February 18, 2013
4 mins read

አዜብ መስፍን የአዲስ አበባ ከንቲባ?

(ዘ-ሐበሻ) የቀድሟ ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከዚህ ቀደም በምርጫ ትወዳድርበት የነበረውን የትግራይ ክልል በመተው በአዲስ አበባ ከተማ ለምርጫ እንደምትቀርብ ከወደ አዲስ አበባ የመጡ ዜናዎች አመለከቱ። “የአቶ መለስ ዜናዊን ሌጋሲ እኔ አስፈጽመዋለሁ” በሚል በአቶ መለስ የቀብር መታሰቢያ ፕሮግራም ላይ በድፍረት የተናገረችው ወ/ሮ አዜብ በአሁኑ ወቅት የፌደራሉ ፓርላማ አባል ብትሆንም ኢሕአዴግን ወክላ በመጪው የቀበሌና የወረዳ ምርጫ ላይ ኢሕ አዴግን በመወከል በበቂርቆስ ክፍለከተማ እንደምትወዳደር የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።
በተለይ “አፍቃሬ ኢሕአዴግ” በመባል የሚታወቀው የአቶ ልደቱ አያሌው ኤዲፓ በዚህ ምርጫ ላይ ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በከፊል ብቻ እንደሚሳተፍ ባሳወቀበት በዘንድሮው ምርጫ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ይወዳደራል ተብሎ የሚጠበቀው የኢዴፓው ወንድወሰን ተሾመ ነው። አቶ ወንደሰን ተሾመ ኢዴፓ ብቸኛው ያቀረበው እጩ ሲሆን ይህም እጩ ከወ/ሮ አዜብ በሚወዳደሩበት የምርጫ ጣቢያ እንዲወዳደር የተደረገው የፖለቲካ ትርፍ ኢሕአዴግ ለማግኘት አስቦ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ትዝብታቸውን ለዘ-ሐበሻ ይገልጻሉ።
ባልተለመደ መልኩ ከትግራይ ክልል ተነስታ በአዲስ አበባ ከተማ ለምርጫ የምትወዳደረው ወ/ሮ አዜብ ምርጫው የተበላ እቁብ በመሆኑ በቀጥታ አሸንፋ የአዲስ አበባ ካቢኔ ውስጥ በመግባት የኦሕዴዱን ኩማ ደመቅሳ ቦታ በመቀበል የከተማዋ ከንቲባ እርሷን ለማድረግ የታቀደ ነገር እንዳለ ያስታውቃል ያሉት ታዛቢዎች በተለይም ከሰሞኑ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ቅርርብ አላቸው የተባሉ አንዳንድ የአዲስ አበባ መጽሔቶች “የሴት ጠ/ሚ/ር ማየት ናፈቀን” የሚል ጽሁፍ ሁሉ እንዲጽፉ መደረጉን ከወ/ሮ አዜብ ወደ አዲስ አበባ ከንቲባ መምጣት ጋር አያይዘውታል ይላሉ- ታዛቢዎቹ።
አቶ አርከበ እቁባይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በነበሩበት ወቅት በአዲስ አበባ የታዩ ለውጦችን ቢያደርጉም የአዲስ አበባ ሕዝብ በምርጫ 97 ወቅት “አርከበ ለከተማዋ እድገት ብትጥርም፤ ኢሕአዴግን ወክለህ ብቻ ስለመጣህ አንመርጥህም” የሚል ምላሽ ከህዝቡ አግኝቶ ኢሕአዴግ በምርጫው በ0 በተሸነፈበት ወቅት ከወ/ሮ አዜብ ጋር እንደማይዋደዱ የሚነገርላቸው አቶ አርከበ በባልየው በአቶ መለስ ዜናዊ “በአዲስ አበባ ላይ ቀለም ከመቀባት በስተቀር ያመጣኸው ለውጥ የለም” በሚል በስብሰባ ላይ በግልጽ ተሰድበው ነበር።
በአሁኑ ወቅት ሕወሃት በክፍፍል ላይ እንዳለ እየተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የአቶ ስብሃት እና የወ/ሮ አዜብ ግሩፕ በየፊናው ተፋጧል። አሁን ወ/ሮ አዜብን በአዲስ አበባ ከንቲባነት አማሎ ድርጅቱን የማዳን ሥራ እየተሰራ ነው የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ።

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop