July 17, 2024
11 mins read

እየተሸረሽረ የመጣው የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ተዓማኒነት

የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን በሌላው የማህበረሰብ ዘንድ ተአማኒነት ያሳጡ ጉዳዮች ፦

( Issues that have made Protestant churches less credible in the eyes of the rest of the community.)

protestantተዓማኒነት ( credibility) የሚለው ቃል የታማኝነትን እና የመታመንን ልቀት ወይም ጥራት የሚያመለክት ቃል ሲሆን፣ ይህም አንድ ሰው ፣ አንድ ድርጀት ፣ አንድ ተቋም ወይም አንድ መረጃን የሚያስተላልፍ ጣቢያ እምነት የሚጣልበት እና ሊታመን የሚገባው መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይህም ተዓማኒነት በተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ማለትም በኅይማኖት ተቋም ፣ በግንኙነት ፣ በንግድ፣ በጋዜጠንነት እና በሌሎችም ዋና ዋና ነገሮች ውስጥ አስፈላጊ ሓሳብ ነው ።

ለተዓማኒነት( credibility) አስተዋፅዖ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ታማኝነት፣ እውቀት፣ ወጥነት፣ ግልጽነት እና አስተማማኝነት የሚሉትን ያካትታል። አንድ ግለሰብ ወይም ተቋም በሆነ ነገር እንደ ተአማኒ ሲታወቅ፣ የበለጠ በሌሎች ዘንድ መታመን፣ መከበር እና እንደ ቁም ነገረኛ ሊወሰድ ይችላል። እምነትን መገንባት ( Building credibility) እና ማቆየት በሌሎች ዘንድ መተማመንን ለመፍጠር እና ከሌሎች ጋር አወንታዊ ግንኙነቶችን ለመፍጠር ወሳኝ ጉዳይ ነው።

ተዓማኒነት በብዙ ምክንያቶች ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ ነው። ቤተ ክርስቲያን በሌላው የማህበረሰቡ አካላት ዘንድ ተዓማኒነት ያላት ስትሆን እንደ ተቋም የነቢይነት ጽምጿ ፣ ትምህርቶቿ፣ እሴቶቿ እና ተግባሯ በአባሎቿም ሆኑ ሌላው የማህበረሰቡ አካላት ተቀብለውት ለመሄድ እድላቸው ሰፊ ነው ። ይህም ብቻ አይደለም ቤተ ክርስቲያን አባሎቿ በሰፊው የማህበረሰብ ህይወት ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ( Influence) እና አስሚታ ( Impact) የመፍጠር እድሏ ከፍተኛ ይሆናል፣ ይህ ሁኔታ ሰዎች እምነት እንዲጥሉባት፣ እርሷንም ለማዳመጥ እና ለመከተል የመነሳሳት እድላቸው ሰፊ ይሆናል።

ቤተ ክርስቲያን በማህበረሰቡ ውስጥ ተዓማኒ ሆና መገኜቷ፣ በአስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ለመናገር እና መመሪያ ለመስጠት የሞራል ሥልጣን ( Moral Authority) ይሆናታል። ታማኝ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ለማህበራዊ ፍትህ፣ ለሰላም እና ርህራሄ ብቃት ይኖራታል። ይህም ብቻ አይደለም ቤተ ክርስቲያን ተዓማኒ ስትሆን እምነት የሚጣልባት፣ አዳዲስንም አባላት የመሳብ እና ነባሮቹን የማቆየት እድሏ ሰፊ ይሆናል ። በአካባቢዋ ያሉ ሰዎችም ሐቀኛ፣ ግልጽ፣ እና በእምነታቸው እና በተግባራቸው እውነተኛ ወደ ሚያዩአቸው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይሳባሉ። በዚህም ምክንያት በውስጧ ቀጣይነት ያለው አባልነት እና እድገትም ( Membership and Growth) ይፈጠራል ።

ይሁን እንጂ ከተዓማኒነቷ ስትጎድል ግን ዳፋው ብዙ ነው። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ጭምሮ አንዳንድ የአፍሪካ አገራት የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት በብዙ ፈተናዎች ምክንያቶች በማህበረሰቡ ዘንድ ተዓማኒነታቸውን ( credibility) እያጡ እንደመጡ ይነገራል ። የአብያተ ክርስቲያናቱን ተዓማኒነት አሳጡ ከሚባለው ዋና ዋና ነጥቦች ውስጥ አንዳንድ ቁልፍ ነጥቦች የሚከተኩት ናቸው፡-

1.የብልጽግና ወንጌል ( Prosperity Gospel)፦ የብልጽግና ወንጌልን የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያናት መልክ ካጠፋና ምስክርነቷን ካጎደፈ ትምህርት አንዱ ነው። ሰዎች አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ይህንን ትምህርት ሊከተሉ ሊያስፋፉም ይችላሉ። ይህ ትምህርት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ተቃራኒ ሆኖ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች መጠነ ሰፊ ቦታ መያዙ፣ በቁሳዊ ሀብት እና በሥጋዊ ደህንነት ላይ አፅንዖት የሚሰጠው የእግዚአብሔር ሞገስ (as signs God’s favor) ምልክቶች፣ ተስፋ አስቆራጭ እንዲሆን አድርጎታል።

በአስተማሪዎቹ ቀመር ለብዙ አማኞች ቃል የተገባላው የገንዘብ እና የብልስግና በረከት ተስፋ ያለመፈጸሙ፣ በስጡ ይሰጣችኋል” ስሌት ብዙ አማኞች ገንዘብ የተበሉ መሆናቸው፣ ብዙዎቹን ፕሮቴስታን ቤተ ክርስቲያኖችን በጥርጣሬ እና በእምነት ማጣት ዐይን እንዲታዩ አድርጓቸዋል። የቤተ ክርስቲያንን ተዓማኒነት አሳጡ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የብልጽግና ወንጌል መምህራን ምዝበራና አጉል ተስፋዎች ናቸው።

  1. የገንዘብ አያያዝ እና ሙስና (Financial Mismanagement and Corruption) የተጠያቂነት እጦት አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ያለ በቂ የተጠያቂነት መዋቅር (Lack of Accountability) መስራታቸው ፣ የሥነ ምግባር የጎደላቸው ድርጊቶች እንዳይታረሙ አስችሏል፣ ይህ የአብያተ ክርስቲያናቱን ታማኝነት አሳጥቷል ከሚባሉት የተጠኑ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው።
  2. የአስተምህሮ ውዥንብር( Doctrinal Confusion) ከቀጥተኛው የክርስትና አስተምህሮ መውጣት እና ግልጽ የሆነ ትምህርትና ግንዛቤን ወደማጣት፣በአማኞች መካከል ግራ መጋባትን እየፈጠረ መምጣቱ የቤተ ክርስቲያንን ተአማኒነት አዳክሞታል። ይህም አንደ አንድ የእምነት መታጣት ምክንያት ተደርጎ ተወስዷል።
  3. . የቤተክርስቲያን መሪዎች የሞራል ውድቀት ( Moral Failures of Church Leaders) ማለትም የመሪዎች የሥነ ምግባር ጉድለትን የሚመለከቱ፣ ቅሌቶች እንደ ምንዝርና ሌሎች የሥነ ምግባር ጉድለት ድርጊቶች ይፋ እየሆኑ መምጣታቸው ብዙዎች የመሪዎችን ቅንነትና ጽድቅ እንዲጠራጠሩ አድርጓቸዋል። ይህ ዓይነቱ የአንዳንድ የፕሮቴስታንትን አብያተ ክርስቲያናትን ሁኔታ ሌሎች በቤተ ክርስቲያን ላይ ተዓማኒነት እንዲያጡ አስችሏቸዋል ተብሎ እንደ ምክንያት ይቀርባል ።
  4. ቅይጣዊነት፣ / አስተቃይጦ ( Syncretism) የክርስትና እምነት ከባህላዊ ሃይማኖቶች እና ልማዶች ጋር መቀላቀሉ። ከመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ስጦታዎች ጋር አመሳስሎ ሌሎች የባህላዊና ሳይንሳዊ ልምምዶችን ( extra sensory perception telepathy፣ hypnotism and mesmerism) እንደመንፈስ ቅዱስ ሥራ ተቆጥረው በስፋት በአገልጋዮች ዘንድ ተግባር ላይ መዋላቸው። ተፈውሳችኋል የተባሉ ሰዎች ሳይፈወሱ መገኜትና መሞታቸው፣ የአብያተ ክርስቲያናቱን ተዓማኒነት በውስጥና በውጭ ባሉት ዘንድ ጎድቶታል።
  5. የፖለቲካ ጥልፍልፍ ( Political Entanglemen)፦ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና የፖለቲካ መሪዎች መካከል ያለው የቅርብ ግንኙነት የሥነ ምግባር አጠራጣሪነትን መፍጠሩ እና እንደዚህ አይነቱ መጠላለፍ ቤተክርስቲያንን ከመንፈሳዊ ተቋምነቷ ይልቅ ለፖለቲካ መጠቀሚያ መሳሪያ ተደርጋ እንድትታይ ማድረጉ በማህበረሰቡ ዘንድ ታዓማኒነት እንዳይኖራት አድርጓል።

ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋ ለዓለም እንደ ብርሃን በመሆን ጨለማን ለመግፈፍ ነው፤ እንደ ጨው ደግሞ ጣዕም ለመስጠትና ብስባሴን ለመከላከል ። ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሮች እና ሌሎችም በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን የተጋረጡባትን ዘርፈ ብዙ ውድቀቶች ናቸው ። በእነዚህ ውድቀቶች ምክንያት በሌላውም ማህበረሰብ ዘንድ ተዓማኒነቷንና ተደማጭነቷን እንድታጣ አድርጓታል የሚሉ ሓሳቦች ይንጸባረቃሉ። ከዚህ ውድቀት ለመውጣት ምን ይደረግ? ምን ይታቀድ ምን ይሰራ? ሃሳብን ማንዘራሸር እና በጋራ ማሰብ ለጋራ የለውጥ ውጤት ምክንያት ይሆናል።

መልካም የሥራ ሳምንት

ነቢዩ ነኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop