September 2, 2017
11 mins read

ምሁራን በእባብ ተሸውደው የዕፀ በለስ ፍሬ መግመጥ እሚያቆሙት መቼ ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected])

ድንጋይን እሚያናግረው ውሀ ነው፡፡ በመላ አገሪቱ እንደ ውሀ ደም ያፈሰሱ ነፍሰ ገዳይዎች “የኢትዮጵያ ከፍታና ፍቅር ቀን” ማወጃቸው ድንጋዩን ሳይቀር እያናገረ ነው፡፡ እኔን እሚያናግረኝ ግን የደም አፍሳሾች የተለመደ የዶሮ ብልጠት ሳይሆን እነዚህ የዶሮ ብልጦች “እ ኩኩ..ኡ…” ብለው እየጮኹ የሕዝብን ጆሮ ሲያመግሉ “ኩኩ..ኡ..አው ኡኡ…” ብሎ አስተጋብቶ ከጎናቸው እሚቆመው “ምሁር”ና ዜጋ ነው፡፡ እንኳን ምሁር ጦጣስ በዶሮ ብልጦች እንዴት አርባ ሶስት ዓመታት ይታለላል?

ስለመታለል ቅዱሱ መጽሐፍ ሲያስተምር “ዘፍ፡፫፡፩ እባብም ከምድር አውሬ ሁሉ ተንኮለኛ ነበረ” ይላል፡፡ ወረድ ብሎም እባብ ሔዋንን አታሎ የተከለከለውን ፍሬ እንዳስበላት፤ አዳምንም እንድታሳስት እንደመከራት ያስተምራል፡፡ ከምድር አውሬዎች ሁሉ እባብ  ተንኮለኛ የነበረውን ያህል ለገሰ ዜናዊ በምድር ካሉ ሰዎች ሁሉ ተንኮለኛ ነበረ፡፡ እባብ አዳምና ሔዋንን በበለስ ፍሬ እንዳታለለው ለገሰ “አማራ የጭቁን ሕዝቦች ጠላት” በሚባል የደደቢት ዕፀ በለስ በአማራ ያቄሙትን ምዕራባውያንንና ትሉል “ጭቁን ብሔረሰቦችን” አታሎ በአማራ አዘመታቸው፡፡

ማታለሉ የተሳካለት ለገሰ ምዕራባውያንን ከጀርባው የ”ጭቁን ብሔረሰቦች”ን “ወኪሎች” ከፊት አሰልፎ  አማራን ሕገ መንግስት ተመንደፍ፣ ከቤተመንግስት፣ ከወታደራዊና ደህንነት መዋቅር፣ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሌሎችም ቁልፍ ቦታዎች አገለለው፡፡ ሐብቱንና ቅርሱን ዘረፈው፡፡ ከአርባ ሶስት ዓመታት በፊት በወልቃይት የጀመረውን የአማራ ፍጅትና ሥቃይ በመላ አገሪቱ አስፋፋው፡፡ አማራ ከነነፉሱ በደኖ ገደል ተወረወረ፡፡ በዚህ የገደል ውርወራ የልጅ አባታቸው ከነነፍሳቸው ገደል ተጥለው፤ ከሃምሳ በላይ ታጣቂዎች በየተራ ደፍረዋቸው የአባለ-ዘር በሽታ መግል እንደ ጅረት ከማህፀናቸው የፈሰሳቸው የአስራ ሶስት ልጆች እናት እንዳየሁት እኔ ብዙ አደባባይ ያልወጡ ግፎች የተመለከተ ይኖራል ብዬ እገምታለሁ፡፡

ገደል ከመወርወርና እንደ ወልቃይት አማሮች ጉድጓድ ውስጥ ከመሰቃዬት የተረፉት በቤታቸው እንዲመክኑ፣ በወህኒ ቤተ እንዲኮላሹ፣ እንዲጠበሱ፣ እንዲቀቀሉና እንጨት እንዲሰደድባቸው ተደረጉ፡፡ የተቀሩትም ሥራና ንብረት የማፍራት ዕድል እንዲነፈጉ፤ ያያቶቸው ደም ከፈሰበት ምድር እንዲፈናቀሉ፤ ባህር አቋርጠው እንዲሰደዱ፤ ሲሰደዱም በማዕበል እንዲሰምጡ፣ በአረምኔዎች እንዲታረዱ፣ ለአረቦች ተሸጠው ባርያ እንዲሆኑ ተደረጉ፡፡

በዚህ መልክ አማራን ያሰቃየው የለገሰ ቡድን በ፲፱የ፺ ዓ. ም ከኢትዮጵያ በዘረፉት የባንክ ገነዘብ፣ ጤፍና ቡና ከሻቢያ አምበሎች ተጣልቶ ጦርነት ሲፈጥር “ሉአላዊነት” የምትባል የዕፀ በለስ ፍሬ ይዞ ብቅ አለ፡፡ በዚች ዕፀ በለስ ምራቃቸው የተዝረበረበ “ምሁራን”ም “የሰፈር ልጆቹን አሳጪዶ የአገሪቱን የባህር መተንፈሻ አፍንጫ የቆረጠና አማራን ገደል ያስወረወረ ቡድን እንዴት የሉአላዊነት ዕፀ በለስ ይዞ እንደ እባብ ተሳበ?” ብለው አልጠየቁም፡፡ ይልቁንም ጥቂቶቹ በሆዳቸው ብዙዎቹም በየዋህነት እንደ ሔዋን ተታለው የሉአላዊነቷን ዕፀ በለስ እንደ አምባሻ ገመጡና የእነ ለገሰ ካድሬዎች ሆነው ቁጭ አሉ፡፡ በካድሬነታቸውም ጀንዲ በሚያካክል የሉአላዊነት ጥሑፍ ሕዝብን እንደ አዳም አሳስተው ሰባ ሺ ወጣቶች በደኖና ሽራሮ እንደ ሙጃ አስጨረገዱ፡፡ አንድ በሉ፡፡

በበባድሜና ሽራሮ ሰባ ሺ ወጣቶችን እንደ ሙጃ ያስጨረገደው የለገሰ ቡድን ሕዝቡን “በሉአላዊነት” ዕፀ በለስ አታሎ በጤፍና በቡና ዘረፋው ጦርነት ከጎኑ ማሰለፉ የልብ ልብ ሰጠውና በ፲፱የ፺፯ ዓ.ም. “ነፃ ምርጫ” የምትል ዕፀ በለስ “እንቁልልጪ” እያለ አሳይቶ ስንቱን ምሁር የቅቤ ሽሮ እንደሸተተው ርሃብተኛ አስጎመጀው፡፡ ስንቱን ፖለቲከኛ በአዲስ ፉንቃ መብላት መጠጣት እንደተሳነው ኮበሌ አነሆለለው፡፡ ይኸንን “በነፃ ምርጫ” ዕፀ በለሰ የነሆለለ ፖለቲከኛም ድምፅ የተነፈገው የለገሰ ቡድን በለመደው ጭካኔ ከርቸሌ አጎረው፤ ድምፁ በመቀማቱ የተቆጣውን ሕዝብም አሳጨደው፡፡ መቶ ሺዎችን አሰራቸው፤ ወጣቶችን ካምፕ አጉሮ በደረቅ ምላጪ ላጫቸው፡፡ ይህንን በብራና የተጣፈ ዘግናኝ ታሪክ ከአምስት ዓመታት በኋላ ለገሰ “ህዳሴ” የምትባል የዕፀ በለሰ ፍሬ “ምሁራን”ን እንደ አምባሻ አስገምጦ ከአእምሯቸው አስፋቀና ከጀርባው አሰለፋቸው፡፡ ለገሰና ቡዱኑ ህዳሴ፣ ዓባይ ግድብ፣ ኩል…ኩል… ብለው አቀንቅነው “አው ኩኩ ኡ… ኡኡኡኡ..” ብለው ሲጮኹ ሕዝብ በነለገሰ ሲጨፈጨፍ ዲዳ የነበሩት ምሁራን ሳይቀር ክንፋቸውን አራግፈው “አ..ኡው..ኡኡኡ” ሲሉ አስተጋቡ፡፡ ወዲያውም “ህዳሴ… ዓባይ… ግድብ …ዓባይ .. የሕዝብ ጉዳይ! ያገር ጉዳይ” እያሉ ተጠቅሎ በማያልቅ ጥሑፍ ስንቱን አታለው ገንዘቡን በቦንድ አስመዘበሩ፡፡ ሁለት በሉ፡፡

በቦንድ ገንዘብ የራሱን የንግድ ድርጅት እንደሚያደልብ፣ ልጆቹን ውጪ እንደሚያስተምር፣ ሰርጉን እንደሚደግስ የሚታወቀው ይህ የለገሰ ቡድን ህዳሴው ከተዘመረ ከአምስት ዓመታት በኃላ ግፍ የበዛበት ወጣት የመኖር ዋስትና ሲጠይቀው  በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወለጋ፣ በአሩሲ፣ በጋምቤላ፣ በኮንሶ፣ በኦጋዴንና ሌሎችም ቦታዎች ረሸነው፤ ወህኒ አጎረው፤ የሜድትራንያንና የቀይ ባህር ቀለብ አደረገው፡፡

የለገሰ ቡድን ግፍና መከራ አፍንጫቸው የደረሰና ትዕግስታቸው የተሟጠጠ የአማራ ወጣቶች አመጡ፡፡ ለመከራ አሳልፈው በሰጧቸው አባቶቻቸው አፍረው የያቶቻቸውን ታሪክ ለመድገም የወሰኑ ቆፍጣና ወጣቶች እንደ አንበሳ አገሱ፡፡ እንደ አያቶቻቸው በውስጥም በውጪም ተከብረው ለመኖር መሰባሰብና መታገል ጀመሩ፡፡ ይህቺን ቁርጠኝነት የተመለከተው የለገሰ ቡድን “የኢትዮጵያ ከፍታና ፍቅር ቀን” እሚባሉ ዕፀ በለሶች ይዞ “ኩኩ አው..ኡ ኡ…” ሲል ጮኸ፡፡ ጩኸቱን የሰሙና ዕፀ በለሶችን እንደ አምባሻ ገምጠው ሕዝብን በማሳሳት የሚታወቁት እንደ ኤፍሬም ያሉ “ሽማግሌዎች”፣ ጳጳሳት፣ አቡኖች፣ ካህናት፣ ዘልዛላ “ምሁራ”ን፣ ዘፋኞች፣ ትያትረኞችና ተላላኪዎችም ” ኩ..ኩ.. አው! ኡ! ኡኡኡ..” ሲሉ አስተጋቡ፡፡ ሶስት በሉ፡፡

በዕፀ በለስ ዝንተ ዓለም ከሚያታልል እባብ ተሞክሮ እንኳን የሰው ልጅ ከእባብ የተጣበቀ ቫይረስና ባክቴርያም ይማራል፡፡ ዕፀ በለሰ ገማጭ ምሁራን እንዴት ከአርባ ሶስት ዓመታት ልምድ መማር ያቅታቸዋል? ምሁር እንደ ኤፍሬም ይስሃቅ እስከመቼ የዕፀ በለስ ፍሬ እንደ አምባሻ ሲገምጥና የሙታንን እርም ሲበላ ይኖራል? የተከለከለ ዕፀ በለሰን ፍሬ እሚገምጡ “ሽማግሌዎች”፣ “ካህናት”ና  ፖለቲከኞች ዓይኖቻቸውን እሚገለጡት መቼ ነው? “ምሁራን”ስ በእባብ ተሸውደው የተከለከለ የዕፀ በለስ ፍሬ መግመጥና የሙታንን እርም መጠቅሸም እሚያቆሙት መቼ ነው?

 

ተመሳሳይ ጽሑፎች

እስከ መቼ ከትል ያነስን ቦንደኞች? http://quatero.net/amharic1/archives/28589

ዓባይን ማን መቼ ይገድበው? https://zehabesha.info/wp-content/uploads/2014/06/Abay.pdf

 

ነሐሴ ሁለት ሺ ዘጠኝ ዓ.ም.

 

 

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop