September 27, 2023
7 mins read

እንኳን ለመሰቀል በዓል እና መዉሊድም በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን‼️

ዛሬ መስቀልም ነው፣ መዉሊድም ነው።

እንኳን አደረሳችሁ!

378375630 845298806946311 3211979254583976344 n

ለተለያችሁን ጀግኖችም ሆናችሁ ሌሎች ዘመዶቻችን፣ ነፍስ ይማር።

ሳይነኳችሁ ለነካችሁ፣ ሳያባርሯችሁ ለምታሳድዱን፣

በትግስት ሲተዋችሁ በትእቢት ለተሳደባችሁ፣

አላህ ይፍረዳችሁ! ወዳጃችሁ ጋኔል ያባርራችሁ!

የሰላም ጉዞን ለአሰባችሁ እግዜር ይርዳችሁ።

“ጦርነትም ያልፋል። ስለዚህ የመልሶ መቋቋም የሰላም ጉዞ መጀመር ያለበት አሁን ነው።”

በፈለገው ምክንያታዊነት፣ በማንኛውም መመዘኛ ጦርነት ለሰው ልጅ ስቃይ፣ ህይወት መጥፋት እና ውድመት ያደርሳል እንጅ ዘላቂ፣ ስር ነቀል መፍትሔ አያመጣም። ምንም እንኳን አረመኔዎች ባለን ጉልበተኛነት በጦር ኃይል፣ በመግደል ከፍ እንላለን ብለው ሒሳባቸውን ቢያሰሉም፣ ድንቁርናቸው የሚያስከትለውን መዘዝ፣ የረጅም ጊዜ መከራ ከሰው ልጅ  የመተንበይ ግምት ውጭ መሆናቸውን አይተናል። የዘመናት የግጭት ሰንሰለት እንደሚወልድም አይተናል።

ስለዚህ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ በድርድር፣ በዲፕሎማሲ፣ በውይይት፣ በሽምግልና መፈታት አለባቸው።

ቢሆንም፣ የፓሲፊስት ሰማዕታት አመለካከት እንዳለ ሆኖ፣ በጉልበት ብቻ የምፈቱ ግጭቶች በጣም ጥቂት ቢሆኑም አሉ። ብዙውን ጊዜ ጽንፈኛነትንና የተለዩ ሁኔታዎችን ያመለክታሉ። ይህ የመጨረሻ የጦርነት ግዴታ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና በአለም አቀፍ ህግ መሰረት መተግበር አለበት። አሳዛኙ ጉዳይ ግን በሰላም መፍታት ያልተቻለው ግጭት መነሻውና ተንኳሹ ሥልጣኔና ሰብዓዊነት የጎደለው ባለግዜ ወይም ደንቆሮ ፅንፈኛ ስለሚሆን ጦርነቱም አስከፊና ሕግም ሆነ ሰባዊነት የጎደለው ይሆናል። ሰላማዊ ሰው መግደል፣ ባጠቃላይ በሴቶችና በሕጻናት ላይ የሚደረገው እንስሳነት፣  አዝርዕትና እንሥሣትን ማቃጠል፣ የገደሉትን መስቀል፣ መቆራረጥ፣ የአረመኔው ጠባይ ነው። ይህንን እያዩ አሸንፈን ቀን ይወጣልናል የሚሉ መሪዎችም ሆኑ ጀሌዎች የአዕምሮ ዝገት ወይ ሻጋታ አለባቸው።

ለሁሉም ጊዜ አለው። ሁኔታዎች ሲንከባለሉ መጥተው፣ የሽምግልና ጊዜ ከሽፎ፣ በትዕግሥት “ከኔ ይቅር፣ ይሁንልህም” ታልፎ፣  አይቀሬው የጦርነት እልቂት ከተጀመረ በኋላ፣ የታመቀ ቁጭት፣ ትኩስ የበደል ቁስል፣ የምያቅለሸልሽ ትዕቢት፣ የሚዘገንን አረመኔንት እየታዬ፣ የእርቅና የሰላም ጥሪ ቦታ አይኖረዉም። በሳጥናኤልና በጊዮርጊስ መካከል እርቅ አይኖርም። ሳጥናኤል ወደገሃነም ካልተላከ በደልና ጦርነት ዘለዓለማዊ ይሆናሉ። የህዋህትን ጉዳይ አየነው አይደለም?

ተጨማሪ ያንብቡ:  2ቱ ብልጽግናዎች ለዳግም የእርስ በእርስ ጦርነት እያሟሟቁ ነው! | Oromia | Dr. Yilkal Kefale | Amhara Prosperity Party

ይህም ሆኖ በርግጥ ጦርነት አንድ ቀን ማቆሙ አይቀርም። የዚያን ጊዜ ለምያስፈልገው ሰላም፣ ለምያስፈለገው ወደ ሰብዓዊነት የመልስ ጉዞ፣ ጉልበትን፣ ንብረትን ማሰባሰብ፣ ያ የሰላም ጥሩ ተልኮ ይሆናል። መጀመር ያለበትም ዛሬ ነው፣ አሁን ነው! የጦርነት ዕብደት አልቆ፣ ሳያዉቅም በድንቁርና፣ እያወቀም ለሆዱ ሲል የበደለ፣ የገደለ ሁሉ መስከን ሲጀምር አንዳንዱ ጥፋቱ ይገባው ይሆናል፤ ይጸጸትም ይሆናል፤ ከጀሌው ውስጥ ማሩኝ የምልም አይጠፋም። ኢትዮጵያዉያን ያንን የሚያስተናግድ ቄስም፣ ዳኛም፣ ሐኪምም፣ ቴራፔውትም፣ መሃንድስም ያስፈለገናል። አሻፈረኝ፣ አላጠፋሁም የሚለውም በወንጀሉ ሲፈረድበት፣ ሰው ነውና ቅጣቱ በአሸናፊው ሌላ ኢሰብአዊ በደል እንዳይፈጠርበት ያኔ ገለልተኛ የሰላም ልኡካን ያስፈልጉናል። በድህነት የማቀቀች አገር የኋሊት ስትሄድ ቢያንስ ወደ ዜሮ የሚያመጣት ኃይል ያስፈልጋታል። ያ ጉልበት ደግሞ በጦርነት ማቆም ማግስት ከሰማይ አይወርድም፤ ከዛሬው መታነጽ፣ መሰልጠን፣ መሰብሰብ፣ መዘጋጀት አለበት። ጊዜ ይቃጠላል፣  ማለትም የድህነት ሞት የባሰ ይከፋል።

ጦርነትም ያልፋል። ስለዚህ የመልሶ መቋቋም የሰላም ጉዞ መጀመር ያለበት አሁን ነው። ለሰላም የተነሳችሁ ወገኖች ጉልበታችሁ በከንቱ እንዳይባክን ወደዝያ ብታዞሩት?

አላህ/እግዚአብሔር  ይችን ያህል አርቀን ማሰብ እንድንችል ሩህ ለግሶን ይሆን?

 

መልካም መውሊድ! መልካም መስቀል!

Yeshiwork Wondmeneh 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የኦህዴድ መራሹ ብልፅግና  መንግስት  በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በንጹሀን  ዜጎች ላይ እየወሰዳቸው ያሉ የነፃ እርምጃ  ግድያዎች  መንግስት ያሰበውን የፖለቲካ ግብ ያሳካለታል  ወይ ? በኔ አመለካከት እነዚህ የንፁሃን ዜጎች  የጅምላ ግድያዎች  በሁለት በኩል እንደተሳለ ቢላዎ (double edge sword) ናቸው:: ፩- መንግስት እያሰላው

 የኦህዴድ መራሹ ጅምላ ግድያዎች ስሌት (ሸንቁጥ- ከምዕራብ ካናዳ)

January 24, 2025
እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

Go toTop