February 22, 2022
13 mins read

“የተከፈተን የቧንቧ ውኃ ጀሪካን በመደቀን አታቆመውም!!!”-ፊልጶስ

Abiyf

“የተከፈተን የቧንቧ ውኃ ጀሪካን በመደቀን አታቆመውም!!!”

ሴት ልጅ የእናቷ ጓዳ ለማየት ከተሳቀቀች፤ ብዙ ተንገላቶ ላሳደገ አባት እንድ ሱሪ መገዛትና መጦር ሲሳን፤  ቀን ከሌት ደከመኝ ሳትል ከአፋ ነጥቃ እያበላች ላሳደገች  እናት ለሌማቷ የሚሆን ቁራሽ ማቅረብ  ሲያቅት፤ ታናሽ እህትና ወንድም የታላቅን እጅ እያዩ ጾም-ውለው ሲያድሩ ፤  ሥራ ስርቶ  ለማደር ጎሳና ቋንቋ መመዘኛ ሲሆን፤ ጥቂቶች በቁጣን በሚታምሙበት፤ ብዙሃኑ በርሃብ አለጋ በሚገረፍበትና በሚሞትበት አገር የስርዓት ለውጥ ለማምጣት ታግሎ የሚያታግል ሲጠፋ፤ ትግል ቢካሂድና መሰዋአት ቢከፈልም ባቋራጭ ጩሊለዎችና ጎሰኞች ስልጣኑን ይዘው፤ በመግደል፣ በማጋደልና በማሳደድ የገዥነት ዕድሚያቸውን ሲያራዝሙ፤  ስደት አንዱ አማራጭ ቢሆን ምን ያስገርማል?

ለነገሩማ  ሰው  ወደ ሰው አገር መሰደድ  አይደልም ፤ በገዛ አገራችው ዜጎች በማንነታችው  ከመታረድ የተረፋት፤  መሰደድና መከራተት ዕጣ ፋንታቸው ከሆነ  አራት አስርታትን አስቆጠርን እኮ። ያውም  በየሄዱበት ” መስጊድ እንደገባች ውሻ ” እየታዩ። ከወለጋ እስከ አዲስ አበባ፤ ከአፋር እስከ ደብረ-ብርሃን፤ ከቤንሽንጉል እስከ ባህርዳር፤ ከመተከል እስከ  ወሎ።

ለዚህ ሳይሆን ይቀረል አዝማሪው፤

”ግርም ያደርገኛል ያሰብኩት እንደሆን

ሰው በገዛ አገሩ ስድተኛ ሲሆን ”— ያለው።

በሳዊዲ እስር ቤት  የወገኖቻችን የሰቆቃ ዋይታ የገደል ማሚቶ ከሆነ ዓመታት አስቆጥሯል።  እንዳዶቹ  በሳዊዲ እስር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን ከዚህ በፊት አገር አለን ብለው  ተመላሽ ከሆኑ በኋላ ፤ አልሞላልህ ብሏቸው ፤ ”’ ካለፈለን – አለፈልን፤ ካለያስ ምን ምርጫ አለን።” ብለው    ስቃይና ሞትን ለመቀበል፤ ኑሮ እንዲሰደዱ ያስገደዳቸው ናቸው።

የ’ኛን የመከራና የመሳደድ ብሎም  ግዚያዊ መጠጊያ እንኳን ማጣት ሳስብ፤ የቻይናዊያን የሃይምኖትና የፍልስፍና አባት የሆነውን ኮንፊሽየስ  የገጠመውን ያስታውሰኛል።

ኮንፊሽየስ ብቻውን ወደ ጫካ በሜሄድ ጸሎት ማድረግ ይወድ ነበር ይባላል።  ከዕለታት በእንዱ ቀንም ኮንፊሽየስ ራቅ ወደ አለ ጫካ የተለመደውን ጸሎት ለማድረግ  ሄደ።  በአንድ ጥቅጥቅ ካለ ጫካ ከደረሰም በኋላ  በተፈጥሮ ተከቦ፣ በወፎች ዝማሪ ታጅቦና ተደላድሎ ተቀምጦ ጸሎቱን ጀመረ። ብዙ ሳይቆይ ግን  ለጀሮ የሚሰቀጥት  የዋይታና የሮሮ፤  ለቅሶ የተቀላቀለበት ድምጽ  ያለበትን ድባብ ጥሶ ወደ ጆሮ ገባ።

በድንጋጤ ተነስቶም  ሰቆቃ ወደ ሚሰማበት ድምጽን ተከትሎ  ሄደ።  ሲደርስም አንድ ሴት  እያለቀስችና መሬት ላይ እየተከባለለች አገኘ። ሴትዮዋ ” አንድ ቀሪ ልጅን አውሬ በላው” እያለች  ከአውሬው የተረፈውን የልጇን አጽምና የተቆራረጠ ልብሱን ታሳየዋለች። ኮንፊሽየስ የሚስማውንና የሚያየውን ማመን ቢያቅተውም ፤ ግዜ ወስዶ ሲትዮዋን እንደምን አረጋግቶ ማናገር ቻለ።

” አንድ ቀሪ ልጀን አውሬ በላብኝ።” አለች

”ለምን ከተማ ውስጥ አትኖሪም  ነበር? እንዴት ጫካ ውስጥ መኖር መረጥሽ?” ሲል ኮንፊሽየስ ግራ እየተጋባ  ሃዘንተኛዋን እናት ጠየቀ።

”ጌታየ! ከተማ ያሉት አውሬዎች እኮ ከዚህ ጫካ ካሉት ይብሳሉ፤ ከተማ ያሉት አንድ ልጀንና ባሌን ገለውብኝ ነው፤ ቀሪ ልጀን ሊገሉት ሲፈልጉት ለማትረፍ ብየ ከዚህ ጫካ ይዥው የመጣሁት። ይህም ጫክ አልራራልኝም ልጀን በላባኝ። ” በማለት በሲቃ ለማስረዳት ሞከርች። ኮንፊሽየስ የዚች ሴት  ስቃይና መከራ ምንጩ በምትኖርበት ከተማ ያለው ሥርዓት አልበኝነትና የገዥዎቹ ፍጹም አረመኔነት መሆኑን ያውቅ ነበርና፤ ሲትዮዋን ይዞ በከተማዋ ውስጥ  ስለ ህግ የበላይነትና ስለ ሰው ልጅ አንድነት በማስተማር፤ የከተመዋን አገዛዝና የህዝቡንም አመለካከት እንደ ቀየረ ይነገረል።

እኛስ ከሳውዲ አረቢያ እስከ  ወለጋ፣ ከወለጋ እስከ መቀሌ፤ ከመቀሊ እስከ  አፋር፡ ከቤንሻንጉል እስከ መተከል፤ ከአዲስ አበባ እስከ  አጣየ፤  ለቅሶ፣ ዋይታ፣ ስደትና  ግድያ በማስተናገድ ዘመናት አስቆጠርን።  በዚህ ሁሉ ስቃይ፤ የመክራችን ምንጭ ለማመልከትና መፍትሄ ለመፈለግ ያለመሞክራችን ፤ በዓለማችን የሰላም መጨረሻና የደሃ-ደሃዋች ለመሆን በቃን።

አሁን ለደረስንበት ‘ርስ-በርስ የጎሳ እልቂትም ሆነ ለስደት፤ ብሎም በገንዛ ወገን ደም ካልነገድን የማንከብርና  ስልጣን የማንይዝ የመሰለበት፤ በአጠቃላይ ለዚህ  ያደረስንን ምክንያት ምንድነው ብለን አንጠይቅም፣ ብንጠይቅና ብናውቀውም በችግራችን ምንጭና ምክንያት በሆነው ነገር ላይ አንሰራም፤ ብንሰራም በመርህ ላይ ተመስርተን፣ በእውነት – ለእውነት ለአገርና ለህዝብ ስለማይሆን ውጤታማ እንሆንም፤ እናም ይኽው ስው የገዛ ወገኑን ንብርቱንና ሃብቱን አይደለም፣  አርዶና ስጋውን ቅርጫ አድርጎ ካልተከፋፈለ እንቅልፍ የማይወስደው ዜጎችና ትውልዶች  ለመሆን በቃን

ብዙ የአገራችን ተናጋሪዎችና  ፓለቲከኞች አገራችንን ይዟት የሚጠፋውና ለአለንበት የዘር  እልቂት፤ የዘር ፓለቲካና ክልል ነው ሲሉ ይደመጣሉ።  ነገር ግን የዘር ፓለቱካና  በህግ እንዲታገድና ዘርን ማዕከል ያደረገውም ክልል ሌላ መፍትሄ እንዲፈለግለት ሲሰሩ አይታዩም። ትላንት” ህገ-መንግሥቱ የችግራን ዋናው ምንጭ  ነው”  ሲሉ የነበሩ፤ አሁን ወደ ሥልጣነ-መምበሩ ሲጠጉ፤ ጭራሽ የህገ-መንግስቱን  አስፈላጊነት ካልጠቀሱ ቃላት ከአንደበታቸው አይወጣም።

ላለንበት ውስብስብ ችግርና እልቂት ዋናው ምክንያት ህግ-መንግሥቱን መሰረት ያደረገው የዘር ቦለቲካ ስለመሆኑ አጠያያቂ አይደልም። የዘር ፓለቲካ በህግ ሳይታገድና ዘርን መሰረት ያደረገ ክልል ሳይፈርስና መፍትሄ ሳያገኝ፤ የአገርን ልኡዋላዊነት አስከብራለሁ፣ የዜጋውን ደህንነት እጠብቃለሁ፣ ሰላም አወርዳለሁ ማለት ”ላማ አለኝ -በሰማይ—-’’ ነው። እስከ አሁን የተሞከረውም  ”ከእሳት ወደ ”ረመጡ” እንደከተተን ያየነውና ዋጋ እየከፈልነበት ያለ እውነታ ነው።  ለዚህም ነው ”የተከፈተውን የቧንቧ ውኃ ጀሪካን በመደቀን አታቆመውም፤ ማድርግ ያለብህ ራሱ የቧንባውን ውኃ መዝጋት ነው።” የሚባለው።

ህዝብ የአገሩ ባለቤት እንዲሆንና አንድነቱ ጠብቆ፤  ሰው በመሆኑ ብቻ ተክብሮና አክብሮ የሁላችን ኢትዮጵያ እንድትኖረን  ከፈለግን፤ የችግሩን ምንጭ  እናድርቀው፤ እሱም  ህግ-መንግሥቱን መሰረት ያደረገው የዘር ፓለቱካ ነውና በህግ ይታገድ! ዘርንና ቋንቋኝ መዋቅር ያደረገው ክልል መልካ-ምድርና ምጣኔ ሃብትን ማዕከል በማድረግ ይዋቀር።

ይህን በማድረጋችን የሚመጣውን የዘረኞችና የጎሰኛችን ተቃውሞ ደግሞ የሚታገለው ህዝብ ነው። ህዝብ አንድነቱን፣ ሰላሙንና አገሩ ከማንም በበለጠ ይጠብቃልና። እንደ እናንተ እንደ ገዥዎቻችን ህገ-መንግስት ህዝብን መከፋፈልና  አምባገነንነት ቢሆንማ ዛሬ እኮ ኢትዮጵያ የለችም።

ላለንበትም ሆነ ለመጭው ትውልድ አገር እንዲኖረውና በሰላም እንዲኖር ከፈለግን ፤ በፓለቲካው  ዓለም ውስጥ ያለንም ሆን የሰባዊ መብት ተሟጋች ነን የምንል፤ የተጫነብንን የዘር ፓለቲካና  ክልል በህግ እንዲታገድ ሁላችንም የዜግነታችን ድርሻ እንወጣ።  ገዥዎቻችንም  ”ህዝብ ሰላም ሲሆን በሥልጣናችን ላይ ይመጣል።’ የሚለውን  የአምባገነኖች ብሄል ትታችሁ፤  የሚጠበቅባችሁን ብታደርጉ  በሰላምና ለረጅም ግዜ  የመግዛት እድላችሁ ይሰፋል።  ”አገራዊ ምክክር—ምናምን እያላችሁ በህዝብና በአገር ላይ  መቀለዱን ትታችሁ  ወደ”ገደለው” ግቡ ። ያለያ ግን የኋላ-ኋላ  እንደ ማንኛውም አምባገነን ዋጋችሁን ታገኛላችሁ። አሁን ግን ግዜው አላችሁና  ታሪክ ሥሩ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

———//——-ፊልጶስ

የካቲት- 2014

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop