March 31, 2024
5 mins read

የትግራይና የአማራ ክልል የሚወዛገቡባቸውን አካባቢዎች በተመለከተ በሚቀጥሉት ቀናት የሚከተሉት እርምጃዎች ይወስዳሉ

Welkait
Welkait

የወሰን ይገባኛል የሚነሳባቸውን አካባቢዎች (የራያ ፣ ጠለምት እና ወልቃይት) በተመለከተ የትግራይና የአማራ ክልል አመራሮች የፕሪቶሪያውን የሰላም ውል ተንተርሰው በደረሱት የመተግበሪያ ስምምነት መሰረት ታጣቂዎችን ማስወጣት ተፈናቃዮችን መመለስና አዲስ የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋትን ጨምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ለማድረግ መታቀዱን ዋዜማ ስለጉዳይ ከሚያውቁ መንግስታዊ ምንጮች ያገኘችው የሰነድ መረጃ ያመለክታል።

የወሰን ውዝግቡን ለመፍታት የተሰየመው ብሄራዊ ኮሚቴ በቅርቡ ባደረገው ምክክር በደረሰው ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት መከላከያ ፀጥታውንና ሂደቱን የማስተባበር ኃላፊነት ይረከባል።

ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው ያለቅድመ ሁኔታ መመለስ  ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ያሰመረበት መርሀግብሩ የትግራይ ክልል የተፈናቃዮችን ቁጥርና ዝርዝር አሰናድቶ ለመከላከያ እንዲያቀርብ፣ ከተመላሾች መካከል በወንጀል የሚጠረጠሩ ወደ መኖሪያቸው መመለስ እንደማይከለከሉና የተጠረጠሩበት ወንጀል ካለ በተናጠል የሚታይ እንደሆነ ያትታል።

ማናቸውንም የወንጀል ድርጊት ክስ የፌደራል መንግስቱ በሂደት የሚመለከተው ይሆናል።

የቀደመ መኖሪያቸው በአወዛጋቢዎቹ አካባቢዎች የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ታጣቂዎች እና ሚሊሻ እንደታጣቂ ሳይሆን እንደተፈናቃይ ወደ ቦታቸው መመለስ እንደሚችሉም ከስምምነት ተደርሷል።

የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በአማራ ክልል የተመሰረቱ የአስተዳደር እና የፀጥታ መዋቅሮች ይፈርሳሉ።

ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከአካባቢው የሚወጡ ሲሆን የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት ደግሞ እንደታጣቂ ሳይሆን እንደ ነዋሪ መቆየት እንዲችሉ በብሄራዊ ኮሚቴው ስምምነት ተደርሷል።

ከጦርነቱ ተከትሎ የተፈጠሩ የአስተዳደር መዋቅሮች ሲፈርሱ የንብረትና የሰነድ መጥፋት እንዳይኖር መከላከያ ሰራዊት ጉዳዩን ተረክቦ አዲስ ለሚቋቋመው አስተዳደር እንዲያስረክብ ሀለፊነት ተሰጥቶታል።

በዕቅዱ መሰረት ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው ከተመለሱ በኃላ ሁሉን ያካተተ የቀበሌ አመራር ምርጫ ይደረጋል። የቀበሌ አመራሮች የወረዳ አመራሮቻቸውን ይመርጣሉ።

የአካባቢው አስተዳደር በምርጫ ከተሰየመ በኃላ የፌደራል መንግስት በጀት እንደሚመድብላቸው ስምምነቱ  ያብራራል።

ይህ ከተፈፀመ በኋላ በአመቺ ጊዜና ነባራዊ ሁኔታው ተገምግሞ በአካባቢው ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ታቅዷል።

የራያ እና ጠለምት አካባቢዎች ጉዳይን በቅድሚያ በመፍታት የወልቃይት ጉዳይ ይህንን ተከትሎ በተመሳሳይ  እንዲፈታ ለማድረግ አስፈፃሚ ቡድን ተቋቁሞ ስራውን እንደሚያከናውን ብሄራዊ ኮሚቴው ከስምምነት ደርሷል።

ከሁለቱ ክልልሎች የተውጣጣ  ግብረ ሀይል በአፈፃፀሙ ላይ በታዛቢነት የሚሳተፍ ሲሆን ጉድለቶችንና የማሻሻያ ሀሳቦችን በግብረመልስ የሚያቀርብ ይሆናል።

ይህ ስምምነት በተደረስ በቀናት ውስጥ በራያ፡ አላማጣ በኩል የትግራይ ኀይሎች ከአማራ ክልል ሚሊሻ ጋር የተጋጩ ሲሆን ሁለቱ ክልሎች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ሰንብተዋል።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለዋዜማ እንደነገሩት፣ ይህን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት መፈፀም ይጀምራሉ።

[ዋዜማ]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop