ሸንቁጥ አየለ
——————————
የወገኔ ልጆች ተጨንቀዉ እና ተጠበዉ ጣናን እንዴት ማዳን እንደሚቻል በጅጉ ሲያንሰላስሉ እና ሲጽፉ አስተዉላለሁ::እኔም እንደወገኔ ልጆች ዉስጤን የሚበላዉ ጉዳይ ነዉ::እናም ይሄ የወቅታዊ ጉዳይ ላይ በግራም ቢታሰብ ወይም በቀኝም ቢንሰላሰል ሁሉም ድምዳሜዎች የውሚወስዱት ወደ አንድ መስመር ላይ ነዉ::
ከዚሁ ጣናን ከመድረቅ የማዳን ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከአማራ ክልል ዉጭ ያለዉ ማህበረሰብም በዘመቻዉ ጋር መሳተፉን በማስመልከት በርካታ ሀሳቦች እየተነሱ እየተጣሉ ነዉ:: በተለይም የኦሮሞ ወጣቶች ወደ ጣና መንቀሳቀስ በርካታዉን ኢትዮጵያ በደስታ አስፈንድቆታል:: ይሄም መልካም ተግባር ነዉ::ጣና የኢትዮጵያ ነዉ::ኢትዮጵያም የኦሮሞ ናትና ጣናን ማዳን ይገባናል ያሉት ወጣቶች ወይም እንዲህ የወሰኑት ሀላፊዎች ጥሩ አድርገዋል::
እናም ከጣና እስከ ኢትዮጵያ የሚፈስ የጥያቄ ጎርፍ በኢትዮጵያዉያን ህዝነ ልቦና ዉስጥ እየፈሰሰ ጣናን እንዴት ማዳን ይቻላል የሚለዉ የዋህ መሰሉ ጥያቄ ወደ ትልቁ የፖለቲካ ወንዝ ይዞን ይፈሳል::
እናም ጥያቄዉ እንደ ዋዛ ይጀምራል:: ጣናን እንዴት ማዳን ይቻላል? ወያኔ የተባለዉ አረም ከኢትዮጵያ ሳይነቀል የጣና አረም ተነቅሎ ጣና ሊድን ይችላል?
ዝርዝር ዉስጥ አልገባም::ዋናዉን ነጥብ ብቻ መግለጽ እፈልጋለሁ እንጅ:: ጣናን ፈጽሞ ለማድረቅ ወያኔ የሚፈልግበት ብዙ ምክንያት አለዉ::ወያኔ ጣና ሲደርቅ እያዬ ብዙ ጊዜ ዝምታን ሌላ ጊዜ በሎሌዉ ብአዴን በኩል ዘመቻ መሰል የማላገጥ ስራን የሚያከናዉነዉ የአዞ እንባ አነባብ ስለሚያዉቅበት ነዉ:: እናም ወያኔ የመጨረሻ ግቡ ጣናን ማድረቅ: ኢትዮጵያን ድምጥማጧን ማጥፋት: በቀጣናዉ አቅም ያላቸዉ ሀገር ሊሆኑ ይችላሉ ብሎም ወደፊት ነጻ ሀገር ተብላ የምትመሰረተዉን የትግራይን ሀገርነት ይቀናቀናሉ ብሎ የሚያስባቸዉን ክልሎችን ምንም መሰረት እንዳይኖራቸዉ አድርጎ በልዩ ልዩ መልክ ከምድረ ገጽ ደብዛቸዉ እንዲጠፋ ማድረግ ነዉ::
በአጭሩ የጣና አረም ተነቅሎ ጣና እንዲድን ከተፈለገ የኢትዮጵያ አረም ወያኔ መነቀል አለበት:: በመሆኑ የአማራ እና የኦሮሞ ወጣት በዋናነት ሊያተኩርበት የሚገባዉ ነጥብ ወያኔ የተባለዉን አረም ከኢትዮጵያ ነቅሎ ሀገሪቱን መረከብ ላይ ነዉ::