December 20, 2017
13 mins read

ሃላፊነት የጎደለው ስር አትን  ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ለማስወገድ መሞከር አደገኛነቱ  አጠያያቂ አይደለም – ጊሸይ ጊሻ

እንደምንሰማውና  እንደሚታየውም  ህወሃት ኢሃዴግ ( ዛሬም ስላለ) ሃገሪቱ ትርምስ ላይ እያለች  ዜጎች በየቀኑ እንደቅጠል እየረገፉና መንግስትም እንደመንግስትነቱ  ተቋማዊም  ሆነ መንግስታዊ ስልጣኑ ተሸርሽሮ  ማን ሃገሪቱንእንደሚመራ ጭምር ህዝቡ ግራ በተጋባበት ወቅትበማያልቅ ስብሰባ ተወጥሮ እያለ  ጥቂት አድርባዮችና  ከስርአቱ  ያተረፉ  በዘር ፖለቲካ  ሰብእናቸውን ያጥ ግለሰቦች  በሚዲያ  ስር አቱ  እየጠነከረ ነው:  ውስጠ ዲሞክራሲው  እያጎለበተ ነው : ልማቱን እያጡዋጡዋፈ ነው  : ተጠያቂ እከሌ እንጂ እከሌ ትክክል ነው ሲሉ ይደመጣሉ።

በተቃዋሚነት የተሰለፈው ጎራ ደግሞ ከህወሃት ኢሃዴግ የውስጥ ሽኩቻ የሚገኝ ምጽዋት እየተጠባበቀ እክሌ አይሎአል እከሌ ደክሞአል በሚል የራስን ዝግጁነት በሚያንኩዋስስ ፖለቲካ ተጠምዶ ይገኛል። ሁለቱም አካሄድ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ችግር ለመፍታት ሃላፊነት የጎደለው አካሄድ ነው።

ሀወሃት ኢሃዴግ እስከዛሬ ለፈጸማቸው በደሎች ምንም እንክዋን ህወሃት የፈለፈላቸው ቢሆንም እንደሰው ማሰብ የሚችሉ ግለሰቦችን ያሰባሰቡት ሌሎች ድርጅቶች ተጠያቂነት ያለባቸው መሆኑን  ወደ መዘንጋትና የኢሃዴግ ፕሮግራምና  ፖሊሲ ላይ ተመስርቶ የተስናዳው የሌሎች ድርጅቶች ፕሮግራምና ፖሊስ የችግሩ አስኩዋል መሆኑን ያለመገንዘብ ችግር እየታየ ነው።  በኦፒዲኦና በነ አቶ ለማ መገርሳ ቡድን መካከል ያለው  ክፍተት ማለትም  የነአቶ ለማን ቡድን አስተሳሰብ የድርጅት አስተሳሰብ ማድረግ ገና ይጠበቃል። ይህ ደግሞ እነ አቶ ለማና አቶ ገዱ  የሚናገሩትን የህዝቦችን  ትሥስርና አንድነት  የ’ኢትዮጵያዊነት ሱሴ  ነው’ መንፈስ ኦፒዲኦና ብአዴን ከራሳቸው  አልፈው በኢሃዴግ ውስጥ ባለ ቸው ድርሻ አስተሳሰቡ  ገዥነትን ይዞ እንዲወጣ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው  በርግጥም  ፍሬያማና ሃገር አዳኝ የሆነ መፍትሄ ሊያመጡ  የሚችሉት። አሁን  ባለው ሁኔታ ይህን  አቅም ገንብተዋል ወይ የሚለውን  መመለስ መቻል አስፈላጊ ነው። ይህ ደግሞ ከሆነ አቶ ለማ ሊታሰሩ ነው ሊገደሉ ነው የሚለው  ውዥንብር ቦታ የለውም ። በርግጥ ዛሬ  የእነአቶ ለማና የአቶ ገዱ ቡድን አስተሳሰቡ በተለይም በሃገር አንድነትና በህዝቦች መተባበር መከባበር ለረዥም ዘመናት ከፖለቲካ መሪዎች ያጣነው አስተሳሰብና ቁዋንቁዋ መሆኑ ህዝብም  ሆነ ስራቱን  በአንድነት ጥያቄ ላይ  ለሚፋለሙት  ወገኖች  ተስፋን የጫረ በመሆኑ በአየር ላይ ያለ ድጋፍ አግኝተውበታል። በዚያው አንጻር ደግሞ የታሪክ እስረኛ ሆነው በሃገርም ሆነ በተለይ በውጭ በአንድነትና በሃገራዊ ጥያቄ ላይ የጎሪጥ እያዩ ከልብ ሳይሆን ለፖለቲካ ታክቲክ ብቻ ሲሞዳሞዱ ለነበሩ አስመሳዮች ትልቅ ራስ ምታት ከመሆኑም በላይ እንደፐንዱለም ዛረም ወቅት እየጠበቁ አንዴ በጋራ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገራችንን የጋራ መፍትሄ መስጠት ይገባናል ሊላ ጊዜ ደግሞ እኛ የተለየ ጥያቄ ያለንና ጥያቄውንም ማስመለስ የምንችለው እንደኛ ስንቆም ብቻ ነው ብለው ለሚያምታቱት የአቶ ለማን ቡድን የሚደግፉት ታክቲካዊ እንጂ አምነውበት እንዳልሆነ መረዳት አያስቸግርም፡

ህወሃት ኢሃዴግ የሚገዛውን ህዝብ ብሶት ማዳመጥ አቅቶት በቀደደው የዘር ፖለቲካ  በየቀኑ ወገኖቻችን  በአራቱም  ማእዘናት እየረገፉ የሃገርና ይህዝብ አንድነት ከመቼውም በላይ አደጋ ውስጥ ሆኖ አንዱ በአንዱ ላይ ጣቱን እየቀሰረ እንደድርጅት የሙት አመራር ላይ ቢገኝም ተቃዋሚው ዪህን የአደጋ ጊዜ እንኩዋን ተመልክቶ ቢያንስ ህዝብ የሚያምንበት ስብስብ ሆኖ ሊወጣ አልቻለም። ዛሬም እከሌና እክሌ ግንባር ፈጠሩ ተፈራረሙ ሲባል ነው የሚሰማው። የሃገሬ ሰው እዬዬ ሲዳላ ነው ይላል። ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ማንም ማንንንም ሊያገል የሚችል ብቃት ያለው ድርጅት የለም። የአሁኑ መሰባሰብ ምናልባት ለሚቀጥሉት አስር አመታት ታስቦ ከሆነ ጢሩ ነው። አሁን ሃገራችን ላለችበት አጣብቂኝ ፖለቲካ ግን ሁሉ እንክዋን ተቃዋሚዎችንና   ህወሃት እሃዴግንም ጭምር ከመፍትሄው አግልሎ መፍትሄ አገኛለሁ ማለት አይቻልም ። ህወሃትን አግልሎ ብአዴንን ዪዞ ወይም ኦፒዶኦን ይዞ መፍትሄ ማሰብ  የቁርሾ ፖለቲካና  ሃላፊነት የጎደለው አካሄድ ነው። በሁሉም ድርጅቶች ውስጥ ለጥፋታቸው ተጠያቂነት ያለባቸው ግለሰቦች መኖራቸው ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። እንኩዋን በስልጣን ላይ ያሉት ይቅርና  በስልጣን ላይ የሌሉና ስራቱን እንታገላለን የሚሉ የሚጠየቁ ይኖራሉ ። ቂምና ቁርሾ መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ግን መፍትሄ አይደለም ።

በሁሉም መልኩ ሲታይ ለውጥ የምንፈልግ ሃይሎች ከውዥንብር መጥራት ያለብን ጊዜ ይመስለኛል። በጎ ነገር ስናይ በጎውን በማጎልበት ላይ የተመሰረተ ህሊና ዪዘን ካልተነሳን በቆሸሸ መንፈስ ለሃገር መፍትሄ ለማምጣት አንችልም። ኢትዮጵያዊነት መንፈስ አብቦ እንዲወጣ አስተሳሰቡ ራሱ  ለናፈቀን ሰዎች የነአቶ ለማ መድረክ ላይ ወጥቶ በድፍረት ሃሳቡን ማንሸራሽር ያስደሰተን ቢሆንም አቶ ለማና ጉዋደኞቹ ድምጽ አጥተው በአደባባይ መናገር ያልቻሉ የሚሊዮን ኦሮሞዎች ድምጽ እንጂ ኦሮሞነት ለኢትዮጵያዊነት ርቆ አይደለም። ኦሮሞነትንና ኢትዮጵያዊነት ያራቁ ፖለቲከኖች  በውስጣችን የቀረጹብን የስነልቦና ሰለባ ነው። ትግሬነትና ኢትዮጵያዊነት አማራና ኢትዮጵያዊነት ደቡቦችና ኢትዮጵያዊነት  በፖለቲከኖች  የተነጠቀ የህዝብ መብት ነው። ዛሬም ለእውነት የቆሙ የህዝብ ልጆች ይህንን መብት ለማስመለስ ከመጡ ነገም ከመጡ ደስ ሊለን ይገባል።

የብዙ ብሄር ብሄረሰብ ሃገር  በመሆናችን ሁለ ነገራችን አንድ እንዲሆን የሚጠብቅ አስተሳሰብ ኢትዮጵያዊነትን የሚገልጽ አለመሆኑን ብዙዎች እንረዳለን ። እንኩዋንስ የአንድ ብሄር ወይም ብሄረሰብ ህዝብ  ቀርቶ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት አስተሳሰብ  ወይም የግለሰብ አመለካከት እድል የማይሰጥበት ዲሞክራቲክ ሃገር በተአምር ሊኖር አይችልም። የዲሞክራሲ ጥሩም ይሁን  መጥፎ ገጽታው ይህ ነው። ከዚህ አስከፊ ስርአት ልንላቀቅ የምንችለው እሱ በመረጠልን መንገድ ሳይሆን ሃላፊነት በተመላበት ስሜት መፍትሄ ስንፈልግ ብቻ ነው።

በዘመናቸው ብትጠቅማቸውም ባትጠቅማቸውም ቢጎዱም ቢጎዱዋትም  አደረገችላቸውም አላደረገችላቸውም ሚሊዮኖች ከየብሄረሰቡ ደማቸውን ያፈሰሱላት ሃገር ሰጥተውን ነበር። በኛው ትውልድ በውጭ ጠላቶቻችን ርብርብ እንዲሁም በወቅቱ የህብረተሰቡ ንቃተ ህሊናና የፖለቲከኞቹ ብልጣብልጥነትና ራስ ወዳድነት የተነሳ የ እብሪትና የተንኮል ፖለቲካ ቦታውን ይዘው ሃገራችንና ህዝባችንን አጥተናል። የዛሬው ትውልድ ጥያቄ   አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ተጎጂ አንዱ ባህሉ ቁዋንቁው ሃይማኖቱ ሲከብር ሊላው  እንዳይጠፋ የሃብት ክፍፍል ፍትሃዊ እንዲሆን የግለሰብ ነጻነቱም ሆነ የቡድን መብቱ ሊከበርባት የምትችል ዲሞክራሲያዊት  ኢትዮጵያ – የምትፈልግብኘን ብቻ ሳይሆን የድርሻዬን የማታሳጠኝ ሃገር ነው የምፈልገው የሚለውን  ትውልድ የሚያስባትን ኢትዮጵያ መፍጠር አማራጭ የለውም።

ለዚህ ደግሞ ከሆያ ሆዬ ፖለቲካ ከድርጂት ጠባብ አስተሳሰብ  ወጣ ማለትን ይጠይቃል ። ለህዝብ የቆሙ እውነተኛ ልጆች በህዝባችን ላይ እያንዣበበ ያለውን አደጋ በመገንዘብ የመቻቻል የአብሮነት  የይቅርታ የተግስት መንፈስ በማዳበር እልፎች የወደቁላትን ሃገር በመዘመር ብቻ ሳይሆን  ቢያንስ  የራሳችንን ፍላጎት በመግዛት የሃገርና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ሃላፊነት ያለበት መፍትሄ ሊኖረን ይገባል።

 

ጊሸይ ጊሻ emai    [email protected]

 

 

 

 

 

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop