June 25, 2022
5 mins read

ባዶ ሆነዉ በባዶ የሚነግዱትን መስማት ከሰለቸን ባጀን

 ባዶነት ሰለቸን !

288358186 5211569042256804 2092752397205846827 nሁሉም የመጣዉ ሁሉ በአገር እና ህዝብ ስም ሲምል ሲገዘት ባዶ ካዝና ፣ ባዶ ዲሞክራሲ ፣ ባዶ ሰባዊ መብት አየያዝ ……. ይላል፡፡

ይቀጥል እና ራሱን አልፋ እና ኦሜጋ በማድረግ ብቸኛዉ የአገር እና ህዝብ አለኝታ ራሱ ብቻዉን የሠላም ፣ ዕድገት እና አንድነት ምሰሶ ማድረግ ይዳደዋል ፡፡

ይህም የአምልኩኝ ዳር ዳርታ መሆኑ ነዉ ፡፡ ራሱ እና ግብረ አበሮች የሚያደርጉት ሁሉ ትክክል እና የተቀደሰ ነዉ ብሎ ከማመኑ የተነሳ ጥዋት ያለዉን በረፋድ ለመካድ የለዉጥ አካል አድርጎ የለዉጥ ሀዋርያ መሆኑን እዩልኝ ስሙልኝ ይላል ፡፡

በህዘብ ስም በህዝብ ትከሻ እንደመዥገር ተጣብቀዉ  አገር እና ህዝብ ሲያደሙ ፣ ሲያወድሙ እና ሲያቆስሉ የሚዉሉትን የዕድገት እና ብልጽግና ደቀመዝሙር ማድረግ  ከባዶነት  ይሻላል ብሎ ጆሮ ዳባ ልበስ በባዶ ለባዶ እንድንኖር እና ሳንኖር እየሞትን  መኖርን በባዶ ተለማመድነዉ ፡፡

ይባስ ተብሎ ከሰሞኑ ዞትር ለአለፉት ዓመታት እንደሚሆነዉ በህዝብ ላይ  በማንነት እና በአመለካከት ልዩነት እየተደረገ ባለዉ የዘር ፍጂት ስለሞቱ  የህዝብ ወገኖች እና ዜጎች የህሊና ፀሎት ለማድረግ ፣ ቁጥራቸዉን ለማወቅ እና በአገር ባህል ፣ወግ እና ዕምነት ቀብር ለማድረግ ፈቃደኛ እና ኃላፊነት የሚወስድ አካል ለማግኘት አለመቻሉ በባዶ መኖር እና በባዶ መጀመር አባዜ እንደህዝብ ልማድ ሆኗል ፡፡

ለመሆኑ  በማንነት ላይ ጥቃት ፣ ሞት ፣ ስደት እና የመሳሰሉት የጅምላ የወንጀል ድርጊቶች የአገር አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማናጋት ሆኖ ተብሎ የሚከናወኑ እና በተደጋጋሚ ለረጂም ዓመታት የታዩ መሆኑ እየታወቀ  እንደ ተዘረፈ የአገር ሀብት ፤ንብረት እና የይስሙላ ዲሞክራሲ(ህዝባዊ መንግስት)፣ ኢፍትኃዊነት……ከባዶ እንጀምር ማለት እንዴት ኢትዮጵያ ዓምላክን እና ዕዉነትን የሚፈራ ሠዉ ብታጣ ነዉ ፡፡

ዜጎች በማንነታቸዉ ሲሞቱ ፤ሲገለሉ፤ ሲገደሉ …..ለዓመታት እያየን ይህ የአገር ጉዳይ ፣ የህዝብ ጥያቄ…..አይደለም እየተባለ መኖር ከዚህ በላይ ባዶነት ምን ይምጣ ፡፡ ዕዉነት ኢትዮጵያ ዉስጥ በማንነት የደረሰዉ ግፍ እና መከራ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት  ቢቆጠር ከዚህ በላይ በዓለም ላይ በሰዉ ልጆች በራሳቸዉ አገር ፣ምድር እና ግዛት እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ኢትዮጵያዉያን እና ዐማራ ላይ የደረሰዉ ሰቆቃ ከዕዉነት በላይ ምን ሊሆን እና ማን ሊናገር ይችላል፡፡

ከባዶ መነሳትን ክህደት እና በአገር እና ህዝብ ላይ የማላገጥ ሴራ መሆኑን አዉቀን ሁላችን ለራሳችን እና ለአገራችን የባዶ  ጅምር ነጋዴዎችን በቃ ልንል ይገባል ፡፡

ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ባዶ ሆነዉ አያወቁም ባዶነትን  ለከንቱ ዉዳሴ ትረፍ የሚገለገሉበት የህዝብን እና የአገርን አንጡራ ሀብት እና ንብረት ለግል እና ለቡድን ለሚመዘብሩት መንደርደሪያ መንገድ መሆኑን ይህም የባዶነት ጭምብል እጂ እጂ ማለቱን እና እንደሰለቸን ሊያዉቁት ይገባል፡፡

ነፃነት ወይም ሞት !

ሞት ለፀረ ኢትዮጵያ!

Neilos Amber

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop