ቴዎድሮስ – ፋሲካ ገ/ጻዲቅ ወ/ሰንበት May 15, 2017 ነፃ አስተያየቶች Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ከስም የተጣሉ፡ ስሙ ያስጨነቃቸውስማቸው የጠፋ፡ ያደ’ፈ ስማቸውስሙን አንስማ አሉ፡ ስሙ እያስፈራቸው።አንዳንድ ስም አለ፡ ጥንቱን ያልታደለከክፉ የዋለአንዳንድ ስም አለ፡ ባህሪን ያዘለበመልዐክ ተመርጦበወላጅ አንደበት፡ ይሁን የተባለ። ከስሞች መሀል ታዲያበመልዐክ ከተመረጡትበወላጅ ከጸደቁት፤ቴዎድሮስ ካሣ ቴዎድሮስ ካሣካሣ ቴዎድሮስ ቴዎድሮስ ካሳሁንአይጥማቸውም አሉእኒህ ባለክፉ ስሞችን። ካሣ ሊሆን ዐጼ ቴዎድሮስቢነሣ ለሀገሩ ሊሆን ዋስየጠላቶቹ መበርከት፤ግን ደግሞ መይሣው ካሣኮሶም ጠጥቶ ቢያገሣያሽራል እንጂ ትንፋሹየወገንን አንጀት አራሹ።ለጠላት ግን ውጋት ሆነለአንድነት ሲል ጨከነለሀገሩ እያደላየጠላቶቹን አንገት ቀላ። ቴዎድሮስ ቴዎድሮስአይሆንም አለ ቴዎድሮስአትንኩብኝ ሀገሬንሀገሬን አትንኩብኝአፈሯን አትድፈሩብኝ።እንኳን የውጪውን ጠላትየውስጡንም አልምረውምበሀገሬ አንድነት ከመጣብኝ። የቋራው አንበሳመይሣው ካሣመቅደላ ላይ ሆኖበጀግንነት እያገሳ፤ሞቼ ነው ቆሜሞቼ ነው ቆሜይፈሳል እንጂ ደሜ፤እንዳለ አልቀረም እንደፎከረደሙ መሬት ፈሶሽጉጡን በአፉ ጎርሶነው በጠላት የተደፈረ። ቴዎድሮስ ቴዎድሮስእምቢ አለ ሳልሣዊው ቴዎድሮስአልቀበልም በቁሜየኢትዮጵያን መፈራረስ።አይሆንም አለ ሳልሣዊው ቴዎድሮስዘመናትን አልፎ ሲነሣዘጸዐት ለኢትዮጵያ እያለስለትንሣኤዋ ሲያወሳ። ስለ ይቅርታ ፍቅርስለ ሀገር ኩራት ክብርስለ ንጉስ ስለ ንጉስእንጥሉ እስክትበጠስ፤ኡኡ ኡኡ ኡኡ አለደግሙ በዚህ በኛ ዘመንትንፋሽ ከጎራዴ ከተሻለእጮሀለሁኝ አለ። ምናለ ልሙት ምናለበቁሜ ግን ይቺ ሀገርበቁሜ አታጣም ክብርሳልሞት አይርቅም ፍቅር።እያለሁኝ በህይወትበቁሜ አይፈርስም አንድነት። ስሜ ቴዎድሮስ ነውኮቴዎድሮስ ካሣ ነው ስሜአደራ ነው ትዕዛዝ አለው‘ምጠራበት ስያሜ።የመይሳው ሞክሼአልቀርም ጥርሴን ነክሼ። ኡኡ እላለሁ ኡኡ ኡኡትንፋሼ እስካለ እጮሃለሁአልፈራም ሞትን የማይቀረውንበቁም መፍረስን እንጂመለያየትን እንጂ ‘ምፈራውልቋቋመው ‘ማልችለው። ሀገሬ ወይ ሀገሬእምዬ እናት ሀገሬተሸራርፈሽ አታልቂምእኔ ሳለሁ አትፈርሺምልጆችሽን ወንድሞቼንእናት አባት እህቶቼንአስታርቄ አስማምቼአመጣልሻለሁ አግባብቼ።በስሜ የጠሉኝ ቢኖሩምሞቴን ውድቀቴን ቢመኙምሀገሬ ላይ ሆኜ እጣራለሁአልፈራም አልሸሽም። ሀገሬ እናቴ ሀገሬእኔ ልግባ መቃብሬውርደትሽን ከማይ ቆሜእንደመይሳው ይፍሰስ ደሜ። ስሜ ስሜማ ቴዎድሮስ ካሣበመልዐክ የወጣልኝ ነውከእናት ከአባቴ ስጋ ሳልነሣ። ቴዎድሮስ የሞተላት ምድርሌላ ቴዎድሮስ እያለአንድነቷ እንዴት ይደፈርያውም በገዛ ልጆቿእንደምን ትጣ ክብር። ቴዎድሮስ የሞተላት ምድርተሸጠች አሉ ለደርቡሾችቋራ ሁመራ አርማጭሆለደርቡሽ ተሸጡ አሉገበሬ አላዳናቸው ጮሆ። ምን ይል ይሆን መይሳውየእትብቱን መቀበሪያባዕድ ጠላት ሲገዛው። ሳልሳዊው ቴዎድሮስለሞክሼው ዓላማ በተቆረቆረለአንድነት ባቀነቀነእወህኒ ተወረወረ። ስመ ጥፉ ባገር ሞልቶ ጥሩ ስም ያለው አልታደለቴዎድሮስ ካሣ የተባለ። በዚያ ላይ ዛሬ በሀገራችንመልካም ስም የወጣለትሰውማ ከወደደውማየሰው ፍቅርን ካከለበትሰው ካገነነውማአለለት መከራ ፍዳስቃይ እንግልት አለበትወየውለት ወየውለትመከራውን ማን አየለት። May 7, 2008ቴዲ አፍሮ ታስሮፋሲካ ገ/ጻዲቅ ወ/ሰንበትቶሮንቶ፤ ካናዳ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email