የህግ የበላይነትን የቁራ ጩኸት እያወከው ነው። – ከመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ፊደራሊዝም ነበረ።” የሚሉ እና “አሃዳዊያን ሊወሩን ነው።በህገ መንግሥቱ የተሰጠንን ሥልጣን፣ መብት ና ጥቅም ሊቀሙን ነው።” ብለው የሚጮሁ አሉ። ጩኸታቸው ግን የቁራ ጩኸት ነው። ምንም እንኳ ቁራ የሚጮኸው በከንቱ ጉዳይ ባይሆንም።
ቁራ የሚጮኸው በከንቱ ጉዳይ አይደለም። በቁራ ህይወት ውስጥ ጩኸት ትልቅ ቦታ አለው ። ቁራ ወቅታዊ መልክቱን የሚያሥተላልፈው በጩኸት ነው ።ቁራ ለመሰሉ ቁራ ወቅታዊ መልዕክቱን በመጮኽ ነው ለዝንት ዓለም ሢያሥተላልፍ የኖረው።በአጋጣሚውም የሰውን ጆሮ ይሥባል።ምን ሆኖ ወይም ምን አግኝቶ ነው ይህ ቁራ የሚጮኸው? ሲል ይጠይቃል።የሀገሬ ባለአገር።
ህይወት ዝም ብላ አታሥጮኽምና አንተም ከየትኛውም ጩኸት በሥተጀርባ ያለውን እውነት ጠይቀህ በትዕግሥት አስበህ የጩኸቱን ምክንያት ማወቅ አለበህ። ቁራ የሚጮኸው በምክንያት እንደሆነ ተረዳ። ያለምክንያት እንዳይመሥልህ አንዱ ቁራ ሲጮኽ ሌሎች የሚያጅቡት።
በዚህ ምሳሌ አግባብ፣” የፌደራሊዝም ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ይህቻን ሀገር ሊየፈርሷት ነው።” የሚሉትም ሆነ፣ “የዚች ሀገር ዋሥ ጠበቃ እኔ ነኝ። እመኑኝ። እኔን መንግሥት ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አትፈርስም ።” ብለው የማጮኹት ሁለቱም በሞክንያት በመሆኑ ጩኸታቸው በከንቱነት የሚሥተናገድ፣ ግመሎቹ ይጓዛሉ ፣ ውሾቹም ይጮኸሉ ተብሎ የሚደመደም ከቶም አይደለም።
የሰዎቹ ጩኸትም የውሻ እንዳልሆነ መገንዘቡ በራሱ ትጥቅን ለማሳመር እንደሚረዳ ላሥታውሥህ።” የጩኸታቸው ምክንያት ምንድ ነው?” ብለህ መጠየቅ እና በጥሞና አሥበህ ለመመለሥ መሞከርም ከውድቀት ያድንሃል። በሥሜት የሚናጥ የጩኸቱ አድማቂ እንዳትሆንም ያግዝሃል።
እናንተ ፖለቲከኞች፣በተለይም ግራ ቀኙን አመዛዛኝ ህሊና አለን ብላችሁ የምታስቡ ፖለቲከኞች ጮኺዎቹ ፖለቲከኞችን አቅልላችሁ አትመለከቷቸው።ጮኺዎቹ ኃይል በተቀላቀለ ሥልታዊ ጩኸታቸው የትም ሊደርሱ እንደሚችሉ አሥቀድማችሁ ብታውቁ ኖሮ ይህ ሁሉ እንከን እና ጥፋት ቀድሞም ባልተፈጠረ ነበር።
የትም አይደርሱም የምትሏቸው እኮ ቢያንስ የቁራ ዓይነት ኔት ወርክ የሌላቸው አይደሉም እኮ!።መልካቸው ነጭ እና ጥቁር መሆኑንንም አትንዘጉ።ሁለት መልክ ያላቸው ሰዎች እጅግ አደገኛ ናቸው። በጣም አደገኛ ከመሆናቸው የተነሣ እየሳቁ እና እያሳሳቁ ሊገድሏችሁ ይችላሉ። ባህሪያቸውም የሻያሎክ ባህሪ በመሆኑ የህግ የበላይነት በሌለበት ሀገር ዋጋ ያሥከፍላችኋል።
እናንተ ከለውጡ ጋራ ተለውጠናል ብትሉም ሰዎቹ ከለውጡ ጋር ያልተለወጡ እና ለመለወጥም የማይችሉ ናቸው። (ጠቅላዩ በነዚህ ሻያሎኮች ካልተጠለፉ በሥተቀር፣ ሥልጣን በያዙ ማግሥት ማንነታቸውን አሣምረው ያውቁ ነበር። ከዓመት በፊት” ከእኛ የሚበልጥ ነብይ በእናንተ ውስጥ አለ ።”በሚል ርእሥ የፃፍኩትን ያሥታውሷል።)
ሰዎች ሆይ ፣ ጮኺዎቹ ግለሰቧች የሚኖሩትን ኑሮ እና እንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ ኑሮ አነፃፅሩ። አኗኗራቸው “ጫማና ኮፍያ” መሆኑን ትገነዘባላችሁ።የጩኸታቸው ተባባሪዎች የዳቦ ሥም የወጣላቸው “ቄሮ” “ፋኖ” “ኢጀቶ” “ዙርማ”ና “ወዘተ” አይደሉም።
የጩኸታቸው ተባባሪዎች ከእነሱ ጋር የዓላማ እና የግብ ተመሣሥሎሽ ያላቸው ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ናቸው። እነዚህ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎችም፣ አውቀው በምንቸገረኝነት እና ሣያውቁ በግልብ ሥሜት በመነዳት በፖለታካዊ ሤራ፣ሀገርን ገነጣጥለው፣ መንግሥት ለመባል በቀቢፀ ተሥፋ በህቡ የሚዶልቱትን በገንዝብ እንደሚደግፏቸው ይታመናል።
እነሱም በገንዘቡ፣ የኑሮ ድጎማ የሚያገኙ የዳቦ ተገዢዎችን ፈጥረዋል።ንቃተ ህሊናቸው ዝቅተኛ የሆኑትን በየከተሞቹ በቋንቋ ሥም ከቀበሌ ጀምረው በማደራጀት ለእኩይ አላማቸው አሰናድተዋቸዋል።ይህንን ካለፈው “ያሰብነው ካልሆነ ሽብር እንፈጥራለን።ሜንጫ እናነሣለን።መንገዱን በዲንጋይ እንዘጋለን። ወዘተ።”ካሉት ማሥፉራርቾ ጋራ ማሥተያየት እና እውነት ላይ መድረሥ ይቻላል።
እነዚህ መንግሥት ከመንግሥት ባህሪ ውጪ፣ያውም በህዝብ ብሶት መገንፈል ሰበብ ሥልጣነ መንግሥቱን የያዘ መንግሥት ፣ “የኢትዮጵያ ህዝብን በፍቅር አንድ አድርጎ የሚያሥተዳድር ነው።” ተብሎ ከጅምሩ የተጨበጨበለት መንግሥት ፣ (“አሥቀድሞ ማመሥገን ኋላ ለማማት አይመችም።”መባሉን ብንዘነጋም።…) በይቅርታ ሥም ሀገርን ለውድቀት የዳረጓትን ያለተጠያቂነት በማግለሉ እና በይቅርታ ሥም የፖለቲካ እሥረኞች እና በውጪ ሀገር የሥርዓቱ ጠላቶች ሆነው ፣በትጥቅ ትግል መንግሥትን ለመጣል በጦር እና በወሬ፣የሚዋጉትን ወደ ሀገር እንዲገቡ ፈቅዷል።
ሆኖም እንደተስተዋለው፣ በአዲስ አሥተሳሰብ በሚመራው አብይ መራሹ መንግሥት ይቅርታ እና ምህረት ወደሀገራቸው የገቡት አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ህግ፣ሥርዓት፣የግለሰብ ሰብዓዊ መብት የማይገባቸው ከቶም ከህግ በላይ የሆኑ እንዲሁም በሥመ ዘር፣እና ቋንቋ ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጩ ሆነው ተገኝተዋል።በዚህ ምክንያትም ሀገሪቱ የህግ የበላይነት የማይከበርባት ጉልበተኛ እንዳሻው የሚያምሥባት በረት እንድትሆን ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል።ዛሬም ሆነ ነገ ጉልበት እና ገንዘባቸውን ለጥፋት አይቆጠቡም።ርዕዮታቸው ቋንቋ እና ዘር በመሆኑ።
ጉልበተኛው፣ ገንዘቡን፣ዘሩን ፣ ቋንቋውን እንዲሁም፣ የዘረጋውን የሽብር መረብ በመተማምን በአራቱም ማዕዘን፣ በሰሜን፣በደቡብ፣በምዕራብ እና በምሥራቅ ፣መንግሥትን በሤራ የማሶገድ ዕቅድ አውጥቶ፣ በህቡ እየተንቀሳቀሰ ግጭት፣ሽብር፣ሁከት፣ግድያ እየፈፀመ እና እንቅስቃ ሴዎችን ሁሉ እየገደበ ያለበት ምክንያት በአንድ ሀገር ውስጥ ሁለት መንግሥት በመኖሩ ብቻ አይደለም ከትክክለኛው የመንግሥት አመራር ይልቅ የቋንቋ አመራር ግዝፍ በመንሳቱም ጭምር ነው።የቋንቋ ርዕዮት ይሉሃል ይሄ ነው።
(በበኩሌ መከላከያ ሠራዊቱ የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌነት ነው።ብዬ አምናለሁ።እዛ አካባቢ የዘር እና የቋንቋ ክፍፍል ከመጣ እና ከወታደራዊ ዲሲፕሊን በማፈንገጥ ሁሉም በየቋንቋው ማንሾካሾክ ከጀመረ፣ ይኸቺ ሀገር ያልቅላታል። እናም ከታች እሥከላይ ሥብጥሩ ሚዛናዊ የሆነ፣በይበልጥ ደግሞ በጠንካራ ወታደራዊ ዲሲፕሊን የታነፀ ቋንቋ መገባብየያ እንጂ ተመላኪ ጣኦት እንዳልሆነ የተገነዘበ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የፊደራል ፖሊሥ እንዳለን ማረጋገጥ ያሥፈልጋል።)
እነዚህ ቋንቋን የጥቅም ማግኛ እና የመከፋፈያ መሣሪያ ያደረጉ፣ሁሉም ክልል ያሉ “ጮኺ ፖለቲከኞች” ሠራዊቱን የግል ዓላማቸው መገልገያ እንዳያደርጉት ፣በወታደራዊ ዲሲፕሊን የጠነከረ እንዲሆን ከማድረግ ባሻገር ፣ የእነዚህን መሰሪ ፖለቲከኞች ተንኳለኝነት ማጋለጥ ያሥፈልጋል።
የእነዚህን የመሠሪ ና ተንኮለኛ ፖለቲከኞች ህይወት እና ኑሮ በጥልቀት ሥትመረምሩ ፣በሴራ እና ባልተቋረጠ ግጭት፣ሥለሚያገኙት ትርፍ ማሥላት እንጂ፣ ደሃ ወገናቸውን ከድህነት ለማላቀቅ አጃቸውን ሲዘሩጉ አያሥተዋሉም።
እነዚህ ሥሥታሞች ናቸው ታዲያ መንግሥት ሆነው ህዝ
ብን ለማሥተዳደር፣ ይህንን የዳቦ ጥያቄ ያልተፈታለትን ህዝ
ብ በራበው አንጀቱ የሚነዘንዙት።
ንዝነዛቸውን እና የአዞ እንባቸውን አትመልከት።የብዙዎቹ የቋንቋ እና የዘር ፖለቲካ ፓርቲዎች ልብ በውስጡ የደበቀ
ውን ለማወቅ በብልሃት የግለሰቦቹን ማንነት መርምር ።…
የልባቸው ከበሮ በጅብ ቆዳ እንደተሰራም እወቅ።ውስጣ
ቸው የሚያሥበውን ለማወቅ ከፈለግህ እኔ እነግርሃለሁ።
ጮኺ እና በሤራ ፖለቲካ የተሞላው አእምሯቸው እንዲህ ነው የሚለው።
( ለራሥ ብቻ የሚሰማ የልብ ውስጥ ንግግር- የሚል ርዕስ ሰጥቼዋለሁ።)
“እኔን ብትመርጥ መንግሥት በመሆን የተንደላቀቀ ኑሮ መኖር በጀመርኩ በማግሥቱ፣ ቋንቋ እመግብሃለሁ። በቋ ንቋህ ትማራለህ፣በቋንቋህ አሥተዳድርሃለሁ ። ቋንቋህን አበላሃለሁ።ቋንቋህን አጠጣሃለሁ።በቃ።ትላንት ህወሓት በ
ቡድን ሥም ለጥቂት የቡድን አባላቱ ጥቅም እንደሰጠ ፣እኔ ም በሤራ ፖለቲካ ለሥልጣን ላበቁኝ ጎዶቼ እንጂ ለአንተ ደ
ነታ የለኝም።
” እውነቴን ነው የምልህ፣ ሥልጣን በያዝኩ ማግሥት የሌብነት መረብ ከመዘርጋት የዘለለ ግብ ከቶም የለኝም። እናም የሌብነት መረቤን በመዘርጋት በተቀላጠፈ መንገድ ብዝበዛዬን አጧጡፋለሁ።በሥልጣኔ ተጠቅሜ፣ ልጆቼን በፍጥነት ወደ አውሮፓና አሜሪካ በመላክ በዓለም በታወቀ ምርጥ ት/ቤት አሥተምራለሁ።የዘረፍኩትንም ብር በዶላር፣ በአውሮፓና አሜሪካ አከማቻለሁ።ከአምሥት ዓመት በኋላ ዳግም እመረጣለሁ ብዬም ተሥፋ አላደርግም።ምኔ ሞኝ ነው – ወደ አደላደልኩት አውሮፓና አሜሪካ መጭ እልልም እንዴ?!። …
“ትላንትም በመንግሥት ቁንጮ ባለሥልጣናት የተደረገው ይሄው ነው። በእኔ የተጀመረ አዲሥ እና እንግዳ ድርጊት አይደለም።ከቶም አልሞኝም። ለዚህ ደሃ ህዝብ ብልፅግና ብዬ ሃቀኛ ና ሀገር ወዳድ ብሆን ፣አብሬ ከማልቀሥ ውጪ የማገኘው ትርፍ የለም።
“የሀገሬ ሴቶች እና ህፃናቶች ፣በግጭቶች፣በጦርነቶች ሳቢያ የበለጠ ተጓጂ እንደሆኑም አውቄ ከነሱ ጋር ሙሾ አላወርድም። ለእነሱ ብዬ፣ከእነሱ ጋር አበሳ መቁጠርም ዓላማዬ እና ግቤም አይደለም። እናቶች ሆይ ለሴትያዝናል። ይጨነቃል ። ብላችሁ እንድትመርጡኝ ግን የአዞ እንባ ማንባቴ አይቀርም።
” አፌን ሰምታችሁ ‘ለሴት ተጨናቂ ፣ ሽቁጥቁጥ እና አዛኝ ነው።’ ትላላችሁ።ልቤን ሥለማታውቁ እኮ ነው ። እኔ ዘወትር ለራሴ ምቾት እና ድሎት ብቻ የምጨነቅ ሰው ነኝ።ሌላው ቀርቶ የሴት ምጥ ና ሥቃይ ከቶም አይሰማኝም።
“ሥለ ሴት የምጥ ሥቃይ ባሥብማ አሥቀድሞ መቼ በዘር እና በቋንቋ እሰባሰብ ነበር?! መቼ የወንዜ ልጆችን ብቻ ሠብሥቤ የፖለቲካ ፓርቲ በመመሥረት “ቋንቋ! ቋንቋ!” ያውም የወንዜ እል ነበር?! ሴት ልጅሥ ዓለም አቀፋዊ እንደሆነች እያወቅሁ እና እኔም ከሴት መፈጠሬ እየታወቀ መች በሴት እጨክን ነበር?!
“ሴቶችን በአፊ የማንቆለጳጵሳቸው፣የማወድሳቸው፣ለሴት ትልቅ ክብር እንደምሰጥ ሁሌ የምናገረው ምርጫውን ለማሸነፍ ሥል ብቻ ነው።ሥልጣን ከያዝኩ በኋላ እውነታውን ታውቄለሽ።አዳሜ። በቋንቋ እየለየሁ በልዩ፣ልዩ፣መድሎ፣መገለል እና ሥቃይ ጣርሺን ሳበዛልሽ።…”(….)
የዚህ ጮኺ ፖለቲከኛ የልቡ እምነት እና እውነት ይኸው ነው። ከላይ ያሥቀመጥኩትን እውነት ከተረዳችሁልኝ ፣ማንኛውም የመንግሥት አሠራር ሥርዓት ከሌለው አደጋው ለራሱ “መንግሥት ነኝ “።ለሚለው እንደሆነ ትገነዘባላችሁ።
በህግ የተደነገገውን፣በሲቪልም ሆነ በወታደራዊ ህግ፣አድርግ አታድርግ ተብሎ የተፃፈውን ለማሥከብር እንዳይችል፣ በውስብስብ የሤራ ፖለቲካ በተተበተበና ወዳጅና ጠላት በተደበላለቁበት መንግሥት ውስጥ ፣ሥልጣነ መንግሥቱን የሚፈልጉ፣በልቅነት የሚቧርቁ፣ በገንዘባቸው ኃይል እንዳሻቸው የሚገድሉ እና የሚያሥገድሉ፣ ጉልበተኞች፣የፖለቲካ ቁማርተኞች በራሳቸው መንግሥት እንደሚሆኑም በማሥተዋል ታዝናላችሁ።
የመንግሥት መንግሥትነት ከተናቀ፣ የእንሥሣ ህሊና ይዘው ሰው የሆነውን ህዝብ እንደሞኝ እና ተላላ አልያም ተነጂ የሚቆጥሩ ግብዞች፣ያሻቸውን ይፈፅማሉ።
ጥር 26/2012 ዓ/ም በኦርቶዶክስ አማኞች ላይ የተፈፀመው እጅግ አሣፋሪ፣አሥደንጋጭ እና ለወላጅ አሣዛኝ የሆነ ድርጊት በግፍ እና በድፍረት የተፈፀመውም ከላይ ባነሳሁት ጭብጥ ምክንያት ነው።
ሁሉም የህግ ጉዳይ በባለቤቷ በኦርቶዶክስ ሲኖዶሥ አማካኝነት መፈታት ሲገባው፣እንዲህ ዓይነቱ ኃይል በለሊት መጠቀም ለምን አሥፈለገ? ያውም በጨለማ።(መለኩ ፋንታ የእግዜር ታናሽ ወንድም ፤ የዛሬን ማርልኝ የነገን አልወልድም።”አለች አሉ ፣የደርጉ ባለሥልጣን- ሻለቃ መላኩ ፋንታ ኮበሌዎችን እያነቀ ለእሣት ሲማግዳቸው ማየት ያሠቀቃት እናት።)…
መንግሥት ሣያሥተውል ” በእነ አክሊሉ ትብታብ” ውስጥ እየገባ ይመሥለኛል። የብርሃኑ ዘሪሁንን የቴዎድሮስ እንባ መፅሐፍን ያሥተውሏል።(ይህንን እውነትም ከዛሬው ፖለቲካ ጋር አቆራኝቼ መፃፊንም አትዘንጉት)
በዛሬዋ ኢትዮጵያ መንግሥት ማለት “ቋንቋ እና ጉልበት ነው። ” ከተባለ ጉልበተኞች ብቻ የሚኖሩበት ሀገር ይፈጠራል።ተገዳዳሪ እና አልገብርም ወይም እንደባርያ አላገለግልም ባይ ይወገዳል። በሥተመጨረሻ፣ ጉልበተኞቹም በወራሪ ጉልበተኛ ይወገዳሉ። እና ይህቺ ሀገር ተረት ትሆናለች።
ሥርዓቱ ዛሬም መብትህን ጨፍላቂ፣አሥፈራሪና አሥገዳጅ ከሆነ አምባገነን ነው “አዲሥ ንጉስ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ?” ማለትህ አይቀርም። ከለውጡ በፊት እንደነበረው ” ከቀበሌ ጀምሮ አንተ ሳታምንበት ፣ወደህና ፈቅደህ ለማድረግ ሣትከጅል፣ ሱቅህ ድረሥ በመምጣት ገንዘብ አምጣ ብለው የሚያፋጥጡህ ከሆነም ለውጡ ከወሬ የዘለለ እንዳልሆነ ትገነዘባለህ።
ወዳጄ አብይ ብቻውን ፣ለውጥ፣መደመር፣ፕሮስፓርቲ ፣አንድነት፣ፍቅር ወዘተ።ማለቱ ብቻ የትም አያደርስህም ።አንተን እና ኢትዮጵያን፣አንቺን እና ሀገርሽን፣የትም የሚያደርሷቸው(የሚፈልጉበት ከፍታ ላይ የሚያዎጧቸው) የህግ የበላይነት እና የፍትህ መደመቅ ነው።ሁለቱም ለሁሉም ህዝብ እኩል ሆነው ሥርዓት ባላቸው ተቋማት ሲተገበሩ ብቻ ነው።
ሁሉም ሰው ጠ/ሚ የሚሆንም ሆነ ተራው ሰው ፣በህግ ፊት እኩል ተጠያቂነት ሲኖራቸው ነው፣ ሀገር የጉልበተኞች መፈንጫ የማትሆነው።ሀይማኖትም መቀለጃ እና ማላገጫ የማይሆነው።
በነገራችን ላይ ጠ/ሚ አብይ እና አጋሮቻቸው ፣ “በህይ ወታችን ተወራርደን የህዝቡን ለውጥ ፈላጊነት ደግፈን የህወሃትን የበላይነት ተቃውመን እንሆ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ለውጥ አመጣን። ” ሲሉ፣ያልደገፋቸው የብዝበዛ መረቡ የተሸረካከተበት እና የተቀደደበት ብቻ እንደነበር ይታወቃል።”በእርግጥ ቀድሞ ማመሥገን ሆላ ለማማት ይቸግራል።”በማለት ” ሰከን ብላችሁ አሥቡ ። ያሉ ጥቂት አሥተዋዮችም ነበሩ።ምክንያቱም ሹፌሩ በመቀየሩ እና “በፊተኛው መንገድ አልጎዝም፣የፊተኛው መንገድ በአደጋ እና በሥጋት የተሞላ ከመሆኑም በላይ መንገደኞችን ለዘግናኝ ሥቃይና ለሞት ዳርጓል። የእኔ መንገድ፣ሥቃይ የማይበዛበት፣የፍቅር፣የአንድነት፣የፍትህ የዴሞክራሲ… ቀና መንገድ ነው።” በማለት የፖለቲካ እሥረኞችን መፍታቱና እና አጅግ ገንቢ ንግግር በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር በመናገሩ ሙሉ ለሙሉ ፣በሹፊሩ ላይ ተሥፋ ማድረግ የዋህነት ነው።እስቲ በተግባር ያለውን ይፈፅም።ሀግን በማሥከበር ፍትህን ያንግሥ።ያልነቀዙ ተቋማትን ይገንባ።ያንጊዜ ማድነቅ ብቻ ሣይሆን ልናግዘው ከጎኑ እንቆማለን ያሉ እጅግ በጣም ጥቂት አሥተዋዮች ነበሩ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ዘረኝነት" በፊዚክሱ ቤተ-ሙከራ ሲመረመር - ከበ.ከ

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share