ኣስገደ ገብረስላሴ (መቀለ)
14 / 03 / 2010
——————————–
የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ጭንቀት የተሞሏበት እና ኣንድ ኣንድ ማእከላይ ኮሚቴ ታመናል ብለው ወደ ኣመሪካ የሸሹ ፣ታመምን ብለው ተደብቀው በሰው ቤት የሚተኙ ፣የስብሰባ መድረክ ረግጠው የወጡ ( የሸሹ ) ፣ በስብሰባ ውስጥ ገብተው የሚጣሉ ፣ በኣጠቃላይ ስብሰባው ጠብ ፣መናናቅ ፣በቂም በቀል ብድር መማላለስ የተሞሏበት ሆኖዋል ። ከነዛ ምክንያት እየፈጠሩ የሚወጡ ፣ኣንድኣንድ የውስጥ ኣዋቂዎች እንደነገሩን ፣
1ኛ ብርሃነ ኪዳነማርያም (መራት) ታመምኩ በማለት ኣመሪካ መግባቱ ተሰማ ።
2ኛ በየነ ሞኩሩ በመሱና ተባላሽታሀል የሚል ከባድ ሂስ ከተሰጠው በኃላ በተጨማሪ ከደብረጽዮን በመድረክ ላይ በተደጋጋሚ ስለተጣሉ ከመድረክ በህመም ምክንያት በመፍጠር ወጥቶ ከቤቱ ውጭ በጓዶኞቹ ቤት ተኝቶ ተገኝቶ ተለምኖ ወደ ሰብሰባ ገባ ።
3ኛ ኣዜብ መስፍን በሙሱና ተባለሽተሻል ስለተባለች ሁለተኛ ኣባይ ወልዱ በጸረ ዲሞክራሲ ፣በትግራይና በገንደር ግጭት ምክንያት ስለሞቱት የትግራይ ተወላጆች ፣ስለወደመ የህዝብ ሀበት እና ስለግጭቱ በዋናነት ኣባይወልዱ ተጠያቂ መሆኑ ስለተነገረው ፣ በትግራይ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠር የህወሓት ኣባል ከኣባልነት በመፍረሱ ፣ቡዙ የመንግስት ሰራተኛ በኣባይ ወልዱ ጸረ ዲሞክራሲ ምክንያት ከክሉሉ በሙሉ ስለወጡ በማድረጉ ፣ የትግራይ ህዝብ የፍትህ ግልጋሎት የህግበላይነት የማህበራዊ ኣገልግሎት ባለማግኜቱ ፣ በክልሉ የለለ የልማት እድገት የውሸት ዳታ በማቅረቡ ከባድ ሂስ ስላኣረፈበት ።ኣዜብ መስፍን እንደ ኣባይ ያለ የመለስ ረኣይ ስትራተጂ እና ፖሊሲ ያስፈጸመ ኣባይ በሆነ መስፈርት ሂስ ማረፍ የለበትም ብላ ስለተጣበቀች ከተሰብሳቢዎች ቡዙ ዘለፋ ስለደረሰባት ፣ ስለኤፈር ኣማራር ውድቀት ስላብጠለጠሏት ክብሬን ተነካ ብላ ከመድረክ ከወጣች በኃላ ከቀናት በኃላ በጀነራል ሳሞራ የኑስ ኣስታራቂነት ይቅርርታ ጠይቃ ልትመለስ ተደርጎ ስትመለስ ፣በደብረጽዬን ገብረሚካኤል እና ቡዱኖቹ ፣ኣዜብ መስፍን የድርጅታችን መተዳደሪያ ደንብ ረግጣ ስለወጣች ኣትመለስም ። ካሁን በፊትም የህዋሓት ማእከላይ ኮሚቴ ኣንጃዎች የፓርቲው መተዳደርያ ደንብ በመጣሳቸው ነው። የተባረሩ ፣
በመሆኑም ኣዜብ መመለስ የለባትም በማለት ከኣቋማቸው ኣልተቀየሩም በመጨረሻ ኣዜብ በድምጽ ኣብላጫ ይቅርታ ጠይቃ በመድረኩ ገብታ በሂስ እየተመታች በጭንቀት ውስጥ ትገኛለች
4ኛ ኣለም ገብረዋህድ ፣ ኣዲስኣለም ባሌማ ፣ሚኪኤለ የኣክሱም ዞን ኣስተዳዳሪዎች በከባድ የሙሱና ብለሽት ከባድ ሂስ እያረፈባቸው ይገኛል ። በተለይይ ቡዙሀብት በምዝበራ እንደኣካማቹ ተነግሮዋቸዋል ።
5ኛ ኪሮስ ቢተው ፣የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ በትግራይ የለለ የእርሻ ምርት የውሼት ዳታ በማቅረብ ።የተፈጥሮ ደን ሽፋን የመስኖ ልማት ሽፋን የውሼት ዳታ መሆኑ ኪሮስን ቢተው የሚነካ ሂስ ኣርፎቦታል ። ይህ እንዳለ ሆኖ ኪሮስ ቢተው የወሼት ልማት ዳታ በማቅረቡ ፣እርዳታ ይሰጡን ለነበሩ ለጋሽ ኣገሮችም የእርዳታ እጃቸው እንዲስቡ ኣድርጓል በማለት ከባድ ሂስ ኣርፎቦታል ።
6ኛ እነዛ ኣንጋፋ ሙሶኞች የህወሓት ከፍተኛ ኣማራር የነበሩ ገና ሂስ እስኪሚያርፍባቸው በሩቅ ሆነው ምንም ገበና እንደሌላቸው ኣመካሪዎች ፣ ኣስተያዬት ሰጭዎች ሆኖው ጸፍ ጭልጥ ብለው ቃላት እየወረወሩ ይታያሉ ።እኒህ ኣዛውንቶች ኣሁን ጭዋ እና ንጹሃን ይምሰሉ እንጅ ኣስቀድመው የዚህ ሀገርና ህዝብ ኣንጡራ ሀብት ዘርፈው ዘርዘራቸው በሁለገብ ያቋቋሙና ልጆቻቸው ያዳላደሉ ናቸው ።
7 በ1993 ዓ / ም ከህወሃት ተገንጥለው የወጡ ማእከላይ ኮሚቴ የነበሩ ገብሩ ኣስራት ፣ስዬ ኣብርሀ ፣ኣውዓሎም ወልዱ ሲቀሩ ሌሎች ማ / ኮሚቴ ነበር ይመለሱ ኣይመለሱ ክርክር ተደርጎ ኣባይ ወልዱና ጥቂት ቡዱኖቹ ሲቃወሙ ሌሎች ግን ተስማምቷል ።
በመጠቃል የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በኣሁኑ ጊዜ በውስጡ ኣንድነቱ ተበጣጥሶ ታክሞ ሊድን በማይድንበት ሁኔታ ነው የሚገኜው ።በኣሁኑ ጊዜ እነዚህ ፍጡራን ለሀገርን ህዝብን ፍተህ ሰላም በማሰብ ኣቅማቸው እደተጨረሰ ኣምነው ስልጣናቸው ለማህበረሰብ ኣስረክበው ፣ገበና ካላቸው ወደ ህዝብ ቀርበው ፍረደን እንደማለት ፈንታ ከስልጣን ጋር የሙጡኝ ብለው መያዝ ኣያዋጣቸው ።
ከላይ የተቀመጠው የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ከተባላሸው ስብሰባ ተያይዞ በመቀለ ከተማ ካሁን በፊት ያልነበረ የጸጥታ ሀይሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የድህንነት ፣ የናሳ ከኖሬሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በስብሰባው ኣካባቢ እያንጃበቡ ከባድ ጥበቃ እያደረጉ ይገኛሉ ተራ የስለላ ወይ ድህንት ሃይሎች ፣ፈደራል ፓለስ የትግራይ ልዩ ይል በሙሉ መቀለ ከተማ ነው ያለው ። የመከላከያ ሀይልም ከወትሮው የተለዬ ኣለ ።