—–
ብአዴን የአማራ ብሄረተኛነትን ሲዋጋ መክረሙን እና ስኬታማ ስራ ማድረጉንም 37ኛው አመት በአሉ አዲስ አበባ መናገሩን በማስመልከት ከዚህ ቀደም የዘጋነው አጀንዳ ላይ አንድ ድንጋይ ለመወርወር ያህል የሚከተለው ጽሁፍ ሰፍሯል፡፡
—–
ስለብአዴን ስንጽፍ ከድምዳሜ ተነስተን ነው፡፡ ብአዴን አማራን የማይወክል፤ የአማራነት ስሜት የሌለው፤ ለአማራ ጥላቻ እንጅ ፍቅር የሌለው፤ የወያኔ-ትግሬ ጭቃሹም ነው፡፡ ከዚህ መደምደሚያ ተነስተን ወደዝርዝሩ መሄድ ነው እንግዲህ፡፡ ብአዴን ወያኔ-ትግሬ በአርአያና በአምሳሉ የፈጠረው ነው፡፡ ይህ ፍጡር ከፈጣሪው ትእዛዝ፤ ፍላጎት፤ ፈቃድና ስሜት ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ በመልክም፤ በግብርም ፈጣሪውን ይመስላል፡፡ ከፈጣሪው ከተለየማ ምኑን ፍጡር ሆነው! የፍጡሩን ብአዴንን ሁኔታ ለመረዳት በቅድሚያ የፈጣሪውን ወያኔ-ትግሬን ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ወያኔ-ትግሬ አፈጣጠሩ አማራን በመጥላት ነው፡፡ ከተፈጠረበት እለት ጀምሮ ለአማራ የማይበርድ ክፉ ጥላቻ ይዞ የኖረ እና አሁንም ይሻለዋል ሲባል እየባሰበት የመጣ ነው፡፡ አፈጣጠሩ አማራን አጥፍቶ ታላቋ ትግራይን መገንባት ስለሆነ አማራ እስካልጠፋ እና ያች የህልም አገርም እስካልተገነባች ድረስ ጥላቻውና ክፋቱ አይለቀውም፡፡ ከዚህም በመነሳት በአማራ ላይ ይህ ነው የማይባል ግፍ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ አማራውን መጥፋት ያለበት የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ነው ብሎ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ እስካሁን በትግል ሰነዳቸው እንዳሰፈሩት ያሏትን ነገር መሬት ጠብ ሳትል በጠራራ ጸሀይ ፈጽመዋታል፡፡
ይህ ወያኔ-ትግሬ ታዲያ ይህንን የጥፋት ተልእኮውን ለማሳካት ይረዳው ዘንድ በአማራ ስም የሆነ ድርጅት ማቋቋም ነበረበት፡፡ የሻእብያ፤ የወያኔ ቅሪቶችን እና አማራ ጠል የሆኑ ሌሎች ብሄረሰቦች አባላትን ሰብስቦ በአመራር ደረጃ አስቀመጠ፡፡ እንደገናም በልዩ ልዩ ጸረ ማህበረሰብ አመላቸው የተገለሉትን ጠንቅ ሰዎችን ሰብስቦ የእነዚህ ተደራቢ አድርጎ አዋቀራቸው፡፡ ወያኔ-ትግሬም እነዚህን የሰበሰባቸውን ሰዎች የክፋትና የጥላቻ እስትንፋስ እፍ አለባቸው፡፡ በዚህም የፈጣሪያቸውን ባህርይ ተላብሰው ቀሩ፡፡ ስለዚህም የሚያደርጉት ሁሉ ፈጣሪያቸው የሚፈልገውን እና የሚያስደስተውን ነው፡፡ ብአዴን ማለት ባጭሩ ለራሱ የቆመና ለራሱ አላማ የሚኖር ሳይሆን ለወያኔ-ትግሬ የቆመ ጉዳይ አስፈጻሚ ነው፡፡ ዋና ስራውም የወያኔ-ትግሬን ጸረ አማራ ጉዳይ ማስፈጸም ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የወያኔ-ትግሬ ፍላጎቶች፤ እቅዶችና ትግበራዎች በብአዴን በኩል ተፈጻሚነት ያገኛሉ፡፡ እስካሁን ድረስ ራሱ ብአዴን በአማራ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍ ፈጽሟል፡፡ በወያኔና ሌሎች ግብረአበሮቹ አማካኝነት በአማራ ላይ የደረሰውን በደል አልተቃወመም፤ አላስቆመም፤ አላወገዘም፤ ወይም አሜን ብሏል፡፡
ባጭሩ ብአዴን ለአማራ ምንም ማለት እንዳልሆነ ይልቅም ጠላት ወይም የጠላት ጉዳይ አስፈጻሚ እንደሆነ ለማሳያነት ዋና ዋናዎቹን እንያቸው፡-
አማራው እንዳይነሳ፤ የሚደርስበትን በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንዳያውቅ እና እንዳይመክት አደንዝዞ እና ሸብቦ ያዘ፡፡ ስለዚህ ብአዴን ለወያ-ትግሬ አማራውን አፋኝና አሞኝ ቡድን ነው፡፡ በስም የአማራ ወኪልነት በመቀመጡ የህዝቡን ስነልቡና በውሸት በመስለብ አደንዝዞ አስቀመጠው፡፡ እስካሁን የአማራ ታሪክና ማንነት ላይ ያልተቋረጠ ዘመቻ ሲካሄድበት አንዲትም ቀን ተቃውሞ መግለጫ እንኳ አላወጣም፡፡ ታሪኩ በውሸት ሲፋቅና ሲደረት ሲደለዝ ምንም ትንፍሽ ብሎ አያውቅም፡፡ የአማራን ታሪክና ማንነት የማይጠብቅ ድርጅት በምንም መልኩ የአማራ ጠበቃ ሊሆን አይችልም፡፡
እስካሁን ድረስ በአባል ድርጅቶች (አቻ ድርጅቶች) አማራ ሲሰደብ እና ሲወገዝ አንድም ቀን ለምን ብሎ ጠይቆ አያውቅም፡፡ ከሌላ አካባቢዎች በግፍ የተገደሉ፤ የተዘረፉ፤ እና የተፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ ጉዳየ ነው፤ ህዝቤ ናቸው ብሎ ተከላክሎ ወይም ነቅፎ ወይም ረድቶ አያውቅም፡፡ ይህ ነው የሚባል የተግባር እርምጃ እንዲወሰድ አላደረገም፤ በቃል እንኳ አውግዞ መግለጫ ሰጥቶ አያውቅም፡፡ ከዛ ይልቅም ከራሱ ክልላዊ መንግስት ውጭ ያለው አማራ ወራሪና ነፍጠኛ በመሆኑ እንደማያገባው ሲሳለቅ ነው የሚስተዋለው፡፡ ይህም ከአማራ ክልል ውጭ የሚኖሩ አማሮች ወኪል አለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡ በዚህም ስሌት ብአዴን ወያኔ-ትግሬነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የአማራ ክልል ወኪል እንጅ የአማራ ወኪል አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ በሌላ አገላለጽ ከክልላቸው ውጭ የሚኖሩ አማሮች ተወካይ ስለሌላቸው በገዛ አገራቸው መጻተኛና ስደተኛ፤ መንግስት የሌላቸው ፍጥረቶች ናቸው ማለት ነው፡፡ ብአዴን የአማራ ክልል እንጅ የአማራ ተወካይ ባለመሆኑ (የክልል ውክልናውን እንኳ እንዲሁ ውክልና ብለን እንውሰደው ተብሎ ነው) ከክልሉ ውጭ የሚኖረው አማራ አገር አልባ፤ መንግስት አልባ፤ ከርታታ ነው፡፡ ከዚህም ተነስተን አማራ ተወካይ ስለሌለው ነው ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጸምበት እንላለን፡፡ ስለዚህ ብአዴን የአማራ አይደለም፤ አማራም ተወካይ የለውም፡፡
በአማራ ክልል ያለው ህዝብ በወያ-ትግሬ ኢኮኖሚያዊ ሴራ ሳቢያ በአለም ቁጥር አንድ ደሀ ሲሆን ብአዴን ያደረገው አንዳች ነገር የለም፡፡ የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለመለወጥ ምንም አልፈየደም፡፡ የድህነቱ መጠን መክፋቱን አይደለም ሊገልጸው ይቅርና በተቃራኒው በውሸት ሪፖርት እንዳደገና እንደበለጸገ ያስመስላል፡፡ ይህም ፈጣሪው ወያኔ-ትግሬ ህዝቡን እያራቆተ የራሱን ኪስ በማድለብ ነገር ግን ህዝቡ እንደበለጸገ እያደረገ የሚያወራው ፕሮፓጋንዳ አንዱ አካል ነው፡፡ የክልሉ የተፈጥሮ ሀብት በየጊዜው እየወደመ ሲመጣ ምንም መከላከያ ያላደረገ ድርጅት ነው፡፡ በደርግ ጊዜ የተተከሉ ዛፎችና ጫካዎች በወያኔ-ትግሬ እየተመነጠሩ ሲጋዙ በተቆረጡበት ቦታ እንኳ እንደገና እንዳያቆጠቁጡ ሆነው ነው፡፡ አይደለም የተፈጥሮ ሀብትን ማልማት ይቅርና ጫካ በተመነጠረበት ቦታ እንኳ መልሶ እንዲያቆጠቁጥ ያላደረገ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ሀብትን የመከላከልም ሆነ የማልማት ስራ አልሰራም፡፡ ይህም የወያኔ-ትግሬ አማራን የማራቆትና የማደህየት ተልኦ አንዱ ክፍል ነው፡፡
ክልሉ እጅግ በጣም አነስተኛ የመንገድ ትስስር ያለው ነው፡፡ ይህም ህዝቡ ለጤናውም ሆነ ለንግድ ወይም ለትምህርት ወደከተማ ማእከላት ቶሎ መድረስ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ለምሳሌ ያህል በጎንደርና ሸዋ ብዙ ወረዳዎች መንገድ ጨርሶ የሌለባቸውና በመሰላል የሚኬድባቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ ቦታዎች ነዋሪ በተለይ ምድሩ ተራራማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የሚገኝ እና ከአለም ህዝብም ከኢትዮጵያ ህዝብም ፈጽሞ የተገለለ ነው፡፡ ብአዴን ለዚህ ምንም ነገር ሲደርግ አልታየም፤ አላደረገምም፡፡
ወያኔ-ትግሬ ሲሶውን ጎንደር ወደትግራይ ሲከልል እና የተቀረውን ለሱዳን ሲሸጥ አልተከላከለም፡፡ ከጎጃም ቆርጦ አንድ ክልል ብሎ ሲፈጥር፤ የወሎን ሩብ ወደትግራይ ሲከልል፤ ሸዋን ቆራርሶ አንድ ዞን ብቻ ሲያስቀራት:: የአማራ ታሪካዊ ቦታዎች፤ ርስት ጉልቶች በጉልበት ሲወሰዱ በመከላከል ፋንታ አንዳንድ የብአዴን አባላት የእኛ አይደሉም ብለው እንደሚከራከሩ አውቃለሁ፡፡ አንድ ድርጅት የሆነ ህዝብ ተወካይ ነኝ ካለ የዛን ህዝብ ንብረት መጠበቅ አለበት፡፡ ብአዴን ግን ይህንን አላደረገም፡፡ ስለዚህ አማራ በወያኔ እጅ እንጅ በራሱ ልጆች አይደለም፡፡ ወይም ብአዴን የወያኔ-ትግሬ ነጭ ለባሽ እንጅ የአማራ ወኪል አይደለም፡፡ አማራው ከስራ ሲባረር፤ የቅጥር አድሎ ሲፈጸምበት፤ እድገት ሲከለከል ጠበቃ የሚሆንለት እና የሚከራከርለት አካል የለውም፡፡ ብአዴን እስካሁን እንዲህ አይነት ችግር ለገጠማቸው አማሮች ምንም ነገር አላደረገም፡፡ ስለዚህ የወያኔ-ትግሬ እንጅ የአማራ ወኪል አይደለም፡፡
የሌላ ክልሎች ትናንሽ መንደሮች ሳይቀሩ ኤሌክትሪክ አላቸው፡፡ የአማራ ግን አይደለም የገጠር መንደሮች የገጠር ከተሞች የላቸውም፡፡ የአማራ ህዝብ በጨለማ ውስጥ ነው ብሎ ደፍሮ መናገር ይቻላል፡፡ ይህም ብአዴን ለአማራ ህዝብ ምንም እንደማይገደው ያመለክታል፡፡ የአማራው ሴት ልጆቹ በድህነት ብዛት ወደአረብ አገርና ወዘተ እየተሰደዱ ክብራቸውን አጥተው ሲማቅቁ የብአዴን አለሁላችሁ ደምጽ የለም፡፡ ይህንን ለመከላከልም ምንም ነገር አያደርግም፡፡ ስለዚህ ለአማራ አልቆመም፡፡ ከሁሉ ከሁሉ ደግሞ ወጣቶችን እያነቀ ለወያኔ-ትግሬ እስር ቤትና ስቃይ የዳረጋቸው ብአዴን ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁሉ ተመዝኖ ቀልሎ የተገኘው ብአዴን የወያኔ-ትግሬ እንጅ ከአማራ ጋር አንዳ መልካም ግንኙነት እንደሌለው አረጋግጠን እንዝጋው፡፡
ምስጋናው አንዱዓለም