June 24, 2024
14 mins read

‘ሕይወቴ አደጋ ላይ ነው’ የሚሉት የ‘ጦርነት ይቁም’ ሰልፍ አስተባባሪው ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ ተሰደዱ

b249e9a0 3139 11ef b7f5 2d174badf3ee.jpg
አቶ ዳንኤል ሺበሺ

በአገሪቱ የሚካሄዱ ግጭቶች እንዲያበቁ እና ለችግሮች ሰላማዊ መፍትሄ ለመጠየቅ በኅዳር ወር ማብቂያ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ካስተባበሩት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የነበሩት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ‘ሕይወቴ አደጋ ላይ ነው በማለት’ ከአገር ተሰደዋል።

የ“ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም ይስፈን” ሰልፍ አስተባባሪዎችን “ከባድ መከራ ደርሶባቸዋል” የሚሉት አቶ ዳንኤል፣ አሁንም የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እያሳደዷቸው መሆኑን ይናገራሉ።

የሰልፉ አስተባባሪዎች መታሰራቸው እንዲሁም “መንግሥታዊ ጫናው” ሰልፉን ላልተወሰነ ቀን ለማራዘም እንዳስገደዳቸው ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ቃል ያስታወቁት ፖለቲከኞቹ፤ ወከባ ደርሶብናል ይላሉ።

ነገር ግን “ብናራዝምም አልተወኑም” የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ “በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሁሉም ታሰሩ” ሲሉ የሰልፉ አስተባባሪዎች ሰልፍ እናካሂዳለን ብለው ከተነሱ በኋላ እስራት፣ ማዋከብ እና ዛቻ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።

እናም ይህ ሰልፍ አብዛኞቹን አስተባባሪዎች ለእስር እሳቸውን ደግሞ ለስደት እንደዳረጋቸው ተናግረዋል።

“አንዱ ተሰዶ አሜሪካ ገብቷል፤ እኔም ተሰድጄ ባለሁበት አለሁ። አንድ ሰው ተደብቆ ነው ያለው። ሌሎቹ በሙሉ ታስረው አዋሽ አርባ ናቸው። አቶ የሽዋስ ነበር የቀረው፤ እሱንም አንድ ሳምንት አስረው ለቀቁት።…

“ሁላችንም ላይ ከባድ መከራ ደርሷል። የሥነ-ልቦና ጫናው፣ የኑሮ ሁኔታው፣ ከሥራ መፈናቀሉ፤ አንድ ሰው ሲታሰር እሱ ብቻ አይደለም የሚታሰረው ብዙ ነገሮች ናቸው አብረው የሚታሰሩት። ቤተሰብ አብሮ ይታሰራል” ይላሉ።

ከታሰሩ የሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል የኢህአፓ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት (ከሦስት ወራት በኋላ ተፈተዋል)፣ ኢህአፓ ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ፣ የኢዜማ የቀድሞ መሪ አቶ የሽዋስ አሰፋ (ሁለት ጊዜ ታስረው ተፈተዋል)፣ የኢዜማ የቀድሞ አባል አቶ ናትናኤል መኮንን እንዲሁም የትንሳኤ ሰባ እንደርታ አመራሮች አቶ ጊደና መድኅን እና አቶ ካልአዩ መሀሪ ይገኙበታል።

ፖለቲከኛው አቶ ዳንኤል እንደሚሉት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ናቸው ባሏቸው ግለሰቦች በሚንቀሳቀሱበት ቦታ እና በቤታቸው ጭምር ክትትል እና ወከባ እንደተፈጸመባቸው ጠቁመው፤ ከአዲስ አበባ ውጭ በሚኖሩት ቤተሰባቸው ላይ ወከባና ድርደባ እንደተፈጸመም ይናገራሉ።

በተጨማሪም ታኅሣሥ ወር ማብቂያ ላይ ለገና በዓል ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በቁጥጥር ስር ውለው፤ ቄራ እሳት አደጋ ፖሊስ ጣቢያ ለ15 ቀናት እንደታሰሩ የሚናገሩት አቶ ዳንኤል “የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶች ተለቀቅሁ” ይላሉ።

መጋቢት 25 ከሌሊቱ 9፡00 እስከ ጠዋት 1፡00 ላይ እርሳቸው በሌሉበት ቤታቸው ተፈትሾ ሰነዶች እና የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ተወስደውብኛልም ብለዋል።

“በአስቸኳይ በ24 ሰዓት ውስጥ አገር ጥሎ እንዲወጣ” የሚል ማስጠንቀቂያ ደረሰኝ የሚሉት ፖለቲከኛው፤ በተፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት አገር ጥለው ወጥተው በአሁኑ ጊዜ በስደት ላይ ይገኛሉ።

“ልክ እንደ በቴ ኡርጌሳ እና እንደሌሎች የተገደሉ ሰዎች እርምጃ ይወሰድ ተብሎ ስለተወሰነ፤ ያን መረጃ ስላገኘሁት ነው አገር ጥዬ የወጣሁት” ሲሉ ከቤታቸው አባታቸውን ለማስታመም እንደወጡ በዚያው መቅረታቸውን ተናግረዋል።

“የሴራ ፖለቲካ”

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ ቆዩት አቶ ዳንኤል ሺበሺ፤ በረጅም ዘመን የፖለቲካ ሕይወታቸው የተለያዩ ፓርቲዎች አባል እና አመራር ነበሩ።

በ1990 ዓ.ም. ወደ ‘ተቃውሞ ፖለቲካ’ እንደተቀላቀሉ የሚናገሩት ፖለቲከኛው፤ በኢዴፓ አባልነት በተደራጀ የፖለቲካ ቡድን ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ።

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየሰሩ በእነ አቶ ልደቱ አያሌው “ተመልምለው” ኢዴፓን የተቀላቀሉት ፖለቲከኛው፤ ከኢዴፓ በኋላ በቅንጀት፣ በአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)፣ በሰማያዊ ፓርቲ እና ኢዜማ በተባሉት ፓርቲዎች ውስጥ አመራር ነበሩ።

2006 ዓ.ም. በሽብርተንነት ተከሰው ለሦስት ዓመታት የታሰሩም ሲሆን፤ በተደጋጋሚ በመታሰር የእስር ቤትን ጠባብ ክፍሎች ተለማምደዋል።

አቶ ዳንኤል ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ “ተስፋ ያለው ፓርቲ” እንመሥርት በሚል ኢዜማ ፓርቲን እንደመሠረቱ ይናገራሉ።

“እውነተኛ፣ ሀቀኛ የሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ኃይል ለመፍጠር ነው” ርዕይ በመያዝ ፓርቲውን እንደመሰረቱ የሚናገሩት አቶ ዳንኤል እውነታው ውሎ አድሮ ግን እንደ ውጥናቸው አልሆነም ይላሉ።

በተለይም የትግራዩ ጦርነት እና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ መካተት ላይ “ሰፊ ልዩነት” በመፍጠሩ ከ40 በላይ ከሚሆኑ አባሎች ጋር ፓርቲውን በይፋ መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

“ታምራት ላይኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ፖለቲካ ላይ ነበርኩ” ሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ከ20 ዓመታት በላይ የፖለቲካ ልምዳቸውን ተንተርሰው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሲገመግሙ ሁኔታውን “አዙሪት” ነው ይሉታል።

“ለአፍታም ቢሆን ከአገር እወጣለሁ [እሰደዳለሁ] ብዬ አስቤ አላውቅም” ሲሉም፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ “አደገኛ እና መሰሪ” ሆኗል በማለት ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ።

“ፖለቲካችን የሴራ ነው። ሀቀኝነት የለበትም። ችግሮችን በኃይል ነው መፍታት ነው የሚፈለገው። ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የመብት ተሟጋቾችን እንዲሁም እውነት የሚናገሩትን ማሳደድ እና ማጥፋት የፖለቲካ [ባህል] እየሆነ መጥቷል” ሲሉ አስጊ ነው ያሉትን ነገር ገልጸዋል።

አቶ ዳንኤል የኢትዮጵያን አሁናዊ ሁኔታ “በጣም ከባድ” ሲሉ ገልጸው፤ የአገሪቱ ፖለቲካ ከብሔር ፖለቲካነት ወጥቶ ሀሳብ ላይ መመሥረት አለበት በማለት፤ አሁን ላለው ችግር የሽግግር መንግሥት እና የልሂቃን ድርድር ለኢትዮጵያ ችግር መውጫ ቀዳዳ ነው ብለው ያምናሉ።

ከስምንት ወራት በፊት “ጦርነት ይቁም፤ ሰላም ይስፈን” በሚል ለኅዳር 30/2016 ዓ.ም. ሕዝባዊ ሰልፍ የጠሩ ፖለቲከኞች መንግሥታዊ ወከባ እና ማሳደድ እንደተፈጸመባቸው ከአስተባባሪዎቹ አንዱ ሆኑት ዳንኤል ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“የአገራችን ጉዳይ አስጨነቀን” ያሉ ዘጠን ፖለቲከኞች በተለይም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ጦርነትን የሚቃወም ሰልፍ ለማዘጋጀት ወስነው በመንቀሳቀሳቸው እስርን ጨምሮ ወከባ እና ጫና እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።

“ሶማሌ ውስጥ መጀመሪያዎቹ አካባቢ የተደረገውን፣ ቡራዩ ላይ፣ ሻሸመኔ ላይ ሰው ተዘቅዝቆ እስከሚሰቀል ድረስ የደረስንበትን አሰብን። እንደገና የትግራይን ጦርነት፣ ከዚያም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ሁኔታዎች ስላሳሰቡን… ጦርነት መቆም አለበት የሚል ስምምነት ላይ ደረስን” ሲሉ ሰልፉ እንዴት እንደተጠነሰሰ አብራርተዋል።

ኅዳር 30 ሕዝቡ መንግሥትን እንዲወተውት “በመላው አገሪቱ” ሰላማዊ ሰልፍ የጠሩት አስተባባሪዎቹ፤ ሰልፉን ለማካሄድ እንቅስቃሴ ከጀመሩ አንስቶ የደኅንነት መሥሪያ ቤቱን ጨምሮ የአገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ጫና እንዳደረሱባቸው አቶ ዳንኤል ተናግረዋል።

“የደኅንነት መታወቂያ አሳየኝ” ያሉት አንድ ግለሰብም ከእንቅስቃሴያቸው እንዲገቱ እንዳስጠነቀቋቸው የሚናገሩት አቶ ዳንኤል፤ “በሕይወትህ ላይ እርምጃ እንወስዳለን” ሲሉ እንዳስፈራሯቸው ገልጸዋል።

ሰልፉ ሊካሄድ ከታሰበበት ዕለት ጥቂት ቀናት አስቀድሞም የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም “ዛቱብን” ይላሉ።

“ቀጥታ እኛን የሚመለከት፤ ሰላማዊ ሰልፉን የሚመለከት፤ ይህን ሰልፍ የሚያዘጋጁ አስተባባሪዎች፤ ሰልፍ የሚወጡ ሰዎች ላይ ነጻ እርምጃ ለመውሰድ [ኢታማዦር ሹሙ] ዛቱ። ‘በራሳቸው ላይ ፈርደው ይህን ሰልፍ ማድረግ ይችላሉ፤ ከዚያ ውጪ ሰልፍ ማድረግ አይችሉም’ ብለው ጦርነት በእኛ ላይ አወጁብን” ሲሉ ከሥልጣናቸው ውጪ ጣልቃ በመግባት ዛቱብን ይላሉ።

ይህን ተከትሎም ኅዳር 27/2016 ዓ.ም. አራቱ የሰልፉ አስተባባሪዎች ከሌሎች 97 “ተጠርጣሪዎች” ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግሥት አስታውቋል።

አስተባባሪዎቹ እርምጃውን “ሰልፉን ለማስቀረት” ተወሰደ ቢሉትም፤ መንግሥት ግን ሰልፉን “በአዲስ አበባ ታጣቂዎች አስርጎ በማስገባት ሁከት እና ግርግር ለመፍጠር” የተደረገ ሽፋን ነው ብሎታል።

Source- BBC Amharic

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop