February 28, 2015
35 mins read

በሥራ ሂደት ባለቤቶች የተጥለቀለቀች ብቸኛዋ ሀገር! – ነፃነት ዘለቀ

ነፃነት  ዘለቀ (ከአዲስ አበባና ከፊንፊኔ)

ሰሞኑን አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ የወያኔውን የዱርዬ መንግሥት በርካታ ቢሮዎች ማንኳኳት ነበረብኝ፡፡ ጉድ አየሁላችሁ፡፡ የጉድ ጉድ! ስንቱን ነግሬያችሁ እንደምዘልቀው ግን አላውቅም፡፡ በሀገራችን ተዝቆ የማያልቅ  ብዙ ጉድ እየፈላና እየተንተከተከ ነው፡፡ በአንዲት ሀገርና በአንዲት መናገሻ ከተማ ስንት መንግሥት እንዳለም ለማወቅ ሞክሬ አልተቻለኝም፡፡ አንዱ ጋ ስትሄድ አዲስ አበባ ይልሃል፤ ሌላው ጋ ስትሄድ ፊንፊኔ ይልሃል፤ ወደ አንዱ ኤፍ ኤም ብትሄድ ደግሞ ሸገር ይልሃል፡፡ አንዱ “ወደናዝሬት ልሄድ ነው” ሲልህ ሌላው “ወደአዳማ ልሄድ ነው” ይልሃል፡፡ ስሞችም ፖለቲካዊ ይዘት እየተላበሱ በአጠራር ልየነት መቀያየምና በነገር መጓነፍ ይታያል፡፡ “እህሉ አንድ ዓይነት ሴቱ አሥራ ሁለት” የሆነበት ዘመን ሆኗል፡፡ ዘመነ ግርምቲ! ቧይ!! አዲስ አበባ – ፊንፊኔ፣ ናዝሬት – አዳማ፣ ደብረ ዘይት – ቢሾቱ፣ አዋሳ – ሀዋሳ፣ ጅጅጋ -ጅግጅጋ፣ አለማያ- ሀሮማያ፣ ውጥንቅጡ የወጣባት ሀገር – ሰው በስያሜም ይለያያል? በስያሜና በተሰያሚ መካከል እኮ የባሕርይ ግንኙነት የለም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ለምን በዚህ ቀላል ነገር ይሻኮታሉ? በተለመደው ቢጠራ ችግሩ ምን ይሆን? ባቢሎን በሣሎን፤ ባቢሎን በኢትዮጵያ፡፡

ወደ አንዱ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሂድ – ወግ ነውና ሲዳሩ ማልቀስ የወያኔ “መንግሥት”ም ያው መንግሥት መባሉ ነው እንግዲህ፡፡ እናም ስትሄድ ምን እንደሚገጥምህ ያየሁትን ልነግርህ ነው – ተዘጋጅ፡፡

በብዙ መሥሪያ ቤቶች ከዘበኛ ጀምሮ እስከላይኛው ሥራ አስኪያጅ ወይም ሥራ አስፈጣሚ ድረስ የምታገኘው ከትግሬው ብሔር የተገኙ ጥቂት የተማሩ ወይም ሞፈር ቀምበር ሰቅለው የመጡ – ግን እንደከተመኛ የለበሱ – ማይም ሰዎችን ነው – ከመደነቋቆር በስተቀር የማትግባባቸው ፍጹም ማይማን፡፡ አልፎ አልፎም የመሥሪያ ቤቶች የመግባቢያ ቋንቋ የሀገሪቱ ኦፊሴላዊ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ ቀርቶ ትግርኛ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ – ይሄ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ይህን ያነሳሁት ለወቀሣ ሣይሆን የትግሬው ጠባብ ቡድን ወደ ዘጠና ሚሊዮን የሚገመተውን መላዋን የሀገሪቱን ሕዝብ በምን ያህል ብልጫ ገለባብጦ አንድን የመንግሥት መሥሪያ ቤት በቁጥጥሩ ሥር እንዳደረገው ለማሳየት ነው፡፡ እንጂ ማንም ዜጋ በፈለገው ቋንቋ የመግባባት መብቱ ተፈጥሯዊ እንጂ ሰብኣዊ ስጦታ እንዳይደለ እረዳለሁ፡፡ በትግርኛችን የብሔራዊ አገልግሎት ድርሻን መውሰድ ቀንቼበት ወይም ተመቅኝቼ አይደለም፡፡ ሁሉም የኔው ነው፡፡

መሄድ የነበረብኝ መሥሪያ ቤቶች በውነቱ ጥቂቶች ነበሩ፡፡ ነገር ግን በነዚያ መሥሪያ ቤቶች በታዘብኩት የተወላገደ ሀገራዊ ምስል ምክንያት ሌሎች ብዙዎችንም ጨመርኩ – ለግንዛቤየ ስል ብቻ (just for curiosity purpose)፡፡ እናም መከላከያና ውጭ ጉዳይም አልቀሩኝም – ከሃይማኖቱም ፓትርያርክ ጽ/ቤትና ምግባረ ብልሹ ማለትም “ምግባረ ሠናይ” የሚባለውን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስታን ሆስፒታልን ጭምር በሰበቡ ጎበኘሁ፡፡

አንድ ነገር ማስቀደም ፈለግሁ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ሥርዓት ከነጮቹ ውስጥ ያን ወንድምና እህቶቻቸው በጥቁሮችና በቅይጦች ላይ የዘረጉትን የአፓርታይድ አገዛዝ አጥብቀው የሚቃወሙና የሚታገሉም ነበሩ፡፡ እነዚያን ዓይነት ጤናማ አእምሮ የነበራቸውና ያላቸው ምርጥ የዓለማችን ዜጎች ከየቆሻሻ ክምሮች ውስጥ እያፈነገጡ የሚወጡበት ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ይታያል፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር መሆኑ አዲስ አይደለምና ከወያኔም አንጀተ ብቡ እንደማይጠፋ ሁሉ ከለዬለት ሰይጣንም ተስቶትም ቢሆን ምሕረትን የሚያደርግ አይጠፋም፡፡ የነዚህ የፀረ አፓርታይድ ነጭ ታጋዮች ጉዳይ ግን ለየት ይላል፡፡ እነሱን የመሰሉ ፀረ ጽዮናውያንም እንዳሉ ስንሰማ ለሰዎች አእምሯዊ ዕድገት ያለን አድናቆት ይጨምራል፡፡ የሚገርማችሁ ነገር የሚጓዙበትን ብርሃን መሰል ጨለማ የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ ሲረዱ ከ32 እና ከ33 ዲግሪ የኢሉሚናቲ የዕድገት ደረጃ ሣይቀር እየወጡ የጓደኞቻቸውን የቀን ቅዠት የሚያጋልጡና መልካም ሕይወትን መኖር የሚጀምሩ ደጋግ የቀድሞ የሉሲፈር እምነት አራማጆች አሉ፡፡ በበኩሌ ምንም እንኳን ትልቅ አደጋ የሚጋረጥባቸው መሆናቸውን ብረዳም በነዚህ ወደኅሊናቸው የሚመለሱ ሰዎች በጣም እደሰታለሁ፡፡ በዚህ መልክ የዘርም ይሁን የእምነት ጓዶቻቸውን የዕውር ድንብር የጨለማ ጉዞ እየከዱ ወደ እውነት ጎዳና የሚገቡና በስህተታቸው የሚጸጸቱ አሉ፡፡ በሀገራችንም የነዚህን ዓይነት ከጠማማ መንገድ ተመለሾችን ቁጥር እንዲያበዛልንና የነፃነታችንን ቀን እንዲያቀርብልን ፈጣሪን በጸሎት ተግተን እንወትውተው፡፡

የሩዋንዳን ነገር ሣልጠቅስ ማለፍ አልወድም፡፡ አክራሪ ሁቱዎች ቱሲዎችን በሚጨፈጭፉበት ጊዜ ለዘብተኛ ሁቱዎች  ቱሲዎችን የመታደግ ብዙ ታሪካዊ ሥራ ሠርተዋል፡፡ በቤታቸው ሸሽገው አደጋውን እንዲያልፉ ያደረጉ የጤናማ አእምሮ ባለቤት ሁቱዎች ነበሩ፡፡ እንደጓደኞቻቸው ሣያብዱና ሣይወፍፉ በጭፍጨፋውም ሣይሣተፉ ለቱሲዎች መልካም ነገርን በማድረግ አሁን ላለው አንጻራዊ ሰላም የበቁ፣ በዚያም ምክንያት ኅሊናቸውን በደም ታሪክ ያላጨቀዩ ሁቱዎች አሉ፤ ለደግ አሳቢ አእምሮ ምሥጋና ይድረሰው፡፡ ሁሉም ያልፋል፤ የማያልፍ ነገር ቢኖር ኖሮ ቁጭት ንዴታችን ወሰን ባልተገኘለት፡፡

ከፍ ሲል ያልሁትን ያልሁት አለምክንያት አይደለም፡፡ ደጋግ ትግሬዎች አለን፡፡ ከነፈሰው ጋር የማንነፍስና በወገኖቻችን መገፋትና መሳደድ/መሰደድ የምንከፋ፣ የምንበሳጭና የምንቆጭ ጥሩ ጥሩ ትግሬዎች አለን፡፡ አላህ ጨርሶ አይበድልም፡፡ ከንፍሮም ጥሬ ይወጣል፡፡ እናም ጥቂቶችም ቢሆኑ በአሁኑ ሸውራራ የትግሬ አገዛዝ አንጀታቸው የሚያርር በዚህም ምክንያት የዘር ሐረጋቸው ያመጣውን ሀገራዊ መቅሰፍት ለመንቀል ከጭቁኖች ጋር ለመታገል የቆረጡ አሉ፡፡ ትግላቸው እስከሞት የሚያደርስ መሆኑን እያወቁ ለኅሊናቸው ሲሉ ከመከረኛው ሕዝብ ጎን ተሠልፈው የሚዋደቁ እነአብርሃ ደስታና አሥራት አብርሃም፣ አብርሃም በላይ – እንዴት ነገሩ ይሄ አብርሃ የሚሉት ስም … ብቻ ጥቂት የማይባሉ ትግሬዎች አሉን፡፡ ጌታ ጥሎ አይጥልም፡፡ ጥቂትም ቢሆኑ የመከራ ገፈታችንን የሚጋሩ ትግሬዎች መኖራቸው ሸክማችንን የሚጋራን ከመኖሩ አኳያ መጠነኛ እፎይታ ይሰማናል፡፡ በተረፈ ተከድኖ ይብሰል፡፡ ለዛሬ ግን ለምን ይከደናል? ያየሁትን እዘከዝከዋለሁ፡፡

በዬመሥሪያ ቤቱ ኃላፊውም ዘበኛውም ጽዳቱም ትግሬ ነው፡፡ ለይስሙላ ቢሮ ተቀምጦ የሚገኘውን ኃይለ ማርያም ደሳለኝን የመሰለ መናጆና “ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት” ባዩን ዜጋ ታዲያ ከቁም ነገር እንዳትቆጥሩት – አንድም ሥልጣን የሌለው በዓይን ጥቅሻና በቀጭኒቱ ሽቦ ከትግሬዎች መንደር የሚታዘዝ መጋጃ ነው፡፡ ይህ በጣም ግልጽ ነው፡፡  ወ/ሮ ትብለፅ ጎይታይ – የሰው ኃይል አስተዳደር የሥራ ሂደት ባለቤት፣ አቶ መሓሪ ሽኑን – የወጪና ገቢ ቁጥጥር የሥራ ሂደት ባለቤት፤ ዶክተር ሐጎስ ዕንቋይ – የአማራ ክልላዊ መንግሥት ዕንባ ጠባቂ የሥራ ሂደት ባለቤት፣ አቶ ዘርዑ መዓሾ – የደቡብ ሕዝቦች ክልል የመሬት ድልድል የሥራ ሂደት ባለቤት፤ ወ/ሮ ሐረጓ ግደይ – የአዲስ አበባ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ፤ ወጣት አረጋዊ አስገዶም – የአዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ የዘርፍ ሰብሳቢ፤ እማሆይ አብረኸት ፍትዊ የኪዳነ ምሕረት ገዳም እመምኔት፤ አባ ናትናኤል ኪሮስ የአ.አ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፤ አቡነ ናትናኤል የኦርቶደክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክና… አቶ ማለትም ዶክተር ኃይለሚካኤል ጎይቶም የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዕድሜ ልክ ፕሬዝደንትና በወያኔ ማዕከላዊ ጽ/ቤት የሙስና ማቀላጠፊያ ዘርፍ  የሥራ ሂደት ባለቤት … አይ! ያሣፍራል፡፡ አንዳርጋቸው ያቺን ስድ ሴት በተመለከተ ሲናገር የአማርኛውን “ያሸማቅቀኛል” የሚለውን ቃል በስሜታዊነት ዘንግቶት በእንግሊዝኛው “cringe” አደርጋለሁ ብሎ ነበር፡፡ እኔም በዚህ የትግሬው ገዢ መደብ ክሪንጅ አደረግሁ – ተሳቀቅሁለት – ተሸማቀቅሁላቸው፡፡ አንጎል ምን ያህል ቢጠፋ የዚህችን ቀመር የኋላ ጦስ እንዴት ያጧታል? እንዴ! ከታች እስከ ላይ በትግሬ አስይዘህ ስታበቃ፣ ሌላውን ዜጋ እንደባይተዋር ወርውረህ ስታበቃ፣ ሌላውን ዜጋ በተለይም አማርኛ ተናጋሪውን ጨፍጭፈህና አስጨፍጭፈህ ንቀህና አዋርደህ ከሀገሩ ጉዳይም አግልለህ የትሚናውን ጥለህ ስታበቃ፣ … በዚህ በተደናበረ አገዛዝ ስንት ዓመት ትኖራለህ? የአንዲን ቃል ልድገመው – ተሸማቀቅሁላቸው፡፡ እኔ ያፈርሁት በነሱ ነው፡፡ ማይምነት ለካንስ እስከዚህን ያጋልጣል? ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን ሁሉ ነገር ዐይን ዐዋጅ ሆነባቸውና ተጨነቁ፡፡

ትግሬዎቹ የተማሩ ቢሆኑና ለቦታው ቢመጥኑ ለኔ ጉዳየ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለቦታው የሚመጥን ሰው ከሆነ ትክክለኛ አገልግሎት ይሰጣልና የሚበሳጭና የሚናደድ ተስተናጋጅ አይኖርም፡፡ እነሱ ግን ምኑንም ስለማያውቁት በዘር ብቻ እየተጠራሩ ሀገሪቱን የጨረባ ተዝካር አድርገዋታል፡፡ የአምስተኛ ክፍል ጄኔራልና የአሥረኛ ክፍል ዶክተር ባለሥልጣን ባለባት ሀገር – የመካከለኛና ዝቅተኛ ቢሮዎች ባለሥልጣናት እስከምን ድረስ ሊማሩ እንደሚችሉ ይታያችሁ፡፡ ሀገሪቱን ከዳር እዳር እየተጫወቱባት እኮ ነው፡፡ ኧረ ጓዶች ፍጠኑና ይህችን ሀገር ከዚህ አረንቋ በቶሎ እናውጣት ማለትም አውጧት፡፡

በየቀበሌዎችና ወረዳዎችም ሄጃለሁ፡፡ ሁሉም ቦታ አዛዥ ናዛዡ ትግሬ ነው፤ ልብ አድርጉ – የሌላ ዘውግ ተሹዋሚ የለም እያልኩ አይደለም – ሞልቷል፡፡ ግን ራሱን ችሎ አይሠራም – ከጥቃቅን ነገሮች በስተቀር፡፡ ኦነግ ወይም ከወሮች አንድኛው እንዳይለጠፍበት በመስጋት ሁሉም የሌላ ብሔር “ሹም” ክፉኛ እየተሳቀቀ ነው ሥራ ውሎ የሚገባው፡፡ በተረፈ የትግሬው ባለሥልጠን ደረቱን ነፍቶ ሲነፈርርና በሥነ ልቦናዊ የበላይነት እርካታ ሲንጎማለል ታያዩታላችሁ፡፡

ባይገርማችሁ የዛሬ ሁለት ዓመት አሥረኛ ክፍልን ማለፍ ያቃተው አንድ ወጣት ትግሬ አሁን የአንድ ወረዳ ሥራ አስፈጻሚ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ተሹዋሚ ትግሬ በችሎታውና በትምህርቱ ሣይሆን በዘውጋዊ ቀረቤታው ነው፡፡ የቀረቤታው ልክ ደግሞ ከትግሬም ትግሬ እየተማረጠ ነው፡፡ ቅድሚያ አድዋ፣ ቀጥሎ ሽሬ፣ ቀጥሎ አክሱም … ዓይነት እጅግ የወረደ ጎጠኝነትና መንደርተኝነት፡፡ በትምህርትና በችሎታ መመደብማ ለይቶለት ገደል ከገባ ሃያ አራት ዓመታትን ሊያስቆጥር ጥቂት ወራት ብቻ ቀርተዋል፡፡ መለስ – ባለበት ሲያስመልሰው ውሎ ይደርና –  በሕይወት እያለ ለፖለቲካው እስከታመነ ድረስ ዘበኛንም ሚኒስትር ማድረግ እንደሚቻል በኩራት ተናግሮ ነበር፡፡ ለንግግርም ለከት የሌላቸው እንዴት ያሉ ባለጌዎች ናቸው እኮ! ፈጣሪን ምን ቢበድሉት ይሆን እንዲህ አበለሻሽቶ የፈጠራቸው? እኛስ ብንሆን ኃጢኣታችን ምን ያህል ከተራራ ቢገዝፍ ይሆን ካልጠፋ አምባገነን እነዚህን የመሰሉ የሲዖል ትሎች የሰጠን? እስኪ ቁጭ ብላችሁ አስቡት፡፡ ሀሁንና ኤቢሲዲን ባልቆጠሩ ማይማን እንዴት ሀገር ትተዳደር? ምን ዓይነት ውርጅብኝ ነው? በስማም!

ጭንቀቴን ልናገር፡፡ አሁን በትግሬ ወያኔ ከላይ እስከታች የተጥለቀለቀውን የሀገሪቱን ቢሮክራሲ ነገ ነፃ ስንወጣ እንዴት አድርገን ነው የምናስተካክለው? ማን ነው ወንዱ ይህን ሁሉ በትግሬ የተጨናነቀ መሥሪያ ቤት ሁሉ አስተካክሎ እውነተኛ የሁሉም ብሄሮች የተማሩ አባላት በውድድር አልፈው ሀገሪቷን እንዲመሩ የሚያደርግ? በጣም ከባድ የቤት ሥራ ተጎልቶላችኋል፡፡ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ካልታከለበት ከሆድና ከዘረኝነት የቤት ጣጣ በስተቀር አንድም ዕውቀት የሌለውን ይህን የወያኔ መንጋ በሠለጠነና በተማረ ኃይል ለመተካት ትልቅ ችግር ይገጥማችኋል – እናንት ኢትዮጵያውያን፡፡ እኔ ኢትዮጵያ ነፃ በወጣች ማግሥት ይህን ጉድ ላለማየት እግሬ ባወጣኝ  ከሀገሬ የምሰደድ ይመስለኛል፡፡ እፈራለሁ፡፡ አሁን ያለው ሁኔታ በጣም ያስፈራል፡፡ ሁሉም በአንድ ብሔር ይያዝ? አደገኛ መቅሰፍት ነው! የሚገርምህ ሌላ ነገር – ወያኔ ከሆንክ የፈለገውን ዓይነት የአካል ጉድለት ቢኖርብህ ከሥራህ የሚያነቃንቅህ የለም፡፡ ጣቶች የሌሉት ፖሊስ፣ እጅግ እግር የሌለው (በአርትፊሻል የሚንቀሳቀስ) የጥበቃ አባል ታገኛለህ፡፡ የትግሬነት ማንነት ብዙ ምናልባትም ሁሉንም ህጎች ይደፈጥጥልሃል፤ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ዘረኝነት በምንም ዓይነት ምድራዊ ህግ የሚገዛ አይመስለኝም፡፡ ህግ የሚሠራው ለሌሎች እንጂ ለወያኔ አይደለም፡፡ ይህም በጣም አሣፋሪ ነው፡፡ ከህግ ውጪ ይነግዳሉ፤ ከህግ ውጭ ያመርታሉ፤ ከህግ ውጪ ያከፋፍላሉ፤ ከህግ ውጪ የሀገርን ሀብት ይቀራመታሉ፤ ከህግ ውጪ ያስገባሉ፤ ከህግ ውጪ ያስወጣሉ፤ ከህግ ውጪ ይጠቃቀማሉ፤ ከህግ ውጪ ሌሎችን ያፈናቅላሉ፤ ከህግ ውጪ የፈለጉትን ቦታ አጥረው ይይዛሉ – ይሸጣሉ- ይለውጣሉ፤ ከህግ ውጪ – ከፈለጉ ላይመልሱ ጭምር –  ከባንክ ይበደራሉ፤ከህግ ውጪ ያሻቸውን ሁሉ አላንዳች ማመንታት ይፈጽማሉ፡፡ እነሱ ህግና እግዜር ሆነዋል – ኧረ ከማያውቁት እግዜሩም በላይ፡፡ እኛን ምሥኪኖቹን ምን ይዋጠን?

ሌሎች ዜጎችን ስታዩዋቸው አንጀታችሁን ይበሉታል፡፡ ሀገሪቱ በአንድ ብሄር ቁጥጥር ሥር እንደመዋሏ ሌሎች የቀላዋጭነት ጠባይ ይታይባቸዋል – ሀገሪቱ የነሱም እንዳልሆነችና ባይተዋር የመሆናቸውን ጉዳይ ሳይወዱ በግዳቸው እንዳመኑ ያህል ትረዳላችሁ – ከሁኔታቸው፡፡ ለበርካታ ዓመታት በቅልውጥናና በማጎብደድ መኖር የበታችነት ስብዕናን ሣያዳብር የሚቀር አይመስለኝም – ስለሆነም ኢትዮጵያውያንን ከዚህ አገዛዝ ነፃ አውጥቶ የራሳቸውን ሰብኣዊና ብሔራዊ ማንነት እንደገና ለማላበስ ከፍተኛ ትግል ሣያስፈልግ አይቀርም፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ እንደልቡ ሲደነፋና ሌሎችን እያንጓጠጠና እያላገጠባቸው ሲያዝ የምታዩት ትግሬ ነው – ባለጌው የሕወሓት ጀሌ ማለቴ ነው፡፡ ሌላውማ እንደኔው አክስትና አጎት በልመና አዲስ አበባን እያጥለቀለቀ ነው፡፡ ግራ የተጋባ ነገር ነው የገጠመን፡፡ ማጣፊያው ያጠረን ግራ መጋባት፡፡ ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ ያቃተን ትልቅ አደጋ፡፡

ትግሬ ያልሆነ የይስሙላው ባሥልጣን ለምሳሌ ጽዳቷ ቢሮውን ለማጽዳት ብትገባ ልታዘው የመጣች መስሎት የሚያሸረግድላት አይጠፋም – ትግሬ በመሆኗ ብቻ፤ በራስ የመተማመን ነገር ከብዙዎች ዜጎች ሙልጭ ብሎ ጠፍቷል፤ ፍርሀት ነግሦአል፡፡ በየቦታው የሚታየው የሌሎች ወገኖች መሳቀቅ በአንዲት ሀገር የተለያዬ ዜግነት መኖርን ያመላክታችኋል፡፡ “ለካንስ አእምሯዊ የዕድገት ደረጃውን ባልጨረሰ ሰው መገዛት እጅግ ከባድና አዋራጅም ነው” ብላችሁ ትተክዛላችሁ – ልክ እንደኔ፡፡ በየሄድኩበት ቦታ ሁሉ በሀፍረት እየተሸማቀቅሁ እመለሳለሁ፡፡ ደግሞም የሚከረፋኝ ነገር አለ፡፡ በቃ – ቢሮውም፣ ሕንፃውም፣ ምኑም ምናምኑም እንዳንዳች ነገር ይሸተኛል – እጅግ የሚቀረናና የሚከረፋ ሽታ፡፡ የሽታው መንስኤ እንደሚመስለኝ ማይምነቱ፣ ዘረኝነቱ፣ መድሎው፣ በየሥፍራው የሚታየው የማስመሰል፣ የመዋሸትና በግልጽ የማጭበርበር ወያኔዊ ባሕርይ በድምሩ የፈጠሩት ግማት ነው፡፡ የመሥሪያ ቤቱ ጋጋታ፣ የሥራ ሂደቶቹና ንዑስ የሥራ ሂደቶቹ ብዛት፣ የሥራ ፈት “ሠራተኛ”ው መርመስመስ፣ የቴሌቪዥኑና የጋዜጣው ዐይን ያወጣ ቅጥፈትና ዕብለት፣ የውሸቱ ምርጫ የማታለልና ሕዝብን የማነሁለል ሂደት፣ ዘገምተኛ ዜጎችን ሣይቀር ያጡ የነጡ ድሆችን በካድሬነት መልምሎ በማሠማራት በሕዝብ ላይ የሚደረገው ወከባ … ሲታይ ሀገር በነሲብ እየተነዳች እንደሆነ ግልጽ ይሆንላችኋል፡፡ ከምርጫ ውጪ ሌላ ዜማ የለም፤ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያካሂዱ ይመስል በም..ር..ጫ(በትግርኛ ሥልት አንብቧት) ወሬ ናውዘዋል – የማያውቁትን ምርጫ፡፡ በየሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ትርምስ ነው፡፡ እዚህም እዚያም ውክቢያ ነው፡፡ መርመስመስ ነው፡፡ ለቀልድ በተቋቋመ የሚንስትር መሥሪያ ቤት ውስጥ አንድ ሚኒስትር ሦስትና አራት ሚኒስትር ዴታ፣ ሃያና ሠላሣ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤቶች … ቅብጥርስ ቅብጥርስ፡፡ ግን ሁሉም ከንቱ፡፡ ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡ ሁሌ ቁልቁል፡፡ የመፈክሩ ዓይነት አበዛዙ… ሙስና የዕደገት ፀር ነው … እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን … ራዕይህን ከግብ እናደርሳለን … አንተ ብትለየንም ራዕይህና ውድ ባለቤትህ አዜቢና ከኛ ጋር ናቸው(ከራሴው ምርቃት ጋር)፤ ከሦስት ዓመታት በላይ የወሰደ በየትም ሀገር ያልታዬ ሀዘን – በዚህስ ሰሜን ኮሪያም ሳትበልጠን አትቀርም – ወዲያው ነው የረሱት የነኪምን ሞት፡፡ የባልና ሚስት ወይም የልጅ፣ የወንድምና የእህት ሞት እንኳን በስድስት ወርና በዓመት ይረሳል፡፡ ሕይወት በየፈርጁ ነው፤ የሞተ ይረሳል -ያልሞተ ኑሮውን ይቀጥላል፡፡ በሞተ ሰው ምክንያት ሕይወት ቀጥ አትልም – እንደኢትዮጵያ፤ እኛ ከመለስ ሞት በፊት እንደነበርነው ቀጥ ብለን አለን – እንዲያውም ብሶብን፡፡ በሞተ ማላዘን የጤናማነት ምልክት አይደለም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መለስን ከልባው ወደውት አይመስለኝም – ለማስመሰል ነው፡፡ እንደታዘብኩት በርሱ ስም ልጁን የሚጠራ እንኳን አልገጠመኝም፡፡ ይህ በራሱ የሚያሳየው እርሱን የወደዱት ለጥቅማቸው እንጂ ማፈሪያቱን እንደማይክዱት ነው፡፡

ደግሞም… የዓላማና ግቡ ዝርዝር … የዚህ ሚኒስትር መ/ቤት ራዕይ …. ዓላማዎች …. ግብ …. የሥነ ምግባር መርሆዎች … ታማኝነት፣ ግልጽነት፣ ሃቀኝነት፣ ተጠያቂነት፣ ቅንነት፣ ለሕዝብ ታዛዥነት፣ … አቤት አቤት የሚነበበው ጉድ! በተግባር ግን ሁሉም ከዜሮ በታች፡፡ መጥኔ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን! ሶማሌና ጂቡቲ በስንት ጣማቸው! ምነው ጂቡቲያዊ ወይም ፊጂያዊ ወይንም ዶሞ ሃይቲያዊ ሆኜ በተፈጠርኩ ኖሮ፡፡

ለማንኛውም የቤቴን የሰሞኑን አዲስ ሹመት ልግለጽላችሁና ልሰናበት፡፡ መቼም ጊዜው የቀልድ ሆኗል፡፡ የቤተሰቤ አባላት ለጊዜውና ለአሁኑ ስድስት እንደሆኑ ይታወስልኝ – ቡችዬንና ውርየን ጨምሮ፡፡

 

በህገ መንግሥታችን አንቀጽ 39 መሠረት የነፃነት ዘለቀ ቤት አዲሱ የሥልጣን መዋቅር

 

ዶክተር ነፃነት ዘለቀ

የቤቱ የውጭ ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

ረዳት ፕሮፌሰር ሸዋርካብሽ እርገጤ

የቤቱ የቤት እመቤትነት ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ወጣት ዘገየ ነፃነት (ወንድ ነው)

የቤቱ ፀረ-ኢሣት አባላትን የማብዛትና ፎክስሙቪስን የማዘውተር ንዑስ የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ሕጻን ደምመላሽ ነፃነት

የቤቱ የሞሰብና ድስት ጉዳዮች ንዑስ የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ችሎማደር (ቡቺ)

የግቢው ፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች የሥራ ሂደት ባለቤት

በድምጽሽ ይራዱ (ውርዬ)

የቤቱ ሞሰብ ገልብጥ ዐይጦችን አባራሪ ግብረ ኃይል የሥራ ሂደት ባለቤት

 

ማሳሰቢያ፡- ይሄ አበበ ገላው የተባለ ልጅ ነገር መፈልፈል ይዟልና ለርሱ ሸር ላለመመቸት ስል              የኔን የዶክትሬት ማዕረግ ያገኘሁት እንደወያኔዎቹ ከሴንቸሪ ዩንቨርስቲና ከመሳሰሉት           ዲግሪ ቸብቻቢዎች በዶላር ገዝቼ ሣይሆን በላቤና በጥረቴ በቤተሰብ ጉባኤ የተሰጠኝ            መሆኑን እንዲሁም ክብርት ባለቤቴ በሆም ኢኮኖሚክስ የረ/ፕሮፌሰርነትን ማዕረግ ከዚሁ       ቤተሰባችን ያገኘች መሆኗን ልገልጽ እፈልጋለሁ(አይ የምትጠምቀው ጠላ – የዶሮ ዐይን              ይመስላል፡፡)

ዘግይቶ የደረሰኝ አዝናኝ ወሬ!

የወያኔ የምርጫ ቡችሎች እንዲህ አደረጉ አሉ፡፡ በዚያን ሰሞን ደብረ ዘይት አካባቢ የምግብ ዘይትን ከየሱቁ ያጠፋሉ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሲንጫጫ በየቀበሌው ያመጡና ሕዝቡ ወደነዚያ ቀበሌዎች በመሄድ ዘይት እንዲገዛ ያስነግራሉ፡፡ ነዋሪው ወደየቀበሌው ሲሄድ ግን “የምርጫ ካርድ የማይወስድ ዘይት አይሰሸጥለትም” ይሉና በግድ ካርድ ያስወስዳሉ፡፡ ይቺ ናት ምርጫ፡፡ ሕዝብን እያስራብክና በመሠረታዊ ፍላጎቱ እየመጣህ ምርጫ ካርድ እንዲወስድ ማስገደድ፡፡ ከዚያም በኮሮጆ ገልባጭ ልዩ ኃይል የሕዝብን ካርድ ለወያኔ ማዛወር፡፡ ከዚያም የግፍ አገዛዝህን መቀጠል፡፡ ቀልደኞቹ የወያኔ የምርጫ አስፈጻሚ ካድሬዎች ልክ ይሕዋ ምሥክሮች     ይቺን ጽሑፍ አይተዋታል?” እያሉ ሃይማታውን ለማስፋፋት እንደሚሞክሩት የወያኔ ጭፍሮችም በየመንገዱና በየጥጋጥጉ በየመውጫና መግቢያ በሮቸ እየጠበቁ “የምርጫ ካርድ ወስደሃል?” እያሉ ሲያሰለቹ ብታዩ ደግሞ አዲስ ሃይማኖት ተመሠረተ ወይ ትላላችሁ፡፡ የጉድ ሀገር፡፡ አፉን ከፍ በሚውል የምርጫ ካርድ መውሰጃ ጣቢያ ስንትና ስንት ሚሊዮን ሕዝብ መመዝገቡን ስንሰማ የወያኔውን ውሸት ለከት የለሽነት እንረዳለን፡፡ በ97 ያ ሁሉ ሕዝብ ተመዝግቦ 26 ሚሊዮን ነበር የተባለው – እርግጥ ነው ያ ቁጥር እውነትም ሊሆን ይችላል፡፡ በቀጣዩ የ2002 “ምርጫ” ግን ጥቂት መቶ ሺዎችን መዝግበው ሲያበቁ በሀገሪቱ 32 ሚሊዮን መራጭ እንደተመዘገበ ቅንጣት ሣያፍሩ በሚዲያቸው ለፈፉ፡፡ ቁጥር የሚያውቁ አይመስሉኝም እነዚህ ደነዝ ወያኔዎች፡፡ ከሁሉም የበደላቸው እርጉሞች፡፡

 

 

 

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop