April 14, 2022
18 mins read

ያልተገራ ምላስ (ጥሩነህ)

ያልተገራ ምላስ የክፉ መንፈስ አንደበት ነው። ቃል ተግባር ይሆናል፤ የተንኮል ቃል ደግሞ ደም ያፋሳሳል፤ ንብረት ያወድማል፤ የጃዋርን ተክብቢያለሁ ያስታዉሷል። ቃሉ አንድ ነው እርኩስ መንፈስ የተጫነው በመሆኑ ለአያሌ ሰወች እልቂት ምክንያትት ነበር።

ከጉራፈርዳ፤ አርባጉጉ እስካሁኗ ሰአት ያለው የሰው ልጆች ሞትና ስደት ያልተገራ ምላስ ውጤት ነው።

ያልተገራ ምላስ ቋንቋ አለማወቅ አይደለም፤ ክፋት፤ ጠላትነት፤ ተንኮል ነው። በውስጥ ያለን የልብ ቁስል ወደውጭ ማስወጫ የአንደበት ተጠሪ ነው። ችግሩ ከተፈጥሯዊው የሰውነት አካል ከምላሱ ላይ አይደለም። ችግሩ ያለው ከአስተሳሰቡ ነው፤ ከክፋቱ ነው። በእንግሊዝኛው malice የሚሉትን እመርጣለሁ፣ “the term malice is defined as ‘having an intent to harm’ and is usually associated with printed or spoken words that defame someone’s character, accuse them falsley or to cause public humilation…”

ይህንን ነው እየተቀባበሉ በአማራ ላይ ያላቸውን ጠላትነት በቃልም በተግባርም የሚገልጹት። ቃል እንዲሁ ቃል ብቻ አይደለም በተግባር ይደገፋል። ወራሪው ትግሬ ስልጣን ከመያዙ በፊት ጀምሮ እስካሁን ቃልን ተከትሎ ተግባርም እየተፈጸመ ነው።

ዛሬ በኦሮሞ ባለስልጣናት የሚወረወሩት ቃላት የነገ ተግባራት ናቸው። የነገውን ደም መፋሰስ ዛሬ በቃላት ባልተገራ ምላሳቸው ይነግሩናል። ምላሳቸው በአዕምሮአቸው ያለውን በልባቸው የተጻፈውን የሚነግረን ነው። ከተለያዩ ምላሶች ይነገሩ እንጂ ሃሳቡ አንድ ነው፤ አማራን ማውረድ ኢትዮጵያን ማዳከም ነው። አንዱ የኦሮሞ ድርጅት ከአንድ ቦታ ሆኖ መርዙን ሲዘራ ሌላው ይቀበለውና ጨምሮበት ብዙም የሃስብ ልዩነት ሳይኖሮው አሳልፎ ለሚቀጥለው ምንደኛ ያስተላልፈዋል።

278214313 512706783924657 5662909753108088032 n

ሸኔ ኦነግ ነው፤ ኦነግም ብልጽግና ነው፤ አንድም ሶስትም ናቸው። በተለያየ መድረክ የተቀመጡ ይምሰሉ እንጂ ቃላቸው አንድ ነው። ቃል ተግባር ሲሆንም እንዲሁ። የኦሮሞ ጥያቄ አልተመለስም ሲሉን ለብዙው ግራ ያጋባል፤ ምክንያቱም ሁሉም በጃቸው በደጃቸው መሆኑን ስለሚያውቅ ነው። ከታንኩ እስከባንኩ ከሰማዪ እስከምድሩ ሁሉም በጃቸው ነው፤ የመሬት ወረራም ያለገድብ እየተከናወነ ነው፤ ሌሎች መስተናገድ እስከማይችሉበት ደረጃ የደርሰ የቋንቋ የበላይነትን ከቃል ወደ ተግባር አሸጋግረውታል። ታዲያ የኦሮሞ ጥያቄ የቱ ነው? የኦሮሞ ጥያቄ አልተመለሰም የሚሉት የኛ መሬት በሚሉት የሚኖሩት አነሱን የማይመስሉ የነሱን ደም የማይጋሩ የሚሏቸውን መውጣት አለባቸው የሚለው የስግብግብ ቃል ነው፤ አሱም ቃል ተግባር ሆኖ ብዙወች ተጨፍጭፈዋል ተሰደዋል። ይህ ሙሉ በሙሉ እስከሚሳካ ድረስ የኦሮሞ ጥያቄ አልተመለስም የምትለዋ ለቅሶ ትቀጥላለች። ባልተገራ ምላሳቸው የነገውን ተግባር ዛሬ በቃል ይነግሩናል። ያልተገራ ምላስ ሃፍረት አያውቅም ይሉንታ በአጠገቡ አያልፍም።

ያ ያልተገራ ምላስ የማይገናኙ ነገሮችን አጣምሮ እኩል ሊያደርጋቸው ይጥራል፤ ሸኔና ፋኖን፤ እስክንድርና ጃዋርን ወዘተ። የእናዋጣ ውድድር ላይ የሚውለበለብ ምላስ፤ ሰወችን በማነነታቸው የሚያርደውን፤ የሚዘርፈውን የሚያሰድደውን ሽኔን ሃገሩን ለማደን ከተዋደቀው ፋኖ ጋር ባንድ መለኪያ ላይ የሚያስቀምጥ ከተበላሽ ጭንቅላት ባልተሞረደ ምላስ አንደበት የሚተነፈስ የርኩስ መንፈስ ቃል ነው።

ሌባ የሚጣላው የዘረፈውን ሲከፋፈል ነው አንደሚባለው አቅፈው ደግፈው ኮከትኩተው ያሳደጉት ሸኔ ወደ ስልጣናቸው ቀርብ እያል ሲመጣ እናጠፋዋለን ግን እኛ ሸኔን ስንወጋ እንንተም ፋኖን ዉጉ ይላሉ። የአናውጣ ያልተገራ ምላስ ውጤት ነው። መሰረቱም የሚመረቅዝ በጥላቻ የቆሰለ ልብ ነው። ይህ አማራን የማሪያም ጠላት አድርጎ ማሳየትና በቃልም በተግባርም አማራን ለማዳካም፤ የህዝብ ጠላት አድርጎ የማቅረብ አባዜ ኦፌኮም የሚጋራው ነው። እንደ አሸን የተፈለፈሉት የኦሮሞ ድርጅቶች እርስበራሳቸው ባይተማምኑም በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ያገናኛቸዋል፤በአማራ ላይ ሁሉም አንድ ናቸው። ከምላሳቸው ከሚወጣው እስከተግባሩ ልዩነት የላቸውም። የዛሬውን መኖር እረስተው በትናንትናው ትርክት ላይ ህይዎታቸውን እየገፉ ነው።

የኦፌኮም ምላስ ይህን የጋራ አስተሳሰባቸው እንደሆነ ሳያፍር አስቀምጦታል። የኢትዮጵያ ህዝብ አሸባሪ የሚለውን ሼኔን የኦሮሞ ነጻ አውጭ ሲል የክርስትና ስም ሽጥቶታል። ባንጻሩ ደግሞ የአማራ ፋኖ በኦሮሞ መሬት ግብቶ ጥቃት እያደረሰ ነው ሲል እንደሁልጊዜው ተረት ተረት ተጫውቷል። ይህ ቃል ነው ነገ ደግሞ ተግባር ነው፤ በኦሮሞ መሬት አለና አማራን አጥፉ መልዕክት ነው። ቃሉ ወደ ተግባር ይቀየራል። ሟችን ገዳይ አድርጎ የሚጸንስ ልብና ያልተገራ ምላስ የሚበትነው የሃሰት ወሬ መገለጫቸው ነው። ፋኖ ገብቶ አጠቃ የሚሏችወ አካባቢወች ሁሉ የነሱ “ነጻ አውጭወች” የሚገላበጡባቸው አካባቢወች ናቸው። ማንንም አሽንፈው ቦታወችን አልያዙም የታደሏቸው አካባቢወች ናቸው።

‘Scapegaoting is like the obnoxious uncle Dolamd: ignorant, entitled, divisive.” Vindy Teja. ጥፋትን በሌሎች ላይ ማላከክ እድገቱን ካቆመ አስተሳሰብ የሚፈልቅ ነው። እነኦፌኮ ችግራቸው ሁሉ አማራ ነው፤ ምላሳቸው የሚለው ይህንኑ ነው ተግባራቸውም የሚገለጠው በዚሁ ከፋፋይ ሃሳብ ላይ ተንጠልጥሎ ነው።

በጋራ ከመኖር ተለያይቶ መጥፋትን መፍትሄ አድርገውታል። እኛና እነሱ በሚል የዘቀጠ አስተሳሰብ ላይ የተሰነከል ህልውና ስለሆነ የሚገፉት ኦነጋውያን ያደረሱትን የህይወት ጥፋትና የመፈናቀል አስከፊ ድርጊት አይታያቸውም። የተዘረፉትን ባንኮች አያስቧቸውም። በሌላ በኩል ይህን አሳፋሪ ተግባር በአማራ ላይ ለመለጠፍ በስብዕና ያልተገራው ምላሳቸው ተራ አይጠብቅም። አማራን ለማውገዝ አንዱ ባንዱ ላይ ይደረባል፤ ይሰባበራል።

በፋሲካ የተሽጠች ባሪያ ሁልጊዜ ፋሲካ ይመስላታል እንደሚባለው አንዴ የተነገራቸውን የማይረሱት አዲስ መማርም የማይችሉት የኦሮሞ ልሂቃል ሊያሞኙን ሲሞክሩ ተጨፈኑ እንኳን አይሉንም። የሚኖሩት የሚምስሏቸው ዘረኞች በፈጠሩላቸው የውሽት አለም ስለሆነ እውንታን አያዩም፤ወደፊት ያለውን ህይወትም በሃሳባቸው ውስጥ እንኳን አያገላብጡትም። በተሰጣቸው ትርክት ላይ ተቸንክረው ቀርተዋል።

“The future belongs to those who believe in the beauty of their dreams”

Eleanor Roosevelt.

ባሉበት ቁሞ ቀር ሆኖ ነገን ማየት፤ ለነገ ማለም አይቻልም እንደማለት ነው። የተረት ተረቱ ጨዋታ ነገን አያሳይም፤ በትናንትን ተረት ትዝታ ተሳፍሮ መቆዘምን እንጂ። ይህን የውሸት ትርክት ማጋለጥና እውነተኛውን ታሪክ ለትውልድ ማስተላለፍ የአማራ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ ሃላፊነት ነው። ፍትህ የአማራ፤ የኦሮሞ፤የወላይታ ወዘተ የግል ፍላጎት አይደልም። የሁሉም የሰው ልጆች ጉዳይ ነው። ዛሬ ለአንዱ የተጓደለው ፍትህ ነገ ለሌላውም ይጓደላል። ፍትህ ሁለንተናዊና በየትም ያለ ወይም መኖር ያለበት የተፈጥሮ ህግ ነው። ለዚህ ነው ፍትህ ለሁሉም ስለሆነ ሁሉም በጋራ ለፍትህ መታገል ያለበት። አለዚያ ሁሉም በየተራ በእብሪቶኞች መዳፍ የሚደቆስ ይሆናል። ዛሬ የአማራ እጣ ፈንታ ሊሆን ይችላል ነገ ሁሉም በየተራው የውሸት ትርክትና የግፍ ሰለባ ይሆናል። ያልተገራ ምላስ ሁሉንም ትገርፋለች፤ ዝቅ ታደርጋለች ፤ አካላዊ ጉዳትም ያለጥርጥር ይከተላል።

መልካም ምላስ የሰው ልጆችን ያቀራርባል፤ ያስተሳስራል፤ ለመጪው ትውልድ ትልቅ ተውፌት ፈጠሮ ያልፋል፤የሰላ ምላስ ከልብ ንጽህና ከአእምሮ ብልጽግና ይወለዳል፤ መልካሙንና የሚያስተሳስረውን ያወጋል፤ ለዚህም ያፋቅራል።

“አሁንም ልጆቸ፤ወዳጆቸ አንዱ ባንዱ ምቀኝነት ይቅር ያንዱን ሃገር አንዱ እኔ እደርባለሁ እንዳትባባሉ፤

እኔ እስካሁን በፍቅር እንዳኖርኳችሁ እናንተም ተስማምታችሁ በፍቅር እንድትኖሩ እለምናችኋለሁ”

ይህ ዘመን ተሻጋሪ ንግግር ከሰላው የሚኒልክ ምላስ የወጣ ነው። የቅን ልቦና ውጤት ነው።

በተቃራኒው ልቡ የመረቀዘ አእምሮው የደነዘ ያልተገራ ምላስ የሚያወጣው በለው ግደለው፤ ይህ ይኛ ሰው አይደለም መሬቱም የኛ ነው የሚል የውሻ ባህሪ ነው። መጥፎ ምላስ፤ ያልተገራ ምላስ የክፉ ልብ ውጤት ነውና ሰወችን ያለያያል ያጋድላል።

ሌላ ሃገር ያላቸው ይመስል ይህችን ውድ ሃገራቸውን ለመበታተን ልቦናቸውን አለት ያደረገው አእምሯቸውን ያደነዘው ትርክት እንደተጠናወታቸው ስናይ ባልተፈጠሩ ከማለት ባሻገር ምን ይባላል?

“ አገሬ አርማ ነው የነጻነት ዋንጫ

በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ፤

እሾህ ነው አገሬ፤

በጀኛው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፤

ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።”

ገብረ ክርስቶስ ደስታ

አገሬ አገርህ ናት። ይህች ድንቅ ሃገር የሁላችንም ናት። ይህን ያልተረዱ የሃሳብ ድኩማን በሀገራችን ላይ የሚያድረሱትን በደል በዝምታ አንቀበለም። ጽንፈኞች ኢትዮጵያን እንዳሽቸው ጠፍጥፈው ሊሰሯት ዳቦ አይደለችም።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop