የተሟላ ነፃነት እና ዘላቂ ብሄራዊ አንድነት በተማፅኖ ዕዉን አይሆንም

በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ታሪክ ኢትዮጵያን በማሳነስ እና ህዝብን በመከፋፈል አንዱን እና ዋነኛዉ ኢትዮጵያዊ የህዝብ ክፍል የሆነዉን ብዙኃን ዓማራ ኩሁሉም ብሄራዊ አዉድ በማግለል ከፍተኛ በደል እና ግፍ የደረሰዉ በኢህአዴግ /ሕወኃት የህወኃት /ኢህአዴግ -ህገ መንግስት መሠረት አድርጎ ነዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ ያገለለ ያልተማከለ የአገር አስተዳደር በማቋቋም የኢትዮጵያን የቆየ የግዛት አንድነት እና የባህር በር ማሳጣት ዕኩይ ታሪካዊ ስህተት የተፈፀመዉ በኢህአዴግ ጊዜ  የሆነዉ ብሄራዊ ክህደት ነዉ ፡፡

ይህ ሁሉ በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዉያን ላይ የደረሰዉ የመከራ ዘመን መራዘም  የፀረ-ኢትዮጵያዉያን ድርሻ በትልቁ የሚታይ ቢሆንም የአመታት ተገፊ እና መከራ ገፊ ሆኖ በአገሩ ባይተዋር ሆኖ በራሱ አገር እና ምድር መፃተኛ፣ ስደተኛ እና የሞት ተራ በማንነቱ የሚጠባበቀዉ ብዙኃን ዓማራ አለመንቃት፣ አለመደራጀት እና በአንድነት በጠንካራ የህብረት ክንድ ለነፃነቱ እና ለብሄራዊ አንድነቱ በፅናት አለመቆም የራሱ ድርሻ ነረዉ ፤ አለዉ ፡፡

ዛሬም ከሶስት አስርተ ዓመታት የስደት ፣ የዉርደት እና የሞት ዘመን በኋላ እንኳን የዓማራ ህዝብ ህብረት እና አንድነት ለኢትዮጵያ ዘላቂ  አንድነት መሰረት እና የማዕዘን ድንጊያ መሆኑን የሚያወቁ ፀረ-ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ  ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራዊነትን ከስሩ መገርሰስ በሚል አፍራሽ ሴራ  አበዉ“ ሀረጉን ሲስቡ ዛፍ ይወዛወዛል ”እንዲሉ  የኢትዮጵያ ጠላቶች ቀጥለዉበታል ፡፡

“ዉሾች ይጮሃሉ…ግመሎችም መጓዛቸዉን ቀጥለዉበታል  ” ይህም ድህነት፣ ስደት ፣ዉርደት ….ሞት ቀጥለዋል…ሟችም አትግደሉን በማለት ገዳይን ይማጣናል ፡፡ ቁም ነገሩ ነፃነትም ሆነ ዘላቂ ብሄራዊ አንድነት ዕዉን የሚሆነዉ ዛሬም ከሰላሳ ዓመታት የመከራ ጊዜ በኋላ ከጠላት ተማፅኖ እና ችሮታ እንደሆነ መመኘት ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  መማር እንችላለን ወይ? -አንዱዓለም ተፈራ

የየትኛዉም ህዝብ እና አገር ህልዉና፣ ነፃነት እና አንድነት ዕዉን የሚሆነዉ በአንድ ወገን ምኞት እና በሌላ ወገን በጎ ፍላጎት እና ችሮት ሳይሆን በህዝብ ጠንካራ የአንድነት እና የዓላማ ፅናት መርህ እና መንገድ ያደረገ ህዝባዊ ህብረት ብቻ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያም ሆነ የዓማራ ህዝብ ስጋት እና ዉርደት ታሪክ የሚሆነዉ በተባበረ ኃይል በሚመራ ህዝባዊ ትስስር እና ህብር ብቻ ነዉ ፡፡ ኢትዮጵያን መታደግ ዕዉን የሚሆነዉ ኢትዮጵያዉያን ራሳቸዉን እና አገራቸዉን ከዉስጥ እና ከዉጭ ጠላት ሴራ እና ወጥመድ ሲከላከሉ እና ሲያድኑ  ነዉ ፡፡ ራሱን ያዳነ ዓለሙን ያድናል እና የዓማራ ህዝብ ዕየሞተ ከለመኖር ኖሮ ማለፍን መምረጥ አማራጭ የሌለዉ ምርጫ በመሆኑ ኢትዮጵያን ከገባችበት የጥፋት ጉድጓድ ለማዉጣት እና ከጥፋት ለመታደግ የኢትዮጵያዉያን ህብረት እና የዓማራ ህዝብ በአንድነት እና እንደ ብረት በጠነከረ የህብረት ክንድ መቆም ጊዜዉ ዛሬ ነዉ ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !!

NEILLOSS Amber

1 Comment

  1. እዚህ ድርድር ላይ እንደ እቴጌ ጣይቱ አይነት ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ካልገባበት የወንድሞቻችን ደም ፈስሶ የተገኘው ድል በመስኮት መብረሩ ነው ባሌን ጎዳሁ ብላ እነ ዶር አብይም አማራውን አንገት ሊያስደፉ የሚሄዱበት እርቀት ሳይቆይ ዳፋው እነሱው ላይ ያርፋል፡፡ ብቃት ያለው ሰው ከመሃከላችው እስክ አሁን አልታየም፡፡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው እነ ጄነራል ተፈራ፤ እነ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤እነ ዘመነ ካሴ፤እነ አቻምየለህ ታምሩ፤እና አራቱ በድርደሩ ላይ እንዲገኙ የተጠቆሙት መገኘታቸው አስፈላጊ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአሜሪካ 52ኛ ግዛት ስላልሆነች ጆሮ አለመስጠት ነው አሁን እንደ ተጀመረው ዱቄት የሆነ የትህነግ ሰራዊት ካለ አቡክቶ መጋገር እንጂ መንገላጀጅ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ አሜሪካ ነጻ በሆነው በኢትዮጵያ ግዛት አልፋ እነዚህን ወንጀለኞች አውጥታ ከሆነ ያለው መንግስት ባስቸኳይ መልቀቅ አለበት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share