July 31, 2015
18 mins read

ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለምን በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ በብዛት አይሳተፉም

የሴቶች በብዛት በፖለቲካ ጉዳይ ያለመሳተፋቸው በብዙ ሰዎች አዕምሮ ውስጥ ስለሚጉላላ የግል አመለለካከቴን ለአንባቢያን ለማካፈል የዚህ ርዕስ ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡

በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ውስን ሆኖ መታየቱ ያስደንቃል፤ ብሎም በመንግስት ስራ ላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ በቁጥር አናሣ ናቸው፡፡ መልሱ ግን ቀላል አይመስልም፤ይህ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲና የእኩልነት መብት አለ በሚባልባቸው አገሮችም ውስጥ ቁጥራቸው የጎላ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን ሴቶች እንኳን በአገር ቤት በውጭው አለም ወጥተው በሚኖሩባቸው አገሮች ባሉት የኮሚኒቲ ጽ/ቤቶች ውስጥ እንኳ በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ለመድረስ ሲጣጣሩ አይታዩም፡፡ ይህ ስርዓት መቼ ይቀየር ይሆን?

አንዳንዶች ወንድ/ሴት ይሁን ችሎታ ካለው ሁሉም ሰው በአገሩ ጉዳይ የመሳተፍ መብት አለው ሲሉ ሌላው ወገን ደግሞ የስራ መደቡ ሳይፈጠርላቸው የመሳተፍ መብት አላቸው ማለት ብቻ በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ የፖለቲካ ስርአቱ እንቅፋት ሲሆንባቸው ተሳትፎአቸው ውስን ይሆናል፡፡ በመሆኑም ወንዶች በሚሳተፉበት ነገር ላይ የተሳትፎቸውን ራዕይ ለማሳካት የሚጥሩ ጥቂት ናቸው፡፡

ሴቶች ከፈለጉ በፈለጉበት ጉዳይ ውስጥ ለመሳተፍ ሙሉ ነጻነት አላቸው፡፡ነገር ግን ፍላጎት ቢኖራቸውም በጉዳዩ አይገፉበትም እየተባለ የሚነገረው ለይሰሙላ እንጂ ተግባራዊ ሲሆን አልታየም፡፡ምክንያቱም የቤተስብ ሃላፊነትና የግላቸው ችግር ስላለ ነው ይባላል፡፡ስለዚህ በመጀመሪያ የቤት ውስጥና የውጭ ችግራውን ለማቃለል ቅድመ-ፕላን ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ካለዚያ ተገለልን ወይም ዕድሉ አልተሰጠንም እያሉ ማማረራችውን ማቆም አለባቸው፡፡ ለምሳሌ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የሴት መሪ ለመሆን ዕድል ያገኙ በማላዊ፤ በላቤሪያና በጥቂት አገሮች ነው፡፡ ይሁን እንጂ በሚኒስቴርነት ደረጃ ላይ የደረሱ ብዙ አሉ፡፡በሥራቸውም አመርቂ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ በፖለቲካ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ ፍላጎቱ ቢኖራቸውም በትዳርና በቤተሰብ ሃላፊነት ስለሚጠመዱ ወደ ማህበራዊው ኑሮ ያደላሉ፡፡ በተጨማሪም የአገራቸው የፖለቲካ ስርዓት ግፊት ያደርጋል፤የማህበራዊና የኢኮኖሚ ችግሮቻቸው ወይም ሃላፊነታቸውም ይጫናቸዋል፡፡ ለማናቸውም የእኩልነት መብት የመሰጠቱ ጉዳይ መቅደም ይኖርበታል፡፡የማህበራዊ፣የፖለቲካዊና የኢኮኖሚ ምክንያቶች ካሉበት ክልል ወጥተው በትምህርት እንዲገፉ፤ በባህል አካባቢ ያለባቸው ተጽእኖ እንዲቃለልላቸው ተደርጎ በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ መደረግ አለበት ብሎ አሳማኝ ማረጋገጫ የሚያቀርብ/የሚከራከር ግለሰብ ይኖር ይሆናል?

ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ እንዳይሳተፉ የሚታወቅ እንቅፋት መኖሩ ከማይካድበት ሃቅ አንዱ ጠንካራ የገንዘብ መሰረት የሌላቸው ስለሆኑ፤ቢርቁት እንኳ የማይለቃቸው የቤተሰብ ሃላፊነት ስላለባቸውና የባህል ተጽእኖ ሌላው የማህበራዊ ኑሮ ችግራቸው ነው፡፡ሴቶችና ወንዶች የሚሰሩአቸው የሥራ ዓይነቶች ተለይተው በሃይማኖት እምነት ተጠቁመዋል፡፡

በከፍተኛ ደረጃ ሊማሩ የሚገባቸው የትምህርት አይነቶች ተለይተዋል፤ስለፖለቲካ ምንነት ለማወቅ እንዲጋለጡና ሌሎችም ተዛምዶ ላላቸው ነገሮች በልጅነታቸው ግንዛቤ እንዲያገኙ አልተደረጉም፤ በሚሉትና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከማተኮሬ በፊት አንዳንድ ጉዳዮችን ግልጽ ማድረግ ያሰፈልጋል፡፡

በእርግጥ የተወሰኑ ሴቶች ስለአገራችን ፖለቲካ ሁኔታ እንዲያውቁ ተደርገው አስተዋጽኦ ያበረከቱ ቢኖሩም እነኝህ ሴቶች ብዙሃኑን አይወክሉም፡፡ሆኖም በአገር አቀፍ/በቀበሌ በፓርቲ ደረጃ እንዳይሳተፉ የሚያግዳቸው ነገር አለ፤ለምሳሌ በፖለቲካ ውስጥ ለመሳተፍ ጥረት ሲያደርጉ ሲታዩ፤መድረክ ላይ ወጥተው ንግግር ሲያደርጉ ድሮም ፖለቲካ ለሴት አይሆንም፤ሴቶች ለማድቤት ስራ እንጂ ለፖለቲካ ስራ አይመጥኑም እየተባለ ሲፌዝባቸውና ድምጻቸውን በማሳማት እንዳይታወቁ ጭቆናና ተጽዕኖ ሲለሚደረገባቸው በትምህርትም አይገፉም፡፡ ወደባልትናው ስራ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፤ በወንዶቸ በአጭሩ ይቀጫሉ፤ ጠቃሚ ነገር ሲሰሩም ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና አይሰጣቸውም ወይም አይመሰገኑም፡፡

ለዚህ ጉዳይ አንድ በፍርድ ቤት ውስጥ የተሰማ ገጠመኜን ልጥቀስ፡፡ ባልና ሚሰት የሆኑ ግለሰቦች በጋራ የንግድ ድርጅት ከፍተው ሲያካሄዱ የሥራ ድርሻ ክፍፍል ያደርጋሉ፡፡ሚስት የዋጋ ተማኝ ስትሆን ባል ደግሞ እቃ አቅራቢ ሆነው ሲሰሩ ዕዳ ያለበትን አንድ ግለሰብ ከስሰው ፍርድ ቤት ቀርቡ፡፡ ዳኛውም የዕቃ ዋጋ የሚተምን ማነው? ተብለው ሲጠየቁ ሚስት እንደሆነች ተናገሩ፡፡ ለመሆኑ በባህል ሴት የቤት ስራ እንጂ በዋጋ ትመና ላይ ትሳተፋለች? በማለት ዳኛዋ ተገረመዋል፡፡

በትምህርታቸው አድገው አልፎ አልፎ ከከፍተኛ የስራ ደረጃ ላይ ቢደርሱም በፖለቲካው አለም ውስጥ እጅግም ስለማይታወቁ ከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ በተወዳዳሪነት ቀርቶ በእጩነት ደረጃ እንኳ ቀርበው አያውቁም፤መርጫ ለማሽነፍ በህዝብ ታውቀው ለመወዳደር በፓርቲ ውስጥ መታቀፍ አለባቸው፡፡ይህ በማይሆንበት ጊዜ ለወንዶች እድል ይከፍታል፤ሴቶች ከተሳተፉ ለውጥ እንደሚያመጡ ስለሚታወቅ ይህ ለወንድ ፖለቲከኞች አይዋጥላቸውም፡፡ ህዝቡም በሴቶች ላይ እምነት አይጥልም፡፡ እነሱም/ሴቶችም ፍላጎት እንዳላቸው ስለማያሳውቁ በፖለቲካ አለመብሰላቸውን ያመላክታል፤ይህ የሚያሳየው የወንድ የበላይነትንና ፖለቲካና አገር ማስተዳደር ለወንዶች ብቻ ተወስኖ የተሰጠ የስራ ድርሻ አድርጎ የዓለም ህዘብ ያየዋል/ይቆጥረዋል፡፡

የማህበራዊ ኑሮ ባህላችንና የሀይማኖት እምነታችን ሴቶችን ጨቁኖ በመያዝ ሴቶች እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሆነው እንዲታዩ/ልጆችና ባሎቻቸውን ቀዳሚ ተንከባካቢ እንዲሆኑ፤ዶልተዋል፤ የቤት እመቤት ብቻ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ አድርገል ለማለት ያሰደፍራል፤ይህን ሁሉም ሰው ያምንበታል፤ሴቶች አስተያየታቸውና አመለካከታቸው ጠቃሚ እንዳልሆነ በባህል ስለታመነበት ድምጻቸውን እንዳያሰሙ ተደርገዋል፡፡

ይሁን እንጂ ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ ጊዜው አሁን ነው፤አገራችን ከጥንት አንስቶ በወንድ ተገዝታ ለህዝቡና ለአገሪቱ የጎላ ለውጥ እንዳላሳየች ታሪክ ይመሰክራል፡፡ይህ የሚያመለክተው ወንዶች ህዝብ ረግጦ ለመግዛት እንጂ አገር ለማሻሻል/ለማሳደግና ሕዝብ ለማስተዳደር ያልታደሉ መሆኑን ነው፡፡ለለ ስለዚህ በሌሎች አገር ከወንዶች ይልቅ ሴቶች አገራቸውን የማሻሻል አቅጣጫ ለማሳየት የበቁበቻው አሉ፤ለየት ያለ መንገድ መሞከሩ አይጎዳምና አገር የመምራቱን እድል ለሴቶች ይሰጥና ይሞከሩ፡፡

ለምሳሌ ላቤሪያ ከብዙ አመታት ጦርነትና የምስልቅል የህዝብ ኑሮ በኋላ አገር የመምራት ፍንጭ የሌላቸውን የጦር መሬዎች አንስቶ በሴት ለመተካት በመቻሉ በብዙ የሰለጠኑ አገሮች ምስጋናን አትርፈዋል፡፡አፍሪካ መሪ አልተፈጠረባትም የሚለውን ለማስተባበል በአገራቸው አስችለዋል፡፡ ሰላም ለማስፈንና አገርን አንድ አድርገው ለመምራት በቅተዋል፡፡የእስያንና የአፍርካ አገሮች ለናሙና ያህል ተጠሩ እንጂ ባደጉ አገሮችም በከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣን ላይ የወጡ አለም ያፈራቸው ከወንድ የሚበልጡ አገር የመምራት ችሎታ ያላቸው ጠንካራና ኃይለኛ ሴቶች አሉ፡፡ይህ የሚያሳየው ከወንዶች ይልቅ ሴቶች አገር የመምራት፤ የህዝብ ሰላምና መብት ጠብቀው የማስተዳደር ችሎታ እንዳላቸው ነው፡፡ የስቶች ችሎታ ያልታየና ያልተነካ፤አርቆ የማየት የተፈጥሮ ሞያ ያላቸው ለመሆናቸው በባለሙያዎች ተረጋግጧል፡፡

ለሴቶች የፖለቲካና አገር የማስተዳደር ችሎታቸው በአለም ዙሪያ ታውቆላቸው ሳለ በአፍሪካ አህጉራት ግን ሴቶች ከቤት እመቤትነት ሌላ ስራ አይፈልጉም፤ ፍላጎትም የላቸውም የሚባለውን አጉል አስተሳሰብ በሰለጠነው አገር በተግባር አሰመሰክረዋል፡፡

ስለዚህ ሴቶች የወንዶችን ያህል እንደሚሰሩ ስለታወቀ ሴቶች እህቶቻችን ስለሃገራቸውና ስለፖለቲካ ተሳትፏቸው ጉዳይ ሊያሰቡበት ይገባል፡፡ አፍሪካ የወንድ የበላይነት የነገሰባት አህጉር በመሆኗ ሴቶችን በባህል ተጽእኖ መያዟ መወገድ አለበት፡፡

ሴቶች በፖለቲካ ስራ ላይ እንዲሳተፉ አገር ወዳድና አርቆ አሰተዋይ ተባባሪ የወንዶች እገዛ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ በቀር ሴቶች የፖለቲካ ስልጣን ላይ አይወጡም፡፡የአዋቂዎችን አባባል ስናስታውስ “የእሳቱን ግለት ያልተቋቋመ ሰው ማእድ ቤቱን መልቀቅ አለበት” የሚባል አባባል አለ፡፡ ከወንድ ሌላ ስለፖለቲካ ጉዳይ የሚያውቅ የለም የሚለውን አስተሳሰብ የአፍሪካ ህዝብ ስለሚያምንበት በውዴታም ሆነ በግዴታ ስልጣኑን ይዞ ይቆያል እንጂ ከእሱ የተሻለ መሪ አስቀምጦ ውጤት መጠበቁ አይሆንልበትም፡፡ለምን ቢባል ብቅ የሚለውንና ለአገሩ የሚያስበውን ያርቁታል፤ይህንን ለመቋቋም በተለይ ወጣቱ ትውልድ በዘመናዊ ትምህርት የመታነጽ ዕድል ስላገኘ የወንድ ፖለቲከኞችን መታገል፤የወንድ የበላይነትን ጉዳይ ማመንመን ይኖርበታል፡፡

ሴቶችም ቢሆኑ ስልጣን ይዘው ካልተሳካላቸው ሴት ስለሆኑ ብቻ እንዳልሆነ ማወቅ አለባቸው እንጂ ሴት ስለሆንኩኝ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ከአዕምሮአቸው ውስጥ ማስወገድ አለባቸው፤ወንዶች ምን ጊዜም የበላይ ናቸው በሚለው ኋላቀር አስተሳሰብ እንዳይታለሉ ፤ወንዶች የሚጫወቱትን የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት ታጥቀው መቆም አለባቸው፡፡ ካላሸነፉ አብረው ጥሩ ስም የሚያስጠራ ስራ በመስራት ለመቆም፤ካለበለዚያ ማደግ የለምና የአስተሳሰብ ጠባብነትን ማስወገድ፤ ሴቶች ወንዶች የሚሰሩትን ማለትም ቆራጥንትን፤ብልጥነትን፤አርቆ አስተዋነት፤ ንቁነትን፤ ተባብሮ መኖርን፤ ወድቆ መነሳትን፤የወንዶች የበላይነትን አስተሳሰብን መቋቋም፤ አስተዋይነትንና አለመታለልን የአፍሪካ መሪዎች የሚጫወቱትን እሰጥ አገባ አብሮ መጨወትን፤ሆደባሻነትን፤ ሃዜኔታንና ማለቃቀስን ጠንቅቀው መረዳትና ማቆም አለባቸው፡፡

አሜሪካ ጯሂና የጾታ እኩልነት የሚያስከብር ህግ ቢኖራትም የአገር መሬነቱን ስልጣን ለሴቶች እስካሁን አላሰረከቡም፡፡ ወንዶችን ከመምረጥ ሴቶችን መምረጥ ያስፈልጋል የሚለው የጥንት አመለካከታቸው እሰከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ስላልቀነሰ የመሪነቱን ወንበር ለመልቀቅ እስካሁን አልፈቀዱም፡፡ይህ በመሆኑ ኸለሪ ክሊነተን የአሜሪካ ፕሬዜዳንትነቱን ቦታ ለመያዝ እንደ አውሮፓ ቀን አቆጣጠር 2008 ዓ.ም ላይ ታግላ የውስጥ ጉዳይ በሆነ ነገር ባትመረጥም ጥሩ መሪ መሆን እንደምትችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆና ችሎታዋን በተግባር ለዓለም ህዝብ አሳይታ ስለተረጋግጠላት አሁን የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ለመሆን ትግሏን ለሕዝብ እያሳየች ነው፡፡የእሷ ምሳሌነትም በብዙ አገሮች ውስጥ ሴቶች ሥልጣን ላይ ወጥተው ችሎታቸውን እንዲያረጋገጡ አድርጓል፡፡

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop