በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ታሪክ ኢትዮጵያን በማሳነስ እና ህዝብን በመከፋፈል አንዱን እና ዋነኛዉ ኢትዮጵያዊ የህዝብ ክፍል የሆነዉን ብዙኃን ዓማራ ኩሁሉም ብሄራዊ አዉድ በማግለል ከፍተኛ በደል እና ግፍ የደረሰዉ በኢህአዴግ /ሕወኃት የህወኃት /ኢህአዴግ -ህገ መንግስት መሠረት አድርጎ ነዉ ፡፡
የዓማራ ህዝብ ያገለለ ያልተማከለ የአገር አስተዳደር በማቋቋም የኢትዮጵያን የቆየ የግዛት አንድነት እና የባህር በር ማሳጣት ዕኩይ ታሪካዊ ስህተት የተፈፀመዉ በኢህአዴግ ጊዜ የሆነዉ ብሄራዊ ክህደት ነዉ ፡፡
ይህ ሁሉ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዉያን ላይ የደረሰዉ የመከራ ዘመን መራዘም የፀረ-ኢትዮጵያዉያን ድርሻ በትልቁ የሚታይ ቢሆንም የአመታት ተገፊ እና መከራ ገፊ ሆኖ በአገሩ ባይተዋር ሆኖ በራሱ አገር እና ምድር መፃተኛ፣ ስደተኛ እና የሞት ተራ በማንነቱ የሚጠባበቀዉ ብዙኃን ዓማራ አለመንቃት፣ አለመደራጀት እና በአንድነት በጠንካራ የህብረት ክንድ ለነፃነቱ እና ለብሄራዊ አንድነቱ በፅናት አለመቆም የራሱ ድርሻ ነረዉ ፤ አለዉ ፡፡
ዛሬም ከሶስት አስርተ ዓመታት የስደት ፣ የዉርደት እና የሞት ዘመን በኋላ እንኳን የዓማራ ህዝብ ህብረት እና አንድነት ለኢትዮጵያ ዘላቂ አንድነት መሰረት እና የማዕዘን ድንጊያ መሆኑን የሚያወቁ ፀረ-ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራዊነትን ከስሩ መገርሰስ በሚል አፍራሽ ሴራ አበዉ“ ሀረጉን ሲስቡ ዛፍ ይወዛወዛል ”እንዲሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ቀጥለዉበታል ፡፡
“ዉሾች ይጮሃሉ…ግመሎችም መጓዛቸዉን ቀጥለዉበታል ” ይህም ድህነት፣ ስደት ፣ዉርደት ….ሞት ቀጥለዋል…ሟችም አትግደሉን በማለት ገዳይን ይማጣናል ፡፡ ቁም ነገሩ ነፃነትም ሆነ ዘላቂ ብሄራዊ አንድነት ዕዉን የሚሆነዉ ዛሬም ከሰላሳ ዓመታት የመከራ ጊዜ በኋላ ከጠላት ተማፅኖ እና ችሮታ እንደሆነ መመኘት ነዉ ፡፡
የየትኛዉም ህዝብ እና አገር ህልዉና፣ ነፃነት እና አንድነት ዕዉን የሚሆነዉ በአንድ ወገን ምኞት እና በሌላ ወገን በጎ ፍላጎት እና ችሮት ሳይሆን በህዝብ ጠንካራ የአንድነት እና የዓላማ ፅናት መርህ እና መንገድ ያደረገ ህዝባዊ ህብረት ብቻ ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያም ሆነ የዓማራ ህዝብ ስጋት እና ዉርደት ታሪክ የሚሆነዉ በተባበረ ኃይል በሚመራ ህዝባዊ ትስስር እና ህብር ብቻ ነዉ ፡፡ ኢትዮጵያን መታደግ ዕዉን የሚሆነዉ ኢትዮጵያዉያን ራሳቸዉን እና አገራቸዉን ከዉስጥ እና ከዉጭ ጠላት ሴራ እና ወጥመድ ሲከላከሉ እና ሲያድኑ ነዉ ፡፡ ራሱን ያዳነ ዓለሙን ያድናል እና የዓማራ ህዝብ ዕየሞተ ከለመኖር ኖሮ ማለፍን መምረጥ አማራጭ የሌለዉ ምርጫ በመሆኑ ኢትዮጵያን ከገባችበት የጥፋት ጉድጓድ ለማዉጣት እና ከጥፋት ለመታደግ የኢትዮጵያዉያን ህብረት እና የዓማራ ህዝብ በአንድነት እና እንደ ብረት በጠነከረ የህብረት ክንድ መቆም ጊዜዉ ዛሬ ነዉ ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ !!
NEILLOSS Amber