June 19, 2011
16 mins read

እነደ ዔሳው ብኩርናቸሁን ለሸጣችሁ የኪነ-ጥበብ ሰዎች (ከአሮን)

ኪነጥበብ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያላትን ሚና ራሳቸው የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹ ቢነግሩን የተሻለ ይሆን ነበር።
ዛሬ ግን በአዲስ አበባ ከተማ የታዘብኩት የአርቲስቶች ትያትር አንድ ነገር እንድል ግድ ብሎኛል።ኪነጥበብ የአንድን ማህበረሰብ የነጻነት መንፈስና የሞራል እሴቶች ለመገንባት የምትጫወተውን ሚና ለአርቲስቶቹ ማስታወስ ተገቢ ሁኖ አግኝቼዋለሁ።አንድ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ወደዚህ ክቡር ሙያ ሲሰማራ ማህበረሰቡ በሚኖርበት ጉድፍ ውስጥ ሊኖርበት ሳይሆን ያንን ጉድፍ አጽድቶና አስተካክሎ ንጹህ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የላቀ ሚና ለመጫወት ነው።የኪነ ጥበብ ሰው ክብርና የህዝብ ፍቅር የሚኖረው በማህብረሰቡ ውስጥ የሚታዩ ነውሮችንና ጉድፎችን ሲነቅፍና ለማረም ሲሞክር እንጂ በዚያ ነውር ውስጥ ራሱ ተዘፍቆ ሲኖርበት አይደለም።
ሰሞኑን የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እንወክላለን ያሉ ግለሰቦች ከዘረኛውና ከዘራፊው መለስ ዜናዊ ጋር ተሰብሰበው የወርቅ ብእር ሲሸልሙት በትዝብት ተመልክተናል።ይህ አስገራሚም አሳዛኝም ድርጊት ነው።ለእነዚህ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ክብራቸውም ሃብታቸውም የኢትዮጵያ ህዝብ ነበር።ነፍሱን ይማረውና አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ሃብቴ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ሌላ ሃብት የለኝም ብሎ ሲናገር ብዙ ግዜ ሰምተነዋል።ይህ ክቡር የኪነ-ጥበብ ሰው ወገኖቹ ሲራቡ ዋይ ዋይ ብሎ አልቅሶ፤ሲሰደዱ ልቡ አዝኖ፤በአገሩ ላይ የተነሱ ጠላቶቹን በሚችለው ተሟግቶ ለአገሩ ያለውን ፍቅር አሳይቶ አልፏል።መለስ ዜናዊን ከመሰለ ነውረኛ ዘረኛና ዘራፊ አምባገነን ለሚወረወርለት ፍርፋሪ ህዝቡን ሳይለውጥ እንደተወደደ ተሰናብቷል።
እንዲህ ዓይነት የጥበብ ሰው ሞተ ብለን አንናገርም። የሞተውስ የንጹሃን ደም ከአዲስ አበባ ምድር ወደ ሰማይ ሲጮኽ ሰምቶ እንዳልሰማ የሆነው ነው።የሞተውስ ከነ ህጻን ነብዩ ገዳይ ጋር ማእድ ቀርቦና በብዙ አቤሎች ደም ላይ ተረማምዶ ከነፍሰ ገዳዮች ጎን የተቀመጠው ነው።
ዛሬ በዝህ ክፍ ዘመን ህዝባቸውን የማያውቁ ያከበራቸውን ህዝብ በሰላሳ ዲናር የሚለውጡ መንፈሰ ደካማ አርቲስቶችን ለመታዘብ በቅተናል።ትላንት ጠንቋዩንና እንደርቢ መቺውን አጅበው አረፋ እየደፈቁና በየግንባራቸው ላይ የጥቁር ዶሮ ደም እየተቀቡ ከጠንቋዩ ጋር ሲተውኑ ከርመዋል ተብለው መታማታቸውን ሰምተን በእጅጉ ተግርመን ባለንበት በዚህ ግዜ የመለስ ዜናዊ ማእድ ታዳሚ ሆነው መመልከታችን ከአስገራሚ በላይ ሆኖብናል።እነዚህ የማህበረስቡን ድክመትና በማህበረ ሰቡ ውስጥ የሚፈጸሙ አስነዋሪ ነገሮችን ነቅሰው አውጥተው ህዝቡን ማስተማርና ሞራሉን መገንባት ሲገባቸው በዚያ ነውር ውስጥ ተዘፍቀው መኖራቸው የጥበብ ሰውን ሙያና ክብር አዋርደው የት እንዳደረሱት መረዳት አያዳግተንም።
መለስ ዜናዊን አጅበው በዙሪያው የሰፈሩ አርቲስቶች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ጠንቋይ ጥየቃ መሄድ አያስፈልገንም።መለስ ዜናዊ እዚያው በመዲናችን በአዲስ አበባ ውስጥ ንጹሃን ዜጎችን ገድሎ ሜዳ ላይ ሲጥል እነዚህ አርቲስቶች አላዩ እንደሆነ ልናስታውሳቸው ያስፈልጋል።መለስ ዜናዊ የአገሪቷን ዜጎች አስሮ ሲያሰቃይ እነዚህ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የከበሩ አርቲስቶች አልሰሙ እንድሆነ አሁን ልንነግራቸው ይገባል።የአገሪቷ ዜጎች በአገሪቷ ውስጥ የመናገር የመሰብሰብ የመደራጀትና መሪያቸውን የመምረጥ መብታቸው በመለስ ዜናዊ መታገዱን እነዚህ አርቲስቶች አላዋቁ እንደሆነ አሁን ልናሳውቃቸው እንገደዳለን።
መለስ ዜናዊ ማን እንደሆነ ገና አልገባቸው እንደሆነ ደግሞ መለስ ዜናዊ ማለት የአማራ ጠላት ነው።መለስ ዜናዊ ማለት የኦሮሞ ጠላት ነው።መለስ ዜናዊ ማለት የጋምቤላዊያን ጠላት ነው።መለስ ዜናዊ ማለት የኦጋዴናዊያን ጠላት ነው።መለስ ዜናዊ ማለት የትግሬ ጠላት ነው።መለስ ዜናዊ ማለት የኢትዮጵያ ጠላት ነው።መለስ ዜናዊ ማለት ዘራፊ ዘረኛና ፍጹም ውሸታም ሰው ማለት ነው።ኢትዮጵያችንን በሚችለው መንገድ ሁሉ እያዋረደ ካለ ከዚህ ግለሰብ ጋር መሰለፍ ይቅር የሚያሰኝ ተግባር አይደለም።
በዚህ ግለሰብ መሪነት 8.4 ቢልዮን ዶላር ከአገሪቷ ወጥቶ በውጭ ባንኮች ሲጠራቀም በአዲስ አባባ ከተሞች ውስጥ ከውሻና ከድመት ጋር እየተጋፉ ምግብ የሚለቃቅሙትን እነዚያን ህጻናት እርቲስቶቹ አላዩዋቸው እንደሆነ ዞር ብለው እንዲመለከቷቸው እመክራቸዋሁ።ይህ ሁሉ ችጋር በዚያች አገር ውስጥ እያለ መለስ ዜናዊ ለምን 8.4 ቢሊዮን ዶላር ካገር እንዲወጣ አደረገ ብለው መጠየቅ ባይችሉም ለራሳቸው እንዲያስቡ ላሳስባቸው እወዳለሁ።ይህን ያክል ዝሪፊያ በአገሪቷ ውስጥ እንዲፈጸም የሚመራውን ይህን ሌባ ሰው በወርቅ የተለበጠ ብእር ከመሸለም ይህ ዝርፊያ እንዴት እንደተፈጸመ ይህን ግለሰብ መጠየቅ ቢችሉ ለህዝባቸው አንደበት በሆኑት ነበር።ያን ግዜ ላከበራቸው ህዝብም ውለታውን በመለሱለት ነበር።
ይህ ዘረኛና ዘራፊ ሰው ሳይመረጥ ተመርጬአለሁ ብሎ ስልጣኑን በአፈ ሙዝ አስገድዶ ወስዶ በመንግስቱ ኃ/ማሪያም ዙፋን ላይ መቀመጡን አርቲስቶቹ አላወቁ እንደሆነ አሁን እንግራቸዋለሁ።ይህ ከመንግስቱ ኃ/ማሪያም በከፋ ሁኔታ በሰበብ አስባቡ ንጹሃን ዜጎችን እየፈጀ በንጹሃን ደም የታጠበን እጅ መጨበት ጠንቋይ ቤት ከመመላለስ በባሰ ሁኔታ የሚያሳፍርና የሚያዋርድ ተግባር እንጂ የሚያኮራ አይደለም።ዛሬ መለስ ዜናዊን የወርቅ ብእር የሸለሙት በኪነ-ጥበቡ ጎራ የተሰበሰቡ እነዚህ ግለሰቦች በቃሊት እስር ቤት በዘራቸው ምክንያት ብቻ ታስረው ብልታቸው እየተቀጠቀጠ የሚሰቃዩ ወገኖቻቸውን ሰምተው ያንን ቢያስተጋቡ እንዴት መልካም በሆነ ነበር።በዚሁ እስር ቤት በመለስ ዜናዊ በአሸባሪነት ተከሰውና የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ማታ ማታ አይናቸው በጨርቅ እየተሸፈነ በኤሌክትሪክ ሽቦ ጡታቸውን ለሚገረፍት ለወ/ሮ እማዋይሽ ድምጽ ቢሆኗቸው ኑሮ የህዝባቸው የበኩር ልጅ ሆኑ ብለን እናመስግናቸው ነበር።እነዚህ መንፈሰ ደካማ ግለሰቦች ግን እንደ ዔሳው ለጣፋጭ ምሥር ወጥ ብኩርናቸውን አሳልፈው የሸጡ ስለሆነ ህዝቡ የሰጣቸውን ክብር ሊነሳቸው ግዜው አሁን ነው።
መለስ ዜናዊ ከምእራባዊያን ለሚያገኘውና በውጭ አገራት ለሚያጠራቅመው ገንዘብ ሲል ሶማሊያ ላይ ሰዶ ያስጨረሳቸውን ዜጎች ቁጥር አልናገረም ማለቱን እነዚህ የወርቅ ብዕር የሸለሙ ግለስቦች እንዲያውቁት እንፈልጋለን።መለስ ዜናዊ እንዲህ ዓይነቱን ወረራ የፈጸመበትን ምክንያትና የተሰዋውን ኢትዮጵያዊ ሁኔታ ለሚመራው ህዝብ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ ሲኖርበት አላደረገም።ለምን ቢባል ህዝቡን ስለሚንቅ ብቻ ነው።ከሚናቁትም ህዝቦች መካከል እነዚህ የወርቅ ብእር የሸለሙት ግለሰቦች ይገኙበታል።እንዲህ ለሚንቃቸውና ቅንጣት ታክል ፍቅርና ክብር ለማያሳያቸው ግለሰብ እውቅና መስጠት የሸላሚዎችን የወገን ፍቅር ማጣት ቁልጭ አድርጎ ከማሳየት በቀር የሚናገረው ሌላ ነገር የለም። የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ነን ባይ እነዚህ ግለሰቦች ለሚንቃቸውና ቅንጣት ታክል ፍቅር ለማያሳቸው ለመለስ ዜናዊ የሰጡት የወርቅ ብዕር የሚያስተላልፈው መልእክት ቢኖር እንኳን ናቅከን፤ እንኳን አዋርደከን፤ እንኳን ነጻነታችንን ገፈህ ከሰው ተራ አወጣኸን ከማለት የዘለለ ሌላ ትርጉም የለውም።
ይሄንን ሳንረሳ መለስም የሄዳል ህዝቡም የአገሩ ባለቤት ይሆናል።ያን ግዜ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ነን ያሉና የወርቅ ብዕር የሸለሙት ለምን እንደሆነ ይነግሩናል።
የኪነ-ጥበብ ሰዎች ድምጽ ለሌለው ህዝብ ድምጽ ሁነው የህዝቡን በደለና ስቃይ ኪነ-ጥበባዊ ለዛ ሰጥተው የደፈረሰውን ለማጥራት መሞከር ነበረባቸው።የዘመኑ የአገራችን አንዳንድ አርቲስቶች በመለስ ዜናዊ መሪ ተዋናይነት የሚሠራውን ትራጄድ አጅበው እየተጫወቱ ነው።መለስ ዜናዊ የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ ሲያፈስ እነዚህ አርቲስት ነን ባዮች ደግ አደረክ ብለው ሸልመውታል።መለስ ዜናዊ የአገሪቷ ዜጎች እንዳይጽፍ፤እንዳያነቡ፤መረጃ እንዳያገኙ ሲያግድ አበጀህ ሲሉ የወርቅ ብእር ሸልመውታል።መለስ ዜናዊ ዜጎች በአገራቸው በሰላም እንዳይኖሩ እያሸበረ ከትውልድ አገራቸው ወገኖቻችንን ሲያሳድዳቸው እነዝህ ቲያትረኛ ግለሰቦች መወድስ አቅርበውለታል።ይህ የሚያመስገናቸውም የሚያስከብራቸውም ተግባር አይደለም።

ስለሆነም ለእነዚህ መንፈሰ ደካማ ግለሰቦች ህዝቡ የሰጣቸውን ክብር መንፈግ አለበት።እነዚህ ሰዎች ትያትር በመስራት፤ድራማ በመጫወት፤ፊልም በመሥራት ለህዝብ እያቀረቡና ገንዘብ እያገኙ ሆዳቸውን ሞልተው የሚኖሩ ናቸው።እንዲህ ዓይነት ሥራዎቻቸውን ካለመግዛት አንስቶ ለህዝብ ወገንተኝነታቸውን እስከሚያስዩ ድረስ የሚቻለውን ርምጃ በመውሰድ ለሌው ትምህርት እንዲሆን ማድረግ ይገባል።
በመጨረሻም በመለስ ዜናዊ ዙሪያ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሰባሰባችሁ የዚህ የተከበረ ሙያ ባለቤቶች ነን ያላችሁ እንድታውቁት የሚያስፈልጋችሁ ነገር ቢኖር መለስ ዜናዊ ነገ ተነቅሎ ወደዚያ የሚጣል የአገራችን የአንድነት የሠላምና የእድገት እንቅፋት የሆነ ክፍና ጨካኝ ፍጡር መሆኑን ነው።ዛሬ በሰላሳ ዲናር አሳልፋችሁ የሸጣችሁት ህዝብ ነዋሪ ነው።እናንተ በጭለማም ሆነ በብርሃን የሰራችሁት ሥራችሁ ተከድኖና ከህዝብ ተሰውሮ አይቀርም።ዛሬ እንዲከደንላችሁ የፈለጋችሁት ነውር ካለ ነገ መገለጡ አይቀርም።ከህዝብ አብራክ ወጥታችሁ በህዝብ ገንዘብ ከብራችሁ መልሳችሁ ከህዝቡ ጠላት ከሆነ ሰው ጋር ማበራችሁ በታሪክ ተወቃሽ የሚያደርጋችሁ መሆኑን ነግሬአችሁ አበቃለሁ።
ኢትዮጵያችንን እግዚአብሄር ይባርክ !!!

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop