September 16, 2017
11 mins read

አመረረ −ልቤ

አመረረ  ልቤ ከፋው እያደረ

 ሃገር  ተሸራርፎ ህዝቤም እያለቀ

 

ማነህ አንት ፥ እስኪ ልጠይቅህ

ከማንስ ተፈጠርክ ፥ ከወዴትስ ፈልቅክ ፥

                       

                       ማንነትክን የጣልክ  ፥  ራስክን ያራከስክ

                       አቅልለህ የጣልካት ፥  ማተብክን የበጠስክ ፥

 

ወኔውም የራቀህ ፥ እራስህን የረሳህ

ብር ብር  ብለህ ፥ ዕርስትን  ያፈለስክ ፥

 

                 ኢትዮጵያየ ፥ የኩራት አሻራ

                 የነፃነት ፋና ፥ የማንነት ዳፋ ፥

 

የደግነት ምድር ፥ የጀግኖች መፍለቂያ

አልደፈርም ባይ ፥ የትዕግስት መለኪያ ፥

 

              አትነካ፥ ካልነኳት  

              ከደፈሯት፥ አይጣል ፥

 

የወረስከው ወኔ ፥ ያስታጠቁህ ዝናር

የአያቶችህ  ገቢር ፥ ያላበሱህ ትብዕል ፥

 

           ያሽከሙህ አደራ ፥ የተውልህ ቅርፁ

           ዳፋ ና ደንበሩ ፥ ኮረብታ ና ወንዙ ፥

 

በልቦናህ ይስረፅ ፥ አታድርገው ከንቱ

የሰው ልብስ አያደምቅ ፥ ቢኳኳሉ  ቢያምሩ ::

            

            አዝማች

 

ዘመን ተለወጠ ፥ ሃገር ሆነ ዋዛ

ምድሯም ተሸራርፋ ፥ ጊዜው አቅል አጣ ፥

        

         ኑሮው  እንቆቅልሽ ፥ ሁከት በመሬቷ

         ባዕድነት ገዘፎ  ፥ መተማመን ጠፋ ፥

 

ስደት ልብስ ሆነ ፥ መዳያ  አሸለመ

መዘዙ ሳይጤን ፥ ስንቱ መና ቀረ ፥

         

         ለፍቶ  ከማስነ ፤ እጁን ያረዘመ

         በአቛራጭ ከፍ አለ፥ ነጠቀ ከበረ ፥

 

ኧረ ቤት ይቁጠረው ፥ ፍትህ ያጣ ወገኔ

ሃቅ  ተመስጥሮ ፥ ኑሮው  በትካዜ ::

 

               አዝማች

                 

                 እስኪ ላጠንጥነው ፥  ላስታውሰው የጥንቱን

                 ያ መልካሙን ዘመን ፥ ትዝታ እና ሀሴቱን ፥

 

የእብሮ መኖር ትብዕሉን  ፥ የዝምድና ወጉ

የአባት ክንድ ድጋፉ ፥ የእናት ጓዳ ስንቁ ፥

 

                  ወንድም ለመከታ ፥ ሞገስ እና ክብሩ

                  እህቴ  እጉራሿቷ ፥ የዕራብ የጥማቱ ፥

             

ጓደኛ የጥቃት ፥ የችግር ደራሹ

የአገር ልጅ እልኝታ ፥  መካሪ እስታዋሹ ፥

 

       ሀ ሁ ፊደል ቆጥረን  ፥አንድ ልብስ ተጋርተን

       መንገድ የጋራችን ፥  ተጓርሰን ተካፍልን ፥

 

              በአንድነት ስንነጉድ ፥ ስንቱ እንዳልቀናብን

              ክፉ ቀን መጣና ፥ ይሄው ተራራቅን ፥                       

            

የእፀፅ ድሪቶ ፥  የነገር ባዘቶ

የእድልኦ መርዘን ፥ የዘር ክፍፍሎ ፥

 

              የስደት እባዜ ፥ በላያችን ሰፍሮ

              ኑሩአችንም አረግነው ፥ እንደ ጀብድ ተቆጠሮ ፥

 

ጮቤ ተረገጠ ፥ ድግስ ተደገሰ

ላይመለስ ሲሄድ ፥ ከትብቱ እየራቀ ::

             

            አዝማች

 

               እህት  መቀነቷ ፥ ሁሌ  አለሁ ባይዋ

              ዕርቃ ናፍቃሃት ፥ መላውን ዘይዳ ፥

 

ከጎንህ ልትከትም ፥ አፈፍ ከቀየዋ

በርሃ አቌርጣ ፥ ተርባ ተጠምታ ፥

 

                ጥቃቱን ተጋርጣ ፥ በሾሁ ተወግታ

                ከአውሬው ተታግላ ፥ ደረስኩ መጣሁ ብላ ፥

 

የባህር ዕራት ሆነች ፥  ቀረች ከሃይቅ ሰምጣ

ወገን እንደራባት ፥ ነፍሷም ምድሯን ሽታ ፥

 

 

                    ጋሻህ ልሁን ብሎ ፥ ወንድምህ አርዮ

                   ከሃገር ሃገር ማስኖ ፥ ያላየውን አይቶ ፥

 

 በሳህራ በርሃ ፥ ተቀቅሎ ከስሎ

 ጓዶኞቹን ቀበሮ ፥ ዕንባው ተⶰርግጎ ፥

 

                      ቀን ዕድል ሰጥቶት ፥  ከጎነህ ተስጦ

                     አብረህ ተያያዝከው  ፥ የባዕድ ሃገር ኑሮ ፥  

               

ተመስገን እንበለው  ፥ የአምላክነን ስራ

አንዱነን ተነጥቆ ፥ ሌላው ሲያንሰራራ ፥  

 

                 ተስፋንም  ሰንቆ ፥ ወላጅ እያወሳ

                 ዘመድን ሃገርን ፥ ለመካስ ሲጓጓ ፥

 

በባዕድ ሃገር ደግሞ ፥  አለ ሌላ ሃበሳ

መረገጥ መዋረድ ፥ መወርወር ከሜዳ ፥

             

                በትዝታ ናፍቆት ፥ እህህ እንዳሉ

                በደዌ መወጋት፥ ናላ መዛወሩ ፥

 

በአዙሪት ተሰቅዞ ፥ ሲዳክሩ ሲጦዙ

ማለፍም ይመጣል ፥ ካሰቡት ሳይደርሱ ፥

      

                   ኧረ ሚስጥር ንግርት ፥ ሞቴን ያሳምረው

            እህት ሳትቀምስ አፈር ፥ ወንድም የአሞራ ዕራት ፥  

 

እርርም ኩምትርም ፥ የዕድሜ ልክ ፀፀት

እናት አባት ወልዶ ፥ በቁም መና መቅረት ፥

     

        አዝማች

 

            ወገኔ እስኪ አድብ ፥አገናዝብ በፅኑ

            የሰው መድኃኒቱ ፥ አንተው በመሆኑ ፥

 

እህትህን ደገፍ ፥ ወንድምህን ቀና

ዙሪያህንን ቃኘው ፥ ማን አለን ያለኛ ፥

 

                  ሰው ካልተጋገዘ ፥ በቁም በህይወቱ

                  ካለፈ በኋላ ፥ ፖርሳ መጎርጎሩ ፥

 

ፀጉርነን መንጨቱ ፥ ፅንባ ማዥጎድጎዱ

ለልታይ ካልሆነ ፥ ለሟች እይሆን ስንቁ ፥

 

        ወንድሜ እህቴ ፥ የሃገር ልጅ ማሳናው

        ከህሊናህ ታረቅ ፥ ዙሪያህነን ቃኘው ፥

 

ሃገረም ሃብት ናት ፥ ዘብም ከቆሙላት

አይሻል ብለህ ነው ፥ መንገድ ላይ ከመቅርት ፥  

 

             ክቀየህ ከምድርህ ፥  እግርህ አፈፍ ሲል

             ቀድመህ አንሰላስል ፥ ታደገው ህይወትክን ::         

               

           አዝማች

 

እዮሃ አበባየ ፥መስከረም ጠባየ

እስኪ ቃል እንግባ ፥ ለእማ ኢትዮጵያየ  

 

                የድሮው ቀንደልሽ ፥ ይታይ ያንሰራራ

                መዋረድ ስደቱ ፥ መራራቁ ያብቃ

 

ላይ ያለው ልብ ገዝቶ ፥ ግፉነን አቅቦ

ለህዝብ ለሃገር ይስራ ፥ መቧጠጡን ትቶ ፥

 

                  የሃገርን ቃል ኪዳን ፥ ገለል ያደረገ

                  እርጉም ከመ አሪዎስ ፥ እምየን የካደ ::

 

                      አዝማች

 

                               ከተዘራ አሰጉ

 

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop