አዎን፣ ኢትዮጵያ የአማኞች አገር ናት። ከብዙ ጊዜ በኋላ ፈሪኃ እግዚአብሄር የሚሰማው መሪ ማግኘቷም በበጎ የሚታይ ነው። ቢሆንም፣ የትኛዎቹም የፖለቲካ መሪዎቿ የፖለቲካ ውሳኔያቸውን ከሚከተሉት እምነት ጋር አያይዘው የሚወስኑ ከሆነ፣ ሁሉም እምነቱን እያጣቀሰ ለሚወስደው የተለያየ አቋም መመዘኛ የሆነ የጋራ መስፈርት የሚያሳጣን ይሆናል። ይህ ሀገርን የሚበትን እንጂ፣ የሚያቆም አይሆንም። ፈጣሪ የኢትዮጵያን ሕዝብ በጥበቡ ይጠብቅ!”
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ