January 7, 2015
3 mins read

ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፥ – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፪ሺህ፯ኛ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

ነገ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድራችን በአካል የተገለጸበትን ፪ሺህ፯ኛ ዓመት እናከብራለን። እግዚአብሔር ወልድ በምድር በአካል ከእኛ ጋራ በታየበት ዘመን ያስተማረን ትልቁ ቁምነገር ፍቅርን ነው። በተቃራኒው እኛ የዘመኑ ኢትዮጵያውያን በመካከላችን ፍቅር ጠፍቶ እንበጣበጣለን። በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሌላው ቀርቶ በእምነቱ ሥፍራ እንኳን ሰላም ካጣ ቆይቷል። የዚህ ሁሉ ብጥብጥ እና ፍቅር መጥፋት ምንጩ የትግሬ-ወያኔ እና እሱን መሰል ፀረ-ኢትዮጵያ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች እና ልሂቃን ናቸው። ስለዚህ እኒህን የጥፋት ኃይሎች በጋራ ትግላችን ግስጋሴያቸውን ልናቆመው ይገባል። ክርስቲያኖች ከኢየሱስ ክርስቶስ ምሣሌ መማር ካልቻልን እና ካልተፋቀርን መከራችን ይረዝማል፣ ሥቃያችንም አያባራም። የትግሬ-ወያኔ እና መሰል አጋሮቹም እንደሠለጠኑብን ዘመናት ይቆጠራሉ።

ለዚህ መፍትሔው ፈጣሪያችን በፍርድ ቀን ሲመጣ የሚጠይቀንን ጥያቄዎች፥ ማለትም፦ “ስታመም ጠይቃችሁኛል? ስራብ አብልታችሁኛል? ስታረዝ አልብሳችሁኛል? ስታሠር አስፈትታችሁኛል? ስጠማ አጠጥታችሁኛል?” የተባሉትን ሠርክ እናስታውስ፣ በተቻለንም መጠን የሕይዎት መመሪያዎቻችን ለማድረግ እንጣር።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያንን እንኳን ለበዓለ-ልደቱ አደረሣችሁ፣ አደረሰን፣ ይላል። በዚህ አጋጣሚ ድርጅታችን ማስተላለፍ የሚፈልገው ጥሪ፦ ባለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት በትግሬ-ወያኔ ግፈኛ እና ናዚያዊ አገዛዝ ከምድረ-ገፅ የጠፉትን በቁጥር ከ፭(አምሥት) ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮች እናስታውስ። በገዛ አገራቸው ከቅኝ ተገዢዎች በከፋ መልክ ሰብዓዊ መብቶቻቸውን የተነጠቁትን ኢትዮጵያዊ ዐማሮች እንታደግ።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop