https://youtu.be/lHfh1MWnn2c
ሙስጠፌ ነጭ ነጯን ፊት ለፊት ተናገሩ-|”ፖለቲካው ታሟል … ብልጽግና ፈርሷል
Latest from Blog
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ ብቻ ሳይሆን ሰዎቹ እራሳቸው ፣ እንደክሪስሜስ ዛፍ አሸብርቀው ፣ አምረው ና ተውበው ፣ ወርቅ መስለው ፣ ዝንጥንጥ ብለው በደስታ እየተፍከነከኑ አዲስ ዓመትን ተቀብለዋል ። ይህንን እውነት ዕድሜ ለሶሻል ሚዲያ በቀጥታ ሥርጭት አይተናል ። እርግጥ ነው በእኛው ሻራተንም ” በ20ሺ ብር ብቻ መፈንጠዝ ተችሏል ። ” ማን ከማን ያንሳል ? … ሰው በመሰረቱ በቀላሉ የሚደሰት እና በቀላሉ የሚያዝን ፍጡሩ ነው ። ፍንጥዝያና ጭምትነት ፤ ለቅሶና ሳቅ ደግሞ በጉያው ያሉ የስሜት ነውጦቹ ናቸው ። እነዚህ የስሜት ነውጥች ዘወትሮዋዊ ቢሆንም በአውሮፓው ዜጋ እና በአፍሪካው ዜጋ የሚስተዋለው የስሜት ነውጥ ግን በእጅጉ ይለያያል ። አውሮፓዊው ዜጋ የስሜት ነውጡ ፤ ፈንጠዝያው ና ሐዘኑ ከመንፈስ ደስታ ከማግኘት ጋር የተቆራኘ ነው ። በአመዛኙ ። አፍሪካዊው ደግሞ ሐዘኑ እና ፈንጠዝያው የተቆራኘው ከዕለት ጉርሱ ከአመት ልብሱ ጋር የተቆረኘ ነው ። ያ ማለት አፍሪካዊው ገና መሰረታዊ ፍላጎቱን ያላረካ ምስኪን ሰው ነው ማለት ነው ። ለመሆኑ ይኽ ምስኪንነት ከፍ ሲል ደሞ ምንዱባንነት ( ዘመን በአዲስ እየተቀየረ የትየለሌ ደርሶ እንኳን ) እስከዛሬ እንዴት ሊቀረፍ አልቻለም ? ይኽ ጥያቄ በጥበብ የሚመለስ ጥያቄ ቢሆንም በዋነኝነት ፖለቲካዊ ምክንያት አለው ። መቼም የፖለቲካ ሳይንቲስቶች እንደምታውቁት ዓለምን የሚገዛው ፖለቲካ ነው ። ፖለቲካ የህዝብ የአስተዳደር ዘይቤ ነው እስካልን ድረስ ኢኮኖሚውንም ሆነ ማህበራዊ ጉዳዩን የሚያሽከረክረው እርሱ ነው ። ይላሉ የዘርፉ ልሂቃን ። ) እርግጥ ነው አለምን የሚገዛው ፖለቲካ ነው ። ይሁን እንጂ ይህ ገዢ ፖለቲካ ፈጣሪ እንዳለው አንዘንጋ ።… “ፖለቲካው ዓለምን ይገዛል “ ስንል የፖለቲካ ፈጣሪዎች የፖለቲካውን መሪ ይቆጣጠራሉ ። እነሱ እንዳሻቸውም ይዘውሩታል ። እንደፈለጋቸውም ያሽከረክሩታል ማለታችን እንደሆነ ይሰመርልን ። ለመሆኑ እነዚህ የፖለቲካው ዘዋሪዎች እነማን ናቸው ? መልሱ ግልፅ ነው ። በኢኮኖሚ የፈረጠመ አቅም ያላቸው አገሮች ሁላ ናቸው ። አሜሪካ ፣ ቻይና ፣ ሩሲያ ፣ እንግሊዝ ፣ ጀርመን ፣ ፈረንሳይ ፣ ኢጣሊያን ፣ ሳውዲአረቢያ ፣ እስራኤል ፣ …ቱርክ ። ወዘተ። የፈረጠመ የኢኮኖሚ ያላቸው ናቸው ። እነዚህ አገራት ለሀገራቸው የሚጠቅም ፖለቲካን በዴሞክራሲ ፣ በ’ሪኦተ ዓለም እና በኃይማኖት ሥም በአፍሪካ አገራት ላይ ያራምዳሉ ። ፓለቲካቸውን የአፍሪካ መንግስታት ተቀብለው እንዲተገበሩም በሞኖፖል በያዟቸው የኢኮኖሚና የኃይማኖት ተቋማት አማካኝነት እጅ ይጠመዝዛሉ ። ( ወርልድ ባንክን እና አይ ኤም ኤፍን መጥቀስ ይቻላል ። ) ይህ ብቻ አይበቃቸውም ፣ ህዝቡም በአጠቃላይ እውቀት እንዳይበለፅግ አንድ መግባብያ ቋንቋ ኦንዳይኖረው ያደርጋሉ ። አንድ አይነት ፍጡር ፤ ያውም ክቡር ሰው ሆኖ እያለ በሚነገረው ቋንቋ እንዲጠራ በማድረግ ሰውነቱን ያስረሱታል ። እርስ በእርሱም እንዳይገባባ በቋንቋው ብቻ እንዲማር ያስገድዱታል ። ብሔራዊ ቋንቋ እንዳይኖረው ያደርጉታል ። ወደ 14ኛው እና 15ኛው ክፍለ ዘመን የወረደ አስተሳሰብን የሚያራምድ ግብዝና ተራ ሰው ያደርጉታል ። በዚህ ሰበብ እኔ ትግሬው፣ እኔ አማራው ፣ እኔ ኦሮሞው እኔ …እያለ ባላዋቂነት ውስጥ እየዳከረ ፣ቅልጥ ባለ ግብዝነት ተወጥሮ ፣ ተራ ሟችነቱን ረስቶ ሲያቅራራ እዛም እዚህም ይስተዋላል ። አውሮፖና አሜሪካ ብቻ ሳይሆኑ ሩቅ ምሥራቅ እና የአረብ አገራት በሙሉ የሰው ማንነቱ ሰው መሆን ብቻ መሆኑንን ጠንቅቀው ያውቃሉ ። የሰውን ክቡርነትም በየህገመንግስታቸው አውጀዋል ። ሰው የተለያየ የመግባብያ ቆንቋ ቢናገርም በተፈጥሮው አንድ ነው ። በቋንቋው ንግግርም ነባራዊ ተግባባቶች አይቀየሩም ። በፈለከው ቋንቋ ተናገረው ፤ሙገሳ ሙገሣ ስድብ ስድብ ነው ። የተለያየ ቋንቋ መናገር ተፈጥሯዊ እንጂ እርግማን አይደለም ። እርግማን የሚሆነው አንድ ሉአላዊ አገር አንድ ብሔራዊ ቋንቋ ከሌለው ብቻ ነው ። የአንድ አገር ዜጋ እርስ በእርሱ እንዲግባባ አንድ መግባቢያ ቆንቋ መማር ያስፈልገዋል ። እንዳይግባባ ቋንቋውን ከፋፍሎ አንድ ብሔራዊ ቋንቋ በህግ ወስኖ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዳይማር ማድረግ እርግማን ነው ። ( በበኩሌ የባቢሎን ግንበኞች ፈጣሪን እናገኛለን ብለው ወደሰማይ ግንብ መገንባታቸው ታላቅ ጅልነት እና ፍጹም ቂልነት መሆኑንን ፈጣሪ ያውቃልና እነዚህ ሰዎች በለመግባባት የተነሳ ተበታትነው በየግላቸዎ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ በመሻት ቋንቋቸውን እንደከፋፈል አምናለሁ ። ) እርግማንነቱም ዛሬ ላይ እየታየ ነው ። ኢትዮጵያ ዛሬ በማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት የተዘፈቀችው አንድ ብሔራዊ ቋንቋ ስለሌላት ነው ። የዛሬ ሥመ ጥር ፖለቲከኞች እኮ በአማርኛ በጣፈጠ አንደበት የሚናገሩት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ የአማረኛ ቋንቋ ትምህርት ሥለተማሩ ነው ። ይህ እውነት መሆኑ ቢታወቅም ይህንን ሃቅ ማንም ትንፍሽ አይልም ። ኃያል አገራትም ይህንኑ የትምህርት ሥርዓት ይከተላሉ ። እናም ዜጎቻቸው ሁሉ በዚህ ብሔራዊ ቋንቋቸው መግባባት ይችላሉ ። እኛም ይኽንን እውነት በጥሞና እንድገነዘብ ጥረት ሲያደርጉ ግን አይስተዋሉም ። ከራሳቸው ህገመንግስት ተመክሮ በመነሳት ሩሲያም ሆነች አሜሪካ ስለ ብሔራዊ ቋንቋ አስፈላጊነት አበክረው ሊመክሩን ይገባ ነበር ። የእነሱ አገር ዜጎች አንድ መግባቢያ ቋንቋ ያላቸው ና ሰው መሆናቸውን የተገነዘቡ ከመሆናቸውም በላይ ፣ ነገ ተራ ሟችነታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ እንዲሆኑ በብሔራዊ ቋንቋቸው አስተምረዋል ።( ጥቂቶች ከአፍሪካ ወደ አሜሪካ እና አውሮፖ የፈለሱ እና ዜግነት ያገኙ ኢትዮጵያዊያን ግን ከነድንቁርናቸው የተቀመጡ ፣ የሰውን ሰውነት የካዱ እና በሰው ደም የማቆምሩ ሆነው እናገኛቸዋለን ። ) የኢትዮጵያ ዜጎች ግን ዛሬም በቋንቋ ልዩነት ብቻ ሰው መሆናቸውን ረስተው እርስ በእርስ ሲሰዳደቡ ፣ ሲታኮሱ እና ሲገዳደሉ ይስተዋላል ። ሰው ሰውነቱን በመዘንጋት ብቻ ሳይሆን በቋንቋ ተቧድኖ አንዱ ቋንቋ ሌላውን ቋንቋ ካልገዛ የሚል አስተሳሰብ የነገሰባት አገር ኢትዮጵያ ብቻ መሆኖ በእጅጉ ያስገርማል ። “
ዛሬ ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። ( ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል ። )
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ አብይን የሚያንዘፈዝፉት የእንስቷ ንግግሮች አድምጡት
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ
ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ
ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ
እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! –
“ፋኖ የበለጠ ይደራጃል ወደ ኋላ አይልም!”/ “የትግራይን ህዝብን ይቅርታ ጠይቂያለሁ” “ፋኖ በናፍቆት እየተጠበቀ ነው” ገዱ አንዳርጋቸው (ዶ/ር)
ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር) (ታህሳስ 19፣ 2017) December 28, 2024 መግቢያ እንደተነገርን ኢትዮጵያን “ከዕዝ ወይም ከሶሻሊስታዊ” ኢኮኖሚ አላቆ ወደ “ ነፃ ገበያ ኢኮኖሚ” እንድትሸጋገር ከተደረገ ይኸው ከ31 ዓመት በላይ ሊያስቆጥር ነው። በጊዜው ስልጣንን የተቆናጠጠው የህወሃት አገዛዝ
ሁለ-ገብ ለሆነ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዕድገት መሰረት የሚጥል ህግ፣ ወይስ የኢትዮጵያን ሀብት የሚያዘርፍና ህዝብን አቅመ-ቢስ የሚያደርግ አዲስ የባንክ ህግ- ከኒዎ-ሊበራሊዝም ወደ ባሰ ኒዎ-ሊበራሊዝም የዝቅጠት ጉዞ!
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ
ልዩ ቆይታ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ! – “ዐብይ ቂም የያዘ የነጣቂ መንግስት መሪ ነው”/ “አማራ እየተዋጋ ያለው ሰላምን ፍለጋ ነው” – ክፍል አንድ
የሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) “ገለልተኛ ባለመሆን ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ምክንያት ማገዱ ገለጸ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC)
መንግስት ኢሰመጉ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን አገደ፤ የታገዱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቁጥር አራት ደረሷል
“መካር የሌለው ንጉስ እንዳይሆኑ” ፤ ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የተፃፈ አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም