August 11, 2014
10 mins read

የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት ለማጨናገፍ ችኮላው ለምን?

አልዩ ተበጀ

አብዛኞቻችን የአንድነት እና መኢአድ ዉህደት ተጠናቆ፣ በአዲስ መንፈስ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄን እንቀጥላለን የሚል ተስፋና ጉጉት ነበረን። የኢትዮጵያዉያንን መተባበር የማይፈልገው ሕወሃት/ኢሕአዴግ፣ በሚቆጣጠረው ምርጫ ቦርድ አማካኝነት፣  ዉህደቱን ለማጉዋተት እንደተለመደው መስራት ጀመረ። «መኢአድ ያላሙዋላቸው ወረቀቶች አሉ» በማለት ዉህድቱን ማድረግ እንደማይችል አሳወቀ። (የተለመደው የማሰናከል እጁት ተግባር) መኢአድ ሕዝብ ያውቀው ዘንድ፣  ያለውን ሁኔታ ለማሳወቅ መግለጫ አወጣ። በጉዳዩ ላይም ከምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባዎች በማድረግ ከመፍታት ጀምሮ ሌሎች አማራጮችን እየፈለገ ዉህደቱን ለማሳካት በስፋት መንቀሳቀስ ጀመረ።

ከመኢአድ ጋር ዉህደት ለማድረግ ከ2 ፣ 3 አመታት በላይ ንግግሮች ሲደረጉ ነበር። አገዛዙ የደነቀረዉን ትንሽ እንቅፋት ለማስወገድ አንድ ወይንም ሁለት ሳምንት መጠበቁ ችግር የሚኖረው አይመስለኝም። ነገር ግን እንደ አንድነት ደጋፊ እጅግ በጣማ ያሳዛነኝ እና ልቤን ያደማው ክስተት ተፈጸመ።

የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ለብዙ አመት የተደከመበትን፣ የዉህዱ ሰብሳቢ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሃብታሙ አያሌው የታሰሩበትን ፣ በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በጉጉትና በተስፋ የምንጠብቀዉን፣ ምርጫ ቦርድ ካስቀመጣት ትንሽ መሰናክል ዉጭ፣ ሁሉም ነገር ያለቀለትን፣ የመኢአድ እና የአንድነት ዉህደት እንደማይፈልጉ በመገልጽ የዉህደት አመቻች ኮሚቴን እንዳፈረሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በሚኔሶታ  ቤተክርስቲያን ስሄድ ፣ የአንድነት ድጋፍ ድርጅት አስተባባሪ መሆኔን የሚያዉቁ ሲያገኙኝ ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር የሚያደርገውን እንቅስቅሴ እንደተደሰቱ ነበር በስፋት የሚነግሩኝ። ህዝቡ፣ ደጋፊው ስሜቱ በጣም ተጋግሎ ነበር። በአሁኑ ጊዜ የሕዝቡ መከራ በበዛበት፣ አንድነት ፓርቲ ሌሎችን እያሰባሰበ፣ የተጀመረዉን የሚሊዮኖች ንቅናቄ ይቀጥላል ብለን ስንጠብቅ፣ ያለ ምንም በቂ ምክንያት ሕወሃት/ወያኔ ትንሽ መሰናክል ስላስቀመጠ ብቻ ፣ በየክልሉ ያሉ አባላትና ደጋፊዎች እየፈለጉት፣ ዉህደቱ እንዲቆም ማድረግ በጣም፣ እጅግ በጣም ትልቅ በደል ነው።

በአንድነት እና በመኢአድ መካከል፣ ዉህደት እንዲደረግ ቁልፍ ሚና ከተጫወቱት ወገኖች መካከል አንዱ፣ በሕወሃት/ኢሕአዴግእጅ ስር ታስሮ የሚገኘው ሃብታሙ አያሌው ነው። ሃብታሙ አያሌ ከኢንጂነር ግዛቸው ጋር ብዙ ይከራከር የነበረና ኢንጂነሩም ለሚሰራው ስራ መሰናክል ሆነውበትምእንደነበረ ይታወቃል።  ከአምስት አመታት በፊት፣ ኢንጂነር ግዛቸው ከትናትናው “ዝምአንልም” የዛሬው በአብዛኛውየሰማያዊ አመራሮች አባል ከሆኑት ጋር ተመሳሳይ ችግር እንደነበረባቸው የሚታወቅ ነው:: እነዚህን በርካታ ወጣት የቀድሞ የአንድነት አመራሮችን፣   እንዲሁም እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ያሉትን ማባረራቸው ይታወቃል። ያኔ ፓርቲው ተከፋፍሎ በትግሉና በታጋዮች ሞራል ዘንድ ምን ያህል ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖና ጉዳት እንዳመጣም የሚታወቅ ነው።

ኢንጂነር ግዛቸው የመኢአድ እና የአንድነት ዉህደት እንዲኖር ፍላጎት  ብዙ እንዳልነበራቸው የሚናገሩ አሁንም ጥቂቶች አልነበሩም። (ዉህደቱ ከተሳካ ሊቀመንበር የመሆን እድላቸው በጣም የመነመነ በመሆኑ) የምርጫ ቦርድንም ተንኮል ሳያጡትቀርተው አደለም፣  ምርጫ ቦርድ ለአገዛዙ እንደሚሰራ እያወቁ፣ ምርጫ ቦርድ የሚያቀርባቸውን እንቅፋቶች እንደ ሰበብ በመቁጠር የዉህደት አመቻች ኮሚቴዉን ማፍረሳቸው፣  እንደ አንድ የአንድነት ደጋፊ ልረዳው የማልችለው ጉዳይ ነው። በሚሊዮኖች ዘመቻ የተነሳሳዉን፣  በሚሊዮኖች የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ  ወኔ ለማኮላሸት፣ ከትግሉና ከአገር ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ስልጣን ብቻ በመፈለግ ለሕዝብ ጥያቄ ንቀታቸውን በመግለጽ ትልቅ ጥፋት እያደረጉ ናቸው።

ሕዝቡ አብሮ መስራትን ይፈልጋል። የመኢአድ እና አንድነት ዉህደትን ይፈልጋል። የማይፈልጉት አምባገነኖች ብቻ ናቸው። ኢንጂነር ግዛቸውና ለርሳቸው ድምጽ የሰጡ የአንድነት የምክር ቤት አባላት፣ «ሕወሃት/ሕአዴግን የሚያስደስተዉን ነው ወይስ ህዝቡ የሚያስደስተው ማድረግ የምትፈልጉት ?» ለሚለው ጥያቄ በግልጽ ሊመልሱ ይገባል።

በኢንጂነር ግዛቸው የተወሰደው ሕወሃት/ሕአዴግን ብቻ የሚጠቅም እርምጃ በአስቸኩዋይ ተቀልብሶ ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር የጀመረዉን ዉህደት አጠናቆ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ አፍሮ፣ ትግሉ ወደፊት መዉሰዱ ብቸኛ አማራጭ ነው።

ኢንጂነር ግዛቸው ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ችግር አላቸው። አሁን ደግሞ ከመኢአድ ጋር ከተጣሉ፣ ታዲያ እመራዋለሁ የሚሉት አንድነት ከማን ጋር ነው አብሮ የሚሰራው ? በዘር ከተደራጁ ድርጅቶች ጋር ? ወይስ ተመልሰው ወደ መድረክ በመግባት የ2002ቱን ሩጫ ሊደግሙልን ነው ?

የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች፣ እኛ በሚሊዮኖች የምንቆጠር ነን። ወሳኝ ጊዜ ላይ ነው ያለነው። ጥቂቶች ንቅናቄያችንን ወደሁዋላ ሊጎትቱ አይገባም።በመሆኑም ከመቼዉም ጊዜ በላይ ድምጻችንን ማሰማት አለብን። የአንድነት ፓርቲ የኢንጂነር ግዛቸው ብቻ ሳይሆን የሚሊዮኖች ነው። በደሴ፣ በጎንደር፣ በአርባ ምንጭ፣ በናዝሬት፣ በባህር ዳር፣ በአዳማ ..የምንኖሩ የአንድነት አባላትን የክልል አስተባባሪዎች፣ በዉጭ አገር ያለን  ድምጻችንን እናሰማ። በየአካባቢያችን ከመኢአዶች ጋር አብረን በስራ ተዋህደን እየሰራን ነው። አብረን እየታሰርን፣ አብረን እየተደበደብን  ነው። አገዛዙ ከሚያደርገው በማይተናነስ ሁኔታ ኢንጂነር ግዛቸውና ከርሳቸው ጋር የቦደኑ ጥቂቶች እንዲከፋፍሉን መፍቀድ የለብንም። አንድነታችንን ለማሳየት የምርጫ ቦርድ ወረቀት አያስፈልገንም። ትግሉን ተያይዘን መቀጠል አለብን። ትግሉ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ነው። ትግሉ ወደፊት እንጂ ወደ ሁዋላ አይሄድም ።

 

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop