እገባለሁ ጫካ – እገባለሁ ዱር፤
የበደልን ገፈት – ስጋት ከምኖር፤
አትገባም ወይ ጫካ – አትገባም ወይ ዱር፤
ተቀጥላ ዜጋ – ሆነህ ከመኖር ::
ትናንትም ተበዳይ – ዛሬም ጦም አዳሪ፤
የበይ ተመልካች – የጅቦች ገባሪ፤
የሃብቱ ተመጽዋች – ያገሩ ባይተዋር፤
የመብት ተነፋጊ – የባንዳዎች ገባር፤
ሁለተኛ ዜጋ – ሆኜ ከመኖር፤
እገባለሁ ጫካ – እገባለሁ ዱር ::
ባዕድ አምላኪዎች – ታሪክ ከላሾችን፤
ዘረኛ ጎሠኛ – አንድነት አፍራሽን፤
የ ’ድገት እንቅፋቶች – የኋሊት ጎታችን፤
አትፋለምም ወይ – አትገባም ወይ ከዱር፤
አንገት እየደፋህ – ዘወትር ከመኖር ::
አትሰማም ወይ ጥሪ – አትሰማም ወይ ጩኸት፤
ደሙ ሲተነፍግ – ሲንቀጫቀጭ አጥንት፤
በደም ተለውሶ – ባጥንት ያጠሩትን፤
አሳልፈህ ስትሰጥ – የጦቢያ መሬትን ::
ያ’ገሬ ቁልቁለት – ያ’ገሬ ተራራ፤
ጥንትም ያልተበገርክ – ለጠላት ወረራ፤
ለወገንህ ኩራት – መመኪያ ስለሆንክ፤
አብረኸኝ ተሰለፍ – ጠላት ለማንበርከክ ::
ዱሩ ቤቴ ብዬ – በቃ ወጥቻለሁ፤
በደልን በዓርነት – ፍቄ እመለሳለሁ ::
ወንዙ ጥም ቆራጬ – ደኑ ብርድልብሴ፤
አሸዋው ምንጣፌ – ድንጋዩ ትራሴ፤
ቅጠል ፍራፍሬ – ስራስር በልቼ፤
ሰንደቅ አበቅላለሁ – ነፃነት ዘርቼ ::
የዱር አራዊቶች – ሳትቀሩ ተነሱ፤
እምዬ ኢትዮጵያ ! – እያላችሁ አግሱ፤
ነብርና አንበሳ – አብሩ ባንድላይ፤
ከጣሊያን የባሰ – መቷል አገር ገዳይ ::
ጀግናው ጫካ ገባ – እሰይ በይ ምድሪቱ፤
እጅግ ቢበዛበት – የበደል ገፈቱ፤
ጉብል ከዱር ገባች – ዕልል በይ መሬት፤
ትግልን አርግዛ – ለመውለድ ነፃነት፤
በ’ኩልነት ጸንቶ – እንዲሰምር አንድነት ::
ጎበዝ ! « ጅቡ ከሚበላህ ጅቡን በልተህ ተቀደስ !! »
ለሥር ነቀል ለውጥ፤ በአንድነት በመነሳት፤ ነፃ ሕዝብ እንሁን !!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!
ነፃነት፤ እኩልነትና ወንድማማችነት ይለምልም !!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ !!
የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ( 06/03/2024 ) እኤአ
ለአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ተዘጋጅቶ ሳይላክ የዘገየ ::
.#AmharaGenocide???????? pic.twitter.com/qBgPyWzYn4
— ????ምኒልክ አማራዊት ጥቁር ሰው???? (@FanoAmhara21301) March 7, 2024