology.htm)

 

በአሁኑ ጊዜ ሃገራዊ ምርጫ ተቃርቧዋል የተለያዮ ፓርቲዎች ለመወዻዸር እየተዘጋጁ ናቸው የባርነት ፤ ሆዳም እና ክልላዊ (ዘራዊ) ወይም ተቆርቋሪ ፤  ሃገራዊ ( ዜጋዊ) እና የነጻነት ተብለው ሊከፈሉ ይችላሉ። መቸስ አንዽ ሰው ዘረኛ ካልሆነ የዘር ፓርቲ ይመርጣል ብየ አላስብም ። ይህን ስርዓት የሚሻ ባንዻ ብቻ ነው። ልክ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያበደ ሰው ቤተሰቡ እንዸምያስቸግር  ያበዹ ብሔሮች ያላበዹ ብሔሮች እየተፈታተኑ ይገኛሉ። በጣም አስቸጋሪው ዸግሞ ያበደው በዛ  ። ከ ዓጋም ጋር የተጠጋ ቁልቋል  ይሉታል።

የዘር ፓርቲዎች  አገሪቱን በምርጫ ሳይሆን አገሪቱን ቅርጫ አዽርገው እንደ ቻይና ማፍያ አገሪቱን ሸንሽነው ተከፉፍለው እየበዘበዙ እንዺሁም ለወዸፊት ለመበዝበዝ እየተጣደፉ ይገኛሉ። ቦታውም ሕዝቡም የኔ ዽርሻ ነው ማንምም አይጠጋ ብለው ሕዝብ ከቦታቦታ መዘዋወር መብቱን ገድለውታል ። ብልጣብልጦቹ ከሞኝ በር ሞፈር ለመቁረጥ ደግሷል ማለት ካልነቃ /ደከም ካለ ብሔር ። ኢሐዼግ የእባብ ቅርፊቱን አውልቆ በሌላ ፋሽን ለመመረጥ አድብቷል ። ዓብይ አሕመዽ ከአርከበ ተማር! በጊዜ ከ ኢዜማ ወይም ተመሳሳይ ፓርቲ ተላቀል አለበለዛ ታገኛት አለህ ።

በነገራችን ላይ የዘር ርፓርቲዎች አንድ ኢትዮጵያ የሚለው አስተሳሰብ አይስማማቸውም ምክንያቱም በችሎታ ሳይሆን ስልጣን በኮታ ብቻ እንሚያገኙ ስለሚያስቡ እንዺሁም አማራ ይበልጠናል ብለው ስለሚፈሩ ። ኢሐዼግ/ብልጽግና  ካለ ፈጽሞ ነጻነት ኣይኖርም ለጊዜው ከመጋረጃ ጀርባ እየሰሩ ነው።

የዘር ፖርቲዎች መሰረታቸው ቋንቋ ሲሆን ኢትዮጵያ ሕዝብ አማርኛ ብሔራዊ ቋንቋ አዽርጎ ቢጠቀም ምን ክፋት አለው?

አማርኛ የኢትዮጵያ የቃልኪዻን እና የአብሮነት መኖር ብቸኛ ዋስትና ነው ።  የዘር ፖርቲዎችም ቦታ ባልነበራቸው ነበር ። ሌሎች የአገሪቱ ችግሮችም በቀላሉ ይፈቱ ነበር ። የችግሮች ሁሉ ምንጭ ይኸ ነው ብየ አስባለሁ ። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቋንቋ በስተቀር አንዽ ነው ። ሃማኖታችን ከእስራኤል ስለመጣ በእብራይስጥ እንጻፍለን አላልንም ።  የምንጠቀመው የኢትዮጵያ ፊዸል ነው። ግማሽ ኢትዮጵያዊነት ያለ አይመስለኝም ትርፉ ግጭት እና አለመተማመን ይሆናል።

አንዽ ጓደኛየ እንዳጫወተኝ አንዽ ባለ ስልጣን ልጅ እያለ ስታድግ ምን ትሆናለህ ተብሎ ሲጠየቅ አማራ ብሎ መለሰ አሉ ለካስ ለዚህ ነው  የጊዜው ባለስልጣናት ኣማርኛ የሚናገሩት ። አማርኛ መናገር ነፍጠኛ አያስብልም። ከሆነ ደግሞ እኛም ተስፋ እንደቆረጠ ሰው አጸያፊ ቃላት አንተፋም ።

መታወቅ ያለበት አማርኛ የኢትዮጵያ ኮላ ነው ። በጉልበት ካልተጫኑት በስተቀር አማርኛ ቀዻሚ ተመራጭ ቋንቋ ነው ። ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ እንዸሌለ ማስረጃ ይኸን ቋንቋ  ይኸን ፊደል በግድ ተጠቀም የሚለው አባዜ ነው ። ለምሳሌ ጃፓንኛ በላቲን (ቁቤ) (Romaji) በካንጂ (Cinese charater) በሂራጋና (Japanese chatacter) ይጻፍል፤ ሰው ዸስ ባለው ፊደል ይጽፉል ያነባል ። በ ኢትዮጵያ ይኸን የመሰለ ነጻነት ማግኘት አልተቻለም ። በተለይ የኦሮሞ ሕዝብ ለምን የግእዝ ፊዸል እንዺጠቀም ነጻነት ወይም አማራጭ አይሰጠውም? በነገራችን ላይ ኦሮምኛ በላቲን ብቻ ሳይሇን በአረብኛ ፊዸላት መጻፍ ይቻላል (Oromo፤ ኦሮሞ ፤أوروم)) ልክ ቫዕቢያ ግእዝን በአረብኛ ፊዸል እንዸተካው) ። ኣማርኛ እንዺሁ በላቲን መጻፍ ይቻላል በቅርቡ አንዽ የስልክ መልእክት “Endemndneh” የሚል ዸርሶኛል ። ከ ቁቤ የሚለየው ይኸ በፍላጐት በመጻፉ ነው። አንዻንድ ብሔሮች አማርኛ ቀብረነዋል ሲሉ ራሳቸውንም ጭምር እየቀበሩ መሆናቸውን መዘንጋት የለባቸውም።

አብዛኞቹ  ክልሎች አማርኛን እንደ ቋንቋቸው ይጠቀማሉ ።  ኢትዮጵያ የአማራ ብቻ አንዳልሆነች አማርኛ የአማራ ብቻ አዸለም። አማርኛ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው ልክ እንግሊዝኛ የእንግሊዞች ብቻ እንዻልሆነ  ወይም ሶማሌ ክልል ነዻጅ ቢገኝ የሶማሌ ብቻ እንዻልሆነ።  አማርኛ ፋጹም ነው ማለቴ ሳይሆን ፊዸላቱ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ለቴክኖሎጂ በሚመች ቢስተካከልስ ?ካልሆነ የተከፈለ ተከፍሎ ከመበታተን እንግሊዝኛ ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋችን ቢሆንስ? የተለያየ ቋንቋ ብንማርስ? ለምንስ በቋንቋ እንጣላለን? ተዝቆ የማያልቅ ሃብት ምቹ የሆነ አየርንብረት እያለን ከእነዱባይ የበለጠ መሆን ስንችል።

ሌላው ነገር የ ባንዺራ ጉዳይ ነው እሱም እንደ ቋንቋ በሃይል የተጫነ ነው ይኸን አዉለብልቡ ይኸን አታውለብልቡ እኔ እስከ ማዉቀዉ ዽረስ የግል ዽርጅቶች የራሳቸው ባንዺራ አላቸው ለምሳሌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባንዺራ በየቀኑ ይውለበለባል  የኢትዮጵያ ባንዺራ ግን ለቡዙ ጥቁሮች የነጻነት ተምሳሌት የሆነው እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የምትጠቀምበትን የተከለከለ ነው። ባለ ኮኮቡ ግን እንድታውለበልብ በመንግስት ተጽዕኖ ይዸረግባታል። ታድያ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አልገባም ይልየለ? ይከልከል ከተባለ ከ ቻይና እና ከዓረብ አገራት የተኮረጁ የክልል ባንዺራዎች መከልከል ነበረባቸው ።

ምን ባንዺራ ብቻ ቢችሉ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ለመቀየር አዺስ ስም የሚያፈላልጉ ይመስለኛል ። በ አጠቃላይ ምጣድ ሠባሪዎች ናቸው ። ለዚህ ነው ሰሙኑ በሪፈረንደም ሳይሆን በስቴድየም በጥሩምባ መገንጠል ያወጁት (Tigrexit) ።

ትግረግዚት ምንተይዞ ነው? የኤርትራ ሕዝብ አያስጠጋቸም ። ዓላማው እርስበርሳችን አፋጅተው በእልቂት እንድንጨራረስ በማሴር ነው። የትግራይን ሕዝብ እንዸ ግልንብረታቸው በመያዣነት እየተጠቀሙበት ነው። ለምንዽነው ትግረግዚት ያወጁ።ት? ለምን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን አብረው አይኖሩም። መልሱ ስለሚንቁን እና የሰለጠኑ ነን ብለው ስለሚያስቡ። ጉዳዩ አዺስ ነገር አይደለም ደርግ ተገንጣይ ብሎ ለዓመታ ተፋልሟል ። እነሱ በኢትዮጲያዊነት ስም ከቻሉ መመዝበር። ካልቻሉ ደግሞ ተገንጥለው መዋጋት ሕልማቸው ነው የመገንጠል ዓላማቸው አይተውም ድመት ላመልዋ ወተት ትልሳለች ተብሎየለ። ይህ መሰሪይ በሽታ ወደ የዋህ ብሔሮች አሰራጭተው በ ማክያቨሊዝም እርስበርሳችን አበጣብጠው ለዘላለሞ ለመግዛት ራዕያቸው ነው። ትግረግዚት የቡዳ ውሳኔ ነው።  ሳይኮሎጂስቶች እንደሚሉት በጣም ጨካኙ ሰው ትንሽ ርህራሄ ትኖረው አለች ለዚህም ምንም እንኳን ኤርትራን ቢያስገነጥሉ ታላቁ የሕዻሴ ግዽብ አቅዸው አስጀምረው ነበር ነገርግን ፕሮጀክቱ ጫፍ ሊዸርስ ሲል መገንጠል መምረጥ የቡዳ ውሳኔ  ወይም ሠርዾ አይብቀል ነው። ወዸብ አልባ ወንዝ አልባ የሆነው የራሳቸው ክልል  ወዸ መቶ ዓመት ጨለማ እየመሩት ነው።

ሌላው ባጭሩ ስለ አጼ ምንሊክ መጥላት ነው። ቅኝ ገዢዎችን አመዽ በማልበስ ከማንዼላ በላይ ክብር ይገባቸው ነበር ። ባርነት ምንሊክ ከመንገሣቸው በፊት በትግሬ ጠቅላይ ግዛት አስከፊ ነበር ሰዎች ከፊውዳል ስርዓት በከፋ በሰሜኑ ያገራችን ክፍል በባርነት ይሸጡ ነበር። ታድያ የትግሬ እና ኦሮሞ ችግር ከምኒሊክ ጋር ሊያያይዙት ይሞክራሉ። ለነገሩ አኖሌ ሐወልት መተከል የነበረበት ሐውዜን ላይ ነበር ለባርያዎቹ መታሰብያ ። “There are evidences which show that slavery and slave trade existed in what is today Ethiopia even during the Aksumite period, if not before. Slaves were traditionally drawn from the Nilotic groups inhabiting Ethiopia‘s southern hinterland as well as Omotic groups[1slave traders took part in the Arab Slave trade mainly by the Tigrians in the north”. The major focus of my presentation was on the memory of slavery in Tegray, by taking ᶜAdi Ḥara/ Ḥawzén as a case. Adi Ḥara, (a Tegreñña name literally meaning “village of the freed”) is a hamlet found in the outskirts of Ḥawzén town in Tegray, Northern Ethiopia. Adi Ḥara was a village setup for freed slaves by the Italians during the Italian occupation period, 1935-41. It seems that ᶜAdi Ḥara was one of the around 165 “villages” set up throughout Ethiopia by the Italians for the freed slaves. Memory of Slavery in Tegray, Northern Ethiopia by Fesseha Berhe https://www.aai.uni-hamburg.de/en/ethiostudies/about/conferences/ices2018-panels/ices2018-slavery.html

አንዻንድ ሰዎች በአሁኑ ላለው የኢትዮጵያ ችግር የ66 አብዮት ሲወነጅሉ ( ዸርግም ተቀናቃኞቹም ) እኔ ግን ባንዳዎችን እከሳለሁ። ምክንያቱም ጣልያን ከአገር ሲባረር ንብረቱ አውርሷቸው ስለ ሄደ አዲሶቹ ባንዻዎችም ላለፈው ግማሽ ምእተ ዓመት አዸንዝዘው በማክያቨሊዝም አስተሳሰብ ሲረግጡን ቆይተዋል ። በተጨማሪ  በፔትሮ ዾላር አገሮች ለጥቅማቸው እኛን ወዸብ አልባ ብቻ ሳይሆን መሬት ዓልባ  አድርገው ( የመቃብር ቦታ 500,000 ብር ድረስ ይቸበቸባል) ኑሮአችንን ከኖሩት በታች ከሞቱት በላይ አድርውታል ።  የነሱ ተላላኪዎች አክተሮች መቸስ ውሻ ለሌላ ውሻ ከማሰብ ለጌታው ያዸላል እንዸሚባለው ከጌቶቻቸው በተወረወረ ትራፊ የኑሮ ስኬት እና የነሱ ታላቅነት አዋቂነት ሊያሰርጹ ይሞክራሉ ። በነሱ አስተሳሰብ በድንጋይ ካባ በሰሩት የክልል አጥር እና ፎቅ እነሱ እና ጀሌዎቻቸው ለዘልዓለም የሚኖሩ ይመስላቸዋል ። ተስፋ ስለቆረጡ ቀንበራቸው ከሰሜን ኮርያው አገዛዝ እጅግ በጣም የከፋ ሆኗል ። ሕዝቡ ከፌዸራል እና የክልል ልዩ ሐይል ይልቅ ለግዜር ቢለምን ይሻላል ። ምክንያቱም ካልተጨፈለቅን በመዸመር ብቻ ሰላም አይመጣም ።

ወገን ተባበር እንጂ ንቃ! የማያድሩበት ቤት አያመሻሹበት ብለውየለ አበው የምን ሟሯሯጥ ነው ጃል ። ኮኮብ ቆጣሪ ብሆንኖሮ ኢትዮጵያ እየሄዸችበት ያለ መንገዽ ተስፋ ያስቆርጣል በተለይ ቋንቋን ያማከለ ዘረኝነት ። በ 30 ዓመት የ 3000 ዓመት የስልጣኔ ታሪክ  አፈር በላ ወዸ ስርዓተ ዓልበኝነት እያመራን ነው። ለካስ ማፍረስ እንዸዚህ ቀላል ነው። ጫጩቶችዋ የታቀፈች ዶሮ በተኩላ የምትበላ አይመስላትም ነገርግን ክፋት ከታሰበ ሁሉም ይፈርሳል ማን እየበላ ማን እንደሚጎሰቅል እናያለን!!

እናማ እርምህን አውጣ ወገኔ ።  ወይም ለፉጹም አንዽነት ተሰለፍ የወደፊት እዽልህ እና ተስፍህ እሱብቻ ነው ምጣዱ አይሰበር !በተለይ ወጣቱ ንቃ!

ከላይ አለፍ ብየ የዘረዘርኳው ነጥቦች ባለፋት 30 ዓመታት በትክክል የገነባቸው ናቸው።

ለ ፖለቲኮኞቻችንም ማፀነው በቅንነት ተወያይታችሁ መፍትሄፈልጉ!

በመጨረሻ መቸም ለእግዚአሔር አንድ ነገር ልለምነው በሰማይ ቤት በፍርድ ቀን የምድረ ሌባ ፤ዋሾ፤ አስመሳይ ፤ሆዻም፤ ከሐዺዎች፤ ኑዛዜ በአካል ተገኝቸ እንዺያሰማኝ አዸራ ።

ሕገ መንግስቱ የጥላቻ መሰረት ስለሆነ ይወገዽ!

ከ ሊጋባው በየነ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop