ጆሲ ሚዲያን “ፈይሣ አዱኛ” ይይልህ! – ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ደግሞ ሌላ ነገር እንዳይመስልብኝ፡፡ ባይሆን ሁለተኛ ሰው እንኳን ልሁን ብዬ ነው፡፡ የማይሰማ ነገር የለም፡፡ “የቆዬ ሰው ከሚስቱ ይወልዳል” የሚባለው ትክክል ነው፡፡ እነዚህ ጅሎች ብለው ብለው የታቦታቱን ስም ሁሉ ወደ አፋን ኦሮሞ ለመተርጎም ትልቅ ፕሮጀክት ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ነው አሉ፡፡ ምሽቱን ስስቅ ነው ያመሸሁት፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ራቴን እየበላሁ የዮሴፍ ይጥናን ዩቲዩብ እከታተል ያዝኩ፡፡ ከዚያም በሚኒሶታ ያለው አንድ ቅሌታም ጳጳስ ይሠራው ያለውን ነገር ሰማሁ – ጳጳስ ቅሌታም የማይባል ከሆነ ይቅርታ፡፡ አቶ በላይ መኮንን ማለቴ ኦቦ “ቀሲስ” በላይ መኮንን ታቦት ሰርቆ ከሀገር እንደወጣ ሰምቼ ስለነበር ያ ሤራ ምን እንደነበር ዮሴፍ ምንጮቹን እየጠቀሰ ያብራራ ጀመር፡፡ ከዚያም ”መድኃኔ ዓለም” የሚለውን ስም “ፈይሣ አዱኛ” ብለው መተርጎማቸውንና የኦሮሞ ቤተ ክርስቲያን በማቋቋም ላይ መሆናቸውን በጠቀስኩት የዩቲዩብ የዜናና ሀተታ አውታር አደመጥኩ፡፡ ደነቀኝ፡፡ ገረመኝ፡፡ የጅልነታቸው ለከት ማጣት እጅግ አስደመመኝ፡፡ በዓለም በጅልነት ቢወዳደሩ አጠገባቸው የሚደርስ እንደማይኖር ተረዳሁ፡፡ ከ1ኛ እስከ መቶኛ እነሱው ይሆናሉ – በጅልነት፡፡ ሌላ ጅል ቢኖር ከ101ኛ ጀምሮ ቢቀጥል ነው፡፡ ከነማን ጋር ነበር ያን ሁሉ ምዕተ ዓመት የምንኖረው ግን? ተረኝነት ይህን ያህል ያጀዝባል እንዴ? እስከዚህ ያሳብዳል ወገኖቼ? እነዚያኞቹ አሁን እንዲህ ሊያፍሩና ሰማይ ምድር ሊደፋባቸው “እንኳንስ ከአሜሪካ ከመንግሥተ ሰማይም እናስመጣሃለን!”፣ “ጦርነትን መዋጋት ብቻ ሣይሆን ጦርነት ራሱን ጠፍጥፈን መሥራትም እንችላለን!” እስከማለት ደርሰው ጉራቸው ሰማየ ሰማያትን አለፈ – እግዜሩም ሰማ፡፡ የነዚህ ደግሞ ባሰና ከማስገረምም አልፎ በሣቅ ይገድሉን ያዙ – እግዜሩም ሰምቶ እንደኛው በሣቅ እየተንፈቀፈቀ ነው፡፡ ኧረ የመካሪ ያለህ እንበል! በሀፍረት አሸማቀው ሊገድሉን እኮ ነው ምንድን ነው ዝምታው! አንዳች መፍትሔ ፈልጉ እንጂ!

“ፈይሣ አዱኛ” ያጥፋኝ ነው የምላችሁ እነዚህ ጅሎች በዚህች አገር አምስት ዓመት ሥልጣን ላይ ቢቆዩ የአማራና የሌሎቹን ተውትና የትግራይን ስም ራሱ “ኦሮምታገሮ” ወደሚል መለወጣቸው አይቀርም – እነሱን እንኳን ይበሏቸው – ወደሽ ከተደፋሽ ነው ነገሩ፡፡ የለገሣ ዜና ቦምብ እና የኢሱ አፎርቂ ፈንጅ አይደል አሁን እዚህና እዚያ እንደብጉንጅ እየፈነዳዳ ሀገራችንን መቀመቅ እየከተታት ያለው? ጅራፍ አጩኾ ድምጹን የማይሰማ ካለ ደንቆሮ ብቻ ነው፤ ስለዚህ ባጠመዱት ወጥመድ መግባት ያለ ነውና ሁሉም የሥራውን ማግኘቱ አይቀርም፡፡ ለሰው የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ስትሰጥ ላንተ ቢያንስ የመቶ ሃምሣ ዓመት የቤት ሥራ እንደማይታጣልህ እርግጠኛ መሆን አለብህ፡፡ ምክንያቱም በሠፈሩት ቁና መሠፈር አለና፡፡ ፈጣሪ “በቀልን ለኔ ተዋት!” ያለው ለምን መሰለህ? ስለስም ከተነሳ አይቀር የኔንም ለውጠው “ለመፋ ጉዲቱ ካሢቾዳ” ሳይሉኝ አይቀሩም፡፡ እንዴ! ምን ጉዶች ናቸው በል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቋንቋችንን ማጎልመስ ውጤቱ በሁሉም ዘርፍ የላቀ ነው - ባንትይሁን ትዕዛዙ

ይልቁንስ የልጅነት ጨዋታ አስታወሱኝ፡፡ በልጅነቴ በኔ የጓደኞች ክበብ በትርጉም እኔን “የሚስተካከል” አልነበረም፡፡ጓደኞቼ መዝናናት ሲያምራቸው “በአማርኛ እንዲህ የሚባለው በእንግሊዝኛ እንዴት ይባላል?” ይሉኝና ስነግራቸው ይስቃሉ፡፡ ሲስቁልኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አሁን በነዚህ ጅሎች ስንስቅ ደስ ይበላቸው አይበላቸው አላውቅም፡፡

“Plant religion ድፍት ያርጉህ!” ማለት ተክለ ሃይማኖት ድፍት ያርጉህ ማለት ነበር – ያኔ፡፡ ከበደ ሞላ – Heavy Full፤ በቀለ ማሞ – Germinated Baby፤ ይሄ መሸጦ ባሪያ አለፈለት – This sold slave has passed him (መንግሥተ ኃይለ ማርያምን እኮ ነው!)፤  ከመሬት ተነስቶ ነገር ይፈልገኛል- He finds me a thing standing from the ground፤ እመ ብርሃን ታውቃለች – Mother of light knows…፤ አይሄድ አይመጣ ቁርጥ አባቱን! – He doesn’t go; he doesn’t come; he cuts his father…፤ … እንዲህ እንዲህ እያልን፣ እያስባልንና እየተባባልን በቀልድ እንዝናና ነበር፡፡ አሁን ግን የምር አደረጉትና በሣቅ ሊፈጁን ፈለጉ፡፡ እነዚህ ቀን ሰጠን ያሉ የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ነፈዞች ቋንቋም ቁም ነገር መስሏቸው ሲጃጃሉ ሳይ አንጎላቸው ከነጭ ጭቃ የተፈጠረ ስለመሆኑ በትክክል ገባኝ፡፡ ትልቅ መረገም ነው፡፡ ብዙ ያውቃሉ የሚባሉት የሃይማኖት አባቶች እንዲህ ካደረጉ ልጆቻቸው እነ ለማ መገርሣና ሽመልስ አብዲሣ ከታከለ ኡማና አቢይ አመድ ጋር በመመሳጠር የፌዴራል ተብዬውንና የአዲስ አበባን መሥሪያ ቤቶች በተለይም የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ እጅግ በአብዛኛው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በሆኑና ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ተልእኮ በተሰጣቸው በነወርዶፋና ጫላ ማስያዛቸው አይፈረድባቸውም፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ አቅም ራሱ ሌላ የምታገኘው ከስንት አንድ ነው – ይበልጡን ጉርሙና አያንቱ ናቸው፡፡ በቋንቋም እኮ መግባባት እያቃተን ነው፡፡ከጥቂት ጊዜ በኋላ አስተርጓሚ ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡ እነዚህ ሰዎች በእልህ ስለተነሱ ባንኩንም፣ ጅምሩክንም፣ ምኑንም ምኑንም አፍ በሌላቸው የገጠር ኦሮሞዎች እያስያዙ ሥራውን መበደል ብቻ ሣይሆን ባቢሎንን በኢትዮጵያ እየገነቡ ናቸው፡፡ የኮሮናን በሽታ ለማከም ቻይና በስድስት ቀናት ውስጥ ግዙፍ ሆስፒታል ትገነባለች እነዚህ ይሉኝታቢሶች ደግሞ በሁለት ዓመታት ውስጥ በተረኝነት ሕወሓታዊ የዘር ልምሻ ተለክፈው በኬኛ ፖለቲካ ሁሉንም ነገር ካለደረሰኝ ለራሳቸው ገቢ ያደርጋሉ፡፡ አፋርን፣ ሶማሌን፣ ደቡብንና ሌሎች ቤረቤረሰቦችንማ ከነመፈጠራቸውም ረስተዋቸዋል፡፡ ወገኔ – ትንሽ ሰው አያግኝ፤ትንሽ ሰው አያሸንፍህ፣ ትንሽ ሰው ራሱ አንሶ ሌላውን ያሳንሳልና አያጋጥምህ፡፡ በየመዝናኛው በወረምኛ ሲደነፉ ስታይ በነዚያኞቹ ቦታ ከምንጊዜው ተተኩ ብለህ ትገረማለህ፡፡ እውነቴን ነው – ትንሽ ሰው በፍጹም ጥጋብ አይችልም፡፡ እነዚያም ጥጋብ ባለመቻላቸው የሚሠሩትን አጡና የላይኛው ተቆጣቸው -ለዚያውም “ፈይሣ አዱኛ” የሚውልበትን ዕለት 27 ዓመታትን ያህል ታግሶ፡፡ ተቆጣናም ሳያስቡት ድባቅ መታቸው፡፡ እነዚህኞቹም ማዕዱ ከመቅረቡ ጠገቡና ገና ከአሁኑ ቁንጣኑ ሊገድላቸው ነው፡፡ ሰው የገዛ ሞቱን በገዛ እጁ ያፋጥናል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኮረና በኢትዮጵያ ከባድ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ሁሉም ያስብበት – ሰርፀ ደስታ

አሁን ለመጻፍ ምንም ፍላጎት አልነበረኝም፡፡ ከሞነጫጨርኩ አይቀር ጥቂት ነገር ላክልና ልተኛበት፡፡

እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞዎች እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትግሬና አማራ ሁሉ በነዚህ ገልቱዎች እንዳትጨነቁ፡፡ ችግሩ ያለው ከተራው ዜጋ ሳይሆን ልሂቅ ተብዬው ጋ ነው፡፡ ተራውማ ዓለም ብታልፍ አብሮነቱን አይጠላም፤ ተጣላ ስላሉትም አይጣላም –  መሠሪዎች ከሚጭሯቸው የተወሰኑ መጥፎ አጋጣሚዎች በስተቀር፡፡ የአማራ ገልቱ እንዳለ ሁሉ የትግሬም ገልቱ አለ፡፡ የጉራጌ ሃቱ እንዳለ ሁሉ የኦሮሞም ሃቱ አለ፡፡ ሃቱነት ወይም ገልቱነት የጎሣና የብሄር ኮታ የለውም፡፡ ዋናው ነገር አመራሩን የያዘው ነው፡፡ ጫፉን የያዘው ገልቱ ከሆነ ነገሮች ይበላሻሉ፡፡ ምክንያቱም በሀገራችን የእስካሁኑ ተጨባጭ ሁኔታ የሥረኛው የላይኛውን ከመከተል ያለፈ ብዙም አቅም ያለው አይመስልም፡፡ ስለዚህ ወዳጆቼ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣና ጄኔራል መርዳሣ ሌሊሣ በነዚህ ዐይጠ መጎጦች ከማንም በበለጠ ቅር እንዳትሰኙ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ሁሉም ሊሆን የግድ ነው፡፡ እኛም ልንማር የግድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሰፊ ሕዝብም እርጥቡን ከደረቁ ሊለይ የግድ ነው፡፡ የኛው ክፍያው በዝቶ አንገሸገሸን እንጂ ትምህርት ሁሉ ካለ ምንም መስዋዕትነት በነፃ እንዲገኝ አይጠበቅም፡፡ በአንድ በኩልም በታላቅ መስዋዕትነት የሚገኙ ትምህርቶችም አሉና የኛም ከነዚህ አንዱ እንደሆነ እንቁጠረው – ከነዚህም ሆነ ከነዚያኞቹ ግን እንማርና መጪውን ዘመን እናስተካክል – ቢያንስ ለልጆቻችን ስንል፡፡ ባይሆን መጪውን መስዋዕትነት ቀለል እንዲያደርግልን መጸለይ እንጂ በምናየው የቂልነት ተግባር ሁሉ ብዙም መሣቅ አይገባንም ታዲያ – ካስቻለን ሣቃችንን ቆጥበን ወደ ምህላው እንግባ፡፡ የጅል በትር አስቀያሚ መሆኑን ከጃዋራውያን ሜንጫ በከባድ ወጪ እየተማርን ነውና ይህን የሰይጣን ቁራጭ ከነጌታው እንዲገላግለን ፈጣሪን በየእምነታችን አጥብቀን እንለምን፡፡ “ፈይሣ አዱኛ” በያለንበት ይጠብቀን፡፡ ቻው፡፡ (ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት፡፡)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የብሄር እኩልነት!

https://youtu.be/pYymrRxfOw8

 

 

10 Comments

  1. የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ከአንድ የግል ዩንቨርስቲና ከአንድ ብሄር ብቻ ቅጥር ለመፈጸም መዘጋጀቱ አነጋጋሪ ሆኗል
    February 3, 2020 – ምንሊክ ሳልሳዊ –

    የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ለማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ክትትል ጀማሪ ኦፊሰርች ከአንድ የግል ዩንቨርስቲና ከአንድ ብሄር ብቻ ቅጥር ለመፈጸም መዘጋጀቱ አነጋጋሪ ሆኗል::

    የከተማው ገቢወች ቢሮ ለስራ ቅጥር ባወጣው ማስታወቂያ ላይ ለፈተና የተመረጣችሁ ብሎ የለጠፈውን ዝርዝር ተመልከቱ:: ሀሉም በሚባል መልኩ ሪፍት ቫሊ ከተባለ የግል ኮሌጅ የመጡ የአንድ ብሄረሰብ አባላት ናቸው:: ለምን ብሎ የሚጠይቅ የለም ወይ?

    1) ሌሎች የግል ዩኒቨርሲቲዎችስ?
    2) በጥራታቸው የተመሰከረላቸው በአህጉር ደረጃ ከፊት ተሰላፊ ከሆኑት እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካሉ ተቋሞች የተመረቁት ልጆችስ የት ገቡ? ማስታወቂያውን አልሰሙም ነበር?
    3) ተቀጣሪወችስ በብዛት ከአንድ ብሄረሰብ ለምን ሆኑ?
    4) ሀገሪቱ አሁን እየተመራችበት ካለው ፖለቲካ አስተሳሰብ አንፃር እነዚህ ከአንድ ብሄረሰብ የወጡ ተቀጣሪ ወጣቶች የአዲስ አበባን ህዝብ በቅንነት እና ከፖለቲካ ነፃ በመሆን እንዴት ሊያገለግሉ ይችላሉ?

    እንደዚህ አይነት የተግማማ ስራ መጋለጥ መተቸት አለበት:: መቆምም አለበት:: አልሰማሁም ደሞም እኔ ቀጣሪ አይደለሁም ማለቱ የማይቀር ቢሆንም ኦሮሞ ከሚገባው በላይ የመንግስት ቦታ ከተሰጠው ስራየን በ24 ሰዓት ውስጥ እለቃለሁ ሲል ቃል ለገባው ጠቅላይ ሚንስትር በጊዜ ንገሩት::

    የአዲስ አበባ የገቢወች ቢሮ ስራ ቅጥር ሁኔታ.

    • “ኢህአዴግ እንኳን ለሰው ህይወት ለዶሮም ሞት የሚጨነቅ ድርጅት ነበር”— አቶ አባዱላ ገመዳ

      Forbes › sites › 2016/06/09 › w…
      Why Bill Gates Wants to Give Away 100,000 Chickens – Forbes

      The Independent › uk
      How to avoid getting malaria – sleep with a chicken | The Independent

  2. ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ብዙ ሰዎች ብዙ ህብረተሰቦች ቢቀበሉት አይፈለግምን?ጅቡቲ ያሉ ሶማሌዎችና አፋሮች፥ ሶማሌያውን፥ደቡብ ሱዳኖች፥ ኡጋንዳዎች፥ ሰለ ኦርቶዶክስ ተሰብከው ቢቀበሉስ? ቻይናዎችና ጃፓኖች ኦርቶዶክስን ቢቀበሉ? ጥሩ አይደለም? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይህን አትፈልግምን? ትፈልጋለች ብዪ አስባለሁ። ታዲያ እነዚህ ህዝቦች በአማርኛ ነው የሚሰበክላችው? ያመኑበትን ታቦትም ሆነ ሌላ የዕምነት ሰያሜ በአማርኛ ነው መጥራት ያለባቸው? ኦርቶዶክስ የግድ ከአማርኛ ጋር ይያያዛል እንዴ? የራሺያ ኦሮቶዶክሶች የመድያኔልምን ታቦት መድሃኒአለም ብለው ነው የሚጠሩት? ዋናው ጉዳይ ምንድነው? እምነቱ ወይስ ቋንቋው? ኦሮሞዎች አዳኝን ፈይሳ ቢሉ ለምን ያስገርማል? እምነቱን እኮ የራሳቸው ማድረጋቸውን ነው የሚያሳየው። የማይተረጎም የሰው ስም ብቻ ነው። ሰው እምነቱን በራሱ ቋንቋ ሲገልጽ የበለጠ እርካታ ይሰማዋል።
    ጉዱ ካሳ፦ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው የተናገሩት አሽሙርና የጥላቻ ንግግር ግን አግባብ አይደለም። ስትፈልጉ ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት የኦሮሞ ድርሻ ትልቅ ነበር ትላላችሁ እዚህ መጥተው ደግሞ ከእናንተ ጋር ነበር እንዲ ይሄን አመት ያህል የኖርነው? በማለት ንቀትዎንና ጸጸትዎን ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ በነበረችበት አትቀጥልም። የነበራትን ይዛ በተጨማሪ ኦሮሞንም መምሰል አለባት፤ ሌሎች ልጆቿንም እንዲሁ። ተፈጥሮአዊ ነው፤ ሊገረሙም ሊናደዱም አይገባም። ይልቅ ኢትዮጵያ ሁሉንም እንድትመስል ከራስዎ ወገን ወጣ ብለው ሌሎችን የሚያካትት ሃስብ ያፍልቁ። ለምሳሌ የሲዳማው ጨምበላላ የኢትዮጵያ ኦፊሻል ዘመን መለወጫ ቢዮንስ?
    መኮንን

    • መኩ! ንቀት ከተባለ ንቀቱ መላውን ኦሮሞ ሣይሆን በኦሮሞ ሥም የሚንቀሣቀሱትን እነዚህን ጭንጋፍ ኦሮሞዎች ነው። አንድ ሰው አንድ ነገር ሲያነብ ወይም ሲሰማ እንዲገባው ከሚፈልገው ውጪ እንዳይገባው የአእምሮ በሩን ስለሚቆልፍ እንጂ አነሣሤ አዋኪና በጥባጭን ከማጋለጥ ውጪ ንቀት የሚባል ነገር እንደሌለበት ግልጽ ነው። ሙሥሊም ኦሮሞ ከክርሥቲያን ኦሮሞ ይበልጥ ክርሥቲያን ሆኖ ክርሥትናን ለመበታተን እንዴት እየተራወጠ እንዳለና ለዚህም ድል ባንድ ማዕድ እንዴት እየተዝናና እንዳለ እያየን ነው። በዐረብኛ የሚሦልትና ዱኣ የሚያደርግ ሙሥሊም ኦሮሞ በማያገባው ገብቶ ለምን በግዕዝ ትቅድሣላችሁ ብሎ ክርሥቲያን ኦሮሞዎችን ከዘመናት ወንድሞቹ ሢለይ ያልተቆጨ ሰው እነዚህን ከንቱዎች የሚያወግዝን ሰው ለመንቀፍ ለምን እንደሚጣደፍ አይገባኝም። አዎ፣ ወንድምና ወንድምን ለመለያየት ወጥመድ ከሚጥል ጋር ሣይተዋወቁ ለዘመናት መኖር አሁንም ልድገመው የሚገርም ክሥተት ነው።መረገምም ጭምር።

      • “እነዚህ ጅሎች ብለው ብለው የታቦታቱን ስም ሁሉ ወደ አፋን ኦሮሞ ለመተርጎም ትልቅ ፕሮጀክት ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ነው አሉ፡፡ ምሽቱን ስስቅ ነው ያመሸሁት”
        በማለት የጻፉት እርስዎ አይደሉም?
        “ከነማን ጋር ነበር ያን ሁሉ ምዕተ ዓመት የምንኖረው ግን? ተረኝነት ይህን ያህል ያጀዝባል እንዴ? እስከዚህ ያሳብዳል ወገኖቼ? “
        ያለውስ ማነው?
        ጉዱ ካሳ፦ የሚወረውሩት ፍላጻ የት እንደሚያርፍ ማስተዋል አይገባዎትም? አንባቢ እንዴት ይረዳው ይሆን ብለው ራስዎን አይጠይቁም? በንዴት ተነሳስው ያሰቡትን ቢጽፉ እንኳ እንዲታተም ከመላክዎ በፊት ንዴትዎን አብርደው ደግመው ማንበብ ይገባዎታል። ካልተሳሳትኩ ከዚህ ቀደምም ስለአጫሉ ሁንዴሳ እንዲሁ ግልብ ነገር ጽፈው አስተያየት ሰጥቼዎት እርሰዎም አስተያየቴን እንደተቀበሉ ገልጽውልኛል።
        እንግዲያው ልንገርዎ። ይህን ጽሁፍ ሰዎች በተለያየ መልኩ ሊረዱት ይችላሉ። ከነኚህ ውስጥ አንዱ፦
        ማነው ጻሃፊው__ የአማርኛ ተቆርቋሪ
        ማንን ይወክላል__ አማራን
        ምን አለ__ ከናንተ ጋር (ከኦሮሞ ጋር) ነው ይህን ሁሉ አመት የኖርነው?
        ምን ማለቱ ነው__ከናንተ ጋር መኖራችን ይቆጨናል፤
        ምንን ያስታውሳል_____ ከጋላ ጎረቤት ይሻላል ጎረቤት እየተባለ በባለጌዎች ሲነገር የነበረውን ተረት
        እያለ የሚቀጥል የሃሳብ ሃረግ ወይም ትርጓሜ።

        • አዎ እኔው ነኝ የጻፍኩት። አጭር ቃል፦ ኦሮሞንም አማራንም ትግሬንም ሌላውንም በሁለት ከፍዬ አያለሁ ፤ ኢትዮጵያዊና ፀረ ኢትዮሥጵያዊ ብዬ። ነገር አንሰንጥቅ – “የበላን ያብላላዋል” ካላልን በሥተቀር። ጅሎች ያልኳቸው በርግጥም ጅሎች ናቸው- ሌላ ቃል ሥላጣሁ። ሥለጅሎች ጥብቅና መቆም ይቻላል። አንድ ነገር ነው ይሄ። “እኔ ጅል አይደለሁም” ማለት ይቻላል – ይህ ሌላ ነገር ነው። ግን በደፈናው “እገሌ ኦሮሞን ጅል አለ” ብሎ የተለዬ አካሄድ መሄድ ከንቱ ነው። ፕሮ. ፍቅሬ ቶሎሣን፣ ታዬ ደንደኣን፣ ታዬ ቦጋለን፣ አብዲሣ አጋን፣ ጄ. ደምሴ ቡልቴን፣ አፄ ኃ/ሥላሤን፣ ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያምን፣ እኔ ራሴን… ጅል እንደማልል ይታወቅልኝ። ልድገመው – ነገርን አናወሣሥብ፤ ማለት የምፈልገውን የማውቅ እኔ ራሤ ብቻ ነኝ! ሞኝነት በዘር አይሄድም፤ ብልጠትም በዘር አይሄድም። በነገራችን ላይ “ከጋላ ጎረቤት” ወይም “ከወሎ ጎረቤት” ይሻላል ባዶ ቤት ነበር ተረቱ። አንድ ሰው አለው ሌላው ተከተለው፤ የትም አገር ያለ ነው። ብርቅ አይደለም አይለጠፍምም። አማራም ላይ ይተረታል። ወሎና ገለባ ጎጃሜና ተልባ ሲባል ወሎየዎችና ጎጃሜዎች መታነቂያ ገመድ አቀብሉን አላሉም። ትንሹንም ትልቁንም እያካበድን ነገር ኣናወሣሥብ። ይልቁንሥ ለማደግ እንሞክር፤ ባለንበት አንርገጥ። …

  3. I am ashamed of you for writing such a nonsense article. Every one has a right to worship the almighty God in his own language. The bible doesn’t forbid that. Please clean Yourself from hatred before speaking about others. May God forgive you for your arrogance and stupidity!

    • Wellsaid dear Tinsaye

      This is the cat of non christian and bigots like mahibrekidisan who are addicted to defamation of church servants. Mahibrekidusan did such heinous act multiple times; They sent women to monks and filmed them to defame monks and well known church scholars . They defame Memhir Begashaw , Tizitaw and Mirtenesh like that. It is alll about making money and taking the naive laity , thier financial resources, to them.

      Downwith Mahibrekidsuan, Yosef Yitna , the youtuber who sell info by defaming monks and bishops. .

      please be attentive tho these criminals who make thier living by demeaning church servants . Some were turned to heretics becusqe of these money minded people.

  4. አዎ እኔው ነኝ የጻፍኩት። አጭር ቃል፦ ኦሮሞንም አማራንም ትግሬንም ሌላውንም በሁለት ከፍዬ አያለሁ ፤ ኢትዮጵያዊና ፀረ ኢትዮሥጵያዊ ብዬ። ነገር አንሰንጥቅ – “የበላን ያብላላዋል” ካላልን በሥተቀር። ጅሎች ያልኳቸው በርግጥም ጅሎች ናቸው- ሌላ ቃል ሥላጣሁ። ሥለጅሎች ጥብቅና መቆም ይቻላል። አንድ ነገር ነው ይሄ። “እኔ ጅል አይደለሁም” ማለት ይቻላል – ይህ ሌላ ነገር ነው። ግን በደፈናው “እገሌ ኦሮሞን ጅል አለ” ብሎ የተለዬ አካሄድ መሄድ ከንቱ ነው። ፕሮ. ፍቅሬ ቶሎሣን፣ ታዬ ደንደኣን፣ ታዬ ቦጋለን፣ አብዲሣ አጋን፣ ጄ. ደምሴ ቡልቴን፣ አፄ ኃ/ሥላሤን፣ ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያምን፣ እኔ ራሴን… ጅል እንደማልል ይታወቅልኝ። ልድገመው – ነገርን አናወሣሥብ፤ ማለት የምፈልገውን የማውቅ እኔ ራሤ ብቻ ነኝ! ሞኝነት በዘር አይሄድም፤ ብልጠትም በዘር አይሄድም። በነገራችን ላይ “ከጋላ ጎረቤት” ወይም “ከወሎ ጎረቤት” ይሻላል ባዶ ቤት ነበር ተረቱ። አንድ ሰው አለው ሌላው ተከተለው፤ የትም አገር ያለ ነው። ብርቅ አይደለም አይለጠፍምም። አማራም ላይ ይተረታል። ወሎና ገለባ ጎጃሜና ተልባ ሲባል ወሎየዎችና ጎጃሜዎች መታነቂያ ገመድ አቀብሉን አላሉም። ትንሹንም ትልቁንም እያካበድን ነገር ኣናወሣሥብ። ይልቁንሥ ለማደግ እንሞክር፤ ባለንበት አንርገጥ። …

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share