February 10, 2013
7 mins read

“ማህበረ ቅዱሳንን” ያያችሁ!

ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
በአንድም በሌላም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እምነት ተከታይ ሆኖ ራሱን “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት የሚጠራ ነፍሰ ገዳይ ሳለ መንፈሳዊ ጭምብል አጥልቆ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሆነ ንዋያተ ቅድሳትና የተለያዩ ቅርሳቅርሶች ከዬ ገዳማቱና አድባራቱ እያደነ ከመዝረፍና ከመመዝበር አንስቶ ለዓላማው ያልተንበረከኩ ሊቃነ ጳጳሳት: ካህናትና ዲያቆናት በማሳደድና ነፍስ እስከ መግደል ድረስም የተሰማራ የጥቁር ራስ ስብስብ መሰሪ ድርጅት የማያውቅ ሰው ይኖራል የሚል እምነት የለኝም፡፡
በእርግጥ ማህበሩ በመላ ሀገሪቱ ባሰማራቸው ለዓመታት በስለላ የሰለጠኑ አባላቱና በተለያዩ የመንግስት የሃላፊነት ቦታዎች የተቀመጡ ግለሰቦች ጭምር በመጠቀም “ማህበረ ቅዱሳን የተቃቃመው ጥንታዊትና ሐዋሪያዊት የሆነችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ስርዓተ አምልኮ ለትውልድ ማስተላለፍ ነው፡፡ ዓላማውም አበው ትተውልን ያለፉት ትውፊት፡ ደንብና ስርዓት ጠብቆ ማስጠበቅ ነው።” ሲሉ በነጋ በጠባ ቁጥር ሳይታክቱ እንዲለፍፉ በማድረግ በሰራውና እሁንም ድረስ እየሰራው ባለ ፕሮፖጋንዳ “ማህበረ ቅዱሳን” ሲባል “ብዙዎቻችን” የምናወቀው ሃጢአት የማያውቃቸው፡ ቅዱሳን፡ ንጹሐንና የመላእክት ዘር ያለባቸው ንኡዳን አድርገን በመቁጥር ነው። እንግዲህ ይሄው ቀኑ ደረሰና “የቤተ ክርስቲያን ስርዓትና ትውፊት ጠብቆ ለማስጠበቅ የቆምኩ መንፈሳዊ ማህበር ነኝ” እያለ ሕዝብ ሲያደኖቅር ዓመታት ያስቆጠረ ድርጅት የሃይማኖት መሪዎች እየፈጸሙት ላለው ጥፋት ይሄው ጭራሽ መራጭና አስመራጭ ሆኖ በመሪ ተዋናይነት ተሰልፎ ሽርጉድ እያለ ይገኛል። (ስም ማጥፋት ወይንም ደግሞ ተራ ውንጀላ አይደለም እየተባለ ያለው ለማረጋገጥ ከተፈለገ የሚቀጥለውን ሊንክ በመጨቆን እውነቱን ሊያረጋግጡ ይችላሉ።

&ውድ አንባቢ! በእርስዎ ቤት “ስርዓት መጠበቅ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቃሉም እንዴት እንደሚተረጉሙት እርግጠኛ ባልሆነም በበኩሌ ግን፡
 ስርዓት መጠበቅ ማለት ስርዓት ማፍረስ ከሆነ፤
 ስርዓት መጠበቅ ማለት ቀነኖ መጠስ ከሆነ፤
 ስርዓት መጠበቅ ማለት የቀደመውን እያፈረስክ አዲስ መስራት ማለት ከሆነ፤
 ስርዓት መጠበቅ ማለት እንዳሻህ መሆን ከሆነ፤
 ስርዓት መጠበቅ ማለት ለሕግ አለመገዛት ማለት ከሆነ፤
 ስርዓት መጠበቅ ማለት የወደድከውን ማድረግ ማለት ከሆነ ቀድሞውንስ ትውፊት አክባሪ ስርዓት ጠባቂ/ጠበቃ ብሎ ማህበር ማቋቋም ለምን አስፈለገ? ብዬ እጠይቆት ዘንድ ግድ ብሎኛል። መቼም ስርዓት ሲጣስ፡ ቀኖና ሲፈርስና የአበው ትውፊት ሲዘነጋ የሕግ ያለህ! በማለት “ስርዓት ለመጠበቅ፤ የአበው ሐዋሪያዊ ግብር ለመዘከር እንዲሁም የቅዱሳን ትውፊት ለትውልድ ለማስተላለፍ የቆምኩ ነኝ ባይ ማህበር “ማህበረ ቅዱሳንን ያያችሁ!” በማለት ጮክ ብዬ ስጮክ አብረውኝ “ማህበረ ቅዱሳንን” ፍለጋ ለመውጣታቸው አልጠራጠርም፡፡ ነገሩ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የመታደግ ጉዳይ ነውና!

“ማህበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ እቺ ቤተ ክርስቲያን ድሮ ድምጥማጥዋ ጠፍታ ነበር” ለምትሉ ተሳላሚዎች “ቤተ ክርስቲያን” ከዚህም በላይ መበጣጠስ ነበረባት/አለባት ከሆነ ቁጭታችሁ “አልተሳሳታችሁም” ከማለት ውጭ በመላእክት ቋንቋም ቢሆን መግባባት ስለማንችል ፍርዱ ለአንባቢ ትቸዋለሁ። በተረፈ ይህ ሀገር የመበተን እንዲሁም ትውልድን የማኮላሸት ልዩ ተልኦኮ ይዞ የተነሳ ማህበር በየትኛው ህገ ደንብና ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሰረት ፓትሪያሪክ ለመሾም በሚቋቋመው ኮሚቴ ውስጥ ሊገባ እንደቻለና እንደገባም ሌላ አዲስ አባባ በሚገኘው የክፋት ሁሉ ማከፋፈያ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አከባቢ የነገሰውን ስርዓት አልበኝነትና የተንሰራፋውን የውንብድና ድርጊት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። እዚህ ላይ ግልጽ ማድረግ የምፈልገው ነጥብ ቢኖር እንደው ስንዴውንና እንክርዳዱ መለየት ያቃተው ብዙሐኑ ሕዝብ በሚገባው መልኩ ለመግለጽ ተሞከረ እንጅ “ማህበረ ቅዱሳን” ዛሬ ይህን ቢያደርግ በግሌ ምንም የሚደንቀኝ አይደለም፡፡ እያደረገው ያለው ሁሉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ለማፈራረስ ይዞት የተነሳውን ዓላማ አንዱ ክፍል በመሆኑ ሲፈለግ በትክክለኛ ስፍራው መገኘቱ ለመግለጽ እወዳለሁ። “ማህበረ ቅዱሳን” ይህን ሲያደርግ ደግሞ በፓትሪያሪክ መርቆሬዎስ ለሚመራው በውጭው ዓለም ለሚገኘው ጉባኤ እያስተላለፈው ያለው መልእክትም እንስተዋለን የሚል እምነት የለኝም።

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E- mail- [email protected]
United States of America
February 8, 2013

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop