July 1, 2017
9 mins read

በርግጥ ጠላቶቻችን በዝተዋል ሆዳም አማራውን ጨምሮ ቢሆንም ግን እናቸንፋቸዋለን!!    (አንተነህ ገብርየ)

የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል ይላሉ አበው።እናቴ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ቢሆንም ሌላዋ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር የምጋራት እናቴ ደግሞ ኢትዮጵያ በፔትሮሊየም ዘይት የጠገቡ የአረብ ካፒታሊስቶችና ምዕራባውያን በቀጠሯቸው አገር በቀል ቅጥረኞች እያነሰች እንደ ዳቦ እየተቆረሰች ስትሄድ፤እውነተኛው የሀገሪቱና የጀግኖች ልጆቿ ታሪክ እየተፋቀ፤የሀገር ሀብት እየተዘረፈ፤ልጆቿን በጠራራ ጸሐይ ግንባር ግንባራቸውን በአልሞ ተኳሽ እየመቱ ሲገድሉ፤የሀገሪቱ ቅርሳቅርሶች ተዘርፈው ባህር ማዶ ሲሻገሩ፤ዜግነት በደረጃ ተመድቦ ትግሬ 1ኛ ደረጃ ለትግሬ ያጎነበሰና እንባ ያበሰ በ2ኛ ደረጃ 3ኛ ይህን ፋሽስታዊና ወራሪና ተስፋፊ ቡድን መውረድ አለበት በማለት የሚፋለሙ የዜግነት መብታቸው ተገፎ እጣ ፈንታቸው ስደት፤ሞትና እሥራት የሆነባቸው ትውልዶች ባሉበት ወቅት መገኘት አደገኛ ውጋት ነው።

የእኔው ቆይታ ከዚህ በኋላ የራሱ ጉዳይ ብየ መተው አልቻልኩም ለምን ቢባል? ልጆች አሉኝ ለልጆቼ ምንድን አይነት ኢትዮጵያ? ምን አይነት ኢትዮጵያዊ ታሪክ ነው የማወርሳቸው? እንኳን በሕይወቱ የሞተ ሰው አስከሬን አላስቀብር ያሉ ትውልድንና ታሪክን የካዱ በልተውና ዘርፈው የማይጠግቡ ደፍቶ በላዎች ከደደቢት በርሃ ወጥተው ከእምየ ምኒልክ ቤተመንግሥት ገብተው አልወጣልን ያሉ የባንዳ ዘሮችና ቅጥረኞችን አስቀምጨ እንዴት ዝም ልበል በማለት የፖለቲካውን ምሕዳር መከታተል ከጀመርኩ ሰነባብቻለሁ።በነዚህ ባሳለፍኳቸው ጊዚያቶች የተመለከትኩት አንድ ጎልቶ የታየ ጉዳይ ቢኖር ጎጠኞችና የውጭ ጌቶቻቸው በመገንጠል አባዜ ምን ያህል እንደተዘፈቁና ኢትዮጵያ ስትነሳ አብሮ የሚነሳው አማራው ላይ ከመፈክር አልፈው በተግባር ሁሉም በአማራው ላይ ጣቱን እንዲቀስር ማድረግ መቻላቸውን ነው።እውነት ትመነምናለች እንጅ አትበጠስምና አማራውን ከክርስትና ሃይማኖት ጋር በማጣመር እንዲሁም አማራው ጨቋኝና የሌሎችን መብት እንዳፈነ ተደርጎ ቢሰበክም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ መሄድ ከንቱ ድካም ስለሆነ ጥሬውን ሀቅ እያወቁ«ዘር በማጽዳትና በማጥፋት» የተሰለፉ ባለጊዜዎች ከፍለው የማይጨርሱት እዳ ውስጥ እንደገቡና ለዚህም ያለምንም ትሕትናና ይቅርታ ሂሳባቸውን ተገደው እንደሚከፍሉ ማወቅ የውዴታ ግዴታ ነው።

እኛ ከ5ሚሊዮን በላይ የሚሆን አማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል ስንል እንጉልቻሙ ፓርላማ ተብየው 2.7 ሚሊዮን ነው ብሎ አምኖ ተቀብሏል።አንድ አማራስ ቢሆን በምን ሂሳብ ዘሩ እንዲጠፋ ወይም እንዲገደል ይፈረድበታል?አማራ በመሆኑ?ለኢትዮጵያ ውድ ሕይወቱን፤ደሙን፤አጥንቱን ስለከፈለ?፤የሀገር አንድነትን ስለአስከበረ?የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አላስደፍርም በማለቱ?አፋሩ፤ሀረሬው፤ሶማሌው፤አኝዋኩ፤ቬንሻንጉሉ፤ደቡቡ፤ኦሮሞው፤ትግሬው በየትኛውም ክልል መኖር ሲችል ከትግራይ በስተቀር አማራው በአማራ ክልል እንኳን የመኖር መብቱ ተነፍጎ ባይተዋር ሆኖ ይገኛል።ለምን?አማራ ሆኖ በመገኘቱ?ጠቅለል ለማድረግ እነዚህ ከፍ ሲል በጠቀስኳቸው ክልሎች ይቅርና የአማራ ክልል በሚባለው እንኳን ለምን የመኖር መብቱ ተገፈፈ?ዛሬ በትግራይ ሰው በላ ሠራዊት ዳባትና ወገራ በመድፍ እየታረሱ አይደለም እንዴ?ከነዚህ ሁለት ወረዳዎች ተወላጅ የሆኑ ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሆዳም አማራ በአማራው ላይ ጣቱን ነቅሶ ከነማን ጋር እየተሞዳሞደ እንደሆነ በዝርዝር በመረጃ አስደግፎ ማሳየት ይቻላል።ለጹሑፌ መነሻ የሆነኝ መርከቡ ዘለቀ ድርጅቶችንና የድርጅቶችን ሽኩቻ ማን ለማን እንደሚቀርብ ያሳየበትን በሳል ጹሑፍ አንብቤ እንደጨረስኩ እኔም ያለኝን ድንጋይ መወርወር ይገባኛል በሚል ነው።

ማጠንጠኛው እውነቱን የያዘ ያሻውን ያህል ሞጋች ቢመጣም ማቸነፉ ስለማይቀር በአማራ ስም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቅ ማለት የጀመራችሁ ወዳጅ ማብዛት የጠላትን ቁጥር የመቀነስ ሥራ እንደ አንድ ግብ ተወስዶ በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ኃላፊነት ይጠበቅባችኋል።እርስ በእርስ መጠላለፍ ማክተም አለበት ይህ ካልሆነ መንገዱ ሠለጠኝ ብላ ገበያውን አልፋ ሄደች አይነት ነገር ይሆናል ሰከን ብለን እናስብ በተረጋጋ መንፈስ የሠሩት ውጤት ያስገኛል።ማየት ያለብን እኛ በእኛ ለዚያውም በውጭ አገር ስንቆራቆስ ፈንጠያ የሚወርዱት ኦነጋውያን፤ሻብያ፤ህወሃት እስከ ግበረ በላዎቹና ግንቦት ሰባት በሚል የሚጠራው ድርጅትና የሱ ልሳን የሆነው ኢሳት ናቸው።ስለዚህ እዛ ከሰው በላው ሠራዊት ጋር ግንባር ለግንባር እየተፋለመ ያለውን በጎበዝ አለቆች የሚመራውን የአማራ ተጋድሎ ማዳከም ሳይሆን ማጠናከርና ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ እንጅ በተስፋ አለንልህ ማለት ብቻውን ፋይዳ አይኖረውም።ብልጥ ልጅ እየበላ ያለቅሳል ይባላለ እኛ ደግሞ ጠላቶቻችን ብዙ ቢሆኑም ቀስ በቀስ ትኩሳታቸውን ማብረድና ሰልፋቸውን እንዲያሳምሩ ማድረግ ሥልጡንነት ነው።ታክቲክና ስትራቴጅያችን ተመጋጋቢ መሆናቸውን ደጋግሞ መፈተሽ ያሻል-ግንቦት ሰባት የሀሰት ካባ ለብሶ እነኦነግን አጃቢ አድርጎ ከሻብያና ህወሃት እየሰራ እያለ ያ ሁሉ ገበን እንዳይወጣ በኢሳት የውሸት ዜና ማስተላለፊያ ሚዲያ ስንት ድራማ እየተሠራ እያየን አንድ የአማራ ራዲዮና ቴሌቪዥን ለማቋቋም 1.7የሚሆን ዲያስፖራ እያለ ኃላፊነቱን ለሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አሸክሞ ማንጎላቸት ወይም ማሾፍና ድጋፍን መንፈግ ለአማራው ሕዝብ ያለንን ንቀት ወይም ከበሬታ ጥርት አድርጎ የሚያመላክት ነው።

ድል ለአማራው ተጋድሎና ለኢትዮጵያ!!

 

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop